Sunday, June 24, 2012

ዘማሪት ዘርፌ ከበደ እና አባ ወ/ትንሣኤ በሚኒሶታ ዑራኤል ቤ/ክ

 በመላው ዓለም የእውነትን ወንጌል በማዳረስ የሚታወቁት አባ ወ/ትንሣዔ እና በውብ ድምጿ «ታሪኬን ቀያሪ» እያለች  ስለኢየሱስ ክርስቶስ  ሕይወትነት በዜማ ስትመሰክር የቆየችው ዘማሪት ዘርፌ ከበደ በሚኒሶታ ቅ/ዑራኤል ቤ/ክ አገልግሎታቸውን አበረከቱ። ማኅበረ ቅዱሳን የተባለው ድርጅት አባ ወ/ትንሣዔን ተሐድሶ እና መናፍቅ፤ ዘማሪት ዘርፌንም ከእነ ምርትነሽ ጋር አንድ ላይ  ፕሮቴስታንታዊ ኃይሎች የሚላቸውን ሰዎች ለመጨፍለቅ ባዘጋጀው  የስም ማጥፋት ሙቀጫው፤ሲወቅጣቸው መቆየቱ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ አባ ወ/ትንሣዔም ወንጌልን ሰብከዋል፤ ዘማሪት ዘርፌም «ታሪኬን ቀያሪ» እያለች ስትዘምር ውላለች።  ይህንኑ ዜና ዘሐበሻ ጋዜጣ ዘግቦታል።
(ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ)

 በሕዝብ ዘንድ በስብከታቸው እጅግ ተወዳጅ የሆኑት አባ ወልደትንሣኤ እና ዘማሪት ዘርፌ ከበደ ታላቅ መንፈሳዊ ፕሮግራም (መርሃ ግብር) አዘጋጁ። ሴንት ፖል ሚኒሶታ የሚገኘው ቅዱስ ዑራዔል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ በላከው መግለጫው እንዳስታወቀው ዘማሪቷና ሰባኪው በሚኒሶታ ለ3 ተከታታይ ቀናት ትልቅ መርሃ ግብር አዘጋጅተዋል።
አርብ ሰኔ 22 (ጁን 29) ከምሽቱ 6 ሰዓት እስከ ምሽቱ 8 ሰዓት ፣ ቅዳሜ ሰኔ 23 (ጁን 30) ከምሽቱ 5 ሰዓት እስከ ምሽቱ 7 ሰዓት እንዲሁም እሁድ ሰኔ 24 (ጁላይ 1) ከጠዋቱ 7 ሰዓት እስከ ረፋዱ 11:30 በሚደረጉት መንፈሳዊ መርሃ ግብሮች ላይ የሚኒሶታና አካባቢው የሆኑ በሙሉ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረበው የቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ በዚህ መርሃ ግብር ላይ ዘማሪት ዘርፌ ከበደ መዝሙሮቿን በማቅረብ ከም ዕመናን ጋር ትዘምራለች፤ እንዲሁም አባ ወልደትንሣኤ ስብከታቸውን ያቀርባሉ።
ዘማሪት ዘርፌ ወደ ሚኒሶታ በሕዝብ ጥያቄ መሠረት ለ2ኛ ጊዜ የምትመጣ ሲታወቅ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ስትመጣ ምእመናኑ በደስታ ተቀብሏት ነበር። አባ ወልደትንሣኤም እንዲሁ በተለያዩ ዓለማት እየተዟዟሩ የሚያገለግሉ ሲሆኑ በሚኒሶታ በተደጋጋሚ በመምጣት የ እግዚአብሔርን ቃል አካፍለዋል።
ዘማሪት ዘርፌ በሕይወት ታሪኳ ዙሪያ የተሠራው ;ፓራሜራ ፊልም ብዙ ምእመናንን እምባ እንዳራጨ ይታወቃል።
የቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አድራሻ
ቅዱስ ኡራኤል ቤ/ክ በሴንት ፖል ሚኒሶታ
1144 Earl St, Saint Paul, MN 55106
ስልክ ቁጥራቸው የሚከተለው ነው 651.771.7129
*******************************************************
ማስገንዘቢያ፤
አቶ ፍቅር ለይኩን በአባ ሰላማ ድረ ገጽ ላይ ላወጣው ጽሁፍ ደጀብርሃን ብሎግ መልስ መስጠቷ ይታወሳል። በዚሁ መልስ ላይ አቶ ፍቅር ለይኩን እነ ደጀሰላም ብሎግ ያሻቸውን ሰለፈለጉት ሰው ማንነት ሲጽፉ አንድም ቀን የምክር ይሁን የማስተማር መልእክቱን ሳይሰጥ ቆይቶ አባ ሰላማንና ሌሎች ድረገጾች በመረጃ አስደግፈው ለሚያወጧቸው ጽሁፎች  ትክክል አይደላችሁም ሲል በጽሁፉ ለማስጠንቀቅ መፈለጉን  በመተቸት በሰጠነው  መልሳችን ላይ አስረጂ እንዲሆነን  የግርጌ ሊንክ ፊደል [ ለ  ] ላይ መረጃ አስቀምጠን ነበር። ይሁን እንጂ የመረጃውን ሊንክ አንባቢ እንዳያገኘው ወዲያውኑ እንዲደመሰስ ተደርጓል።  እኛም  መረጃውን ጉግል ሰርቨር ከሚሰበስበው ኢንዴክስ  ከተመዘገበውን ካቼ በመፈለግና በመቅዳት በራሳችን ሆስት ሰርቨር መረጃውን ለማስቀመጥ ችለናል።አንባቢዎችም መረጃውን በቀድሞው ሊንካችን ማግኘት ይችላሉ። በዚሁ አጋጣሚ ለአቶ ለይኩን በመረጃ ዘመን የተሰወረና የማይገለጥ የለም፤ ለማለት እንወዳለን። [    ] በመጫን ያረጋግጡ!!

