Thursday, August 9, 2012

ማኅበረ ቅዱሳንን ሲኖዶስ አላዋቀረውም፤ ማኅበሩን በአክራሪነት መፈረጅም ቤተክርስቲያንን መፈረጅ አይደለም!


የዚህ አክራሪ ማኅበር ድረ ገጽ ብጹእ አቡነ እስጢፋኖስ የተናገሩት ነው በማለት እራሱን የሲኖዶስ ተጠሪና የቤተክርስቲያኒቱ ራስ የሆነ ያህል ክብር እንደተሰጠው በመቁጠር «ቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ አውጥቶ ያዋቀረውን ማኅበር በአክራሪነት መፈረጅ ቤተ ክርስቲያንን መፈረጅ ነው» ብለዋል ሲል የእወቁልኝ ዜና ለመስራት ሞክሯል።
የተወሰደው ቃል:
«በጉባኤው ማጠቃለያ ላይም ብፁዕነታቸው ባስተላለፉት መልእክት በአንዳንድ ግለሰቦችና ድርጅቶች ቅዱስ ሲኖዶስ ሕግ አውጥቶ ያዋቀረውን ማኅበረ ቅዱሳንን በአክራሪነት ስም መፈረጅ ቤተ ክርስቲያንን መጥቀስ በመሆኑ ይህን የሚያደርጉ አንዳንድ አካላት ከድርጊታቸው መታረም እንዳለባቸው አሳስበዋል»
በመሠረቱ ማኅበሩ ራሱ ለደርግ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ብላቴ የጦር ካምፕ ውስጥ ተመሰረትኩ፤ የዳቦ ስሜንም አቡነ ገብርኤል «ማኅበረ ቅዱሳን» ብለው ሰጥተውኛል እያለ በአዋጅ ሲናገር አቡነ እስጢፋኖስ የለም፤ እኛ ሲኖዶሶች ነን የቆረቆርንህ ሊሉ አይችሉም።   የሕይወት ታሪኩ ስለሚታወቀው ማኅበር አፋቸውን ሞልተው ሲኖዶስ ነው የመሰረተው ይላሉ ብለን አንገምትም። ብለው ከሆነም ስህተት ስለሆነ ተቀባይነት የለውም። እውነቱ ግን ማኅበረ ቅዱሳን በድሮው አቶ፣ በኋለኛው ቄስ እንትና የሴቶች ድንግልና የተመሰረተ መሆኑን ጋዜጠኛ ግዛው ዳኜ በፖሊስ ፕሮግራም ላይ ዜና እንደሰራበት የሚዘነጋ አይደለም።
አቡነ እስጢፋኖስ ማኅበረ ቅዱሳንን የመሰረተው ቅዱስ ሲኖዶስ ነው ብለው ከሆነ መቼ፤ የት፤ እንዴትና ለምን? ተብለው ቢጠየቁ መልሳቸው ምን ይሆናል? ቅዱስ ሲኖዶስ እንደማኅበር ይንቀሳቀስ ዘንድ መተዳደሪያ ደንቡን ስላጸደቀለት እኛ ነን ያደራጀነው ሊሉ አይችሉም። ራሱ ተደራጅቶ በመምጣት እውቅና ስጡኝ ብሎ በጠየቀ ማኅበርና ሲኖዶስ ራሱ ወጣቶችን  በመጥራትና በማቋቋም፤ እንደማኅበር በማዋቀር ይሰራ ዘንድ በማሰማራት መካከል ትልቅ ልዩነት አለ።  ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን በንጹሃን ሴቶች ደም ጭዳ፤ በእነቄሱ በኩል የተመሰረተና ጥቂት የዋሃንን በማሰባሰብ የተቋቋመ፤ በኋላም ቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ሰተት ብሎ በመግባት ያለከልካይ መተኛት እንዲችል፤ የመተዳደሪያውን ቁርበት አንጥፉልኝ ያለ  የጅብ እንግዳ ማኅበር ነው። ከዚህ የወጣ የምስረታ ታሪክ የለውም።
ሌላው አስገራሚውና  ምስክርነት ተሰጠኝ በማለት ጅቡ ያቀረበው የውሸት ቃል፤  «ማኅበሩን በአክራሪነት መፈረጅ፤ ቤተክርስቲያንን መፈረጅ ነው» የሚለው የጅቡ የጩኸት ድምጽ በቤተክርስቲያኒቱ ከለላ ለመብላት ያዘጋጃቸው ጠቦቶች እንዳሉ ያመላከተ ፍንጭ ሊሆን ይችላል። ምክንያቱም እኔን መንካት ቤተክርስቲያንን መንካት በመሆኑ በእኔ ላይ ክፉ ነገር የምትጎነጉኑ ሁሉ በየትኛውም ዓለም የቤተክርስቲያኒቱ ክፍል ውስጥ የምትገኙ ሁሉ  ወዮላችሁ! ከመበላት አትድኑም በማለት ራሱን በማግዘፍ ለጥፋት የመዘጋጀቱ ምልክት ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። ከዚያ ባሻገር ብላቴ ላይ የተቋቋመ የጎረምሶች ቡድን ቢነካ ቤተክርስቲያኒቱ እንደተነካች የሚቆጠርበት አንዳች ምክንያት ሊኖር አይችልም። ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ደም የዛሬ 2000 ዓመት ገደማ የተመሠረተች ሆና ሳለ የ20 ዓመቱ ጅብ ቁርበቱን አንጥፎ ውስጧ ስለተኛ ብቻ ራሱን የ2000 ዘመን ነባር እንግዳ አድርጎ ሊቆጥር የሚችልበት ምክንያት አይታየንም።

