Sunday, April 7, 2013

እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ (ክፍል አምስት)



 የጽሁፉ ባለቤቶች (ለእስልምና መልስ አዘጋጅዎች ነው)
አንደኛው፡
የጥንቱ የመጨቆንና የማንቋሸሽ መንገድ እንደገና ተጀመረ፣ እነዚህ መንገዶች ከጣሊያን ወረራ ጥቂት ቀደም ብሎ በተከሰተው ምስጢራዊው የልጅ ኢያሱ ሞት አበቁ፡፡
ሁለተኛው፡
ሙሉ ለሙሉ አዲስ ወደ ሆነ አቀራረብ በድንገት ቀልበስ ማለት ነበር፡፡ ስለዚህም በ1935 በመጀመሪያዎቹ አካባቢ ንጉሱ ኃይለስላሴ እራሱን የተለያየ ማህበረ ሰብ አካላት መሪ አድርጎ ማቅረብ ጀመረ፡፡ እርሱም በተለያዩ ቦታዎች ላይ በታላቋ ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት እኩልነት እንደሚኖር ንግግር አደረገ፡፡ አያይዞም በግንቦት 22 1935 ለሐረር የማህረሰብ መሪዎች ንግግርን አደረገ፡፡ የንጉስ ኃይለስላሴም ዋና መልእክት የነበረው ሁሉንም ሃይማኖቶች፣ ሁሉንም ጎሳዎች፣ በአዲሲቱ የኢትዮጵያ ሞዴል ማለትም “ክርስትያን ባልሆነው ነገር ግን ከልዩ ልዩ አካል በተውጣጣው የኢትዮጵያ ሞዴል” ውስጥ ለማካተት መሞከር ነበር፡፡ እርሱም የሁሉም ሃይማኖት እኩልነት ያለበት ህገ መንግስትን እንደሚያወጣ ቃል ኪዳንን ገባ፡፡ ሙስሊሞችን የማባበሉ የእርሱ አዲሱ ጥረት ያካተተው በአዲስ አበባ ውስጥ የአረብ ቋንቋ ጆርናል እንዲታተም እና በሚኒልክ ትምህርት ቤት ውስጥ አስተማሪ በነበረው ግብፃዊ አማካኝነት እንዲዘጋጅ የተደረገው እርምጃ ነበረበት፡፡ በመጨረሻም ቀደም ሲል በአፄ ሚኒሊክ በ1904 ቃል የተገባበትን የታላቁ መስጊድን ግንባታ ፈቀደ፡፡ በዚህም መሰረት እና በመሐመድ አሊ ኩባንያ ተፅዕኖ መሰረት የአረብ-እስላማዊ የንግድ ማዕከል በአዲስ አበባ መርካቶ ኢትዮጵያን በመደገፍ የድጋፍ መግለጫን አወጣ፡፡ በግንቦት 30 1935 በመሐመድ አል ሳዲቅ “የአገሪቱ የሙስሊም ኮሙኒቲ መሪ” በነበረው የተሰጠውን መግለጫ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በጋዜጣው ላይ አውጥቶታል፡፡
ሦስተኛው፡
በኃይለስላሴ ተደርጎ የነበረው ሦስተኛው እርምጃ በአረብ አገሮች ውስጥ እርዳታን መፈለግ ነበር፡፡ በ1935 ውስጥ ወደ ግብፅ፣ ሊቢያና አረቢያ መልእክተኞችን ላከ፡፡ የእርሱም ዓላማ የወታደርና ሌላም ዓይነት የቁሳቁስ እርዳታን ለመጠየቅ አልነበረም፡፡ እርሱ ፈልጎ የነበረው ለእርሱ የኢትዮጵያ አዲስ ሞዴል ማለትም የሐበሻ ሕዝቦች መንግስት የስምምነት (የተቀባይነት) ምልክት እንዲሁም ከሙሶሊኒ ጋር ለሚያደርገው ትግል የሙስሊም ሕዝቦችን ድጋፍ ለማግኘት ነበር፡፡ እርሱም የተደባለቀ ውጤት ነበረው፡፡ በሊቢያ የነበረው ሚሽን ያልተሳካ ነበር ምክንያቱም የሳኑሲ የፀረ ጣሊያን እንቅስቃሴ ተደምስሶ ነበርና፡፡ በጣም ጠቃሚው ደግሞ የግብፅ ሕዝብ ነበረ፡፡ በእርግጥ ግብፃውያን በሙሶሊኒ በኩል ሊከፈት ስላለው ጦርነት ያን ጊዜ አስታዋሽ አያስፈልጋቸውም ነበር፡፡ በ1935 የኢትዮጵያና የእርሷ እጣ ፈንታ፣ በግብፅ፣ እንዲሁም በሶርያ በኢራቅና በፍልስጥዔም ውስጥ የሕዝብን አመለካከት በመካፋፈል ዋና ጉዳይና አጀንዳ ነበር፡፡
በአጠቃላይ የመካከለኛው ምስራቅ የፓን አረብ አገሮች አገር ወዳድነት እንዲሁም የእስልምና በፖለቲካው መድረክ ውስጥ መነቃቃት፤ “የኢትዮጵያ ጥያቄ” እንዲሁም ከእርሱ ጋር አብሮ ያለው ያልጠራ አመለካከት ከዚህ እንቅስቃሴ ማዕከል ውስጥ እና የማንነት ትርጉም ውስጥ ገብቶ፤ የፖለቲካ መረጋጋት በሌለበት ሰዓት እንደገና ሊተረጎም ነበር፡፡ እጅግ ብዙ የሚሆኑት ግብፃውያን ብሪቴንን ከሚያዳክም ማንኛውም ነገር ጋር ተባብረው ነበር፡፡ ብዙዎች ሌሎች ደግሞ ሙሶሊንን በመደገፍ ዝግጁዎች ሆነው በክርስትያን ኢትዮጵያ ላይ መጥፎውን ሁሉ ይመኙ ነበር፡፡ መጽሐፎችና ጽሑፎች የኢትዮጵያን ወንጀል በመግለፅ ተጻፉና በጊዜው የነበረውን የንጉሱን የኃይለስላሴ የመጨረሻ ደቂቃ ንቃት ላይ ማላገጣቸውን ቀጠሉ፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያን ይደግፉ የነበሩትም ቀላል ቁጥር አልነበራቸውም በተለይም ሳይጠቀስ የማይቀረው እና የአገሪቱን ጠቃሚ እገዛ ያመጣው በግብፅ ውስጥ “ኢትጵያን የሚመክት ኮሚቴ” መቋቋሙና መንቀሳቀሱ ነበር፣ እርሱም ሊበራሎችና አክራሪ ያልሆኑ የካይሮ ሙስሊሞች አንድነት ድርጅት ነበር፡፡ 

