(የሊቃነ ጳጳሳቱ ገመና በዜና ቤተክርስቲያን ተጋለጠ፤ ጳጳሳቱም ስለ ገመናቸው መጋለጥ ተቃጥለዋል!)
የጽሁፍ ምንጭ፦ ዐውደ ምሕረት
በትናንትናው
ዕለት የዜና ቤተክርስቲያን ጋዜጣ ርዕሰ አንቀጽ ሰፊውን ጊዜ ወስዶ ሲያወያይ ነበር ሰኞም ይቀጥላል
(የማሕበረ
ቅዱሳን ብሎጎች ይህን መርዝ ሳንረጭ አያስተኛን አያሣድረን በማለት ቅ/ሲኖዶስ ሌላ ሰብሳቢ መርጦ ጉባኤውን ለመቀጠል ወሰነ የሚል ነጭ ውሸት በሰበር ዜናነት አስነብበውናል፡፡ ሲኖዶሱ እንዲህ ያለ ውሳኔ እንዳልወሰነ የተረጋገጠ ሲሆን እነዲያውም ቀኑ ያልታሰበና ያልተጠበቀ አጀንዳ የተስተናገደበት ቀን ነበር፡፡ ዝርዝሩን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡)
በትናንትናው
ዕለት የነበረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በጠዋቱ ውሎ አጀንዳቸው ተቀባይነት እንዲያገኝ የከረረ አቋም ይዘው የሚገኙት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲኖዶሱ ሃሳባቸውን ይቀበል ዘንድ ግድ እያሉ የነበረ ቢሆንም የአብዛኛው ጳጳሳት ፍላጎት አጀንዳዎቹን አለመቀበል ስለሆነ ጉዳዩ መክረር ጀምሮ ነበር። ከሰዓቱን ግን የዜና ቤተክርስቲያን ዘገባ እጃቸው ላይ በገባ አባቶች ጉዳዩ ይታይልን ተብሎ ስለተጠየቀ ሲታይ ሁሉን አጀንዳ አስጥሎ ፊታውራሪ ሆነ።