Saturday, May 12, 2012

የማይዘልቅ ማኅበር በጠጅ ይጀመራል የማያድግም ልጅ ዓይነምድሩ ይበዛል!


                  
                 የጽሁፉ ምንጭ፤ አባ ሰላማ Wednesday, May 18, 2011 ፖስት
አንድ ማኅበር ለመጀመሪያ ጊዜ በጠጅ ከተጀመረ የሰካራሞች መሰብሰቢያ ይሆንና በመጨረሻ በብጥብጥ ይበተናል፤ ምክንያቱም ማህበሩን የጀመረው ግለሰብ በጠጅ ከጀመረው የሚቀጥለው ተረኛም ከማን አንሼ በሚል ስሜት ለአባላቱ ጠጅ ስለሚያቀርብ፤ ቀጥሎ ማህበር የሚደግሰውም እንዲሁ እንደጓደኞቹ ስለሚወዳደር ማህበሩ በጠጅ ተጀምሮ በጠጅ ይበተናል ማለት ነው ሰካራሞች የሚናገሩትን እና የሚሠሩትን ስለማያውቁ ሁልጊዜ መስከራቸው ሕይወታቸውንም ሆነ ኢኮኖሚያቸውን ያቃውሳልና።
የማያድግ ልጅም ከሚበላው ፍሬ ነገር ይልቅ ወደ ውጭ የሚያወጣው ዓይነ ምድር ከበዛ ሰውነቱ ንጥረ ምግቦችን መቀበል ስለማይችል ሆዱ ተነፍቶ መሞቱ ወይም ቀጭጮ አቅመ ቢስ ሆኖ መቅረቱ አይቀርም፤ የማያድግ ልጅ እንትኑ ይበዛል የተባለው ለዚህ ነው።
ማኅበረ ቅዱሳንም ገና ሲጀመር ዓይነምድሩ የበዛ በነገር የተጀመረና በጠንቋዮች ምክር ስለሚመራ ባጭሩ መቀጨቱ የማይቀር ነው። ማህበረ ቅዱሳን በነ አቡነ ማቴዎስ፤በነ ቀሲስ ዳኛቸው፤ በነ ኃይለ ጊዮርጊስ በነ አቶ ታየ [የሽዋ ንጉሥ ሊሆን የነበረ] ወዘተ በደገሱት የተንኮል ድግስ ወጣቱን በነገር እያሰከረ ሲያወላግድ ከዚህ ደርሷል። ዛሬም መካኒሳ አካባቢ በአንድ ግለሰብ ቤት ውስጥ በሚደረግ ምሥጢራዊ ስብሰባ ነገር እየተቀበለ ወደ ቤተ ክህነት ብቅ ይልና በግማት የተሞላውን ዓይነምድሩን ጥሎ ይሄዳል። 

Friday, May 11, 2012

....ተሃድሶ መናፍቃን አይደሉም!

«ቅዱስ ሲኖዶስ አባ ሠረቀ ብርሃንና ዲ/ን በጋሻውንን የኃይማኖት ህጸጽ የለባቸውም ተሃድሶ መናፍቃንም አይደሉም አለ»

       Adiós ማቅ !!!!!       bienvenidos አባ ሠረቀ ወበጋሻው!!

                       የጽሁፉ ምንጭ፦ ዐውደምህረት
በትናንትነው ዕለት የተጀመረው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የጀመረው ከጥቅምቱ ስብሰባ ወደ ግንቦት የተዘዋወሩ ጉዳዮችንን በመመልከት ሲሆን የመጀመሪያ አጀንዳውም ሊቃውንት ጉባኤውየሐይማኖት ህጸጽአለባቸው ተብለው ስለ ቀረቡ ወገኖች አጣርቶ የደረሰበትን እንዲያቀርብ ማድረግና ውሳኔ መስጠት ነበር። በዚህም መሰረት ማቅ ይወገዙ ይከሰሱልኝ ሲል ካቀረባቸው ሰዎች መካከል የአባ ሠረቀ ብርሃን እና የዲ/ በጋሻው ጉዳይ ታይቶ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል። ይህ ውሳኔ ለማኅበረ ቅዱሳን ትልቅ ውድቀት እንደሆነ ታዛቢዎች እየተናገሩ ይገኛሉ።

Thursday, May 10, 2012

የሰናዖር ማበር



በትልቅ ቸርነት ሌሊቱን አንግቶ
በጽልመቱ ቦታ ፀሐይን አብርቶ
ጨለማን በብርሃን ለለወጠ ጌታ
ምስጋና ሊያቀርቡ፤ ሊያደርሱ ሰላምታ
ወፎች እንኳን አውቀው ሲያሰሙ እልልታ
ክፉ ማኅበር ክፉ  ያነሰ ከእንስሳ
ጠዋት ከመኝታው ከእንቅልፉ ሲነሳ
በስመ አብ ብሎ ማመስገን ሲገባው
መርዝ ሃሳብ ያወጣል ጠማማ ልቡናው
ከደካሞች ጋራ እንዳይኖር ተስማምቶ
ተንኰል የሚዘራ ከመካከል ገብቶ