ካለፈው የቀጠለ.................ክፍል 3
ፕሮቴስታንቶች
አንዳችም ሊያደርጉት ያልተቻላቸውንና በሌሎች ሃይማኖት በተከበበች ምድር አስደናቂ እንቅስቃሴ ያደርግ የነበረውን የሰንበት ትምህርት ትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴ በድርጅታዊ ፍቅር ታውሮ የበታተነው ማኅበረ ቅዱሳን በሚል ስም የተቋቋምው ድርጅት ነበር። ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ላይ ያለውን የሰንበት ትማህርት ቤቶች እንቅስቃሴ በክፉ ዓይን ማየት የጀመረው ዓለማያ ግብርና
ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ገና እግሩን በተከለበት ወቅት ነው። በዚህ ወቅት ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል ማኅበር በሐረር ስሙም የማይታወቅ ስለነበረ
በሐረር ያሉ ካህናትም ሆኑ ምእመናን ቦታ አልሰጡትም ነበር። ነገር ግን
ጥቂት ቆይቶ ማኅበረ ቅዱሳን ለጠቅላይ ቤተ ክህነትና ለሐረርጌ ሀገረ ስብከት አቤቱታ አስገባ። አቤቱታውም ሐረር ውስጥ ያሉት ሰንበት ትማህርት ቤቶች በሙሉ ተሐድሶ ናቸው የሚል ነበር። ለጊዜው የሀገረ
ስብከቱ ጽሕፈት ቤት የማኅበሩን ክስ አጥብቆ ተቃወመ። የሐረር ሕዝበ ክርስቲያንም ሁኔታውን ሲስማ አጥብቆ ተቃወመ።
ማኅበረ
ቅዱሳንን ሐረር ምድር ላይ ላለማስገባት ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ተጀመረ። ሁኔታው ያላመረው
ማኅበረ ቅዱሳን የሐረር ሕዝበ ክርስቲያንን የሚከፋፈልብትን አንድ ረቂቅ ተንኮል አርቅቆ አወጣ። ያም በሐረር
የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን የተሐድሶ አባላት የሚያሳይ የሐሰት ሰነድ ነበር። ሰነዱ በቃለ
ጉባኤ መልክ የተዘጋጀ ሲሆን የተሐድሶ አባላት የሆኑ ከመላው ኢትዮጵያ ተሰብሰበው ለሐረር እንቅስቃሴ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰጡ ለሐረርም መሪዎችን እንደሾሙ የሚናገርና ስሞችንም የሚዘረዝር ነበር።
በዚህ
የሐሰት ሰነድ ላይ መልአከ ሰላም ጴጥሮስ
አዘነን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ፤ የሀገረ ስብከቱን የመዝገቡ ቤት ኃላፊ፤ ሌሎች ካህናትና ታዋቂ ምእመናን የያዘ ነበር። በሰነዱ ላይ
የተዘረዘሩት ቀንደኛ የሆኑ ማኅበር ቅዱሳንን አላፈናፍንም ያሉ ሰዎች ነበሩ። በወቅቱ የሀገረ
ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት መምህር ብርሃነ ህይወት (አባ ዜና ማርቆስ የተባሉት በስሜን አሜሪካ ባሉት ታላቅ አባት ምትክ የተሾሙት ) በደስታ ቸኩለው ተሐድሶዎች ቤተክርስቲያኔን ወረዋል በማለት በሸኚ ደብዳቤ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ፤ ካህናቱን፤ የደብር አስተዳዳሪውን ታላቁን ሊቅ መልአከ ሰላም ጴጥሮስ ከስራና ከደሞዝ አገዱአቸው።