የሙስሊም ወንድማማቾች መሪና በሙባረክ ዘመን ከርቸሌ ወርደው የነበሩት ሙሐመድ ሙርሲ ስልጣን ላይ ይወጣሉ ተብሎ ከተፈራበት ጊዜ አንስቶና ስልጣኑ ላይ ከተፈናጠጡ ጀምሮ የግብጽ ክርስቲያኖች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ። ከግብጽ ክርስቲያኖች ውስጥ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ አማኞች እስከ 15 ሚሊዮን በሀገር ውስጥ ሲኖሩ ወደ 2 ሚሊየን የሚጠጉት ደግሞ በተለያዩ ዓለማት ውስጥ ተሰደው ይገኛሉ። እስከ 640 ዓ/ም ድረስ የግብጽ ሕዝብ 100% የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የነበረ ሲሆን በእስልምና ወረራና መስፋት የወደደ በውድ፤ ያልፈለገ በግድ እስልምናን እንዲቀበል ተደርጎ፤ የተረፈውም የእስልምናን የበላይነትና የሚጣልበንት ቅጣት ለመቀበል የመስማማት ውል ገብቶ እንደክርስቲያን ለመኖር የቻለ ቢሆንም ከመገደል፤ ከመሰደድና ንብረቱን ከመቀማት አላመለጠም ነበር። ከጋማል አብደል ናስርና፤ በይበልጥም በሁስኒ ሙባረክ አገዛዝ ዘመን የተሻለ ዋስትና የነበራቸው ቢሆንም ከግብጹ የአመጽ እንቅስቃሴ ወዲህ ነገሮች ሁሉ ተለዋወጠው ኮፕቲኮቹና የሶሪያ ኦርቶዶክስ፤ የግሪክ ኦርቶዶክስ፤ የሮማ ካቶሊክ፤ ፕሮቴስታንትና ሌሎች ክፍሎችም ቁጥራቸው ትንሽ የማይባሉ ክርስቲያኖች አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ወድቀው ይገኛሉ። ይህ አደገኛ ሁኔታም በመረቀቅ ላይ ባለው አዲሱ የግብጽ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 2 ላይ እስልምና የመንግሥቱ ሃይማኖት መሆኑን በማስቀመጡ የተነሳ ነው። ይህም ማለት ይላል «ክሪስቲያን ፖስት» ጋዜጣ ህግ አውጪው ህጎችን የሚያወጣው በእስልምና ሃይማኖት መሰረትነት ላይ ስለሆነ በአጭር ቃል የሀገሪቱን ህግ የሸሪአ ህግ ይመራዋል ማለት ነው ይለናል።
በዚህ የእስልምና ህግ ስር ክርስቲያኖች ለመኖር የሚችሉት እስልምናው በሚፈቅድላቸው መንገድና መጠን ስለሚሆን በሀገሪቱ ውስጥ እንደዜጋ ሳይሆን እንደባሪያና አሳዳሪ ስርዓት የመኖር ግዴታን የሚቀበሉ ይሆናሉ ማለት ነው። መሐመድ ሙርሲ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት እንደሚያቋቁሙ ቃል ቢገቡም እየሆነ ያለው ግን ዲሞክራሲውን የሚለካው የመንግሥቱ ሃይማኖት እንጂ የዜጎች ሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች እንዳይደሉ እየታየ ነው።
በሸሪአ ህግ መሰረት የሰረቀ እጁን እያፈራረቁ መቁረጥ፤ በዝሙት የተገኘ በድንጋይ ተደብድቦ መገደል፤ ከእስልምና ወደክርስትና የገባውን አልመለስም ካለ ማረድ፤ እንዲቀየር ያባበለውን ዛፍ ላይ መስቀል ወዘተ ቅጣቶች ክርስቲያኖችን ይጠብቃቸዋል ወይ? ለሚለው ጥያቄ እስካሁን በይፋ የተነገረ ባይሆንም የእስልምና መንግሥት እስከተቋቋመ ድረስ ይህ መሆኑ ስለማይቀር ብዙዎቹን ክርስቲያኖች ድንጋጤ ላይ ጥሏቸዋል።
