አማኝ ያመነውን የሚኖር በፍቅርም የሚማርክ ጀግና ነው። አክራሪ ግን ጥቂት እውቀቱን ከዱላ ጋር ለማስከበር የሚሞክር ነው። የከረረ ነገር መበጠሱ አይቀርም። የከረረ ነገር ሲከርም ሲበጠስም ስጋት ነው። አክራሪነት የአለሙ ልከኛ ሰው እኔ ነኝ። ከኔ በቀር በአለም ላይ ማንም መኖር የለበትም። ከምስራቅ ስገላበጥ ምእራብ እደርሳለሁ። ከሰሜን ስራመድ ባንድ ስንዝር ደቡብን እረግጣለሁ። ስለዚህ ከኔ ውጪ ማንም መኖር የለበትም ብሎ እንደማሰብ ነው። የአክራሪነት ምንጩ አለማወቅ ነው። አክራሪ ሰው በከሳሽነት መንፈስ የተያዘ እንጂ የሚያሳየው ማራኪ ስራ የሌለው ነው። ጥቂት እውቀቱ ከሰፋች የካደ ስለሚመስለው ላለማወቅ ተጠንቅቆ የሚጓዝ ነው። እርሱ ካለበት ገድጓድ ውጪ አለም ያለ የማይመስለው ። የለመድኩት ሰይጣን ይሻላል ብሎ ከመቃብር ጋር በኪዳን የሚኖር ተስፋ የሌለው ሳይሞት መኖር ያቆመ ሳይቀበር እውቀቱን የጨረሰ ሰው ነው። የአክራሪነት ወንድሙ አለማወቅ ነው።
Saturday, February 23, 2013
አማኝ እንጂ አክራሪ አትሁን!
አማኝ ያመነውን የሚኖር በፍቅርም የሚማርክ ጀግና ነው። አክራሪ ግን ጥቂት እውቀቱን ከዱላ ጋር ለማስከበር የሚሞክር ነው። የከረረ ነገር መበጠሱ አይቀርም። የከረረ ነገር ሲከርም ሲበጠስም ስጋት ነው። አክራሪነት የአለሙ ልከኛ ሰው እኔ ነኝ። ከኔ በቀር በአለም ላይ ማንም መኖር የለበትም። ከምስራቅ ስገላበጥ ምእራብ እደርሳለሁ። ከሰሜን ስራመድ ባንድ ስንዝር ደቡብን እረግጣለሁ። ስለዚህ ከኔ ውጪ ማንም መኖር የለበትም ብሎ እንደማሰብ ነው። የአክራሪነት ምንጩ አለማወቅ ነው። አክራሪ ሰው በከሳሽነት መንፈስ የተያዘ እንጂ የሚያሳየው ማራኪ ስራ የሌለው ነው። ጥቂት እውቀቱ ከሰፋች የካደ ስለሚመስለው ላለማወቅ ተጠንቅቆ የሚጓዝ ነው። እርሱ ካለበት ገድጓድ ውጪ አለም ያለ የማይመስለው ። የለመድኩት ሰይጣን ይሻላል ብሎ ከመቃብር ጋር በኪዳን የሚኖር ተስፋ የሌለው ሳይሞት መኖር ያቆመ ሳይቀበር እውቀቱን የጨረሰ ሰው ነው። የአክራሪነት ወንድሙ አለማወቅ ነው።
መስከረም 29/2005 ዓ/ም ይህንን ዘግበን ነበር!
