Tuesday, May 8, 2012

«የሁለቱ ማቆች የታክሲ ውስጥ ወግ »

                                 ምንጭ፦ደጀ ሰላዓም ብሎግ
ሁለቱ የ"ማኅበረ ቅዱሳን" አባላት በትላንትናው ዕለት ሰኞ ከምሽቱ 3፡20 ሰዓት ላይ ከአራት ኪሎ ወደ ቤላ በሚሄደው ታክሲ ጋቢና ውስጥ ጎን ለጎን ተቀምጠው ወጋቸውን ይጠርቃሉ፡፡ በእነርሱ ቤት በታክሲዋ ከተሳፈሩት ሰዎች ውስጥ ከእነርሱ በስተቀር ስለቤተክርስቲያን ሚስጥርና ወቅታዊ ሁኔታ የሚያውቅ ማንም የለም፡፡ ይሁን እንጂ፣ ያላዩት አንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ የሆነና እነርሱን በደንብ የሚያውቅ ዘጋቢያችን ከጀርባቸው ልጥፍ ብሎ የሚነጋገሩትን በጥንቃቄ ያዳምጥ ነበር፡፡
ሰዎቹ ማንያዘዋልና ዘማሪ ኤፍሬም ነበሩ፡፡ ማንያዘዋል ትውልዱ ከወደ ደብረብርሃን ሲሆን፣ የዘርዓ ያዕቆብ ዘር ነኝ በሚል እየተመፃደቀ ዘወትር ነጭ በነጭ ለብሶ በመንሸራሸር ባህርይው ሰው ሁሉ ሊለየው ይችላል፡፡ ከዚህም በላይ በጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት የልማትና ተራድዖ ክፍል ውስጥ ሲሠራ በፈጸመው የሙስና ተግባር ከሥራው መባረሩ ይታወቃል፡፡ ከዚያ ደግሞ "ማኅበረ ቅዱሳን" በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አካባቢ የቲዎሎጂ ምሩቃን ማኅበር ተጠሪ እንዲሆን አስመድባው እዚያ ላይ ሆኖ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡ ኤፍሬም የ"ማኅበረ ቅዱሳን" አባል ከመሆኑ በስተቀር ይህን ያህል የሚታወቅበት የጎላ ገጽታ የለውም፡፡

አባትነት በገንዘብና በፖለቲካ ሲፈተን



                              የጽሁፉ  ምንጭ፦አውደ ምህረት
ብፁዕ አቡነ አብርሃም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከምእመናን ተለምኖ በተገኘ ገንዘብ የተገዛውን የዲ.. እና አካባቢው መንበረ ጵጵስና /ቤት እንዲያስረክቡ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወሰነ። ማኅበረ ቅዱሳን እያለ ራሱን በሚጠራው ድርጅት አቀንቃኝነታቸው የሚታወቁት ወጣቱ ጳጳስ አቡነ አብርሃም በአሜሪካ በተለያየ ስቴቶች በተካሄዱ ጉባዔያት አማካይነት ከምእመናን በተሰበሰበ የአሜሪካ ዶላር 265 000.00 የተገዛው መንበረ ጵጵስና በራሳቸው እና በወሮ. ሀረገወይን ስም ለምን ለማዛወር እንደፈለጉ ባይታወቅም መንበረ ጵጵስናው የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ንብረት መሆኑ እየታወቀ አላስረክብም ማለታቸው በዘመናዊ አነጋገርየመርካቶ ቁጩዐይነት ቢሆንም የኢትዮጵያና የአሜሪካ መንግሥታት እንዲያውቁት ተደርጎ በአስቸኳይ እንዲያስረክቡ ከዚህ በታች አባሪ በሆነው ደብዳቤ መታዘዛቸውን ቤተ ክርስቲያን ገለጸች።
 ጽሁፉን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ(ጽሁፉን አሳድገው ያንብቡ)

መቼም መስከረም ሳይጠባእንደሚባለው የዋሽንግተንና አካባቢዋ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል መንበረ ጵጵስናውን በሥርዐት እንዲያስረክቡ በተደጋጋሚ ቢጽፍላቸውም አሻፈረኝ ብለው መንበረ ጵጵስናውን ለማኅበረ ቅዱሳን /ቤት (ደጀ ሰላምና አሃቲ ተዋህዶ ብሎግ ማዘጋጃ) አከራይተው እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ ታውቁዋል። እኒህ ጳጳስ እንደሚታወቀው ቀደም ሲል ከመርካቶው ራጉኤል ቤተ ክርሰቲያን ባካበቱት (በዘረፉት ቢባልም ሥራቸው ነውና ራሳቸው ይፈሩ!) ገንዘብ .ኤም.. አጠገብ ፎቅ ቤታቸውን ሠርተው ሳያፍሩ ያስመረቁ ሲሆን፣ በቅርቡም በባንክ ሂሣብ የተጠራቀመውን ከዲ. ከወሰዱት የሀገረ ስብከቱ ገንዘብ እና አቶ አሥራት የሚባል (የጎጃሙ ባለአውሊያ) የቸራቸውን ብር 400 000.00 በመጨመር ሁለት ሚሊዮን ብር በሚጠጋ ገንዘብ ልዩ ላንድ ክሩዘር ገዝተው -መንፈሳዊ የሆኑ ተግባራትን እያከናወኑበት ይገኛሉ።

Monday, May 7, 2012

የአባ ኅሩይ ወንድይፍራው የመባረር ምክንያት ሲተነተን!