የማኅበረ ቅዱሳን ምንቸት ግባ፤ ማኅበረ ቅዱሳንን የምትቃወም ምንቸት ውጣ!!!



ብጹእ አቡነ ገብርኤልን ከአስመራ ሊቀጵጵስና ዘመናቸው ጀምሮ ስለእሳቸው በሲኖዶሱ አካባቢ የተባለውን ነገር ብዙ ብዙ ሰምተናል። ከዓመታትም በኋላ ምድረ አሜሪካ ከኮበለሉ በኋላም  ቢሆን ወያኔ ወይም ሞት ብለው ከተቃውሞ ጎራ መሰለፋቸውን በተለያዩ ሚዲያዎች አይተናል። አቡነ ጳውሎስን ቤተክርስቲያን እንደገባች እንትን…….  ሙልጭ አድርገው ሲያክፋፉ ተመልክተን፤ እንዴት ተደርገው ቢበደሉ ይሆን? ሊቀ ጵጵስናቸውን ግምት ውስጥ እስኪያገባ ድረስ ለዚህ ዓይነት አንደበት የበቁት ብለን ታዝበንም ነበር። በእርግጥ ይህ ተቃውሞ ሰልፍ በአሜሪካ ውስጥ እንደፖለቲካ ስደተኝነት የመኖሪያ ፈቃድ ለማስገኘት የሚያስችል የመረጃ ማጠናከሪያ መንገድ በመሆኑ ጥሩ ጥበብነቱን አድንቀን ተቀብለንላቸዋል።
የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት ከተቻለና የግል የገቢ ካፒታልን ማሳደግ የሚያስችል የቤተክርስቲያን ምስረታ ከተጠናቀቀ በኋላ ያገኙትን ገንዘብና ዝና ከጥሩ ነፋሻ አየር ጋር በነጻነት ለመተንፈስ ደግሞ በትውልድ ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ እንደመኖር ተመራጭና ለሚዛን የሚደፋ ሌላ ስፍራ ባለመኖሩ ብጹእ አባታችን አውጥተው፤ አውርደው ሁኔታዎችን ሲጠብቁ  የአሜሪካው ሲኖዶስ የጳጳሳት ሹመት የሚሰጥበትን ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው ወደ ውጤት በመቀየር፤ ሲኖዶስ ማለት በአቡነ ጳውሎስ የሚመራው ነው በሚል የተለመደ የተቃውሞ ጥበባቸው ከፓትርያርኩ ጋር የመደራደሪያ ሰነድ ለመጨበጥ ችለዋል።  በተቃዋሚነት ሰልፍ በመውጣት የመኖሪያ ፈቃድ ማግኘት እንደቻሉት ሁሉ፤ የአሜሪካውን ሲኖዶስም በመቃወም፤ ሲዘልፏቸው የነበሩትን የአባ ጳውሎስን ፓትርያርክነት 3600/ሶስት መቶ ስልሳ ዲግሪ/ ተገልብጠው ከእሳቸው ወዲያ ማንም የለም በማለታቸው ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ አዲስ የመኖሪያ ፈቃድ አግኝተው ሀገር ቤት መመለሳቸውን አይተናል። ባንድ ጊዜ ሁለት መኖሪያ ፈቃድ ማግኘት ብልጠትንና የታክቲክ ስፖርትን ማወቅ ይጠይቃል።
ስለእሳቸው ባህርይ መምህር ጽጌ ስጦታው «ይነጋል» በሚለው መጽሐፉ «ዘክልዔ ልብ» ሲል በደንብ አድርጎ የገለጸበት ነገር በእውነትም አንድ ቦታ የማይረጉ እንደዓሳ ጎበዝ ዋናተኛ መሆናቸውን ነው ።