Wednesday, April 3, 2013

እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ (ክፍል አራት)


   የጽሁፉ ባለቤቶች፤ (ለእስልምና መልስ አዘጋጅዎች ነው)

የሙሶሊኒ ግመሎች

በታዋቂው የአፍሪካ ቀንድ የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ኤሪሊች ሃጋይ በ2007 ከተጻፈውና Saudi Arabia & Ethiopia [ISLAM, CHRISTIANITY & POLITICS ENTWIND] ከተሰኘው መጽሐፍ ምዕራፍ አንድ ላይ የተቀናበረ ታሪካዊ ጽሑፍ፡፡
የክርስትያን ኢትዮጵያ መንግስት በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ጊዜ ከጣሊያን ወረራ በፊት በሰኔ 1934 ከሳውዲው ኢማም ያህያ ጋር የድሮውን ነገር ግን በጣም ጥሩ ያልነበረውን ግንኙነታዊ ድልድይ ለመመስረት ጥረት አድርገው እንደነበር ታሪኩ ይገልጣል፡፡ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ያሉትን እስላማዊ ማህበረ ሰቦችን ያገናኘው ቀይ ባህር ከክርስትያን ኢትዮጵያ መንግስት ጋር ብዙ ግንኙነትን ለማሰራት ባለማስቻሉ፡፡ በኢትዮጵያ ነገስታትና በተለያዩ የአረብ አገር መሪዎች መካከል የነበረው የታሪካዊ ግንኙነት ታሪካዊ ዘገባ የሚመስለው ጥቂት ነበረ በማለት የታሪክ ተመራማሪው ያስረዳል፡፡ የዚህ ሰንካላ ግንኙነት እና ወዳጅነት ስምምነት መጥፋትም ዋናው ምክንያት የኢትዮጵያ መንግስት ሃይማኖት ነው፡፡
ለዚህ የወዳጅነት አለመኖር ችግር በተመለከተ የሚገኘው ታዋቂ ታሪክ በአስራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ በንጉስ ፋሲለደስ የተሞከረው ሙከራ እንደነበረ ጸሐፊው ታሪካዊውን ማስረጃ ያቀርባል፡፡ ንጉሱ ከየመኑ ኢማም አል-ሙታዋኪ አላ አል-አላህ ጋር (በመልእክተኞቻቸው አማካኝነት) ውይይት አድርገው ነበር፡፡ ውይይቱም ያጠናከረው ነገር በኢትዮጵያና ከቀይ ባህር ማዶ ባሉት አጎራባች አገሮች መካከል ጥልቅ የሆነ መሰረታዊ ችግር የመኖሩን እውነታ ብቻ ነበር፡፡ የየመኑ ኢማም የኢትዮጵያ መንግስት ያቀረበውን የንግድና የፖለቲካ ትብብር ጥያቄ አልቀበልም ብሎ ነበር፡፡ ምክንያቱ ምን ነበር? የየመኑ ኢማም ከኢትዮጵያ መንግስት የጠየቀው ጥያቄ ነበር፣ ጥያቄውም የሃይማኖት ለውጥ ነበር፣ ፕሮፌሰር ኤርሊች ማስረጃውን ጠቅሶ እንደሚከተለው እንደነበር አስቀምጦታል፡ ገዢውም ያለው “የኢትዮጵያው ንጉስ” ማለትም ፋሲለደስ “በቅድሚያ የነጃሺን ፈለግ መከተል አለበት” ነበር፡፡ በመሆኑም የወዳጅነት ስምምነቱ እንዲኖር ንጉሱ በቅድሚያ ሃይማኖቱን “ወደ እስልምና መለወጥ አለበት” የሚል ሰበብ ነበር፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ መሰረታዊ ችግር ነው ጥልቅ የሆነ ዘላቂ ችግር ከውጭ ብቻ ሳይሆን ከውስጥም አገሪቱን የከበባት መሆኑን የሚያሳየው፡፡