አባ ኅሩይ ወንድይፍራው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ሆነው  በማኅበረ ቅዱሳን አድማና በደጋፊዎቹ የሲኖዶስ አባላት አባቶቹ ድጋፍና የሞት ሽረት ትግል በተባረሩት በአባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል ምትክ መመደባቸው ይታወሳል። ማኅበሩም  በተለመደ ቅልስልስ የድመት ባህሪው  ከሥራቸው ተጎዝጉዞ «አባታዊ መመሪያዎትንና ምክርዎን እንሻለን» ሲል የተነሱትን አባት በረገመበት አፉ ተተኪውን ሲመርቅ መስማታችን  የሚዘነጋ አይደለም።
ይህ  ማኅበር «አባ ሠረቀ ብርሃን ተሐድሶና የሙስና ምሕዋር ናቸው» በማለት ሲወነጅላቸው የመቆየቱ  ምክንያት ማጭበርበሪያ ስልቶቹን ሁሉ አውቀው መፈናፈኛ ስላሳጡት እንጂ አባ ሠረቀ ብርሃን ሙሰኛና ተሐድሶ ስለነበሩ እንዳልሆነ የሚያረጋግጥልን ሰውዬው ሰንገው ከያዙበት ማደራጃ መምሪያ ተነስተዋል ከተባለበት ጊዜ አንስቶ «የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ»እንዲሉ የተበላበትን የስም ማጥፋት  የእቁብ ፋይል  ዘግቶ አዲሱን ሹም ወደ ማወደስ መሸጋገሩ ነበር።  አባ ሠረቀ ከቦታቸው ከተነሱ ተሐድሶነታቸው ቀርቷል ማለት ነው? ወትሮውንም ተሐድሶ ያላቸው እስኪነሱለት እንጂ ከዚያ በኋላ እንኳን አንዴ አስር ጊዜስ ቢሆኑ እሱ ምን ተእዳው!!
አዲሱን ሹም እየደባበሰ እንቅልፍ በማስያዝ ጉዳዩን ማስፈጸም እንጂ ቤተክህነት ውስጥ መታደስና ቅን መሆንን የሚወድ እልፍ አእላፍ ስላለ ያንን ሁሉ መከታተል ልብን ማውረድ መሆኑን ስለሚያውቅ ስለ አባ ሠረቀ ማኅበሩ ድሮውንም ጉዳዩ አይደለም።
 አባ ኅሩይ መመሪያ እየሰጡት ሳይሆን ማኅበሩ የተገላቢጦሽ መመሪያ እየሰጠ ሹሙ ላለፉት ወራቶች ማኅበሩን በታማኝነትና በቅንነት ሲያገለግሉት ቆይተዋል።
ይሁን እንጂ ማኅበሩ ከሰለፊያው የአሸባሪ ቡድን ጋር በድርጊት የሚመሳሰሉ አባላት እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ከገለጹበት እለት ጀምሮ አሸባሪው በተራው ሽብር ገብቶ ሰንብቷል።
ይህ ማኅበር እንዲህ ያለ ክፉ ቀን ይደርሳል ብሎ ሳይገምት በትእቢት ተወጥሮ ከብዙዎች ጋር ሲላተም ቆይቷል። «አንድ ሳር ቢመዘዝ ቤት እንደማያፈስ፤ አንድ ሰው ቢባረር ምንም አይጎዳንም» እያለ ባበጠ ልቡ ይህንኑ ሲተገብር በመቆየቱ ልክ ከጥቁሩ የአሸባሪ መዝገብ ላይ ስሙ ሲጠራ ካደነዘዛቸው ጥቂቶች በስተቀር አብዛኛዎቹ አካሄዱን ሲቃወሙ የቆዩ ሁሉ  ከጠቅላይ ቤተክህነት ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተክርስቲያን የሚጠባበቀው ነገር ቢኖር በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተነገረው ቃል ሲተገበር ማየትን ብቻ ነው።
ይህንኑ ማኅበር እያንዳንዱ የጠቅላይ ቤተክህነት መምሪያዎችና ክፍሎች ሁሉ ሳይቀሩ የቀብር አፈሩን  ቶሎ፤ መለስ መለስ አድርጎ ለማጠናቀቅ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ምን ትጠብቃላችሁ? በሚል ሃሳብ ከዚህ ቀደም ማኅበሩ ለመፈጸም  ፈቃደኛ ያልሆነባቸውንና «ይልቁንም የራሳችሁን ስራ ሰርታችሁ ባሳያችሁን ነበር » ሲል የጻፈውን ተመጻዳቂ ደብዳቤውን ለማሳፈር ጊዜው ዛሬ ነው በማለት መረጃ አስደግፈው ደብዳቤ እንዲጻፍለት አስደርገዋል።