Sunday, June 24, 2012

ዘረኛ ያልሆነ ማን ነው?


Naod ቤተሥላሴ
www. naodlive.com

ዘረኝነት፤ ብሔርተኝነት፤ ጎሰኝነት፤ ጎጠኝነት፤ መንደርተኝነት፤ ቡድነኝነትየሚባሉ ነገሮች ሁሉ የፍርደ ገምድልነት (Injustice, prejudice) መጀመርያዎች እና መገለጫዎች ናቸው ብል ብዙ የተሳሳትኩ አይመስለኝም፡፡ ከዚህ ቀጥዬ የማነሳው ጥያቄ ግን ከላይ በርዕሱ የጠቀኩትን ጥያቄ ነው፡፡ ዘረኛ፤መንደርተኛ... ያልሆነ ማን ነው?

ከቤተክርስቲያን ስወጣ፤ አንድ ጓደኛዬ፤ ከሆነ ከማላውቀው ልጅ ጋር አብሮ ወደ እኔ ሲመጣ አየሁት፡፡ ከዚያ ‹‹ተዋወቀው፤ የአዲስ አበባ ልጅ ነው!›› አለኝ፡፡ የአዲስ አበባ ልጅ ካልሆነ ከእኔ ጋር መተዋወቅ የለበትም? አንተ ራስህ የአዲስ አበባ ልጅ ሳትሆን ተዋውቄህ የለም? ብዬ ልገስጸው ከጅዬ ነበር፡፡ ግን ያው ጨዋ ነኝና…‹‹የጎረቤቴ ልጅ ካልሆነ አልተዋወቀውም›› ብዬ ቀልጄ እንግዳውን ተዋወቅኩት፡፡ የፈራሁት ግን አልቀረም


ከተዋወቅኩት ልጅ ጋር ያለኝ ጠባያዊም ሆነ ልማዳዊ የጋራ ነገር ‹‹አዲስ አበባ መወለድ ብቻ›› ሆኖ ቀረ፡፡ ኮከባችንም፤ ጨረቃችንም፤ ቅዠታችንም የማይገጥም ሆነና ትውውቃችንን Abort አደረግነው፡፡ ይሄ ገጠመኝ እስከዛሬ ትዝ የሚለኝ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡

Friday, June 22, 2012

ካስቀኑት ያልቀረ እንደዚህ ነው ማስቀናት!!