ዘረኛ ያልሆነ ማን ነው?


Naod ቤተሥላሴ
www. naodlive.com

ዘረኝነት፤ ብሔርተኝነት፤ ጎሰኝነት፤ ጎጠኝነት፤ መንደርተኝነት፤ ቡድነኝነትየሚባሉ ነገሮች ሁሉ የፍርደ ገምድልነት (Injustice, prejudice) መጀመርያዎች እና መገለጫዎች ናቸው ብል ብዙ የተሳሳትኩ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ ቀጥዬ የማነሳው ጥያቄ ግን ከላይ በርዕሱ የጠቀኩትን ጥያቄ ነው፡፡ ዘረኛ፤መንደርተኛ... ያልሆነ ማን ነው?

ከቤተክርስቲያን ስወጣ፤ አንድ ጓደኛዬ፤ ከሆነ ከማላውቀው ልጅ ጋር አብሮ ወደ እኔ ሲመጣ አየሁት፡፡ ከዚያ ‹‹ተዋወቀው፤ የአዲስ አበባ ልጅ ነው!›› አለኝ፡፡ የአዲስ አበባ ልጅ ካልሆነ ከእኔ ጋር መተዋወቅ የለበትም? አንተ ራስህ የአዲስ አበባ ልጅ ሳትሆን ተዋውቄህ የለም? ብዬ ልገስጸው ከጅዬ ነበር፡፡ ግን ያው ጨዋ ነኝና…‹‹የጎረቤቴ ልጅ ካልሆነ አልተዋወቀውም›› ብዬ ቀልጄ እንግዳውን ተዋወቅኩት፡፡ የፈራሁት ግን አልቀረም


ከተዋወቅኩት ልጅ ጋር ያለኝ ጠባያዊም ሆነ ልማዳዊ የጋራ ነገር ‹‹አዲስ አበባ መወለድ ብቻ›› ሆኖ ቀረ፡፡ ኮከባችንም፤ ጨረቃችንም፤ ቅዠታችንም የማይገጥም ሆነና ትውውቃችንን Abort አደረግነው፡፡ ይሄ ገጠመኝ እስከዛሬ ትዝ የሚለኝ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡

Friday, June 22, 2012

ካስቀኑት ያልቀረ እንደዚህ ነው ማስቀናት!!

