Friday, February 24, 2012

ኪዳናት ስንት ናቸው?


                                         እግዚአብሔር ስንት ኪዳን ሰጠ?

      “..........አዎ! እግዚአብሔር ልጆቹ ይጠቀሙ ዘንድ በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ ቅዱሳኑ ጋር ቃል ኪዳን  ገብቷል፡፡ ከእነዚህም ኪዳነ አዳም፣ ኪዳነ ኖኅ፣ ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ዳዊት እንዲሁም በጌታችንና   በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች በሙሉ የተሰጠ ሐዲስ ኪዳን ተጠቃሾች ናቸው ….....”             
                  
                                 ( የአንድ አድርገን ብሎግ አስተምህሮ)

 
                   «.....ፊተኛው ኪዳን ነቀፋ ባይኖረው፥ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር»ዕብ ፰፣፯
    « ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው»ዕብ ፱፣፲፭
                                 (መጽሐፍ ቅዱስ)
  
አንድ አድርገን ብሎግ  የአዲስ ኪዳኑን የኢየሱስ ክርስቶስን ኪዳንና  ሌሎችንም ዘርዝሮ የኪዳነ ምሕረትን ጨምሮ ብዙ፣ ብዙ ለመዳን የሚሆኑ ኪዳኖች  እግዚአብሔር ለሰው ልጆች እንደሰጠ ያለምንም መሸማቀቅ በኩራት ዘግቦልን ይገኛል። ስህተቱን የከፋ የሚያደርገው እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠው «ኪዳን» ሁለት ብቻ መሆኑን በመጽሐፍ ቅዱስ የተነገረውን በመካድና በዚህ የክህደት አስተምህሮ ውስጥ ሌሎችንም ይዞ ወደጥፋት ለማምራት ማወጁ ነው።
 አንድ አድርገን ብሎግ ክህደቱን ለማስፋፋት «ኪዳነ አዳም፣ኪዳነ ኖኅ፣ኪዳነ አብርሃም፣ ኪዳነ ዳዊት እንዲሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ ሐዲስ ኪዳን» እግዚአብሔር ለእኛ ጥቅም የሰጠን ኪዳኖች ናቸው ሲል ያለምንም ሀፍረት ጽፏል።
መጽሐፍ ቅዱስ ግን እግዚአብሔር የሰጣቸው ኪዳኖች ሁለት ብቻ መሆናቸውን በግልጽ አስቀምጧል። «ነቀፋ የተገኘበት ፊተኛውና የዘለዓለም ርስት የሚሆን አዲስ ኪዳን » ናቸው በማለት።
 «.....ፊተኛው ኪዳን ነቀፋ ባይኖረው፥ ለሁለተኛው ስፍራ ባልተፈለገም ነበር»ዕብ ፰፣፯
                     
          «  « ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው»ዕብ ፱፣፲፭                         
        

                    «ፊተኛው ወይም ብሉይ ኪዳን»

እግዚአብሔር ይህንን ኪዳን የሰጠው ለሰው ልጆች ሁሉ ሳይሆን እርሱ ለመረጣቸው ሕዝቦች ብቻ ነበር። ይኸውም ከጥፋት ውሃ በኋላ የአባታቸውን የኖኅን ገመና የሸፈነውና፣ የበረከት ልጅ ሆኖ የተመረቀ በምድር ቡሩክነት  የተመረጠው የሴም ዘር  ነበር። «እንዲህም አለ፦ የሴም አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ፥ ከነዓንም ለእነርሱ ባሪያ ይሁን»፱፣፳፮  የተመረጡትና የበረከት ምርቃት የወረደላቸው ሴማውያን የእግዚአብሔር«ሕዝቦች» ሲባሉ ከነዓናውያን ግን «አሕዛብ» ተብለው መቅረታቸውንና የመጀመሪያውንም ቃልኪዳን እግዚአብሔር የሰጠው ለእነዚህ ሴማውያን እስራኤል ብቻ እንደሆነ ከቅዱሱ መጽሐፋችን ላይ እናነባለን። የሴም የትውልድ ሐረግ እስከአብርሃም ድረስ ያለውን ከዘፍጥረት ፲፩ ጀምሮ እናገኘዋለን። እንግዲህ እነዚህ ሕዝቦች ናቸው ከአሕዛብ የተለዩ ተብለው በእግዚአብሔር የተመረጡት።
«አሁንም ቃሌን በእውነት ብትሰሙ ኪዳኔንም ብትጠብቁ፥ ምድር ሁሉ የእኔ ናትና ከአሕዛብ ሁሉ የተመረጠ ርስት ትሆኑልኛላችሁ»ዘጸ ፲፱፣፭
«ሙሴና ሌዋውያን ካህናት ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ ብለው ተናገሩ። እስራኤል ሆይ፥ ዝም ብላችሁ አድምጡ ዛሬ የአምላክህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ሆነሃል» ዘዳ ፳፯፣፱
 እነዚህን ሕዝቦች እግዚአብሔር መርጧቸዋል። ከእነዚህ ምርጦቹ ጋር ለእርሱ ቅድስና በሚሆን መልኩ የመሪና የተመሪ ሕግ የሆነውን ውል በሙሴ በኩል በኮሬብ ተራራ ላይ  ሰጥቷል። ይህ ህዝብ በዚህ ህግ እየተመራ ኖሯል። ህጉን ሲጥሱ እየቀጣቸው፣ ሕጉን ሲጠብቁ እየባረካቸው እንደኖሩ ሙሉ የብሉይ ኪዳን መጽሐፍ በሰፊው ይነግረናል። ይህ የመጀመሪያው ኪዳን መሆኑ ነው። ለሕዝብና ለአሕዛብ የሚሆን ሌላ ሕግ እስኪመጣ ድረስ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ጋር ቃል የተገባባበት የቀደመው ኪዳን  ስፍራውም ኮሬብ ነው። ኪዳኑንም በ፲ ቱ ሕግጋት ሥር የሚጸና ልዩ ልዩ አፈጻጸሞችን የያዘ መተዳደሪያ ውል ነበር።

