ሐምሌ
19 2004 ዓ.ም.፣ ዐውደ ምሕረት/www.awdemihret.blogspot.com)
(ይህን ጽሁፍ ያገኘነው ፌስቡክ ላይ ነው። ጸሀፊው ራሱን “ማህበሩ ውስጥ ሆነን የማህበሩን አደጋ ገልጠን የጠቆምን የቁርጥ ቀን የቤተክርስቲያን ልጆች” ሲል ይገልጻል። ጸሃፊው አለኝ በሚላቸው መረጃዎች መሰረት ጽሁፉን አዘጋጅቷል። የማኅበሩን የኑፋቄ ትምህርት ጨምሮ ጊዜ የምጠብቅላቸው ሌሎች መረጃዎች አሉኝ የሚለው ጸሐፊ እንደ ውስጥ አዋቂ የማኅበሩ እቅዶች እነዚህ ናቸው ሲል ይነግረናል። እንደ ጸሐፊው እምነት ማኅበሩ ከቤተክርስቲያን ተገንጥሎ እስከ መውጣት የጨከነ “ራዕይ” ያለው ነው። ለዚህም የሚረዳውን ጥናት የጨረሰ ሲሆን ተጨማሪ ጥናቶችን ለማድረግ ግብጽ ድረስ ሰው ልኳል ይለናል። በብሎጋችን እንዲወጡላችሁ የምትፈልጉዋቸው ጽሁፎች ካሉዋችሁ
awdemihret@live.com ብላችሁ
ብትልኩልን ይደርሰናል። መልካም ንባብ)
ማህበረ
ቅዱሳን ሁለት አይነት እቅድ አለው። አንደኛው ቤተክርስቲያኒቱን መቆጣጠር ሲሆን አሱ ካልተሳካ ደግሞ ሁለተኛውን ማለትም ሂደቶችን አይቶ በቂ የሚለውን አቅም ከገነባ በኃላ ወደፊት ተገንጥሎ የመውጣት ድብቅ ራዕይ አለው፡፡ ሁለተኛው አላማውም በቤተክርስቲያን ላይ አደጋ ለመፍጠርና አባላቱን ይዞ የራሱን ቤተ እምነት መመስረት ሲሆን ጉዞውን 40 በመቶ አድርሷል፡፡ ይህን እቅዱን ለማሳካት የተጠና እስትራቴጂ አዘጋጅቶ ተግባር ላይ አውሏል፡፡
ከእቅዶቹ ዋና ዋናዎቹ እንደሚከተሉት ይቀርባሉ
1- ወደፊት
ማህበሩ ቤተክርሰቲያኒቱን ከተቆጣጣረ ወይም ደግሞ ከተገነጠለ የራሱ አገልጋዮችን ብቻ መጠቀም ስለሚፈልግ ለሚገነጥለው ቤተ እምነት አገልጋይ እንዲሆኑ ካህናትንና መነኮሳትን በገዳማትና በአብነት ት/ቤቶች በጥንቃቄ ማሰልጠን እንዲቻል ከፍተኛ በጀት መድቧል፡፡ ይህን ስውር ተልእኮ ሊቃነ ጳጳሳቱ ነቅተው እንዳያስቆሙት በዘዴና በጥንቃቄ መያዝ
2- ጵጵስና
ለቀሳውስት እንዲሰጥ በቅ/ሲኖዶስ ግፊት እንዲያደርጉ የማህበሩ አባላት የሆኑ ጥቂት ጳጳሳትን ማሳመን በዚህ ጉዳይ ጥናት እንዲሰሩ ስንታየሁ የተባሉ አንድ ቄስ ግብጽ ሃገር ተልከዋል፡፡
3- በቅዱስ
ሲኖዶስ ውስጥ የማህበሩን አላማ በስውር የሚያስፈጽሙ ጳጳሳት እንዲሾሙ ማህበሩ መነኮሳትን መልምሎ በምርጫው ግዜ አባቶች ድምጽ እንዲሰጣቸው በየቤታቸው እየዞሩ የማግባባት ስራ መስራት፡፡ ማግባባቱ ለሃገረስብከታቸው እስከ ሁለት መቶ ሺ ብር በጀት ድጎማ ማድረግን፣ በግል እጅ መንሻ ማዘጋጀትን በአንዳንድ በልማት እቅዶቻቸው ውስጥ የማማከር ድጋፍ ማድረግን ይጨምራል፡፡ ለቤተክርስቲያን ቢጠቅሙም ለማህበሩ አካሄድ ግን አደገኛ ናቸው ያሏቸው አባቶች እንዳይሾሙ አባላት በሆኑ ጥቂት አባቶች በኩል መታገልና በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ወቅት በእያንዳንዱ ሊቃነ ጳጳሳት ማረፊያ ተሰሚ የሆኑ አባላትንና አንዳንድ ባለጸጎችን በመላክ የማሳመን ስራን መስራት፡፡ እንቢ ያሉትን ማስፈራራት
4- የማህበሩን
አካሄድ ትክክል አይደለም መታየት አለበት የሚሉ ጳጳሳትን ሰባኪያንን የአስተዳደር ሰዎችንና የመንግስት አካላትን ህዝቡ እንዲጠላቸው መናፍቃን ሆነዋል ተወግዘዋል ሌላ ተልእኮ አላቸው ወዘተ የመሳሰሉትን ቀለሞች በመቀባት ሃይላቸውን ለማድክም መሞከር፡፡ ይህን በአሜሪካና በአውሮጳ በገንዘብ የሚደግፍ ኮሚቴ በነያሬድ ገ/መድህን በነዳንኤል ክብረት በነህብረት የሺጥላ በነፋንቱ ወልዴ በነዶ/ር መስፍን የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው የማህሩን የጥፋት አላማ የሚያደናቅፉትን ሁሉ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድባቸው በፋይናንስ መደጎም ሲሆን በስውር ሲዲ እያዘጋጁ መበተን፣ ስብሰባ እያዘጋጁ ባለጠጎችን ቤተክርስቲያን ልትፈርስ ስለሆነ እንድረስላት ገንዘባችሁን ስጡን በማለት የማህበሩን አቅም ማደራጀት፣