 
አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በተ/ሃይማኖት ስም ስለሚጠሩ ሦስት ሰዎች ማንነትና ምንነት በሰፊው ጽፈው አኑረውልናል። የትኛው ተ/ሃይማኖት የጻቅድነትን ስያሜ፤ ከማን እጅ እንደተረከበና ይኸው ጥሪ በዘር ማንዘሮቹ በርስትነት ተይዞ እንዲቆይ በግዝት እንዲጸናና ዜና ታሪኩ በመላው ኢትዮጵያ በሰፊው እንዲናኝ ስላስደረገው ተ/ሃይማኖ ማንነት ፤ አፍ በሚያስይዝ ጽሁፍ ስውሩን ደባ አጋልጠው ለትውልድ በማስረዳታቸው ይህም አለ እንዴ? ብለን እንድንገረም ካደረጉን ቆይቷል።
አለቃ ኪዳነ ወልድ ስለሰውዬው ማንነት በነገሩን ወቅት ይህም አለ እንዴ? ብለን ዝም ከማለት ወይም የምንወደው ጻድቅ ተነካብን ብለን ከማኩረፍ ይልቅ ስለነገሩን ታሪክ እንዴትነት ፤የእውነተኛውንና  የጻድቁን ተ/ሃይማኖትን መንፈሳዊ ገድል  ስለቀማው  ሰው ማንነት፤ በማወቅ ብቻ ሳንወሰን ያንን መነሻ አድርገን ሌሎችን መረዳቶችም  እንድናገኝ ዓይናችን በመግለጣቸው ጭምር አመስግነናቸዋል።  ድሮ ከመጽሐፍ ቅዱስ ይልቅ ብዙ የምንታመንበት፤ ዘወትር የምንደግመው፤ ሰውነታችንን የምናሻሽበት፤ የጸሎት መጽሐፋችን የነበረውንም  የገድል መጽሐፍ እንድንመረምር እድል አስገኝተውልናል።
አለቃ ኪዳነ ወልድ ከታሪክ ጭብጥ ተነስተው ስለገለጿቸው፤ ስለሦስቱ ተ/ሃይማኖቶች ማንነትና ታሪክ ወደፊት ለማቅረብ እንሞክራለን። ለዛሬው ግን ለርእሳችን ወደመረጥነው ጉዳይ እናመራለን።
እግዚአብሔር በቅዱሳኖቹ እጅ ድንቅን አድርጓል። ፊትም፤ ዛሬም፤ ወደፊትም ይሰራል። ይህ ግን የሚያስደንቀውና የሚያስገርመው ሥራ የቅዱሳኖቹን ኃይል ሳይሆን ኃይሉን በእነሱ የገለጸ የእግዚአብሔርን ከሃሌ ኩሉነት/ ሁሉን ቻይነት/ የሚነገርበት ዜና  ነው። ይህንን እግዚአብሔር በቅዱሳኖች አድሮ የመሥራት ኃይሉን ቅዱስ ጳውሎስ በአንድ ወቅት ያጋጠመውን ሲገልጽልን፤  በኢቆንዮን ከተማ ውስጥ ከእናቱ ማህጸን ጀምሮ እግሩ የሰለለች ሆና የተወለደ በልስጥራንም በተባለ ስፍራ አንድ ሰው በፈወሰ ጊዜ፤ ህዝቡ ተገርሞ አማልክት ከሰማይ ሰው ሆነው ወርደዋል በማለት መስዋእት ሊያቀርቡላቸው በወደዱ ጊዜ እንዲህ አለ።
«ሐዋርያት በርናባስና ጳውሎስ ግን ይህን በሰሙ ጊዜ ልብሳቸውን ቀደው ወደ ሕዝቡ መካከል እየጮኹ ሮጡ፥ እንዲህም አሉ። እናንተ ሰዎች፥ ይህን ስለ ምን ታደርጋላችሁ? እኛ ደግሞ እንደ እናንተ የምንሰማ ሰዎች ነን፥ ከዚህም ከንቱ ነገር ሰማይንና ምድርን ባሕርንም በእነርሱም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ዘወር ትሉ ዘንድ ወንጌልን እንሰብካለን። እርሱ ባለፉት ትውልዶች አሕዛብን ሁሉ በገዛ ራሳቸው ጐዳና ይሄዱ ዘንድ ተዋቸው። ከዚህም ሁሉ ጋር መልካም ሥራ እየሠራ፥ ከሰማይ ዝናብን ፍሬ የሚሆንበትንም ወራት ሲሰጠን፥ ልባችንንም በመብልና በደስታ ሲሞላው ራሱን ያለ ምስክር አልተወም። ይህንም ብለው እንዳይሠዉላቸው ሕዝቡን በጭንቅ አስተዉአቸው» የሐዋ 14፤ 14-18

Wednesday, June 20, 2012

ቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎቹን አስመረቀ



(ምንጭ፦ ዐውደ ምህረት)
    መምህር አሰግድ ሳሕሉም ከተመራቂዎቹ አንዱ ነው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በስሯ ከምታስተዳድራቸው መንፈሳዊ ኮሌጆች መካከል አንዱና 69 ዓመት የዕድሜ ባለጸጋ የሆነው አንጋፋው ቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ በተገኙበት አስመረቀ። የምረቃ ፕሮግራሙ ደማቅ የነበረ ሲሆን ተማሪዎቹ ቤተክርስቲያንን በቅንንነትና በመልካም ሥነ ምግባር ለማገልገል ቃል ገብተዋል። አዳራሹ በተመራቂዎችና በቤተሰቦቻቸው የተሞላ የነበረ ሲሆን በእያንዳንዱ ተማሪ ፊትም የሚታየው ደስታ ስሜት ልዩ ነበር። በዕለቱ አባታዊ ቡራኬ የሰጡት  ቅዱስ ፓትርያርኩም  “…ያለፉትን ዘመናት መሰናክሎችን እያለፍን መምጣታችን ስለምናውቅ ያለፉትንም ያለፍነው በራሳችን ስላልሆነ አሻጋሪውን አምላክ ከሁሉ በፊት እናመሰግናለን። እናንተ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በኃላፊነት ላይ ነው ያላችሁት እያስረከብናችሁ ነው። በዚህ የተመደበ ሌላ ሥራ የለውም የወንጌል ሥራ በትርፍ ጊዜ የሚሰራ አይደለም። ሁሉንም የምንማረው በጊዜ ነው። ከዚህ በፊት ተምረው የወጡ ብዙ ናቸው። በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ያሉ የገቡትን ኪዳን ይፈጽሙ አይፈጽሙ ተመልካቹ አምላክ ነው። መለኮታዊ አደራ ስለሆነ።….” በማለት አባታዊ መልዕክት አስተላልፈዋል።