 
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በተ/ሃይማኖት ስም ስለሚጠሩ ሦስት ሰዎች ማንነትና ምንነት በሰፊው ጽፈው አኑረውልናል። የትኛው ተ/ሃይማኖት የጻቅድነትን ስያሜ፤ ከማን እጅ እንደተረከበና ይኸው ጥሪ በዘር ማንዘሮቹ በርስትነት ተይዞ እንዲቆይ በግዝት እንዲጸናና ዜና ታሪኩ በመላው ኢትዮጵያ በሰፊው እንዲናኝ ስላስደረገው ተ/ሃይማኖ ማንነት ፤ አፍ በሚያስይዝ ጽሁፍ ስውሩን ደባ አጋልጠው ለትውልድ በማስረዳታቸው ይህም አለ እንዴ? ብለን እንድንገረም ካደረጉን ቆይቷል።
አለቃ ኪዳነ ወልድ ስለሰውዬው ማንነት በነገሩን ወቅት ይህም አለ እንዴ? ብለን ዝም ከማለት ወይም የምንወደው ጻድቅ ተነካብን ብለን ከማኩረፍ ይልቅ ስለነገሩን ታሪክ እንዴትነት ፤የእውነተኛውንና  የጻድቁን ተ/ሃይማኖትን መንፈሳዊ ገድል  ስለቀማው  ሰው ማንነት፤ በማወቅ ብቻ ሳንወሰን ያንን መነሻ አድርገን ሌሎችን መረዳቶችም  እንድናገኝ ዓይናችን በመግለጣቸው ጭምር አመስግነናቸዋል።  ድሮ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ብዙ የምንታመንበት፤ ዘወትር የምንደግመው፤ ሰውነታችንን የምናሻሽበት፤ የጸሎት መጽሐፋችን የነበረውንም  የገድል መጽሐፍ እንድንመረምር እድል አስገኝተውልናል።
አለቃ ኪዳነ ወልድ ከታሪክ ጭብጥ ተነስተው ስለገለጿቸው፤ ስለሦስቱ ተ/ሃይማኖቶች ማንነትና ታሪክ ወደፊት ለማቅረብ እንሞክራለን። ለዛሬው ግን ለርእሳችን ወደመረጥነው ጉዳይ እናመራለን።
እግዚአብሔር በቅዱሳኖቹ እጅ ድንቅን አድርጓል። ፊትም፤ ዛሬም፤ ወደፊትም ይሰራል። ይህ ግን የሚያስደንቀውና የሚያስገርመው ሥራ የቅዱሳኖቹን ኃይል ሳይሆን ኃይሉን በእነሱ የገለጸ የእግዚአብሔርን ከሃሌ ኩሉነት/ ሁሉን ቻይነት/ የሚነገርበት ዜና  ነው። ይህንን እግዚአብሔር በቅዱሳኖች አድሮ የመሥራት ኃይሉን ቅዱስ ጳውሎስ በአንድ ወቅት ያጋጠመውን ሲገልጽልን፤  በኢቆንዮን ከተማ ውስጥ ከእናቱ ማህጸን ጀምሮ እግሩ የሰለለች ሆና የተወለደ በልስጥራንም በተባለ ስፍራ አንድ ሰው በፈወሰ ጊዜ፤ ህዝቡ ተገርሞ አማልክት ከሰማይ ሰው ሆነው ወርደዋል በማለት መስዋእት ሊያቀርቡላቸው በወደዱ ጊዜ እንዲህ አለ።
«ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥ እንዲህም አሉ። እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን። እርሱ ባለፉት ትውልዶች አሕዛብን ሁሉ በገዛ ራሳቸው ጐዳና ይሄዱ ዘንድ ተዋቸው። ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራ እየሠራ፥ ከሰማይ ዝናብን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም። ይህንም ብለው እንዳይሠዉላቸው ሕዝቡን በጭንቅ አስተዉአቸው» የሐዋ 14፤ 14-18