«ሕመሙን የሸሸገ መድኃኒት የለውም» እንዲሉ አበው በአሜሪካ ምዕራብ ስቴቶች የአድባራት አስተዳዳሪዎችና ልዩ ልዩ ክፍል
ሠራተኞች በመካከላቸው ያለውን ፈውስ ያጣ በሽታ ምንነትና መንስኤ በማጥናት ውሳኔ ላይ ለመድረስ መወያየት ከጀመሩ ሰንብተዋል።
አንዳንድ ተሰብሳቢዎች ግን ስብሰባውንና የውይይቱን መንፈስ የሚደግፉ እየመሰሉ ውጤት ላይ ከመድረሱ በፊት መረጃ በማሹለክና
የስብሰባውን የውይይት መንፈስ በማጦዝ ጊዜ ሲገድሉ ታይተዋል። በቅዱስ ፓትርያርኩ በኩል ያላቸውን ተደማጭነት ለማስጠበቅ ጠቃሚ ሃሳብ
ለጉባዔው የሚያቀርቡ በመምሰልና በሌላ በኩልም በማኅበረ ቅዱሳን በኩል ያላቸውን ስውር ታማኝነት ላለማጣት በውይይት ወቅት ጊዜ በመፍጀትና አንድ ሃሳብ ላይ ችክ በማለት የሴራ ጥበባቸውን
ለማሳየት ሞክረዋል።
ስለሆነም ለካህናቱ የውይይት መንፈስ የምናቀርበው ሃሳብ በሰዎች ብዛትና ባላቸው ታዋቂነት ላይ እምነት ከመጣል ይልቅ
ውጤታማ ሃሳብ በሚያቀርቡና ሥራውን ተፈጻሚ ለማድረግ በሚተጉ ጥቂት በሳል ሰዎች ላይ በመመስረት ለመስራት መሞከሩ የተሻለ ነው።
ምክንያቱም ይህንን ቀና ሃሳብ የሚደግፉ ብዙ ካህናት ቢኖሩም እንኳን ሸምቆ ወጊው ማኅበር የስም ማጥፋት ዘመቻውን ይከፍትብናል ብለው
ይፈራሉ። አንዳንዶችም ከዚያ መሰሪ ማኅበር ጋር ሳይለያዩ እና በቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ሳይላተሙ አስመስለው መኖር የሚፈልጉ ስለሆኑ
እንደዚህ ዓይነት ጠቃሚና አስፈላጊ ስብሰባ ላይ ብዙ ሰው ለማሳተፍ መሞከር ትርፉ መረጃ እያሾለኩ እንጀራቸውን የሚጋግሩ ሆድ አደሮችን
ማፍራት ስለሆነ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል።
እንደሚታወቀው ማኅበረ ቅዱሳን በአሜሪካ ባሉት አድባራት ውስጥ በፈለፈላቸው ተባይ ደጋፊዎቹ አማካይነት በየአድባራቱ ጉባዔ
ውስጥ ሃሳብ በመጠምዘዝ፤ ካህናቱን በማከፋፈል፤ ሽኩቻ የሚፈጥር አጀንዳ በማስነሳት እንቅፋት ሲፈጥር መቆየቱ ያታወቃል። የትም ቦታ
የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊዎች እስካሉ ድረስ ሁከትና ብጥብጥ አለ። ሀገሩ የሕግ ሀገር መሆኑ በጀ እንጂ እንደማኅበሩ መሰሪ አባላቱ
አካሄድ የቤተክርስቲያን ኃላፊዎች ማኅበሩን ነቅፈውና ተቃውመው አንድም ቀን ስራቸው ላይ መቆየት አይችሉም ነበር። አስተዳዳሪዎች
አሜን ብለው እጃቸውን በመስጠት ኪሳቸውን ማስቦጥቦጥ ይጠበቅባቸዋል። እምቢ ካሉ ደግሞ የስድብና የስም ማጥፋት ዘመቻ ይከፈትባቸዋል።
አሁንም እየታየ ያለው እውነታ ይህንን ያመላክታል።
ከዚህ በፊት ባቀረብነው ጽሁፋችን እንዳነሳነው የላስቬጋስ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ጢም አልባው መነኩሴ የማኅበሩን ጭነት
ተሸክሞ እየተንገዳገደ ሲበጠብጥ፤ የደብሩን አስተዳዳሪ አስፈንጥሮ ለመጣልና በአቡነ ፋኑኤል ላይ የተልእኰ ዘመቻውን በመክፈት ደብዳቤ
ሲጽፍ ከመቆየቱ ባሻገር አሁንም ደግሞ አጠናክሮ መቀጠሉ ይሰማል።