Sunday, August 12, 2012

ድንግል ማርያም ነኝ ባይዋ “ጣሪያ ቀድጄ እወጣለሁ” አለች!

ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም ይላል የሀገሬ ሰው። እኔ ማርያም ነኝ የምትል ጠላት የሰለጠነባት ሴት አንድ ሰሞን ሀገር ስታምስ ሰምተን እጅግ ተገርመን ነበር። ይበልጥ ያስደነቀን ነገር የአጋንንት መጫወቻ ሆና ሳለ ፤ እኔ ማርያም ነኝ ማለቷ ሳይሆን፤ ማርያም ናት ብለው አብረው በመከተል እንባቸውን እንደጅረት የሚያፈሱ የክፉው መንፈስ አባላትን ማየት በመቻላችን ነበር። አሁን ደግሞ ኢየሱስን ወለድኩ እያለች ህጻን ልጅ አስከትላ /ሎቱ ስብሐት/ ቃለ ጽርፈትን እያስተጋባችና ደብረ ሊባኖስ በመሄድ ኑና ተፈወሱ ስትል መገኘቷ ተዘግቧል።
 ጣሪያውን ቀዳ እንደምትወጣ ብትናገርም ከአፍ በዘለለ ምንም ማድረግ  ሳትችል ፖሊስ ቀፍድዶ ጣቢያ ሲወረውራት ማምለጥ ሳትችል ቀርታለች። ከታች ያለውን ዘገባ «ከአዲስ አድማስ ጋዜጣ» ላይ ያገኘነውን ዜና አካፍለናችኋል። መልካም ንባብ!

በደብረሊባኖስ በቁጥጥር ሥር ውላለች :: የያዘችውን ህፃንኢየሱስ ነውብላለች።

ሦስት ልጆቼን የወለድኩት በመንፈስ ቅዱስ ነው በሚል ተከታዮች በማፍራት ለፈፀመችው የማታለል ወንጀል እና ተከታይዋ የነበረችውን ትዕግስት አበራ፣ ምንነቱ ያልታወቀ ባእድ ነገር በማጠጣት ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረጓ ተከስሳ /ቤት የቀረበችው / ትዕግስት ብርሃኑ፤ ጥፋተኛ አይደለሁም በማለቷ ክሷን እንድትከላከል ተወስኖ ምስክሮቿን ያሰማች ሲሆን  ጥፋተኛ ነች አይደለችም የሚለውን ለመበየን /ቤት ለነሐሴ 10 ቀን 2004 . ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡
ተከሳሿ የዋስትና መብቷን አስጠብቃ ከእስር ከወጣች በኋላ ድንግል ማርያም ነኝ በማለት ሠላሳ ተከታዮቿን ይዛ ደብረሊባኖስ በመሄድ አብሮአት ያለውን አቶ /ገብርኤል የተባለ ግለሰብ፤እሱ ገብርኤል ነው ብታምኑ ትድናላችሁ ባታምኑ ትቀሠፋላችሁበማለት ቅስቀሳ ስታደርግ እንደነበር ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ / ትዕግስት በተጨማሪም የያዘችውን ህፃን ልጅእየሱስ ነው፤ ንኩት ትፈወሳላችሁበማለት ሁከት በመፍጠሯ፣ የአካባቢው ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋላትና በደብረ ጽጌ ፖሊስ ጣቢያ እንደምትገኝ ታውቋል፡፡ ተከሳሿ ማረሚያ ቤት ከገባች በኋላምበተአምር ጣሪያ ቀድጄ እወጣለሁ፤ የሚይዘኝ የለም፤ መንፈሴ ከተቆጣ ሁላችሁም ትሞታላችሁእያለች በእስረኞች ላይ ሽብር እየፈጠረች መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

Saturday, August 11, 2012

አዲሱ የግብጽ ሕገ መንግሥት እስልምና የመንግስት ሃይማኖት መሆኑን ያውጃል!