«መንግሥት ፓትርያርክ ማን ሊሆን እንደሚችል በውስጥ መሰየሙን ይነገራል» ብለን ነበር።
(በወቅቱ ያወጣነውጽሑፍ እዚህ ላይ በመጫን) ወይም ከታች ያለውን በማንበብ ይገንዘቡ።
ከታማኝ የውስጥ ምንጮች የደረሰን ዜና እንደሚያስረዳው ስድስተኛው ፓትርያርክ በመንግሥት ደረጃ ምልመላው ያለቀ ሲሆን ይህ መረጃም በማኅበረ ቅዱሳንና በቀንደኛ ጳጳሳት ዘንድም
የውስጥ ግንዛቤ እንዲያዝ ተደርጎበታል ተብሏል።
የእርቅ ሂደቱ ቢያልቅና የውጭዎቹ ጳጳሳት ከሀገር ቤቱ ሲኖዶስ ጋር በሚደረገው ስምምነት ወደአንድነት ቢጠቃለሉ ሲኖዶሱ በሚሰጣቸው ቦታ የሚመደቡ ሲሆን፤ አቡነ መርቆሬዎስ ግን ለሥራ ብቁ በማያደርጋቸው የጤናና የእድሜ ክልል ውስጥ ስላሉ በፈለጉበት ቦታ ስመ ማእረጋቸው እንደተጠበቀ በጸሎት ተወስነው እንዲቀመጡ የተፈለገ መሆኑም ተዘግቧል።
የውጪው ሲኖዶስ በሚደረገው እርቅ መሠረት በስምምነት ወደአንድነቱ የማይመጣም ከሆነ ራሱ እንዳልፈለገ ተቆጥሮ በነበረበት ሁኔታ ልዩነቱ እንደሚቀጥልም ይነገራል። ይሁን እንጂ የስድሰተኛው ፓትርያርክ ምርጫ ግን ከጥያቄ ውስጥ እንደማይገባና ወደፊት በሚመቻችለት ጊዜ ውስጥ ተመርጦ መንበረ ሥልጣኑን ተረክቦ ሥራውን እንደሚጀምር መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በዚሁ የፓትርያርክነት የምልመላ መዝገብ ውስጥ በአንደኝነት የሰፈሩት ከዚህ በፊት በሰሜን አሜሪካ ሊቀጳጳስ የነበሩትና አሁን ወደ ኢየሩሳሌም ከተዛወሩ ጥቂት ዓመታትን ያስቆጠሩት አቡነ ማትያስ መሆናቸው ተነግሯል።
ውስጥ አዋቂ መረጃዎቻችን ያንን የሚጠቁሙ ሲሆን ለማንኛውም የሚሆነውን ጊዜው ሲደርስ እናያለን።
አንድ አስተያየት ሰጪም እንዲህ ሲል በመደነቅ ጠይቆን ነበር። ያልነው እውን ሊሆን ሲቃረብ አሁን ምን ይል ይሆን?
"ስድስተኛው ፓትርያርክ በመንግሥት ደረጃ ምልመላው ያለቀ ሲሆን " how can that happen.
i think you are reversing the the roles of the government. it is not expected
like this. the church leader is not elected by the proposal of the government
cadres. any way it will be taken as a ring to awaken our fathers, and MK. i
have shared it to the facebook to reach the information to the people. the
government should respect his own constitution!!!!! we know this information
may be true, b/c we also know that the menafkan government officials are
usually support this blog and are using 'aba selama' to reflect their
interests. any way we will expose out the movements to the true followers.
ማውጫ
ማብራሪያ
ቅዱስ ሲኖዶስ ከታሪክና ከትውልድ ወቀሳ ለመዳን ምርጫውን ሊያዘገይ ይገባል!
