ምንጭ፦ ዓውደ ምሕረት ብሎግ
ቀድሞ
መልአከ አሚን አባ ዘካርያስ ይባሉ ነበር፡፡ በብፁዕ
ወቅዱስ አቡነ ተ/ሃይማኖት አንብሮተ እድ ግንቦት 3ዐ ቀን
1979 ዓ.ም፣ እንደ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ታሪከ የቀሳፊውንና ተልእኮውን በሚገባ ባለመፈጸሙ መብረር የተሳነውን
መልአክ ስም ወስደው «አቡነ ቀውስጦስ» ተብለው ተሾሙ፡፡ አባ ቀውስጦስ ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ የሚስማማቸው ሸዋ
ነክ ነገር ብቻ ነው፡፡ ከቅዱሳን ሸዋ፣ ከቤተ ክርስቲያን አለቃ የሸዋ ተወላጅ፣ ዲያቆን ሲሾሙ የሸዋ ተወላጅ በአጭሩ
ዘረኝነት የተጠናወታቸው ከጳጳስነት ይልቅ ያገር ሽማግሌነት የሚስማማቸው አባት ናቸው፡፡ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር
ያወዳጃቸውም በዋናነት ሸዋነት መሆኑን የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡
የአቡነ
ቀውስጦስ ዘረኝነት ጐልቶ የታየው ለአቡነ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን ለማሳነጽ፣ ታቦት ለመቅረጽ፣ ገድል ለማጻፍ
ባደረጉት ጥረት ነው፡፡ በጣልያን ወረራ በ1928 ዓ.ም የተገደሉት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስና የጐሬው ሊቀ ጳጳስ አቡነ
ሚካኤል ለአንድ አይነት አላማ ሞተው ሳለ አቡነ ጴጥሮስ ብቻ እንዲታሰቡ መሯሯጣቸው ለምን ብሎ ለጠየቀ ሰው መልሱን
በቀላሉ ማግኘት ይችላል፤ የአገር ልጅነት፡፡ አቡነ ሚካኤል ግን የሸዋ ተወላጅ ስላልሆኑ አስተዋሽ አጥተው የረባ
መታሰቢያ ሳይኖራቸው እስካሁን አለ፡፡
የከፋ ዘረኝነት እና ፖለቲካ (በ1997 ዓ.ም ይግባኝ ለክርስቶስ ብለው ያሳተሙትን ይመለከቷል) የተጠናወታቸው አቡነ ቀውስጦስ ከግብር ልጆጃቸው የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጋር በመሆን የሸዋ
ተወላጅ ለሆኑት ለአቡነ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ደፋ ቀና ብለው አሠርተው አስመርቀዋል፡፡ በዚህ ቤተ ክርስቲያን
ምረቃ እለት የወጣው “ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ” የተሠኘው መጽሔት ገፅ 53 ላይ ይህን የአቡነ ቀውስጦስን
የዘረኝነት ሥራ የዜና ቤተክርስቲያን አዘጋጅ ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በቅኔው እንዲህ አጋልጦታል፡-