ምንጭ፦ አባ ሰላማ ብሎግ
( ለፒዲኤፍ ንባብ እዚህ ይጫኑ )
ነውራችን
ተሸፈነልን ብለውና ከማኅበሩ የሚከፈላቸውን ረብጣ ብር ከግምት በማስገባት፣ እንዲሁም ከማኅበረ ቅዱሳን ጎን ብንቆም
ፓትርያርክነቱ ለእኛ ይሆናል በሚል ክፉ ምኞት ተይዘው ለአንድ ወንበር እርስ በርስ እየታገሉ፣ የቤተክርስቲያንን
ሳይሆን የማኅበሩን አላማ ለማሳካት በግንቦቱ ሲኖዶስ ከመጠን በላይ ሲፋንኑ የነበሩት አባ አብርሃም፣ አባ
ዲዮስቆሮስና አባ ሳሙኤል፣ እንዲሁም አባ ጢሞቴዎስ፣ “ምንም ቢሆን ማኅበረ ቅዱሳን የከሰሳቸውን ሰዎችና ማኅበራት
ሁሉ ሳናወግዝ አንበተንም፤ ማኅበረ ቅዱሳን ያጠናው በቂ ነው፤ እነርሱን ጠርቶ ማነጋገር አያስፈልግም” በሚል
የማኅበረ ቅዱሳንን ክስ ብቻ በመቀበልና ተከሳሾቹን ሳያነጋግሩ ፍትሀዊነት የጎደለውን ፍርድ በመፍረድ “አውግዘናል”
ማለታቸው ተሰማ። እነዚህ በስም የተጠቀሱ የሰሙኑን የሲኖዶስ ስብሰባ ማኅበረ ቅዱሳን በአቡነ ጢሞቴዎስ ቤት
ያገባላቸውን ግብር በምሳ ሰአት እየበሉ፣ የቀኑን ውሎ ለማኅበሩ አመራሮች ሪፖርት እያቀረቡና በቀጣዩ ስብሰባ ላይ
ማድረግ ስለሚገባቸው መመሪያ ከማኅበሩ አመራሮች እየተቀበሉ ሲኖዶሱን ሲያውኩ መሰንበታቸው ይታወሳል።በተለይም
አባ አብርሃም ከአሜሪካው ሀገረ ስብከት መነሳታቸው ጥቅማቸውን ስላስቀረባቸው በግላቸውም በማኅበረ ቅዱሳንም በኩል
አልተወደደምና፣ ይህን ቂም ለመወጣት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ “ክስ የቀረበባቸው ግለሰቦች ተጠርተው ሳይጠየቁ
እንዴት ይወገዛሉ? ስለዚህ ተጠርተው ይጠየቁና ውሳኔ ይሰጥ” ሲሉ ያቀረቡትን ሐሳብ ለጊዜው ተቀብለው የነበረ
ቢሆንም፣ በዚህ እጅግ የተከፋው ማኅበረ ቅዱሳን “ሰዎቹማ ካልተወገዙ ጤና አይሰጡንም። ስለዚህ ስብሰባው ከመዘጋቱ
በፊት አውግዛችሁ መለያየት አለባችሁ ሲል ተላላኪ ጳጳሳቱን ባዘዘው መሰረት ተልእኮዋቸውን ተወጥተዋል። አንዳንዶቹ
አረጋውያን ጳጳሳት ግን ውግዘት የተባለውን ህገወጥነት “ኧረ ተዉ ምንድነው ለውሳኔ መቸኮል? ተጠርተው ያልተጠየቁ
ሁሉ ተጠርተው ይጠየቁ። አሊያ ይህ ለቤተክርስቲያን የሚጠቅም ውሳኔ አይደለም” ቢሉም ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለግል
ምቾታቸውና ለሥልጣናቸው ብቻ የቆሙት አባ አብርሃም፣ አባ ሳሙኤል፣ አባ ዲዮስቆሮስና አባ ጢሞቴዎስ አሻፈረን በሚል
ማውገዛቸውን አውጀዋል። እነዚህ በቀሚሳቸውና በቆባቸው ካልሆነ በቀር አንድም የጳጳስ ሰብእና የሌላቸውና ሊወገዙ
የሚገባቸው “ጳጳሳት”፣ መጽሐፍ ቅዱስንም ሆነ ህገ ቤተክርስቲያንን እንደማያውቁ ካስተላለፉት ህገወጥ ውግዘት መረዳት
ተችሏል። እንደክርስቶስ ትምህርት ቤተክርስቲያን ያጠፋውን ሰው ጠርታ መምከርና እንዲመለስ ማድረግ የመጀመሪያ ሥራዋ
ነበር። ተመለስ የተባለው ሰው አልመለስ ብሎ ከጸና ግን ታወግዘዋለች። አሁን እነ አባ አብርሃም አስተላለፍን ያሉት
ውግዘት ግን ይህን ስርአት ያልተከተለ፣ ከቤተክርስቲያን ፈጽሞ የማይጠበቅ፣ በእነርሱ መለኪያ የተሳሳተን ሰው
ከስህተቱ ለመመለስ ሳይሆን በዚያው ጠፍቶ እንዲቀር ለማድረግ የተላለፈ የ“ጥፋ” አዋጅ ነው። በእውነተኛዪቱ
ቤተክርስቲያንና በደጋጎቹ አባቶች አይን ሲታይ “ውግዘት ዘበከንቱ” ነው። መጽሐፍ ቅዱስም “እንደሚተላለፍ ድንቢጥ ወዲያና ወዲህም እንደሚበርር ጨረባ፥ እንዲሁ ከንቱ እርግማን በማንም ላይ አይደርስም።” (መጽሐፈ ምሳሌ 26፡2) ሲል የገለጸው አይነት ከንቱ መሆኑን ይናገራል።