የፓትርያርክ ምርጫው ዘመቻ እየገፋ ሲመጣ የማቅ ስውር ብሎጎችና በስሙ የሚጠራው ድረ ገጽ ጭምር የሚያወጧቸው ዘገባዎች
የተጠኑና መጠናቸውም የቀነሰ ሆኗል። «እርቅ ይቅደም፤ ሲኖዶሱ አንድ ይሁን» የሚለውንም ጩኸት በልክ አድርገውታል። በወቅቱ ይህንን
ድምጽ ማስጮህ ያስፈለገበት ምክንያት ማኅበረ ቅዱሳን በፓትርያርክ
ምርጫው ውስጥ እንደሌለበት አንድ እጁን በማሳየት በአንድ እጁ ደግሞ
ወደ ምርጫው ለመግባት የመሸጋገሪያ ስልት አድርጎ በመጠቀም ነበር።
ይህንንም በአንድ በኩል አባላቶቹን በአስመራጭነት ሰግስጎ በመክተት
በሌላ መልኩ ደግሞ የፓትርያርክ ምርጫውን እንደሚቃወም መስሎ የመታየት ስልቱ አስቀድሞ ጥናት የተወሰደበት ስልት ነው። ይህ ስልት
ደግሞ በትክክል ሰርቷል። ምርጫውን እንቃወማለን ብሎ በመጮህ ብዙዎችን አጃጅሏል ፤ በጀርባው ደግሞ አባላቶቹንም በአስመራጭነት በመሰየም
የተሳካ ስራ ሰርቷል። አሁን የቀረው ነገር የሚፈልገውን እጩ በመጠቆም፤ በካርድ ምርጫው ሽፋን የሚፈልገውን ፓትርያርክ አድርጎ ማስቀመጥ
ነው። ይህንንም ስልት በተጠና መንገድ እያስኬደው እንደሚገኝ መረጃዎችና እንቅስቃሴዎች ይጠቁሙናል።
ከአስመራጭ ኮሚቴዎች ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ የወሰደው ማቅ ነው።
- ባያብል ሙላቴ የተባለው ሰው ዊኪሊክስ ሳይቀር የመሰከረለት የማኅበረ ቅዱሳን አባልና በሁለቱ ሲኖዶሶች መካከል እርቅ መምጣት እንደማይችል በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ መረጃ ሲያቀብል የኖረና ቀንደኛ የአባ ጳውሎስ ተቃዋሚ ነው። በወቅቱ አባ ሳሙኤል ከሟቹ ፓትርያርክ ጋር ውዝግብ ውስጥ ስለገቡ ብቻ ደጋፊያቸው መስሎ በመቅረብ እሳት ሲያነድ የቆየ አስመሳይ ሲሆን ዛሬም አባ ሳሙኤል እንደሚመረጡ በማስመሰል እያጃጃለ ቁማሩን ይቆምራል
- ፋንታሁን ሙጬ፤ ይህ ሰው ከኦስትሪያ ካቶሊክ ኮሌጅ ከተባረረ በኋላ / የመባረሩ ምክንያት ሰፊ ነው/ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሆኖ የተሾመ ሲሆን የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ካህናትን በጉቦና በዘረኝነት በሽታ ሥጋቸውን ጨርሶ አጥንታቸውን እየጋጠ ባለበት ሰዓት ፈጀን፤ ጨረሰን ብለው እሪ በማለታቸው ከቦታው የተነሳ ርኅራኄ ያልፈጠረበት ሰው ነው። ከአባ ጳውሎስ ጋር ጥብቅ ወዳጅነት የነበረው ሲሆን ከባል አልቦዋ ሴት ጋር ትስስሩ የጠነከረ፤ ማኅበረ ቅዱሳንን በስልት የሚመለከት መሰሪ ሰው ነው።
- ዓለማየሁ ተስፋዬ፤ ይህ ሰው ተንኮለኛና እንቅስቃሴውን እንደቀንድ አውጣ ከሰንኮፉ ሳያርቅ ብቅ ጥልቅ እያደረገ የሚንቀሳቀስ ሲሆን በቦሌ መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሚና የተጫወተ አደገኛ ጸረ ትግሬ ነው። «ቃሌ» በሚባለውና በብርቱኳን ሚደቅሳ ስም በተመሠረተው የፓልቶክ ውስጥ ተባባሪ ባለቤት /Admin/ ሆኖ የሚያገለግል የሽማግሌ ውሸታም ነው። የኢየሩሳሌም መታሰቢያ ድርጅትን ጥሩ አድርጎ የጋጠ አድመኛና ዘረኛ እንደሆነም በሰውየው የተማረሩ ሰዎች እንባ ቀረሽ እሮሮ ያሰማሉ።
- ጸባቴ ገብረ መስቀል ውቤ /ሙሽራው ይሉታል በቅርብ የሚያውቁት/ መልአከ ሰላም ዓምደ ብርሃን ገ/ጻድቅና ዲ/ን ኄኖክ ዐሥራት የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ስለመሆናቸው ጥርጣሬ እንደሌላቸው በቅርብ የሚያውቋቸው ይናገራሉ። /በእነዚህ ሰዎች ዙሪያ ያገኘናቸውን ተጨማሪ መረጃዎችን ለማረጋገጥ እየሰራን ነው/