የሙስሊም ወንድማማቾች መሪና በሙባረክ ዘመን ከርቸሌ ወርደው የነበሩት ሙሐመድ ሙርሲ ስልጣን ላይ ይወጣሉ ተብሎ ከተፈራበት ጊዜ አንስቶና ስልጣኑ ላይ ከተፈናጠጡ ጀምሮ የግብጽ ክርስቲያኖች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ። ከግብጽ ክርስቲያኖች ውስጥ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አማኞች እስከ 15 ሚሊዮን በሀገር ውስጥ ሲኖሩ ወደ 2 ሚሊየን የሚጠጉት ደግሞ በተለያዩ ዓለማት ውስጥ ተሰደው ይገኛሉ። እስከ 640 ዓ/ም ድረስ የግብጽ ሕዝብ 100% የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የነበረ ሲሆን በእስልምና ወረራና መስፋት የወደደ በውድ፤ ያልፈለገ በግድ እስልምናን እንዲቀበል ተደርጎ፤ የተረፈውም የእስልምናን የበላይነትና የሚጣልበንት ቅጣት ለመቀበል የመስማማት ውል ገብቶ እንደክርስቲያን ለመኖር የቻለ ቢሆንም ከመገደል፤ ከመሰደድና ንብረቱን ከመቀማት አላመለጠም ነበር።  ከጋማል አብደል ናስርና፤ በይበልጥም በሁስኒ ሙባረክ አገዛዝ ዘመን የተሻለ ዋስትና የነበራቸው ቢሆንም ከግብጹ የአመጽ እንቅስቃሴ ወዲህ ነገሮች ሁሉ ተለዋወጠው ኮፕቲኮቹና የሶሪያ ኦርቶዶክስ፤ የግሪክ ኦርቶዶክስ፤ የሮማ ካቶሊክ፤ ፕሮቴስታንትና ሌሎች ክፍሎችም ቁጥራቸው ትንሽ የማይባሉ ክርስቲያኖች አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ። ይህ አደገኛ ሁኔታም በመረቀቅ ላይ ባለው አዲሱ የግብጽ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 2 ላይ እስልምና የመንግሥቱ ሃይማኖት መሆኑን በማስቀመጡ የተነሳ ነው። ይህም ማለት ይላል «ክሪስቲያን ፖስት» ጋዜጣ ህግ አውጪው ህጎችን የሚያወጣው በእስልምና ሃይማኖት መሰረትነት ላይ ስለሆነ በአጭር ቃል የሀገሪቱን ህግ የሸሪአ ህግ ይመራዋል ማለት ነው ይለናል።
በዚህ የእስልምና ህግ ስር ክርስቲያኖች ለመኖር የሚችሉት እስልምናው በሚፈቅድላቸው መንገድና መጠን ስለሚሆን በሀገሪቱ ውስጥ እንደዜጋ ሳይሆን እንደባሪያና አሳዳሪ ስርዓት የመኖር ግዴታን የሚቀበሉ ይሆናሉ ማለት ነው። መሐመድ ሙርሲ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት እንደሚያቋቁሙ ቃል ቢገቡም እየሆነ ያለው ግን ዲሞክራሲውን የሚለካው የመንግሥቱ ሃይማኖት እንጂ የዜጎች ሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች እንዳይደሉ እየታየ ነው።
በሸሪአ ህግ መሰረት የሰረቀ እጁን እያፈራረቁ መቁረጥ፤ በዝሙት የተገኘ በድንጋይ ተደብድቦ መገደል፤ ከእስልምና ወደክርስትና የገባውን አልመለስም ካለ ማረድ፤ እንዲቀየር ያባበለውን ዛፍ ላይ መስቀል ወዘተ ቅጣቶች ክርስቲያኖችን ይጠብቃቸዋል ወይ? ለሚለው ጥያቄ እስካሁን በይፋ የተነገረ ባይሆንም የእስልምና መንግሥት እስከተቋቋመ ድረስ ይህ መሆኑ ስለማይቀር ብዙዎቹን ክርስቲያኖች ድንጋጤ ላይ ጥሏቸዋል።
ሰላፊዎች የሸሪአ ህግ በሀገሪቱ እንዲተገበር ጫና እየፈጠሩ ሲሆን ክርስቲያን የሆነ ማንም በእስልምናው መንግሥት ውስጥ መስራት የለበትም የሚል አክራሪነት እያወጁ ይገኛሉ። ምንም እንኳን በቀጥታ ክርስቲያኖችን ወደእስልምና ማምጣት እንደማይችሉ ቢያምኑም ሰለፊዎች የሚያደርጉት ግፊት ክርስቲያኖች መጪውን ጊዜ በመፍራት ሀገሩን እየለቀቁ ወደምእራቡ ዓለም እንዲሰደዱ ተጽእኖ  የማድረግና ፍርሃትን የማስፈን ስራ እየሰሩ እንደሆነ ተገምቷል።
ይህ እንቅስቃሴ በገፍ በሚፈሰው የፔትሮ ዶላር ድጋፍ  አፍሪካን በሸሪአ የመንከር ትልቁ ዘመቻ አካል ሲሆን ግብጽን በምታክል ትልቅ የዐረቡ ሀገር ምሳሌ ውስጥ ክርስትና እንዴት ይታሰባል? የሚል ቁጭት አላቸው። አህመድ ዲዳት የሚባል የእስልምና ቀንደኛ ሰባኪ በአንድ ወቅት ግብጽ የዐረብ ሊግ ዋና ተጠሪ ሆና ሳለ በግብጽ ውስጥ ሚሊዮኖች ክርስቲያኖች መኖራቸው የሙስሊሙ ዓለም የስንፍና ውጤት ነው በማለት በቁጭት ሲናገር መደመጡ የቁጭቱ ጣሪያ የት ድረስ እንደሆነ ያሳያል።
 ከሊባኖሱ ሂዝቦላህ፤ ከፓለስቲናው ሃማስ እና የመሐመድ ሙርሲው ብራዘር ሁድ የተሳሰረ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ቁርኝት እንዳላቸው ስለሚታወቅ መካከለኛው ምሥራቅን በዚህ የሰለፊ ባህር ውስጥ የመንከር ስውር ዘመቻ አንዱ ክፍል በግብጽ ላይ መቀመጡ የክርስቲያኖቹን መጪ ዘመን ከባድ ያደርገዋል። እስልምናዊ መንግሥት ማለት የዚያ ትግል ውጤታቸው ነው።
የዚሁ ዘመቻ ዋና አካል የሆነው የሰለፊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ውስጥ ዘመቻውን  እያጧጧፈ ይገኛል። የሰለፊ እስልምናን ምንነትና የመስፋፋት ዓላማ በውል ያልተገነዘቡ፤ ከዚያም አለፍ ሲል በጭፍን የጥላቻ ፖለቲካ የታወሩና ስልጣን በቦሌ ወይም በባሌ እጃችን ይግባ እንጂ የሚሉ የጥፋት ተባባሪዎች የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መብት ይከበር ከሚሉ ሰይፍ አምላኪ ሰለፊዎች ጋር  ቀንና ሌሊት ሲጮሁ መስማት አሳዛኝ ነው።  የኢትዮጵያ መንግሥት አንባ ገነን ስለሆነ እንታገለዋለን ማለት አንድ ነገር ነው። እስልምናው ውስጥ ያሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን እየተቃወሙት ሳለ የእስልምና መብት ተከራካሪ ለመሆን የሚፈልጉ ሃይማኖት የለሾች ለእስልምና እንታገላለን ሲሉ ነገሩን አስገራሚ ያደርገዋል። ሰለፊዎች እስልምናን በኢትዮጵያ ውስጥ ለማራመድ በህግ ወይም ያለህግ  ታገድን ሳይሆን እያሉ ያሉት አሁን ያሉትን መጅሊሶች እናውርድ  ነው። ጥያቄውን ከሃይማኖት መብት ጋር በማስተሳሰር የመብቴ ተነካ ጩኸት በማሰማት ከሚመኙት ግብ ለመድረስ የሚደረግ ሩጫ እንጂ እስልምናን  እንደሃይማኖቴ እንዳላመልክ ተከልክያለሁ አይደለም የሚለው።  የመጅሊሱ ችግርና የአዲስ መጅሊስ ምርጫ ፈላጊዎች ማንነት በተነጻጻሪ የሚታይ ነገር እንጂ በዘመቻና በሆ በለው የሚተገበር አድርጎ ማቅረብ ጉዳዩን አጡዞ ሀገር ዐቀፍ ለማድረግ በመሞከር እቅዱ እስኪሳካ መሄድ የተፈለገበትን መንገድ የሚጠቁም እንደሆነ ያሳያል። መጅሊሱን በዓላማው አስፈጻሚ ሰዎች ከቀማ በኋላ በሚጫንለት የፔትሮ ዶላር አክራሪነት መኪና እንደፈለገ ለመሽከርከር ተፈልጎ መሆኑ ለመረዳት ከማንነት ባህሪው መረዳት አይከብድም።

