Thursday, August 16, 2012

ሰበር ዜና፤ ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አረፉ።



ብጹእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ያገኘነው ዘገባ አረጋግጧል። በሳምንቱ መጀመሪያ ገደማ ለሕክምና ዳጃች ባልቻ ከገቡ በኋላ አንዳንዶች ህመማቸውን እንደህመማቸው ቆጥረው ሳይሆን መታመማቸው ይፋዊ ዜና እንዲሆንላቸውና መጨረሻቸውም በሚፈልጉት መንገድ ሲያበቃ ለማየት የቋመጡ  ያህል ሲዘግቡ የሰነበቱበት እውን ሆኖ   በ9/12/ 2004  ዓ/ም ንጋት ላይ  አርፈዋል።
የቅዱስ ፓትርያርኩን ሞት ለረጅም ዘመን ሲጠብቁ የቆዩ ደስ ሲላቸው እስከ ሰውኛ ድክመታቸው ፓትርያርኩ ለዚህች ቤተክርስቲያን የሚችሉትን ያህል ሰርተዋል የሚሉ ደግሞ ማዘናቸው አይቀርም። ደጀ ብርሃን ብሎግ አቡነ ጳውሎስ ከስህተትና ከሰውኛ የድካም ጠባይዓት ፍጹም ነጻ ነበሩ ብላ ባታምንም  ቤተክርስቲያኒቱን ደከመኝ፤ ሰለቸኝ ሳይሉ በማገልገል፤ የተወረሱባትን ሃብትና ንብረት በማስመለስ ረገድ ትልቅ ስራ መስራታቸውን፤ በቅዳሴ አገልግሎት በህመም ውስጥ እንኳን እያሉ ማገልገላቸውን ትመሰክራለች።
አቡነ ጳውሎስን በአስተዳደር፤ በገንዘብ ጉዳይ፤ በዘረኝነት የሚወቅሱ ወገኖች አሁን በሞት ሁሉን ነገር ትተውላቸው ሲሄዱ ፍላጎታቸውን ሊያሟላ የሚችል ጳጳስ በመፈለግ «ትሻልን ሰድጄ ትብስን አመጣሁ» እንዳይሆን ከወዲሁ ትልቅ ፍርሃት አለን።
 በቀጣይ ጽሁፋችን ሙሉ ታሪካቸውን ይዘን የምንቀርብ ሲሆን እግዚአብሔር የወደደውን እንዲያደርግ ከማሰብ ባሻገር በጥላቻም ይሁን መጠን ባለፈ ምስጋና ውስጥ እንዳንሆን አንባቢዎቻችንን ለማሳሰብ እንወዳለን።
እግዚአብሔር በዐጸደ ቅዱሳን እረፍቱን ይስጥልን!

Tuesday, August 14, 2012

ሃሌ ሉያ

የሕይወታችን ባለቤት፤ የመዳናችን ዋስትና፤ የዘላለማዊነት ርስት ለሆነው ለእግዚአብሔር ብቻ የተገባ ይህንን የግጥም ምስጋና ስለወደድነው ከቤተ ጳውሎስ ብሎግ ላይ ወስደን አካፍለናችኋል። ለመዳናችን ሌላ ምስጋና ለማን? ዳዊትም ያለው ይህንን ነው።

መዝ 44፤20-21
የአምላካችንን ስም ረስተንስ ቢሆን፥ እጃችንንም ወደ ሌላ አምላክ አንሥተንስ ቢሆን፥
እግዚአብሔር ይህንን አይመረምርም ነበርን? እርሱ ልብ የሰወረውን ያውቃልና።

ቤተ ጳውሎስ ማክሰኞ ሐምሌ 8/2004 ዓ.ም.

ሃሌ ሉያ ለአብ
ሃሌ ሉያ ለወልድ
ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ
ሃሌ ሉያ በአርያም ላለኸው
ሃሌ ሉያ በልቤ ለነገሥከው
ሃሌ ሉያ ለጥልቁ መሠረት
ሃሌ ሉያ ለምጥቀቱ ጉልላት
ሃሌ ሉያ ለዳርቻዎች ወሰን
ሃሌ ሉያ ከአድማስ ወዲያም ላለኸው
ሃሌ ሉያ ዓመታትን ላስረጀው
ሃሌ ሉያ ሕዝቡን ለታደግኸው
ሃሌ ሉያ ብርሃናትን ለፈጠርከው
ሃሌ ሉያ ስሜን ለለወጥከው
ሃሌ ሉያ ለድካሜ ምርኩዝ
ሃሌ ሉያ ለምስኪንነቴ ሞገስ
ሃሌ ሉያ ለተጨነቁት ዕረፍት
ሃሌ ሉያ ለታወኩት ፀጥታ
ሃሌ ሉያ ሸክም ለተጫናቸው ወደብ
ሃሌ ሉያ ስንጥቁን ልቤን ገጥመህ ለያዝከው
ሃሌ ሉያ በመጽናናትህ ለጎበኘኸኝ
ሃሌ ሉያ ከጥልቁ ስጮህ ለሰማኸኝ
ሃሌ ሉያ ከደጅ ስፈልግህ በውስጤ ላገኘሁህ
ሃሌ ሉያ በማይቻለው ቀን ለቻልኩብህ
ሃሌ ሉያ ለባልቴቲቱ ዳኛ
ሃሌ ሉያ ለሙት ልጅ ሰብሳቢ
ሃሌ ሉያ ለበረሃ ጥላዬ
ሃሌ ሉያ ለምድረ በዳው ጓደኛዬ

Monday, August 13, 2012

በዓውደ ምሕረት ብሎግ አስቀድሞ የተገኘው መረጃ «የደጀ ሰላምንና የአለቃዋ የማቅን» ማንነት ሲያጋልጥ!


