Friday, May 18, 2012

ቅዱስ ሲኖዶስ የግለሰቦችን ነጻነት በመጋፋት፤ስም በማጥፋትና ከማውገዝ የወንጀል ድርጊት ሊቆጠብ ይገባል!

አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ውስጥ ማንኛውም ሰው የመሰለውን እምነት የመከተል መብቱ የተጠበቀ ነው። ከፕሮቴስታንቱ ጎራ ለመቀላቀል ወይም ካቶሊክ  ለመሆን አለያም  እስላም የማንም ክልከላ አይደርስበትም። የሌላውን መብት እስካልነካ ድረስ በመሰለው ቦታ እምነቱን የማስተማር፤ የመስበክ መብቱን እየተገበረ እንደሚገኝ ይታወቃል። ያንንም ስንል ሁሉ ነገር እንከን አልባ ነው እያልን እንዳልሆነም ሳይዘነጋ ነው። እያልን ያለነው ሁሉም እምነቶች ዋና መሠረታዊ ነጥብ በእያንዳንዳቸው በኩል የሚመለከው  አምላክ ከሌላው የተሻለ፤ ዋስትናን የሚሰጥ፤ ዘላለማዊነትን የሚያጎናጽፍ፤ የሚያጸድቅና የሚኰንን መሆኑን በማስረዳት  ለሌላው በማስተማር ተከታዮችና አባላትን ማፍራት መቻላቸው የማይካድ መሆኑን  ነው። በአብዛኛው  ችግሮች የሚመጡት በእምነት ተቋማት በራሳቸው በኩል ሲሆን ሌላውን አዲስና መጤ፤ የሰይጣን ትራፊ እንደሆነ አድርጎ ጥላሸት በመቀባት በትምህርት ሳይሆን በማስፈራራት አባሎቹን ጠብቆ ለማቆየት ሲሞክርና ማብጠልጠል ላይ ብቻ የመንጠልጠል ችግር እየተስተዋለ  ሲገኝ ነው። እንዲያውም አንዳንዶች የእምነት ተቋሙን ስም እየጠሩና የሰይጣን ቁራጭ አድርጎ በመሳል በጽሁፍ፤ በምስልና በቃል የተደገፈ አስተምህሮ የሚያስተላልፉና የሚያሰራጩ በየትኛውም ወገን ባሉ የእምነት ተቋማት በኩል ልቅ በሚባል ደረጃ ሲፈጽም ይስተዋላል።
 ስለስህተት አስተምህሮ ለመስበክ ከእምነቱ መሰረታዊ አቋም ተነስቶ ከሚሰጥ አንጻራዊ ስብከትና ትምህርት ውጪ የሌለ ነገር በመፍጠር ወይም በውሸት ላይ ተመስርቶ  በቀጥታ የእምነቱን ተቋም ስም በመጥራት ለማጥቃትና ለማንቋሸሽ የሚውል ከሆነ አሁን ባለው የኢትዮጵያ ወንጀል ሕግም ይሁን በአማኙ ወይም በእምነት ተቋሙ ላይ ለሚደርስ የሞራል ጉዳት በፍትሐ ብሔር ህግ የሚያስጠይቅ ጉዳይ ነው።

የማቅ ሁለት ባላ!

ማኅበረ ቅዱሳን ከደጀ ሰላም፤አንድ አድርገንና ከሌሎቹ ውርንጭላ ብሎጎቹ ውጪ የዘመቻ አድማሱን በማስፋትበሀገሪቱ  ፖለቲካዊ ለውጥ እንዲመጣ ከሚታገሉ ሚዲያዎች ጋር ኅብረቱን በማሳየት ወደግልጽ እርምጃ ቀይሮታል። ማንም በፈለገው የፖለቲካ አቋም የመሄድና የመሰለፍ መብት እንዳለው ብናምንም ማኅበረ ቅዱሳን ግን ሃይማኖታዊ አቋሙን ከየትኛውም ፖለቲካ ገለልተኛ ሆኖ ለመስራት የተስማማበትን መተዳደሪያ ደንቡን ጥሶ በማኅበሩ አመራር አባል በኩልም ጭምር መግለጫ በመስጠት ለፖለቲካዊ ለውጥ ትግል መድረኮች የጽሁፍና የቃል አቤቱታውን በመስጠት መቀላቀሉን አሳይቷል። ድሮም «ማቅ» ፖለቲካውንና ሃይማኖቱን እያቀላቀለ የሚሄድ እንጂ ስለኦርቶዶክስ የሚገደው አይደለምና ይህንኑ አሳይቷል። ማቅ ሁለት ባላ መትከሉን አቁም!

Thursday, May 17, 2012

ዓሠርቱ ቀናት ለማኅበረ ቅዱሳን!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር ከሚገኙት 
 በርካታ ማህበራት መካከል አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን መሆኑ ይታወቃል፡፡ ይሁን እንጂ ማህበረ ቅዱሳን 
 ከተቋቋመለት ዓላማ  ውጭ በመሆን መንገዱን ስቶ መሄዱን በርካታ የማህበሩ አባላት እየገለጹ 
 ከመሆናቸውም በላይ የማህበሩ አካሄድ ለቤተ ክርስቲያን ከባድ አደጋ እንደሆነ በማስጠንቀቅ 
 ላይ ናቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ አንጋፋው የማህበረ ቅዱሳን መሥራች የነበረው መምህር በድረ ገጽ ላይ 
 ሥውር አመራር እና ግልጽ አመራረ እያለ በመተንተን በሚገባ በማህበሩ ውስጥ የሚሠራውን ሴራ
አስነብቦን እንደነበር ግልጽ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅትም የማህበሩ አካሄድ ከቤተ ክርስቲያኒቱ 
 መዋቅር ሥር እያፈነገጠ ባለበት በዚህ ወቅት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሳይቀር የስህተት 
 ምሳሌ ሆኖ መጠቀሱ ይታወሳል፡፡ እንግዲህ በዚህ የ20 ዓመት ጉዞው ውስጥ ማህበሩ 
 በቤተ ክርስቲያን ስም እያመካኘ ነገር ግን ለራሱ የሚሠራ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ግን ከጥቅሙ 
 ይልቅ ጉዳቱ እያመዘነ መምጣቱን አንዳንድ ለቤተ ክርስቲያኒቱ የሚቆሙ የማህበሩ 
 አመራር አባላት ይናገራሉ፡፡ ትተው እንዳይወጡ ደሞዝ እንዳይሰሩም ጭንቅ የሆነባቸው 
 ወንድሞች በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ በርካታ ናቸውና፡፡ ይህን የምንለው የማህበሩን 
 አካሄድ አታውቁም ብለን ሳይሆን እናስታውሳችሁ ብለን ነው፡፡ የረሳችሁትን እንድታስታውሱ 
 ስንል ያልሰማችሁትን ደግሞ እንድትሰሙ ፈቃዳችን ነው፡፡ ባሳለፍነው ወር ማለትም 
 በሚያዝያ ወር ውስጥ በሰንበት /ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊነት ተሰይመው 
 የነበሩት መልዐከ ጽዮን አባ ኅሩይ ወንድይፍራው ተደርጎ የማይታወቅ ጉዳይ ይዘው ብቅ
  በማለታቸው ሳይሾሙ ተሻሩ፡፡