Sunday, May 13, 2012

አሁን ያሉት የሲኖዶስ አባላት ቤተክርስቲያንን ከውድቀት አያድኑም!

 
እኛ ጠቅልለን የምንናገረውን «ደጀ ሰላም» ከፋፍሎ በማስቀመጥ የጳጳሳቱን ማንነት ይነግረናል።ባልተለሳለሰው አማርኛችን ሲዘረዘሩ  እንቅልፋሞች፤ አድርባዮች፤ ሆዳሞችና ሰራተኞች  መሆናቸው ነው። ደጀ ሰላም ብሎግ የጳጳሳቱን ማንነት ሲተነትን፤
«ሊቃነ ጳጳሳቱ “ሰማዕታት፣ ነውረኞች፣ ዘገምተኞች እና ጥቅመኞች” በሚል በአራት ተከፍለዋል» ይልና…የጠ/ቤተ ክህነቱ ሠራተኞች “የዳኛ ያለህ! ለቤተ ክርስቲያኒቱ ዳኝነት ይታይላት” የሚል ጽሑፍ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አሰራጩ» በሚል ርዕስ በ10/9/2012  ጽሁፉ ማንነታቸውን ይተነትናል።
ዞሮ ዞሮ በአንድ ነገር እንስማማለን።አራት ቦታ ከተከፈሉትና በዘገባው ከተመረጡት  ውስጥ አንዱ እጅ ብቻ «ሰማዕታት» ወይም ሰራተኛ ናቸው ያላቸውን እነማን እንደሆነ ባናውቃቸውና እኛ የምንመርጠው ምንም እንደሌለ ብናምንም «ነውረኞች፣ ዘገምተኞችና ጥቅመኞች» ባላቸው የሲኖዶሱ ¾ ው  አባላት  የቤተክርስቲያኒቱ የጥፋት  ኃይሎች መሆናቸውን በገለጸው ድልድል ላይ እጃችንን አጨብጭበን መስማማታችን እንገልጻለን። ድንቅ ዘገባ ነው ደጀ ሰላም!!
እንግዲህ እንደ ደጀ ሰላም ዘገባ 75% የሆነው የሲኖዶስ አባል ለቤተክርስቲያን ችግርና ውድቀት ኃላፊነት ያለበትና ሆኖ  ለአዲስ የአስተዳደር ትንሣዔ ምንም ለውጥ ማምጣት የማይችል፤ እንኳን የቤተክርስቲያንን ሸክም ሊያቀል ይቅርና እራሱ ሸክም የሆነባት ኃይል መሆኑን ነው። «ከነውረኞች፤ ጥቅመኞችና ዘገምተኞች» የሚመጣ ምንም ለውጥ የለም።  ደጀ ሰላም! እውነት ለመናገር ብለህ በውዴታህ የተናገርከው ባይሆንም በመንፈስ ቅዱስ ተጸፍተህ የተናገርከው ግን እውነት ነው እንላለን። 

የኔን ዓይን ሌላኛው ለምን አያምንም?

ለፈገግታ









Saturday, May 12, 2012

የሲኖዶስን ውሳኔ የሚያወራ ግን እሱ ሊፈጽመው የማይፈልግ፣ በሌሎች ላይ ለመጫን የሚሮጥ አፄ በጉልበቱ ማኅበር ብቻ ነው!