ጉባዔ አርድእት የተሰኘ የአገልግሎት ጉባዔ በቤተክርስቲያኒቱ  እውቅና ምሁር ሠራተኞች  እንደተመሰረተ ይሰማል። እንደ ደጀ ብርሃን ብሎግ እምነት በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ከጥንታዊው የጽዋ ማኅበራት ውጪ ምንም ዓይነት  የተደራጀ ማኅበርም ይሁን ጉባዔ እንዲኖር የማንፈልግ ቢሆንም  እኛን የገረመንና የደነቀን ነገር ማኅበረ ቅዱሳን እሱ ራሱ እንደማኅበር በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ እየነገደና እያጭበረበረ የቆየ ሆኖ ሳለ ጉባዔ አርድእት የሚባል ስብስብ ሊደራጅ መሆኑን ከሰማበት ጊዜ ጀምሮ እንዲህ ጨርቁን አስጥሎ እንዲበር ያደረገው ነገር አስገራሚ ሆኖብናል።
የጉባዔ አርድእት ህልውና እውን መሆን ማኅበረ ቅዱሳን ያሰጋኛል ከሚል የፍርሃት፤ የጭንቀትና የቅንዓት ዓላማ ተነስቶ ጉባዔውን ቶሎ ማዳፈንና ግብዓተ ሞቱን ማፋጠን በሚል እብደት ውስጥ መግባቱን የሚያሳየው እንቅስቃሴ ማኅበሩ በራሱ ምን ዓይነት ማኅበር መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነው። በአጭር ቃል ማኅበረ ቅዱሳን እያለ ያለው በማኅበር ደረጃ ከእኔ በስተቀር በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ፈጽሞ አይታሰብም፤ የኔ የመተዳደሪያ ሕገ መንግሥት ተፎካካሪ የሚያገኘው በመቃብሬ ላይ ነው የሚል አንጀኛ መሆኑን በግልጽ አሳይቷል።
ማኅበረ ቅዱሳን በቅዱስ ሲኖዶስ ተደራጅቻለሁ፤ የቤተክርስቲያኒቱን እምነትና ትውፊት አስከብራለሁ፤ ሕግና ስርዓቷን አከብራለሁ፤ ከዚህም በላይ በእግዚአብሔር እተማመናለሁ የሚል ከሆነ የሌላ ማኅበር ወይም ጉባዔ መቋቋም ስጋት የሚሆንበት ለምንድነው?

 አዎ! ድሮውንም ቢሆን ማኅበሩ አጭበርባሪ፤ አስመሳይ፤ ነጋዴና ከሳሽ ፖለቲካዊ ድርጅት በመሆኑ አቻ የሚሆነውን ወይም ከሱ የተሻለ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚችል ምንም ዓይነት ተቋም እንዲመሰረት ስለማይፈልግ ነው። ይህንንም ባላቋረጠ የማጥፋት እንቅስቃሴው በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል።
የውስጥ አዋቂዎችን መረጃ በመጠቀም ዓውደ ምሕረት ብሎግ ማኅበሩ እያደረገ ያለውን የጥፋት ዘመቻና ለዘመቻው ግብ መምታት እየተጓዘ ያለበትንም ርቀት ሁሉ በመዘገብ  ለመረጃ መረብ አቅርባ ይህንኑ መረጃ እኛም ማሰራጨታችን ይታወሳል።  ከወጣው መረጃ  ላይ ከርእሳችን ጋር የሄደውን ቃል ከታች  ለማሳያነት በጥቂቱ እናቅርብ።
ከዚህ በፊት ሁሉንም የቤተክርስቲያኒቱ አካላት በተለያየ መንገድ እየከፋፈለ ቤተክርስቲያኒቱን ለውድቀት እያፋጠነ የቆየውና ያለው ማሕበረ ቅዱሳን በተለይ በአሁኑ ሰዓት ከአክራሪዎችና ከፖለቲከኞች ጋር ግንባር በመፍጠር እያካሄደ ያለውን እኩይ ተግባር እየተጋለጠበት በመምጣቱና በአገር ውስጥና በውጭ አገርም ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት በመምጣቱ ከዚህ ያድኑኛል ያላቸውን አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስንና አቶ ተስፋዬ ውብሸትን(የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ) በመደበው በጅት በመደለል  በዋና ሥራ አስኪያጁ በአቡነ ፊልጶስ እና በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ ሕዝቅኤል አማካኝነት “ጉባኤ አርድእትን “ አናውቀውም ይታገድልን የሚል ደብዳቤ እንደሚያጽፉ የውስጥ ምንጮቻችን ገልጸዋል።