አሁን ነገሮች እየጠሩ ወደ መቋጫው ደርሰዋል። ፓትርያርኩ ማን መሆኑም እየታወቀ ሄዷል ከማለት ይልቅ ታውቋል ማለት ይቀላል። ከሁሉም የሚያሳስበውና የሚያሳዝነው በእነ ኑረዲን ኢሊያስ፤ በእነ እጅጋየሁ ኤልዛቤል፤ በእነእዝራ የዐመጽ አለቃ ፤ በእነ ፋንታሁን የከሰረ ዐረብ፤ በእነ ኃ/ሥላሴ ሆድ አምላኩ በመሳሰሉ የ21ኛው ክ/ዘመን የቤተ ክርስቲያን ሸክሞች ግፊትና ዘመቻ የሚመረጥ ፓትርያርክ ሊኖረን መሆኑን ስናስበው ያሳዝናል፤ ያበሳጫልም። ትልቁ ሃዘናችን የአቡነ ማትያስን ድክመትና ጥንካሬ በመመዘን ሳይሆን ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው እንኳን ቀጣዩ ፓትርያርካችን አድርገን እንዳንቀበላቸው የሚያስገድዱን ነገሮች ገና ፓትርያርክ ሳይሆኑ ዙሪያቸውን ተሰልፈው ያሉትን ጎግ ማንጉግ ስንመለከት ነው። መንግሥት ደግሞ በኃላፊነት ስሜት ሂደቱን በማገዝ አድማውን፤ ዐመጹን፤ ዘመቻውን፤ ሰልፉንና ጦርነቱን በማስቆም የካርድ ምርጫ ከመንፈሳዊ ምርጫ ጋር የሚስማማ ባይሆንም እንኳን አጠቃላይ ምእመናን በነጻና በግልጽ የተሳተፉበት ምርጫ እንዲመስል ማድረግ ሲገባው ከወሮበሎች ጋር ግንባር መፍጠሩ አሳዛኝም፤ አሳፋሪም ነው። የሾለኩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት አቡነ ማትያስ በሀገረ ስብከታቸው ሳሉ ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን የስልክ መልእክት እንደተደረገላቸውና መመረጣቸው እርግጥ በመሆኑ ጓዛቸውን ሸክፈው አዲስ አበባ እንዲገቡ መደረጉን ነው። ምርጫው ላይ መንግሥት ስውር እጅ መስደድ ምን ትርፍ ለማግኘት ይሆን? የተሳሳተ ስሌትና በስሜት የሚነዳ ተግባር ከመሆን አያልፍም።
በሌላ መልኩም ዜግነታቸው አሜሪካዊ ቢሆንም በአሜሪካ ሕግ ሁለት ዜግነት መያዝ ስለሚቻል አቡነ ማትያስም በዚሁ ሁለት
ዜግነት እየተጠቀሙ መገኘታቸውን መረዳት ተችሏል። ምንም እንኳን የኢትዮጵያ
ሕግ ሁለት ዜግነትን ባይፈቅድም ላለፉት በአሜሪካ ኖረው ከደርግ ውድቀት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለሱ ኢትዮጵያዊ ዜግነትን አድሰው በኢትዮጵያ የጉዞ ዶኩሜንት
እንደሚጠቀሙ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል። በአሜሪካዊ ዜግነታቸው ደግሞ አሜሪካ ውስጥ የራሳቸው የግል ቤተክርስቲያን አላቸው። የጡረታ ባለመብት ናቸው። ይሁን እንጂ ለፓትርያክነት ሥልጣን እርግጠኛ የሆነ ዋስትና
ካገኙ አሜሪካዊነትን የማይጥሉበት ምክንያት አይታየንም። ምክንያቱም አሜሪካዊ ሆነው አርጅተውበታልና እንደወጣትነት ዘመን አያጓጓቸውም።
ይልቅስ ከሰለቹበት አሜሪካዊነት ይልቅ ያላዩት ፓትርያርክነት ይናፍቃልና ዜግነታቸውን መልሰው ለመቅረብ የመቻላቸው ነገር ብዙም አይከብዳቸውም።
ደግሞስ ፓትርያርክን ያህል ሥልጣን ለመስጠት ከተቻለ አሜሪካዊ ነህ፤ አይደለህም ብሎ ማንኛው ሰው ይሆን ሀሞት ኖሮት የሚመረምረው?
