Saturday, May 26, 2012
«ወሶበሂ ይነብብ ሐሰተ እምዚአሁ ይነብብ….ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል»
በመምህር ፈንታ
የማኅበረ ቅዱሳን አፈቀላጤ የሆነው ደጀ ሰላም
በወርሃ መጋቢት መጨረሻ ላይ የሚከበረውን የመድኃኔዓለም ዓመታዊ በዓል አስታኰ በዛሬማ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለውን የመንግሥት
የስኳር ልማት ለማጥናት ሳይሆን ለሽብር ፍጆታ የሚሆን መረጃ ለመሰብሰብ የማኅበሩን አባላት በተሳላሚ ሽፋን ወደ ገዳሙ ከላካቸው
አባላቶቹ የተገኘውን ዘገባ ደጀ ሰላም በገጹ አውጥቶ ነበር።
የስኳር ልማቱን ለማስቆም ሕዝቡ ለጦርነት ተመመ፤
መንግሥት አካባቢውን ለቆ ወጣ፤ ፖሊሶች አለቁ፤ ሬሳ ቆጠራው ቀጥሏል …..ወዘተ የብስጭት ማስተንፈሻ ስሜቶቻቸውን ከልካይ በሌለበት
ድረ ገጽ ውሸቱን በቆርጦ ቀጥል ጥበባቸው እንቶ ፈንቶአቸውን አስነብበውናል።
አሁን ደግሞ ጉዳዩ በወሬ የማይቆም መሆኑን ሲያረጋግጡ
ለጫወታ ወግ ፍለጋ ጥቂት ጊዜ እረፍት የወሰዱ መስለዋል። አንድ ነገር ፈጥረው የሽብር ዜና እስኪያሰሙን ድረስ የሚያስተምሩት የወንጌል
ቃል ስለሌላቸው ጥሩ የእረፍት ጊዜ ይሁንላችሁ ብለናቸዋል።
ይህንን ያህል ለመግቢያ ካልን የጽሁፋችን ርእስ
ወደ ሆነው ጉዳይ እናምራ። ከሁከት ውጪ ነገረ መለኰትን የማያውቁ ሽፍቶች» በሚለው ጉዳይ ተንተርሰን ወደ ርእሳችን ስንገባ ደጀ ሰላም በተሳላሚ ሽፋን በማቅ አባላቶቿ ያስጠናችው የጥናት አንዱ ክፍል በዋልድባ ገዳም «የዘጠኝ መለኰት አማኞች» መኖራቸው መዘገብ
ነበር። ስለዋልድባ መነኰሳት መናፍቅነትና ክሃዲነት ያገኘሁት ውጤት
ነው በማለት በስኳር ጥናቱ ለውሶና ስኳር አድርጎ በማቅረብ ስለዘጠኝ
መለኮት አማኞች ሊያስነብበን ፈልጎ ይህንኑ በኢንተርኔት ላይ ሰቅሎት አግኝተናል።
ከጽሁፏ የተወሰደው ዘገባዋ ይህንን ይመስላል።
ይሁን እንጂ እነ በጋሻውን፤ እነ አባ ሠረቀ ብርሃንንና
ሌሎችንም ሁሉ በአንድ ሙቀጫ አስገብታ በተሐድሶ ስም የምትወቅጠው ይህች ብሎግና ማኅበር ድሮውን በፈጠራና ስም በማጥፋት ላይ ተመስርታ
እንጂ የሃይማኖት እውቀት ስላላት በዚያ ላይ ተመስርታ ወይም የመናፍቃን ጉዳይ የሚያሳስባት ሆኖ አይደለም።
Friday, May 25, 2012
ፋሲካ
ምንጭ፦http://bethelhemm.blogspot.com
በሚያስፈራው ሌሊት ጩኸት
ሲበረታ
ግብጽ ተሸበረች ጌታ
በኩሯን መታ
ሞት መግባት አልቻለም
ወደ እስራኤል ቤት
ታትሞ ስላየ የደም ምልክት
ደጃቸውን ዘግተው ፋሲካ
አደረጉ
በደም ተከልለው ሌሊቱን
አነጉ
ባሕሩን ተሻግረው ከነዓን
ሲገቡም
የልጅ ልጆቻቸው ፋሲካን
አልረሱም
ይህ ሥርዓት አልፎ የእግዚአብሔር
በግ መጣ
ሰውን የገዛውን የሞት
ኃይል ሊቀጣ
የሰው ፍቅር ስቦት ከሰማያት
ወርዶ
ጠላትን ረታው ፋሲካችን
ታርዶ
በመስቀል ተሰቅሎ ስለሆነ
ቤዛ
ወገኖቹን ዋጅቶ በራሱ
ደም ገዛ
ንጉሡ እንዲገባ ደጆች
አይዘጉም
ሌሊቱ አልፏልና የሚያሰጋን
የለም
የሕይወታችን ጉበን በደም
ታጥሯልና
ሞት እያየ አለፈን ኃይሉን
አጥቷልና
ለምሕረት በሚጮኸው የደሙ
ምልክት
ባሕሩን ከፍለን አልፈን
እንገባለን ገነት
የዘላለም አምላክ የምስጋና
ጌታ
ምርኮን የማረከ ማኅተሙን
የፈታ
ሞትን ድል የነሳው የናዝሬቱ
ኢየሱስ
በዙፋኑ ያለው የአርያም
ንጉሥ
ከፍ ከፍ ይበል ይድረሰው
ምስጋና
መከራን ታግሶ ለእኛ
ታርዷልና
ፋሲካን ስናደርግ ኖረን
በእድሜ ጸጋ
ክርስቶስ ፋሲካ መሆኑን
አንዘንጋ፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)