በ1930ዎቹም ውስጥ በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ለሳውዲው ንጉስ ለኢብን ሳውድ የቀረበው ጥያቄም በጣም የማይሆን እድል አጋጥሞት ነበር፡፡ በእርግጥ በዚያን ጊዜ ኢትዮጵያ ጠንካራ የሆነች የክርስትያን አገር ሆና ነበር፡፡ ስለዚህም በዋሃቢያ እምነት ላይ የተመሰረተው የሳውዲ መንግስት የኢትዮጵያን መንግስት የእነተባባር ትያቄ ሊቀበለው አልቻለም ነበር፡፡

ነገር ግን የአፍሪካን ቀንድና አረቦችን ቀይ ባህር ያገናኛል የሚለው ፅንሰ ሐሳብ ለጣሊያን ቅኝ ገዢዎች በጣም ጠቃሚ የነበረ ስልት ነበር፡፡ ከ1890 ዓም ጀምሮ የራሳቸውን አካባቢያዊ ማህበረ ሰብ በኤርትራ ውስጥ መስርተው የነበሩት ጣሊያኖች ማህበረሰባቸውን በቀይ ባርህ ስም ላይ የተመሰረተና “ማሬ ኤሪትርየም” የሚል ስያሜ ሰጥተውት ነበር፡፡ ጣሊያኖቹ በሁለቱም የባህሩ አካባቢ አገሮች ላይ ተፅዕኖአቸውን ለማምጣት አልመው ነበር፡፡ ስለዚህም በሙሶሎኒ ስር ይህ ረቂቅ ሃሳብ በጣም ንቁ የሆነ ፖሊሲ ሆኖ ነበር፡፡ በ1926 ሙሶሊኒ የጣሊያንን ማህበረ ሰብ በዲክታተሪያል ቁጥጥር ስር ካደረገ በኋላ ያወጀው የመጀመሪያው ነገር “የናፖሊዮናዊ ዓመትን” ነበር፣ በዚህም የፋሽስቱ መንግስት እራሱን የሚያረጋግጠው በሜዲትሬኒያን ባህር እና በቀይ ባህር ላይ እንደነበር ይፋ ሆኗል፡፡ በመሆኑም በጣም ሃይለኛ የኤርትሪያ ገዢ የነበረው ጃኮቦ ጋስፓሪኒ ሁለት መልክ ያለውን ተግባሩን ጀመረ፡፡ በአንድ በኩል ጣሊያን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገባበትን ነገር ሲያጠብቅ በሌላ ጎኑ ደግሞ ከአረቢያኖች ጋር ትብብርን ለመመስረት ጥረትን አደረገ፡፡ 
በመስከረም 1926 ላይ ጋስፓሪኒ ከየመኑ ኢማም ያህያ ጋር የትብብር ስምምነትን ፈረመ ይህም ጣሊያኖች የመኖችን እንዲያስታጥቁ መንገድን ከፈተ፡፡ 