ይህ ሁሉ ቢሆንም የዘንደሮው የፓትርያርክ ምርጫ አሳዛኝ፤ ታሪክ የሚያበላሽ፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚያቆስል ከመሆን ያለፈ
አይሆንም። ከዚህም የተነሳ ለመንግሥትና ለቅዱስ ሲኖዶስ ከታች የተመለከተውን ጩኸት ለትልቁ ጆሮአቸው ማሰማት እንወዳለን።
በተለይ ለኢትዮጵያ መንግሥት፤
መንግሥትና ሃይማኖት የተለያዩ ናቸው የሚል ሕግ ቢኖርም እንደኢትዮጵያ ባሉ ሀገሮች ይህንን የአሜሪካውያንን ሕግ ለመተግበር
ይቻላል ብሎ ማሰብ ራስን ማታለል ነው። በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት እነዚህ ሁለት ክፍሎች ግልጽም ስውርም ግንኙነት አላቸው።
በዚህ ጽሁፍ ያንን ወደማብራራት አንገባም። ነገር ግን ማሳሰብ የምንወደው ነገር እንደዜጋም፤ እንደ እምነት ሰውም የምንናገረውን
ሊሰማን ይገባል። ምንም እንኳን የኛ ማሳሰቢያ ሚዛን ባይደፋ፤ ማሳሰቢያችንን መስማት የሚችልበት እድል ባይኖር የመንግሥት ጆሮ ትልቅና ከዝሆን የተሻለ ነው ብለን ስለምንገምት ጥቂት መናገር አስፈልጎናል።
1/ መንግሥት ካለፈው ስህተት ከመማር ይልቅ ስህተትን እንደተመረቀበት ሙያ መደጋገም የለበትም። የፈረንጆቹን አባባል
በመዋስ በአጭር ቃል ላስቀምጥ። «በመጀመሪያ ስታልፍ የመታህ የድንጋይ እንቅፋት፤ ዳግመኛ ስትመለስ ቢመታህ ድንጋዩ አንተ ነህ»
ይላሉ። ስለዚህ ዳግመኛ ስህተት መሥራት የለበትም።
2/ አሁን ላለው የቤተ ክርስቲያን ቀውስና ምስቅልቅል ሙት ወቃሽ አያድርገኝና የምናከብራቸው አባት አቡነ ጳውሎስ ትልቅ
ድርሻ ነበራቸው። ማንን መሾም እንዳለባቸው ያለማወቃቸው፤ ገንዘብና አስተዳደር ላይ የነበራቸው ድክመት፤ ሥርዓተ አልበኞች እየተፈለፈሉና
እየፋፉ የሚሄዱበትን ሁኔታ ለማስቆም የሚያስችል ሥራ ባለመሰራቱ ይህንን ሁሉ ወዝፈው አልፈዋል። ዛሬ ያንን የተረዳ፤ ማስወገድ የሚችል
ብርቱ፤ በሥራው የተመሰከረ፤ ለተግዳሮቶች ራሱን ያዘጋጀ መሪ እንዲኖረን እንፈልጋለን። ስለዚህ መንግሥት ያለፈ ስህተቱን በመድገም
እኔን ብቻ የማይቃወም ይሁን በሚል ስሌት ይህችን ጥንታዊ ቤተ ክርስቲያን ማጥፋት የለበትም።
3/ እርግጥ ነው፤ መንግሥት ቤተ ክርስቲያን ራሷን ችላ
በመንፈሳዊ እድገት፤ በልማትና በማኅበራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ እንድትገባ ይፈልጋል። ድጋፍም እንደሚሰጥ ይገመታል። ነገር ግን የእርስ
በእርስ መጠላለፋችንን እያየ እጁን ለማስገባት መሞከሩ ነገሩን ከማባባስ በስተቀር ጤና የሚሰጣት አይሆንም። ስለዚህ መንግሥት ከራሱና ከጥቂት የቤተ ክርስቲያን ሹመኞች ጋር ብቻ የሚያደርገውን
ግንኙነት በልክ አድርጎ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ያገባኛል ከሚለው ነገር ግን ቦታ ካልተሰጠው ሕዝብ ጋር ሆኖ የእውቀት፤ የታሪክ፤
የባህል፤ የቅርስ፤ የትውፊት ባለቤት የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን ወደፊት እንድትሄድ ድጋፍና እገዛ ማድረግ ይገባዋል።
Subscribe to:
Posts (Atom)