Sunday, June 10, 2012

ኢትዮጵያ ግብረሰዶምንና አራማጆቹ ምዕራባዊያንን አወገዘች !


‹‹ትልቁ ሀብታችን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ነው›› አቡነ ጳውሎስ

  ሪፖርተር ጋዜጣ፤ሰኔ 10/2012 -ትናንት በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በ‹‹ግብረሰዶምና ተያያዥ ማኅበራዊ ቀውሶች›› ላይ ለመነጋገር በተጠራው አገራዊ ኮንፈረንስ የተገኙት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የፓርላማ አባላት፣ ወጣቶችና ሌሎች የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ‹‹ግብረሰዶምንና ግብረሰዶም የሚያስፋፉ ምዕራባዊያንን›› አወገዙ፡፡ በዚሁ ታሪካዊና አንገብጋቢ በተሰኘው አገራዊ ኮንፈረንስ ላይ ከ2,000 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ አምስቱ ዋና ዋና የሃይማኖት ተቋማት የኦርቶዶክት ተዋህዶ፣ የእስልምና፣ የካቶሊክ፣ የወንጌላዊት መካነ ኢየሱስና የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ያወጡትን የግብረሰዶማዊነት የተቃውሞ መግለጫ በአንድ ድምፅ እንደግፋለን ብለዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነትን ካልተቀበላችሁ በማለት የሰብዓዊ መብት ጥያቄ የሚያነሱና ዕርዳታ እንከለክላለን ለሚሉ የምዕራብ አገሮችም ‹‹ዕርዳታቸው በአፍንጫችን ይውጣ›› የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በስብሰባው ላይ የተገኙት የሃይማኖት ተቋማትን በሙሉ ወክለው ጉባዔውን በፀሎት የከፈቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት ሕግ ሳይጻፍ ጊዜ ጀምሮ ከእግዚአብሔር ጋር ትውውቅ ነበራቸው፤ የዛሬ ሳይንቲስቶችም ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ መሆንዋን ይናገራሉ፤›› በማለት በዓለም ላይ ያሉ ሕዝቦች በሙሉ እርስ በርስ ተረጋግጠዋል፤ ብቸኛ ነፃ አገር ኢትዮጵያ ነች ብለዋል፡፡ ‹‹አሁንም የተረገጡትና የማንነት ቀውስ ያለባቸው ወገኖች ተናገሩ ብላ የምትሰማ አይደለችም፡፡ ባህላችን አልተለወጠም፣ ታሪካችን አልተቀነሰም፣ ማንነታችን አልተበረዘም፤ እንዲሁ ዝም ብለን የምንለወጥ አይደለንም፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡

የአዶላ ከተማ የማኅበረ ቅዱሳን ተጠሪ የተማሪዎችን ፈተናና የፈተና ጣቢያውን ኃላፊ አገቱ

                       ምንጭ፤ ዓውደ ምሕረት ብሎግ
ማኅበረ ቅዱሳን በተለያየ የአገሪቱ ክፍሎች ሁከት ማነሳሳትን አላማው አድርጎ ተያይዞታል። ጭር ሲል አልወድም በሚል ባህሪው የሚታወቀው ይሄ አሸባሪ ማኅበር አባላቱ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ሁከት እያነሳሱ ይገኛሉ። የዋልድባን ጉዳይ እነደ መንግስትን ማዳከሚያ ስልት እየተጠቀመበት ያለው ማቅ ደመቅ ባለበት ቦታ በቤተክርስቲያን ውስጥ፤ ምዕመኑ አነስተኛ በሆነበት ቦታ ደግሞ ባሉ ክፍተቶች ተጠቅሞ አመጽ ማነሳሳቱን ስራዬ ብሎ ተያይዞታል። 
 ሰሞኑን ይህን እውነት የሚያጎላ ክስተት በጉጂ ዞን በጨንቤ ወረዳ ተከስቷል። የአዶላ ወረዳ የማቅ ተጠሪ የሆነውና ባለፈው የካቲት 16 በነበረው ግርግር አመጽ በማነሳሳት ታስሮ በገደብ የተለቀቀው ስምንት ስልጣን ደራርቦ በያዘው ቀሲስ መኮንን ጉተማ አስተባባሪነት ሌሎች የማኅበሩ አባላት በሆኑ መምህራን አጋዥነት ክፍያ አነሰን በሚል ሰበብ የተማሪዎቹን ፈተናና የፈተና ጣቢያውን ኃላፊ ለሁለት ቀናት አግተው ቆይተዋል። የክብረ መንግስት ከተማ የሀገር አቀፍ ፈተናዎች አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ግለሰቦቹ የዕርምት ዕርምጃ እንዲወስድባቸው ለጉጂ ዞን ት/ቢሮ ደብዳቤ የጻፉ ሲሆን ለኦሮሚያ መንግስትና ለሀገር አቀፍ ፈተናዎች ድርጅት በግልባጭ አሳውቀዋል። 
ደብዳቤውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

«የሰንበት ት/ቤቶች ማ/ መምሪያ በጠራው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባዔ የአቋም መግለጫ፤ የማቅን ደስታ የገፈፈ ነው»

 
ማኅበረ ቅዱሳን ካለው ባህርይ አንዱ በማኅበራት ጉያ ተሸሽጎ ለዓላማው ማስፈጸሚያ እነሱን መጠቀም ተጠቃሽ ስልቱ ነው። ከነዚህም የመጠቀሚያ መሣሪያዎቹ አንዱ «የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባዔ» የተባለው የመንፈሳዊያን ወጣቶች ማኅበር ነው። የዛሬን አያድርገውና ማኅበረ ቅዱሳን አፉ ላይ በወርቅ የተለበጠ እስኪመስል ድረስ የሰንበት ት/ቤቶች ጉባዔን ስም ሳያነሳ ውሎና አድሮ አያውቅም ነበር። ይህ ኃይል በወጣቶች የተደገፈ ኃይል እንደመሆኑ መጠን ለቤተክርስቲያን ያለው መንፈሳዊ ቅናት ያለምንም ማጋነን ከየትኛውም ወገን በበለጠ የጠነከረ ነው። ያለውን መንፈሳዊ ቅናት በኃይል እስከማስከበር ድረስ ለመሄድ እንደማያመነታም ማኅበሩ ስለሚያውቅ  ልክ «ሳውል» የተባለው ጳውሎስ ያደርግ እንደነበረው ብዙ ድካምና ጉዞ የማይበግረው ኃይል ስለሆነ  የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባዔን የይለፍ ደብዳቤ አስይዞ መንፈሳዊ ቅናቱን ለገዛ ጥቅሙ ሲያውለው ቆይቷል።  ማኅበረ ቅዱሳን ከራሱ ዓላማ አንጻር አሥር ጊዜ «የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባዔ» እያለ ለወትሮው ማንሳቱ ብዙም አያስገርምም። «የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጉባዔ ይህን አደረገ፤ ይህንን ጻፈ፤ ተቃውሞውን አሰማ፤ በኃይል ለማስከበር እንገደዳለን አለ………..» ወዘተ ድምጾችን ማኅበሩ ደጋግሞ ሲጮህና በድረ ገጽ ልሳኖቹ ደጀ ሰላምና ሌሎቹ ሲጮሁለት እንዳልነበሩ ያህል ሰሞኑን በተደረገው የአንድነት ጉባዔው ማጠናቀቂያ «የአቋም መግለጫ» ላይ ትንፍሽም ሳይሉ መቅረታቸው የሚያሳየው  የጉባዔው መደረግ የቀማቸው ነገር እንዳለ ነው።