የማቅ አፈቀላጤ ስለሆነውና ከዳላሱ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ራሱን ስለገነጠለው
ቄስ መሥፍን ማሞ አዲስ የሥራ ፈጠራ ጉዳይ በ10/11/2004 ወይም በ(17/7/2012) ዓ/ም ዝርዝር ሀተታ ደጀብርሃን ብሎግ ማስነበቧ ይታወሳል። ከዚያም ስለ ላስቬጋስ ኪዳነ ምሕረት ጢም አልባው መነኩሴ ጥቂት ዳሰሳ አድርገን ወደምእራቡ
ክፍለ አሜሪካ ተጉዘን፤ በመምህር ወ/ሰማዕት ስለሚመራው ቅ/ሚካኤል ቤተክርስቲያን የማቅ ሰርጎ ገቦች እያደረሱ ስላለው የህውከት
አገልግሎትና የረጋውን ወተት የመበጥበጥ ተልእኰ ከጠቃቀስን በኋላ የካሊፎርኒያና የዲሲ አካባቢ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ አባታዊ
ጉብኝት ለማድረግ ወደ ሲያትል ደ/ም ቅ/ አማኑኤል ቤተክርስቲያን
እንደሚያመሩ ዘግበን እንደነበር ይታወሳል።
አስቀድመን እንደዘገብነው የማቅ ሰርጎ ገብ በጥባጮች፤
በሀገር ቤቱ እንቅስቃሴ እየተዳከሙ ሲመጡ የውጪውን ሀገረ ስብከት የመጠብጠጥ እቅድ ነድፈው፤ የቆየ ዐመላቸውን እየተገበሩ ይገኛሉ። በቅዱስ አማኑኤል ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ጉብኝት
ያደርጋሉን የሰማው መምህረ ህውከት ማቅ አንድም ቀን ተኝቶላቸው እንደማያውቀው ሁሉ አስቀድሞ ጆሮውን አቅንቶ የብጥብጥ አጁን በመዘርጋት
እንቅፋት መፍጠሩን ቅንጣት ሳያፍር «ደጀ ሰላም» የተባለው የማቅ ማእከላዊ ኰሚቴ ቃል አቀባይ ብሎግ ዘግቦ አስነብቦናል። ወደ ህውከትና ዐመጻ እንዲገቡ የሚቀሰቅሳቸውና የስህተት መንገድን አሰማምሮ
ስለቅድስና እንደመታገል አድርጎ በኅሊናቸው በመሳል የሚያነሳሳቸው ከሌለ በስተቀር ምእመናን የዋሃን ናቸው። ገንዘባቸውን፤ ጉልበታቸውንና
እውቀታቸውን ለአገልግሎት የሚያበረክቱትን እነዚህን የዋሃን የእግዚአብሔር ቤተሰቦችን ማቅ እንዴት መጠምዘዝና ለተፈለገው ዓላማ ማዋል
እንደሚቻል ብዙ የሥራ ልምድ ስላለው ይህንኑ ጥበበ ዐመፃውን በሲያትል አማኑኤል ቤተክርስቲያን ተግባራዊ አድርጎ ብጹእ አቡነ ፋኑኤልን የመቃወም ህውከት ለመፍጠር ሞክሯል።
እንኳን እምነት፤ ኅሊና ያለው ማንም ሰው የሚፈርደውና ጥያቄ ሊያነሳበት የሚገባው ነገር፤ ብጹእ አቡነ
ፋኑኤል በሀገረ ስብከታቸው ባሉ አድባራት ተዘዋውረው እንዳያስተምሩ የሚከለክላቸው ምንድነው? ቅዳሴ ቀድሰው፤ ቡራኬ ሰጥተው ከመመለስ
በስተቀር በደብሩ የውስጥ ሥራ ምን አድርገው ያውቃሉ? እያንዳንዱ ደብር የየራሱ አስተዳደር ያለውና በምእመናን የተቋቋመ እንጂ በብጹእ
አቡነ ፋኑኤል አይፈርስ፤ አይቋቋም!! ሲኖዶስ የሰጣቸውን ተልእኰ ከመወጣት ውጪ አድባራቱን ምን በድለዋል? ምእመናንስ
ቤተክርስቲያናቸው የምትሰጣቸውን መንፈሳዊ አገልግሎት ከማግኘት ውጪ ከዐመጻና ከብጥብጥ ምን ያተርፋሉ? እነዚህንና እነዚህን መሰል
ጥያቄዎች ብናቀርብ መልሱ ምንም ይሆናል! ከብጥብጥና ከዐመጻ ምእመናን ምንም አያተርፉም። ይልቁንም ከኋላ ሆኖ ድብቅ አጀንዳውን
እንደ ወፍ ጉንፋን/bird flu/ የሚረጨውና የሚበክለው ማቅ፤
1/ የአድባራቱ ተቆርቋሪ ሆኖ ራሱን በመሰየም መድረክ ከተቆጣጠረ በኋላ ገንዘብ
መዝረፍ፤ አላስቀርብ ካሉት ደግሞ በጥቅም የሚደልላቸውን መሥፍኖች በመፍጠር መገንጠል፤
2/ አባ ፋኑኤልን በሄዱበት ሁሉ እየተከታተለ
ማሳደድ የመጨረሻው ዓላማና ግቡ ስለሆነ ይህንኑ አሽክላ ሥራውን እስከእለተ ሞቱ መተግበር፤
3/ የፖለቲካ ሥራው ከሀገር ቤት ብዙም እያወላዳው
ባለመሆኑ ወደውጪው ዓለም ፊቱን በማዞር በየቦታው ማመስ፤ መበጥበጥና ጉንፋኑን ማራባት ሥራዬ ብሎ ተያይዞታል። የሲያትሉ ቅ/ አማኑኤል
ቤተክርስቲያንም ህውከት የዚያ ተግባሩ አንዱ ማሳያ ነው።