ብሎጋችንን ኢትዮጵያ ውስጥ አንዳትታይ መደረጉ አሁንም ቢሆን እውነት ነው፡፡


 የማቅን ውስጠ ምስጢር ፈልፍላ በማውጣት ከፍተኛ መደናገጥን በመፍጠር ላይ ያለችውን ዓውደ ምሕረት ብሎግ በኢትዮጵያውስጥ እንዳትታይ ከተደረገች ሳምንታት ተቆጥረዋል። አባ ሰላማ ብሎግ የችግሩን ግዝፈት በመጥቀስ በገጹ ካወጣው በኋላም ቢሆን  የዓውደ ምሕረት መዘጋት እስካሁን መፍትሄ አላገኘም። ይህንን ጉዳይ የማቅ ብሎጎች በሬ ወለደ ለማለት ጊዜ ባይፈጅባቸውም የአዘጋገባቸው ቃና ያስገነዘበን ነገር ቢኖር ለምን ድርግም ብላ አትቀርም የሚል ምኞትን ያረገዙ ይመስላል። ምክንያቱም በእውነት «ዓውደ ምሕረት» እንዳትታይ ከተደረገ ሳምንታትን ያስቀጠሩ ሆነው ሳለ ነገረ ስላቅን ማቅረብ የጠላት አሰራር ጥልቅ መሆኑን ያመላክታል። መረዳት የሚገባን ነገር ቢኖር «እውነት አናቷን ሲቀብሯት በጭራዋ ብቅ እንደምትል ማወቅን ለአፍታም መዘንጋት አይገባንም።