Tuesday, April 2, 2013

ድኅነት በሂደት ወይስ በቅጽበት? ለሚለው የዳንኤል ክብረት ስብከት የተሰጠ ምላሽ



ደግመን ደጋግመን እንደምንለው አሁንም እንላለን። ማቅና አገልጋይ ወኪሎቹ ጊዜና እድል ስላረገደላቸው ብቻ በጠለቀ እውቀት ውስጥ  ሆነው የሚያስተምሩና የሚሰብኩ ይመስላቸዋል። ከእነዚህ መንጋና ጎጋ ሰባኪዎቹ መካከል አንዱ የተረት አባት የሆነው ዳንኤል ክብረት የተባለው ሰው ነው። ለስሙ፤ ለክብሩና ለዝናው ዘወትር የሚተጋ፤ ነገር ግን የአስተውሎት ደኃው ዳንኤል ክብረት በአንድ ስብከቱ ላይ እንዲህ በሚል ርእስ ስህተቱን ለተከታዮቹ ሲረጭ ተመልክተነዋል።

«መዳን በሂደት ወይም በቅጽበት?

በዚህ ርእስ ላይ ዳንኤል «መዳን» ባመኑበት ሰዓት በቅጽበት የሚሰጥ ሕይወት ሳይሆን በሂደት የሚገኝ ሀብት ነው ይለናል። ስለዚህም ክርስቲያኖች ለመዳን  ከፈለግን ለድኅነት የሚያበቃ ተጋድሎ እየፈጸምን መቆየት የግድ አለብን በማለት ድነት/መዳን/ በቅጽበት የመሰጠቱን ነገር ክዶ ሊያስክድ ያባብላል። እውነት፤ ዳንኤል እንደሚለው መዳን በቅጽበት የሚሰጥ ጸጋ ሳይሆን ክርስቲያኖች ለመዳን ሂደትን መጠበቅ አለባቸው?  የእግዚአብሔርስ ቃል እንደዚያ ያስተምረናል? ሰው ለድኅነት ስንት ዘመን መቆየት አለበት? በስንት እድሜው ላይ ሊያረጋግጥ ይችላል? ድነኻል ብሎስ ማን ይነግረዋል? ዳንኤል ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚሆን ማብራሪያ መስጠት አልፈለገም፤ እንዲያው ሾላ በድፍኑ ብሎ ፤ ድኅነት በጥረትና በትግል ሂደት የሚገኝ እንጂ በቅጽበታዊ እምነት የሚሰጥ አይደለም ለማለት አጋዥ ምክንያቶቹን በመፈለግ ሊያሳምነን ይሞክራል። ይህንን የሚሉ ካሉ ተሳስተዋል ወይም መናፍቃን ናቸው ሲልም የራሱን ትክክለኛነት ለራሱ ነገሮ ስሙኝ ይላል።  ከየትኛውም ትምህርት ቤትና መምህር እንደዚህ የሚል ቃል እንዳገኘ አይነገረንም።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  በ«ቅዳሴ እግዚእ»  ቅዳሴ ወቅት በእርገተ እጣን ሰዓት በኅብስቱና ጽዋዕ ላይ ካህኑ እንዲህ እያለ በማጠን ይጸልያል።
«ሰፍሐ እደዊሁ ለሕማም፤ ሐመ ከመ ሕሙማነ፤ ያድኅን እለ ተወከሉ በላዕሌሁ»  ትርጉም፤  «እጆቹን ለሕማም ዘረጋ፤ በእርሱ የታመኑትን ያድን ዘንድ እንደ ሕሙማን ታመመ» ይለናል።  እንግዲህ ክርስቶስ ሕማምና ስቃይን ተቀብሎ እንዳዳነን ይህ ቃል ያረጋግጣል። ሰባኪው ዳንኤል በክርስቶስ ስቃይ እኛ መዳናችን በጊዜ ሂደት የሚረጋገጥ እንጂ በሞተልን ሰዓት የተቀበልነው አይደለም የሚለው ከየት አምጥቶ ነው?
ይህንን የዳንኤልን አሳሳች ስብከትና የጥፋት መርዝ ትምህርቱን  በወንጌል ቃል ገላልጠን  ለማሳየት እንፈልጋለን። አንባቢም የዳንኤልን ስብከት ፈልጎ እንዲያዳምጥ እንጋብዛለን ወይም በስተግርጌ ያስቀመጥነውን ሊንክ በመጫን ይህንን ጽሁፍ አንብቦ እንደጨረሰ አዳምጦ እንዲያገናዝብ ለሚዛናዊ ፍርድ አስቀምጥነዋል። ለወደፊቱም እሱንና እሱን መሰል ስሁታን አረፋ እየደፈቁና እየተንዘፈዘፉ በየመድረኩ የሚወራጩ  የሐሳውያንን  የጥፋት መንገዶች ለማሳየት እንመረምራለን። ሕዝቡን ወደጥፋት የሚነዱ የጠላት መልእክተኞች የሆኑበትን ስብከት እንደዚሁ እየመዘዝን ለማሳየት እንሞክራለን።