አባ ኅሩይ ወንድይፍራው የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ
ኃላፊ ሆነው በማኅበረ ቅዱሳን አድማና በደጋፊዎቹ የሲኖዶስ አባላት
አባቶቹ ድጋፍና የሞት ሽረት ትግል በተባረሩት በአባ ሠረቀ ብርሃን ወ/ሳሙኤል ምትክ መመደባቸው ይታወሳል። ማኅበሩም በተለመደ ቅልስልስ የድመት ባህሪው ከሥራቸው ተጎዝጉዞ «አባታዊ መመሪያዎትንና ምክርዎን እንሻለን» ሲል የተነሱትን
አባት በረገመበት አፉ ተተኪውን ሲመርቅ መስማታችን የሚዘነጋ አይደለም።
ይህ ማኅበር «አባ ሠረቀ ብርሃን ተሐድሶና የሙስና ምሕዋር ናቸው» በማለት ሲወነጅላቸው
የመቆየቱ ምክንያት ማጭበርበሪያ ስልቶቹን ሁሉ አውቀው መፈናፈኛ ስላሳጡት
እንጂ አባ ሠረቀ ብርሃን ሙሰኛና ተሐድሶ ስለነበሩ እንዳልሆነ የሚያረጋግጥልን ሰውዬው ሰንገው ከያዙበት ማደራጃ መምሪያ ተነስተዋል
ከተባለበት ጊዜ አንስቶ «የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ»እንዲሉ የተበላበትን የስም ማጥፋት የእቁብ ፋይል ዘግቶ አዲሱን ሹም ወደ ማወደስ መሸጋገሩ ነበር። አባ ሠረቀ ከቦታቸው ከተነሱ ተሐድሶነታቸው ቀርቷል ማለት ነው? ወትሮውንም
ተሐድሶ ያላቸው እስኪነሱለት እንጂ ከዚያ በኋላ እንኳን አንዴ አስር ጊዜስ ቢሆኑ እሱ ምን ተእዳው!!
አዲሱን ሹም እየደባበሰ እንቅልፍ በማስያዝ ጉዳዩን
ማስፈጸም እንጂ ቤተክህነት ውስጥ መታደስና ቅን መሆንን የሚወድ እልፍ አእላፍ ስላለ ያንን ሁሉ መከታተል ልብን ማውረድ መሆኑን
ስለሚያውቅ ስለ አባ ሠረቀ ማኅበሩ ድሮውንም ጉዳዩ አይደለም።
አባ ኅሩይ መመሪያ እየሰጡት ሳይሆን ማኅበሩ የተገላቢጦሽ መመሪያ እየሰጠ ሹሙ
ላለፉት ወራቶች ማኅበሩን በታማኝነትና በቅንነት ሲያገለግሉት ቆይተዋል።
ይሁን እንጂ ማኅበሩ ከሰለፊያው የአሸባሪ ቡድን
ጋር በድርጊት የሚመሳሰሉ አባላት እንዳሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓርላማ ከገለጹበት እለት ጀምሮ አሸባሪው በተራው ሽብር ገብቶ ሰንብቷል።
ይህ ማኅበር እንዲህ ያለ ክፉ ቀን ይደርሳል ብሎ
ሳይገምት በትእቢት ተወጥሮ ከብዙዎች ጋር ሲላተም ቆይቷል። «አንድ ሳር ቢመዘዝ ቤት እንደማያፈስ፤ አንድ ሰው ቢባረር ምንም አይጎዳንም»
እያለ ባበጠ ልቡ ይህንኑ ሲተገብር በመቆየቱ ልክ ከጥቁሩ የአሸባሪ መዝገብ ላይ ስሙ ሲጠራ ካደነዘዛቸው ጥቂቶች በስተቀር አብዛኛዎቹ
አካሄዱን ሲቃወሙ የቆዩ ሁሉ ከጠቅላይ ቤተክህነት ጀምሮ እስከ አጥቢያ
ቤተክርስቲያን የሚጠባበቀው ነገር ቢኖር በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተነገረው ቃል ሲተገበር ማየትን ብቻ ነው።
ይህንኑ ማኅበር እያንዳንዱ የጠቅላይ ቤተክህነት
መምሪያዎችና ክፍሎች ሁሉ ሳይቀሩ የቀብር አፈሩን ቶሎ፤ መለስ መለስ
አድርጎ ለማጠናቀቅ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ ምን ትጠብቃላችሁ? በሚል ሃሳብ ከዚህ ቀደም ማኅበሩ ለመፈጸም ፈቃደኛ ያልሆነባቸውንና «ይልቁንም የራሳችሁን ስራ ሰርታችሁ ባሳያችሁን ነበር
» ሲል የጻፈውን ተመጻዳቂ ደብዳቤውን ለማሳፈር ጊዜው ዛሬ ነው በማለት መረጃ አስደግፈው ደብዳቤ እንዲጻፍለት አስደርገዋል።