ሰላፊዎች የሸሪአ ህግ በሀገሪቱ እንዲተገበር ጫና እየፈጠሩ ሲሆን ክርስቲያን የሆነ ማንም በእስልምናው መንግሥት ውስጥ መስራት የለበትም የሚል አክራሪነት እያወጁ ይገኛሉ። ምንም እንኳን በቀጥታ ክርስቲያኖችን ወደእስልምና ማምጣት እንደማይችሉ ቢያምኑም ሰለፊዎች የሚያደርጉት ግፊት ክርስቲያኖች መጪውን ጊዜ በመፍራት ሀገሩን እየለቀቁ ወደምእራቡ ዓለም እንዲሰደዱ ተጽእኖ የማድረግና ፍርሃትን የማስፈን ስራ እየሰሩ እንደሆነ ተገምቷል።
ይህ እንቅስቃሴ በገፍ በሚፈሰው የፔትሮ ዶላር ድጋፍ አፍሪካን በሸሪአ የመንከር ትልቁ ዘመቻ አካል ሲሆን ግብጽን በምታክል ትልቅ የዐረቡ ሀገር ምሳሌ ውስጥ ክርስትና እንዴት ይታሰባል? የሚል ቁጭት አላቸው። አህመድ ዲዳት የሚባል የእስልምና ቀንደኛ ሰባኪ በአንድ ወቅት ግብጽ የዐረብ ሊግ ዋና ተጠሪ ሆና ሳለ በግብጽ ውስጥ ሚሊዮኖች ክርስቲያኖች መኖራቸው የሙስሊሙ ዓለም የስንፍና ውጤት ነው በማለት በቁጭት ሲናገር መደመጡ የቁጭቱ ጣሪያ የት ድረስ እንደሆነ ያሳያል።
ከሊባኖሱ ሂዝቦላህ፤ ከፓለስቲናው ሃማስ እና የመሐመድ ሙርሲው ብራዘር ሁድ የተሳሰረ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ቁርኝት እንዳላቸው ስለሚታወቅ መካከለኛው ምሥራቅን በዚህ የሰለፊ ባህር ውስጥ የመንከር ስውር ዘመቻ አንዱ ክፍል በግብጽ ላይ መቀመጡ የክርስቲያኖቹን መጪ ዘመን ከባድ ያደርገዋል። እስልምናዊ መንግሥት ማለት የዚያ ትግል ውጤታቸው ነው።
የዚሁ ዘመቻ ዋና አካል የሆነው የሰለፊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ውስጥ ዘመቻውን እያጧጧፈ ይገኛል። የሰለፊ እስልምናን ምንነትና የመስፋፋት ዓላማ በውል ያልተገነዘቡ፤ ከዚያም አለፍ ሲል በጭፍን የጥላቻ ፖለቲካ የታወሩና ስልጣን በቦሌ ወይም በባሌ እጃችን ይግባ እንጂ የሚሉ የጥፋት ተባባሪዎች የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መብት ይከበር ከሚሉ ሰይፍ አምላኪ ሰለፊዎች ጋር ቀንና ሌሊት ሲጮሁ መስማት አሳዛኝ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት አንባ ገነን ስለሆነ እንታገለዋለን ማለት አንድ ነገር ነው። እስልምናው ውስጥ ያሉ ብዙ ኢትዮጵያውያን እየተቃወሙት ሳለ የእስልምና መብት ተከራካሪ ለመሆን የሚፈልጉ ሃይማኖት የለሾች ለእስልምና እንታገላለን ሲሉ ነገሩን አስገራሚ ያደርገዋል። ሰለፊዎች እስልምናን በኢትዮጵያ ውስጥ ለማራመድ በህግ ወይም ያለህግ ታገድን ሳይሆን እያሉ ያሉት አሁን ያሉትን መጅሊሶች እናውርድ ነው። ጥያቄውን ከሃይማኖት መብት ጋር በማስተሳሰር የመብቴ ተነካ ጩኸት በማሰማት ከሚመኙት ግብ ለመድረስ የሚደረግ ሩጫ እንጂ እስልምናን እንደሃይማኖቴ እንዳላመልክ ተከልክያለሁ አይደለም የሚለው። የመጅሊሱ ችግርና የአዲስ መጅሊስ ምርጫ ፈላጊዎች ማንነት በተነጻጻሪ የሚታይ ነገር እንጂ በዘመቻና በሆ በለው የሚተገበር አድርጎ ማቅረብ ጉዳዩን አጡዞ ሀገር ዐቀፍ ለማድረግ በመሞከር እቅዱ እስኪሳካ መሄድ የተፈለገበትን መንገድ የሚጠቁም እንደሆነ ያሳያል። መጅሊሱን በዓላማው አስፈጻሚ ሰዎች ከቀማ በኋላ በሚጫንለት የፔትሮ ዶላር አክራሪነት መኪና እንደፈለገ ለመሽከርከር ተፈልጎ መሆኑ ለመረዳት ከማንነት ባህሪው መረዳት አይከብድም።