አባ ገብርኤል ምንም እንኳን በክብር ደረጃቸው ጳጳስ ቢሆኑ ስህተት የማይጎበኛቸው ፍጹምና ቅዱስ መልአክ እንዳይደሉ ስለምናምን፤ በተሳሳቱት ነገር ተጸጽተው ለደረጃቸው የሚመጥንና ሌሎችም እሳቸው መልካም ነገር እንዳላቸው በማመን ሊማርና ሊመሰክርላቸው እንዲችል ቢያደርጉ የሚጠላ ማንም ባለመኖሩ አየር ጠባዩ ሲደብር ወደ አሜሪካ መሄዳቸውና አየር ጠባዩ ደግሞ ሲስማማቸው ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውን በራሱ እንደስህተት አይቆጠርም።
ይሁን እንጂ አባ ገብርኤል ሀገር ቤት ከተመለሱና ወደ ሀዋሳ ከዘለቁ በኋላ ግን እየሆነ ያለውና የሚታየው ነገር ጥሩ እንዳልሆነ መታየት ከጀመረ ሰንብቷል። አባ ገብርኤል የሃዋሳ ሕዝብ ሊቀ ጳጳስ እንጂ የማኅበረ ቅዱሳን ሊቀ ጳጳስ  እንዳልሆኑ እየታወቀ፤  የሥራቸው መጀመሪያ አድርገው የፈጸሙት ነገር አስገራሚ ነበር።  «ማኅበረ ቅዱሳንን የምትቃወም ምንቸት ውጣ፤ የማኅበረ ቅዱሳን ምንቸት በኔ ሀገረ ስብከት ግባ» የሚል ቡራኬ ለመስጠት ጊዜ አልፈጀባቸውም። ሸምቆ ወጊው ማኅበር በዚህ ቡራኬ ያገኘውን ፈቃድ አሜን ብሎ በመቀበል፤ እነ እገሌን ምቱልኝ፤ እገሌንም ውጉልኝ ለማለት ጊዜ አልፈጀበትም። ይህ ነጋዴ፤ ከፋፋይ፤ መሰሪ፤ ሸቃጭና አስመሳይ ማኅበር እንደ ባህር ዓሳው/ Octopus/ ሰላሳ የመርዝ ጭራውን እያወራጨ፤ የቤተክርስቲያን ልጆችን ከመድረክ አስወገደ። ከሥራ አባረረ። ሺዎች እስከዛሬ ድረስ ከቤተክርስቲያን ተሰደው በየቤታቸው ተቀምጠዋል። ለጸሎትና ለጋራ የመማማር መድረክ እንኳን የግልና የህዝብ አዳራሾችን ለመጠቀም ተገደው ይገኛሉ። አባ ገብርኤል ስለነዚህ ተሰዳጆች ሲጠየቁ ምን የሚሉ ይመስሏችኋል? ጥቂት አፈንጋጮች!!!!!!!!!!
እውን እዚህ ፎቶ ላይ በአንድ ወቅት የተሰበሰቡትና በማኅበረ ቅዱሳን መሪነት አባ ገብርኤል ያባረሯቸው ምእመናን ጥቂቶች ናቸው?
የፎቶ ምንጭ፤dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com

Sunday, August 5, 2012

ማሕበረ ቅዱሳን( ማኅበረ ሰይጣን) ጉባኤ አርድዕት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ከማንም በላይ ስጋት ላይ ጥሎኛል በማለት ለጳጳሳቱ 2.5 ሚሊዮን ብር በመበጀት የእግድ ደብዳቤ እንዲዘጋጅ አስደርጓል ተባለ።