ቅዱስ ሲኖዶስ ባሳለፈው የ2002 ውሳኔ እንደተመለከተው መጻሕፍት፤ መጽሔት፤ የመዝሙር ካሴት፤ ሲዲ፤ ቪሲዲ፤ በአጠቃላይ የድምጽና የህትመት ውጤቶችን ሁሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ስም አሳትሞ ለማውጣት በቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት ጉባዔ በኩል አስመርምሮና የቤተክርስቲያኒቱን ሥርዓት ጠብቆ ለመሆኑ ሲፈቀድለት ብቻ እንዲሆን አስረግጦ ይወስናል። ይህንኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የማኅበሩ አፈ ጉባዔ የሆነው ደጀ ሰላም ብሎግ «እሰይ ቅዱስ ተግባር» በማለት ድጋፉን በድረ ገጹ ላይ በግንቦት 10/2010 ዓ/ም ጽሁፉ ያወጣል። ይህንኑ በማኅበሩ አፈ ጉባዔ «ደጀ ሰላም» አድናቆት የተቸረውን  ውሳኔ ተከትሎም አባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል  የማደራጃ መምሪያ ኃላፊው የማቅ  የ20 ዓመት ልሳኖቹና ሌሎች ህትመቶቹን ሁሉ  በሊቃውንት ጉባዔው በኩል እየተመረመረ እንዲወጣ ትእዛዝ ይሰጣሉ።  አፄ በጉልበቱ ማኅበርም ጆሮ ዳባ ልበስ ይልና በነበረው መልኩ ኅትመቶቹን በጓሮው  እያሳተመ ይቸበችባል።  አባ ሠረቀም የሲኖዶስ ውሳኔ ተከብሮ ለሕትመት ማለፍ በሚገባው መንገድ ለመሄድ ባለመቻሉ የአፄ በጉልበቱ ማኅበር ደንበኛ  ለሆነው «ሜጋ ማተሚያ ድርጅት» ምክንያቱን ጠቅሰው የአፄው መጽሔቶች መታተም እንደሌለባቸው ማገጃ ይጽፋሉ።
አፄ በጉልበቱ፤ «አሁን በዓይኔ መጣህ!» ይልና ሀገር ይያዝልኝ በማለት ቀውጢ በማድረግ አቧራ ያስነሳል። የአፄ በጉልበቱ ጉዳይ ፈጻሚ የማደራጃ መምሪያው ሊቀጳጳስ በግላቸው ቲተር፤ ማመልከቻቸውን ለሥራ አስኪያጁ በማስገባት እግዱ እንዲነሳና ህትመቱ እንዲቀጥል አቤቱታቸውን ያቀርባሉ። እንግዲህ ይታያችሁ!! ሲኖዶሱ በሊቃውንት ጉባዔ በኩል ማንኛውም ህትመት ተመርምሮ እንዲያልፍ መወሰኑን ልብ በሉ!! በውሳኔው ላይ የነበሩት ሊቀጳጳስ ግን ለአፄው ሲሆን እንዲሻር በደብዳቤ ጭምር የሚጠይቁበት ቤተክህነት መሆኑንም አስተውሉ!!  እነ በጋሻው፤ ትዝታውና ምርትነሽ ላይ ሲሆን የሲኖዶሱን ውሳኔ ጥሰዋል እያለ የሚጮኸው አፄ በጉልበቱ ህግ ማስከበሩ በእሱ ላይ ሲመጣ ግን ተላላኪ ጳጳሶቹን ሳይቀር ተጠቅሞ ህግ መሻር እንደሚችል ስንመለከት ከመግረም አልፎ ያሳዝናል።
አፄው በማደራጃ መምሪያው ሊቀጳጳስ በኩል ያቀረበው ማመልከቻ፤ የአባ ሠረቀ ብርሃን  የማገጃ ደብዳቤ እንዲነሳ ከመደረጉ በፊት ህትመቱ  በጓሮ ማተሚያ ቤት ታትሞ ገበያ ላይ ይውላል። እንግዲህ የሲኖዶስ ውሳኔ ውሃ በላው ማለት ነው። ሊቃውንት ጉባዔም  የአፄውን ኅትመቶች ለመመርመር እንደተመኘ አፉን ከፍቶ ቀረ። ከሁሉም የሚያሳዝነው ቤተክህነቱ ለእውነት የቆመ መስሏቸው አባ ሠረቀ ብርሃን ሕግ ይከበር በሚል አቋማቸው ሲዳክሩ አፄ በጉልበቱ ይህንን ሰውዬ ከዚህ ቦታ ካላሽቀነጠርኩት ይልና «የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶና የሙስና ምሕዋር» የሚል ታርጋ ይለጥፍና ዘመቻውን አጧጥፎ አባ ሠረቀን ያስነሳል። አፄውም በትግሉ ውጤት «እፎይ» ብሎ በመተንፈስ «ድሮስ ከእኔ ጋር መወዳደር ለመላላጥ!» በማለት በአባ ሠረቀ ድካም ላይ እንደተሳለቀ  እኛም ግምታችንን አኑረናል። አባ ሠረቀ ብርሃን ለጻፉት ደብዳቤና በአፄው ላይ ህግን ለማሳየት በመጣራቸው የተሰጣቸው ስም ይህንን ይመስላል።
አፄው በሀሰት ስብከቱ ያሰከረው ምድረ ደጋፊ ሁሉ በአባ ሠረቀ መነሳት «እልል!» በማለት ድጋፉንና ደስታውን ለመግለጽ ጊዜ አልፈጀበትም።  አባ ሠረቀ ግን የአፄው ዱላና እንግልት ያረፈባቸው ሲኖዶስ የወሰነውንና ራሱ «ደጀሰላም» ብሎግ የዘገበውን መመሪያ ለመተግበር እንጂ በግል ከልባቸው አንቅተው አፄውን ለማጥቃት ያመነጩት አካሄድ አልነበረም። ይሁን እንጂ አፄው የቀኝ እጁ ጳጳሳት የራሳቸውን ውሳኔ እንኳን እስከመሻር የት ድረስ እንደሚሄዱለት በማሳየት አንድ እውነት ያረጋገጠ ነበር።