Thursday, February 23, 2012

«ክርስቶስን መምሰል»

  ‹‹ለእኔ ክርስትና ክርስቶስን ለመምሰል መጣር ነው››

በጋዜጣ ሻጩ ጐልማሳ ክንድ ላይ ከተደረደሩት የህትመት ውጤቶች መካከል ትኩረቴ ባረፈበት መሔት የፊት ገላይ ከቲያትር ባለሙያዋ ጀማነሽ ሰለሞን ጉልህ ምስል በታች የተፃፈውን “እኔ ክርስትና ክርስቶስን ለመምሰል የጣር ነው” የሚለው ዓ.ነገር እንዲያ ባለ ሁኔታ ደመቅ ብሎ ይሰፍር ዘንድ የቻለበትን ምክንያት ለመፈተሽ የመîሔቱን  የውስጥ ገጾች መግለጥ አስፈለገኝ፡፡ ይህንኑም ባደረኩ ጊዜ በውስጡ ከዚህ አባባል የማይተናነሱ ሃሳቦችን ማግኘቴ ሲገርመኝ ሰንብቶ ይህንን አደርግና እናገር ዘንድ ገፋፋኝ፡፡
ጀማነሽ ሰለሞንን የማውቃት ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት እሷ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቲያትር ጥበባት ዘርፍ ተማሪ በነበረችበትና እኔ ደግሞ ለዚያ ዘርፍ እንደ ቤተ-ሙከራ ሆኖ በሚያገለግለው በዩኒቨርስቲው ባህል ማዕከል አባል ሆኜ ሳለ ነው፡፡ በወቅቱ አብረዋት ከነበሩት እንስት ተማሪዎች በባህሪያቸው ልስልስ ሆነውልኝ ወዳጃዊ ቀረቤታን ከቸሩኝ የሻሽወርቅ በየነና ኤልሳቤጥ መላኩ በተቃራኒ ጀሜ ኮስተር ያለችና ኩሩ ቢጤ ስለነበረች ያንን ሁኔታ አልፌ ገንዘቤ አደርጋት ዘንድ የወቅቱ ስሜቴ ባይፈቅድልኝም ግና ልጅት በትምህርት ቤት ሳለችም ሆነ ወደ ሥራ ዓለም ከገባች በኋላ የተሰጥኦዋን ከፍተኝነት፣ ጉብዝናዋንና ሙያዊ ጥንካሬዋን ከሚያደንቁላት የጥበቡ አፍቃሪዎች አንዱ መሆኔን መካድ አልችልም፡፡

Wednesday, February 22, 2012

ልሳን


ልሳን ምንድን ነው

ሀ . ልሳን ምንድን ነው፤ በመጽሐፍ ቅዱስ የተጠቀሰቸው ቦታዎችሰ
1.ልሳን ቋንቋ ማለት ነው።
ልሳን ማለት ቋንቋ ማለት ነው። በአዲስ ልሳን መናገር ማለትም በአዲስ ቋንቋ መናገር ማለት ነው። በአዲስ ቋንቋ መናገር ሲባልም ተወልደው ባላደጉበት፤ ባልተማሩት ቋንቋ በመንፈስ ቅዱስ ገላጭነት መናገር ማለት ነው። የመጀመሪያውና ትክክለኛው ልሳን የተገለጸው በጰራቅሊጦስ እለት ነው። ታሪኩም በሐዋርያት ስራ ምዕራፍ ሁለት ተገልጿል። ሐዋርያትም ሆነ በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖች የተናገሩት በሚሰማና ሊተረጎም በሚችል ቋንቋ ነበር። ሐዋ 2፡ 6 ይህም ድምፅ በሆነ ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ተሰበሰቡ፥ እያንዳንዱም በገዛ ቋንቋው ሲናገሩ ይሰማ ስለ ነበር የሚሉትን አጡ። ሐዋርያት በልሳን ሲናገሩ የተሰበሰቡት አይሁድ በራሰቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋል። ሐዋርያት የሚያወቁት የራሳቸውን ቋንቋ ብቻ ነበር ነገር ግን እነዚህ ሰዎች የተሰበሰቡት ከዓለም ሁሉ ነበር። ሐዋርያትም የተናገሩት የአለምን ቋንቋ ነበር።ጌታችንም በማር 16፤ 17 በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ ሲል በሚሰማ ቋንቋ ማለቱ ነው።
1ኛቆሮ 14፡ 9-11 እንዲሁ እናንተ ደግሞ የተገለጠውን ቃል በአንደበት ባትናገሩ ሰዎች የምትናገሩትን እንዴት አድርገው ያስተውሉታል ? ለነፋስ የምትናገሩ ትሆናላችሁና። በዓለም ምናልባት ቁጥር የሌለው የቋንቋ ዓይነት ይኖራል ቋንቋም የሌለው ሕዝብ የለም፤ እንግዲህ የቋንቋውን ፍች ባላውቅ ለሚናገረው እንግዳ እሆናለሁ፥ የሚናገረውም ለእኔ እንግዳ ይሆናል።
ብሎ ቋንቋ ሁሉ ሰሚ እንዳለውና እናንተም የምትናገሩት ቋንቋ ሰሚ ባለው ህዝብ መሐከል መሆን አለበት ብሎ ያብራራል።
2.ልሳን መንፈስ ቅዱስ ከሚሰጣቸው ልዩ ልዩና ስፍር ቁጥር ከሌላቸው ጸጋዎች አንዱ ነው።