ሐምሌ 30 2004 .. ዐውደ ምሕረት/ www.awdemihret.blogspot.com / www.awdemihret.wordpress.com) የቅርብ ምንጮቻችን እንደገለጡትጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የተሰኘው በአገር ውስጥና በውጭ አገር ባጭር ጊዜ በርካታ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን እየማረከና እያስከተለ የመጣውን ጉባኤ ለማሳገድ ማኅበረ ቅዱሳን ለጳጳሳቱ ጉርሻ የሚሆን 2.5 ሚሊየን ብር በጀት መደበ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የገንዘብ ምንጩ ከምን እንደሆነ እንዳይታወቅ እና ኦዲት እንዳይደረግ የሚታገለው ገንዘቡን እንዲህ ላለው ሕገ ወጥ ተግባር በስፋት ስለሚጠቀምበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የአመራር አካላትና ከፍተኛ ሊቃውንትን ማዕከል ያደረገው ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ በከፍተኛ ደረጃ እያካሄደው ባለው ቅዱስ ተግባር ምክንያት የማሕበሩ ደጋፊ የሆኑት ጳጳሳት ካህናት ሰባክያንና ምእመናንን ቀልብ እየሳበ በመምጣቱ ማኅበረ ቅዱሳንን የተለመደውን ድጋፍ እንዳያገኝ  እያደረገው መምጣቱ ታውቋል።
ከዚህ በፊት ሁሉንም የቤተክርስቲያኒቱ አካላት በተለያየ መንገድ እየከፋፈለ ቤተክርስቲያኒቱን ለውድቀት እያፋጠነ የቆየውና ያለው ማሕበረ ቅዱሳን በተለይ በአሁኑ ሰዓት ከአክራሪዎችና ከፖለቲከኞች ጋር ግንባር በመፍጠር እያካሄደ ያለውን እኩይ ተግባር እየተጋለጠበት በመምጣቱና በአገር ውስጥና በውጭ አገርም ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት በመምጣቱ ከዚህ ያድኑኛል ያላቸውን አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስንና አቶ ተስፋዬ ውብሸትን(የጠቅላይ ቤተክህነት /ሥራ አስኪያጅ) በመደበው በጅት በመደለል  በዋና ሥራ አስኪያጁ በአቡነ ፊልጶስ እና በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ ሕዝቅኤል አማካኝነትጉባኤ አርድእትንአናውቀውም ይታገድልን የሚል ደብዳቤ እንደሚያጽፉ የውስጥ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

 ከዚህ በፊት እንደገለጽነው አቶ እስክንድር  ከመንግሥት ሥራ ከተባረረ በኋላ ሙሰኞች ወደ የማይባረሩባት ቤተክህነት በመግባት ከግብረ አበሩ ጋር በመሆን ከፍተኛ ምዝበራ እየፈጸመ ያለ ግለሰብ ሲሆን በተለያየ ጊዜ ከማሕበረ ቅዱሳን የአመራር አካላት ጋር ባደረገው ስብሰባ ጳጳሳቱ የግል ቤት በመገንባትና በተለያየ ሥራ የተጠመዱ በመሆናቸው ገንዘብ ስለሚያስፈልጋቸው ለሁሉም የሚከፋፈል 2.5. ሚሊዮን  ብር ከመደባችሁ የእግድ ደብዳቤ ማጻፍ ይቻላል በማለት የማኅበረ ቅዱሳንን ሰዎች  ያሳመነ ሲሆን ጉባኤ አርድእትንም የሚመለከተውን የእግድ ደብዳቤ ለማጻፍ ቅድመ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ታውቋል። ገንዘቡን ለማግኘት  እነ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስና አቶ ተስፋዪ ውብሸት  የተጠቀሙበት ዘዴ አሁን ማሕበሩ  ይህንን ካላደረገ  ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ጉባኤው የጉባኤ አርድእትን መተዳደሪያ ደንብ ያጸድቅለታል። የሚል ሲሆን ይህም ከጉባኤ አርድእት ዓላማ ውጭ እንደሆነ ታውቋል። ምክንያቱም በጉባኤ አርድእት መመስረቻ ጽሑፍ እንደተገለጸው ጉባኤ አርድእት ጉባኤና የቤተክርስቲያኒቱ አካል በመሆኑ በአሏት ሕገ ደንቦች የሚመራ እንጂ  ማሕበር ስለአይደለ የሚጸድቅም ሆነ የሚታገድ መተዳደሪያ ደንብ ስለሌለው ነው፡፡
በመሆኑም  ሐሳብንም ሆነ መንፈስን ሊያግድ የሚችል አካል ስለሌለ ጉባኤው ሊታገድ የሚችል ነገር የለውም። የጉባኤ አርድእትን ራእይ ተልእኮና ዓላማ አግዳለሁ የሚል ካለ በአጠቃላይ የቤተክርስቲያኒቱን ሊቃውንትን ካህናትን ሰባክያንንና ዲያቆናትንን ከቤተክርስቲያኒቱ አስወግዳለሁ ብሎ እንደ መነሳት ነው።