5- ለጥምቀት
ምንጣፍ የሚያነጥፉ የዋህ ወጣቶችን ቀስ ብሎ ወደ ማህበሩ በማስገባት ቤተክርስቲያን አደጋ ላይ ነች ድረሱላት በማለት የአመጽ ትምህርታቸውን አስተምሮ ወደ ነውጥ እንቅስቃሴ እንዲገቡ በማድረግ ተጨማሪ ሃይል እንዲሆኑ ማሰልጠን፣
6- በአዲስ
አበባ እና በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ የሰንበት ት/ቤቶች ሰርጎ መግባትና የማህበሩን መሰረት ማስፋት ካልተቻለ በየአጥቢአው ቢሮ በመክፈት ሰንበት ትምህርት ቤቶችን መበጥበጥ እና ማፈራረስ
7- በመንግስት
ፖለቲካ ውስጥ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነት በተጠና ሁኔታ ማጠናከር ይህም በሃገር ውስጥ ያሉ አባላት መንግስት እንዳይመታቸው የቤተክርስቲያኑን ጉዳይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ በውጭ ያሉት ግን የተለያዩ ሚዲያዎችን እየተጠቀሙ መንግስትን እንዲቃወሙ ተደርጎ እስትራቴጂው ተቀርጿል፡፡ ደጀ ሰላም፣ አንድ አድርገን፣ደቂቀ ናቡቴ፣ savewaldeba,
ecadforum … የተባሉትን
ድረ ገጾች በመጠቀም ጸረ ሰላም ቅስቀሳዎችን ማጠናከር ፡፡
8- ማህበረ
ቅዱሳንን ራሱን ችሎ እንዲወጣ የገንዘብ አቅሙን ቋሚ በሆነ ሁኔታ ማጠናከር ይህም የማህበሩን ህንጻ መገንባት፣የቤተክርስቲያን ልጆች በተለይ መንግስት ሰራተኞች ለቤተክርስቲያናቸው ሳይሆን ለማህበሩ አስራት አንዲከፍሉ ማድረግ፣ በተለያዩ ቦታዎች የንግድ ተቋማትን መመስረት፣ አንድ ባንክ በአባላቱ አክስዮን (እንቅስቃሴው ተጀምሯል።) መክፈት ወዘተ
9- በቤተክርስቲያን
መድረኮችና በግል ሚዲያዎች ላይ የህዝብን ሰላም የሚያውክ የጽንፈኝነት ቅስቀሳ ማጠናከር፡፡ ይህን እንዲመሩ የተወሰኑ መምህራንን መድቦ ጽንፈኝነትን በሃይማኖት ቤተሰቦች ላይ ሽብርን እና ቅራኔን በሃማኖቶች መካከል የማስፋት ስራን አጠናክሮ መቀጠል፣ እንዲሁም በአንዳንድ የአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ፣ ባህር ዳር፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ አርባ ምንጭ፣ደሴ፣ በአውሮፓ አሜሪካ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባሉ ትላልቅ አብያተክርስቲያናት ያሉ መምህራንን በጥቅም በመደለል በቤተክርስቲያን መድረክ ማህበሩን ማስተዋወቅ ችግር ተፈጥሯል፣ ቤተክርስቲያን መሪ የላትም ሲኖዶሱ የሞተ ነው መንግስት ቤተክርስቲያንን እየገደለ ነው እያሉ ሁከት በመፍጠር ህዝቡ እንዲታወክ ቤተክቲያንን እንዲሰለችና እረኞቹን ከበጎቹ ነጥለው ወደ አዲሱ ቤተእምነታቸው እንዲቀላቀሉ መሳብ
10- ቤተክርስቲያን በራሷ እንዳትተማመን
በስነ ልቦና ጦርነት ማሽመድመድ ይህም ጠንከረው የሚሰሩ ሰባኪዎቿንና ሰራተኞቿን በሃይማኖት ስም ከስሶ በማዳከም ፈሪ እንድትሆን ማድረግ ዝም ማሰኘት፡፡ ልጆቿን በየአሉበት ፈልጋ እንዳታስተምር ባገኘችው አጋጣሚ ሁሉ ሰብካ ወደ በረቷ መስብሰብ እንዳትችልማከላከል ፣ የንስሃ አባቶች እንኳ ልጆቻቸውን በየቤታው ሄደው እንዳያስተምሩ፣ በቤተክርስቲያን ግቢ የሚደረጉ ጉባኤዎችን የመናፍቃን እጅ አሉባቸውና ምእመናን እንዳይሄዱ ቅስቀሳ ማድረግ፣ማህበረ ቅዱሳን ከጠራው ጉባኤ ውጭ ሌሎቹ የተሳሳቱ አድርጎ ማቅረብ፣ መዝሙር እንዳይዘመር፣ ሰባኪዎችን ሁሉ ሰው እንዲፈራቸው፣ ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ ቤተክርስቲያን ዝም እንድትል እና ሌሎች እንዲቀድሟት ለማድረግ አባቶችንም ስርአት ተጣሰ ህግ ፈረሰ ብለው በማደናገር ለክፉ ተልኮአቸው ተባባሪ እንዲሆኑ ማድረግ።