የዓውደ ምሕረት ዘገባ ከታች ቀርቧል።

ብሎጋችንን ኢትዮጵያ ውስጥ አንዳትታይ መደረጉ አሁንም ቢሆን እውነት ነው፡፡
የሀገር ውስጥ አንባቢያን አዲሱን አድራሻ www.awdemihret.wordpress.com ተጠቀሙ፡፡
(ነሐሴ 5 2004 .. ዐውደ ምሕረት/ www.awdemihret.blogspot.com / www.awdemihret.wordpress.com )  ብሎጋችን አውደ ምህረት በኢትዮጵያ ውስጥ እንዳትታይ ከተደረገች ዛሬ ሁለት ሳምንት ሆናት፡፡ አድራሻችንን ማለትም www.awdemihret.blogspot.com ማንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ሰው ለመክፈት ቢሞክር የሚያገኘው መልስ No data received Unable to load the webpage because the server sent no data.  የሚል ነው፡፡ ይህ ማለት በግልጽ አማርኛ ብሎጉ እንዳይከፈት ተደርጓል ማለት ነው፡፡ ይህንን እውነት አባ ሰላማ በመዘገብዋአቤት ውሸትሲል አንድ አድርገን ለመተቸት ሞክሯል፡፡ የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያድርቅ እንደሚባለው ሳልዋሽ ቀኑ እንዳይመሽብኝ እያለች የምትሰጋው አንድ አድርገን የምትዋሽበት ጉዳይ ስታጣ ፍጥጥ ካለው እውነት ጋር መታገል ጀምራለች፡፡ ብሎጋችን ኢትዮጵያ ውስጥ አለመስራትዋን አሁንም ቢሆን ማንም ኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ሰው ሊያየው የሚችለው ሀቅ ነው፡፡
አንድ አድርገንብሎጉ ሳይዘጋ ተዘግቷል ይላሉስትል ጽፋለች፡፡ ማንም አንባቢ እንደሚያስተውለው ግን ብሎጋችን ተዘግቷል የተባለው ስለተዘጋ ነው፡፡ እኛ እንደእናንተ ልናገኝ የምንችለው ፖለቲካዊ ትርፍ ስለሌለን እንዲህ ያለ ውሸት አንዋሽም ስለማኅበረ ቅዱሳን የምንጽፈው የሆነውን ነው፡፡ እኛን ዋሻችሁ ለማለት ምክንያት ያገኛችሁ መስሎዋችሁ ነበር ነገር ግን እናንተ የራሳችሁን ውሸታምነት ነው የገለጻችሁት፡፡

በሬ ወለደ የእናንተ ስም እንጂ የእኛ አይደለም፡፡ ብዙ ብዙ ብዙ በሬዎችን አስወልዳችኋል በርካታ ግመሎችን በመርፌ ቀደዳ አሳልፋችሁኋል፡፡ አላማችሁ ሀሳባችሁ መንፈሳዊነታችሁ ሁሉ የተመሰረተው በውሸት ነው፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ብሎጋችን ላይ የሚወጡት ዜናዎች ራስ ምታት ስለሆኑበት መረጃ የሚሰጠው ማነው እያለ በስብሰባ ራሱን እንደሚያደክም እናውቃለን፡፡ የብሎጉ ባለቤት እገሌ ነው እገሌ ነው የለም እገሌ ነው እያለ ወሬ የሆነመረጃእንደሚያሰባስብም እናውቃለን፡፡ ብሎጉን ለማዘጋት አይደለም ሌላም እድል ቢኖረው ከማድረግ ወደ ኋላ አይልም፡፡
ብሎጎችን ኢንሳም ይዝጋው ማንም ማኅበረ ቅዱሳን እዛ ውስጥ ሰው አያጣም፡፡ እነዛን ሰዎች ተጠቅሞ ብሎጉን ከማዘጋት ወደ ኃላ አይልም፡፡ በዛ ላይ ብሎጉ ለምን ተዘጋ ብሎ ጥያቄ የሚያቀርብ አካል እንደማይኖርም ያውቃል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ያለውን ብሎግ ማዘጋት ከባድ አይደለም፡፡