ሐምሌ 30 2004 ዓ.ም.፣ ዐውደ ምሕረት/ www.awdemihret.blogspot.com /
www.awdemihret.wordpress.com) የቅርብ ምንጮቻችን እንደገለጡት “ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የተሰኘው በአገር ውስጥና በውጭ አገር ባጭር ጊዜ በርካታ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንን እየማረከና እያስከተለ የመጣውን ጉባኤ ለማሳገድ ማኅበረ ቅዱሳን ለጳጳሳቱ ጉርሻ የሚሆን የ2.5 ሚሊየን ብር በጀት መደበ፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን የገንዘብ ምንጩ ከምን እንደሆነ እንዳይታወቅ እና ኦዲት እንዳይደረግ የሚታገለው ገንዘቡን እንዲህ ላለው ሕገ ወጥ ተግባር በስፋት ስለሚጠቀምበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የአመራር አካላትና ከፍተኛ ሊቃውንትን ማዕከል ያደረገው ጉባኤ አርድእት ዘኦርቶዶክስ በከፍተኛ ደረጃ እያካሄደው ባለው ቅዱስ ተግባር ምክንያት የማሕበሩ ደጋፊ የሆኑት ጳጳሳት ካህናት ሰባክያንና ምእመናንን ቀልብ እየሳበ በመምጣቱ ማኅበረ ቅዱሳንን የተለመደውን ድጋፍ እንዳያገኝ
እያደረገው መምጣቱ ታውቋል።
ከዚህ በፊት ሁሉንም የቤተክርስቲያኒቱ አካላት በተለያየ መንገድ እየከፋፈለ ቤተክርስቲያኒቱን ለውድቀት እያፋጠነ የቆየውና ያለው ማሕበረ ቅዱሳን በተለይ በአሁኑ ሰዓት ከአክራሪዎችና ከፖለቲከኞች ጋር ግንባር በመፍጠር እያካሄደ ያለውን እኩይ ተግባር እየተጋለጠበት በመምጣቱና በአገር ውስጥና በውጭ አገርም ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት በመምጣቱ ከዚህ ያድኑኛል ያላቸውን አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስንና አቶ ተስፋዬ ውብሸትን(የጠቅላይ ቤተክህነት ም/ሥራ አስኪያጅ) በመደበው በጅት በመደለል
በዋና ሥራ አስኪያጁ በአቡነ ፊልጶስ እና በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ አቡነ ሕዝቅኤል አማካኝነት “ጉባኤ አርድእትን “ አናውቀውም ይታገድልን የሚል ደብዳቤ እንደሚያጽፉ የውስጥ ምንጮቻችን ገልጸዋል።
ከዚህ በፊት እንደገለጽነው አቶ እስክንድር
ከመንግሥት ሥራ ከተባረረ በኋላ ሙሰኞች ወደ የማይባረሩባት ቤተክህነት በመግባት ከግብረ አበሩ ጋር በመሆን ከፍተኛ ምዝበራ እየፈጸመ ያለ ግለሰብ ሲሆን በተለያየ ጊዜ ከማሕበረ ቅዱሳን የአመራር አካላት ጋር ባደረገው ስብሰባ ጳጳሳቱ የግል ቤት በመገንባትና በተለያየ ሥራ የተጠመዱ በመሆናቸው ገንዘብ ስለሚያስፈልጋቸው ለሁሉም የሚከፋፈል 2.5. ሚሊዮን
ብር ከመደባችሁ የእግድ ደብዳቤ ማጻፍ ይቻላል በማለት የማኅበረ ቅዱሳንን ሰዎች
ያሳመነ ሲሆን ጉባኤ አርድእትንም የሚመለከተውን የእግድ ደብዳቤ ለማጻፍ ቅድመ ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ታውቋል። ገንዘቡን ለማግኘት
እነ አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስና አቶ ተስፋዪ ውብሸት
የተጠቀሙበት ዘዴ አሁን ማሕበሩ
ይህንን ካላደረገ
ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት ጉባኤው የጉባኤ አርድእትን መተዳደሪያ ደንብ ያጸድቅለታል። የሚል ሲሆን ይህም ከጉባኤ አርድእት ዓላማ ውጭ እንደሆነ ታውቋል። ምክንያቱም በጉባኤ አርድእት መመስረቻ ጽሑፍ እንደተገለጸው ጉባኤ አርድእት ጉባኤና የቤተክርስቲያኒቱ አካል በመሆኑ በአሏት ሕገ ደንቦች የሚመራ እንጂ
ማሕበር ስለአይደለ የሚጸድቅም ሆነ የሚታገድ መተዳደሪያ ደንብ ስለሌለው ነው፡፡
በመሆኑም ሐሳብንም ሆነ መንፈስን ሊያግድ የሚችል አካል ስለሌለ ጉባኤው ሊታገድ የሚችል ነገር የለውም። የጉባኤ አርድእትን ራእይ ተልእኮና ዓላማ አግዳለሁ የሚል ካለ በአጠቃላይ የቤተክርስቲያኒቱን ሊቃውንትን ካህናትን ሰባክያንንና ዲያቆናትንን ከቤተክርስቲያኒቱ አስወግዳለሁ ብሎ እንደ መነሳት ነው።