Showing posts with label ታሪክ. Show all posts
Showing posts with label ታሪክ. Show all posts

Wednesday, March 13, 2013

እቴጌ ጣይቱ ብጡል

                                                                          (ምንጭ፤wikipedia)
                                                                      
ባለቤት             ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ
አባት    ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም
እናት    ወይዘሮ የውብዳር
የተወለዱት       ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፪ / በደብረ ታቦር
የሞቱት             የካቲት ቀን ፲፱፻፲ ..
የተቀበሩት        ታዕካ ነገሥት በዓታ /ክርስቲያን
ሀይማኖት         የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና

«ብርሃን ኢትዮጵያ» በሚል ቅፅል ስም የታወቁት እቴጌ ጣይቱ ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ከእናታቸው ወይዘሮ የውብ ዳር ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፪ / በጌምድር ውስጥ ደብረ ታቦር ከተማ ተወለዱ። በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሠረት በተወለዱ ቀናቸው ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፰፻፴፫ / በደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነሡ። በልጅነት ዘመናቸው በዚሁ ደብር ውስጥ ዳዊትን ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ በጊዜው ይሰጡ የነበሩትን ሌሎች የሃይማኖት ትምህርቶች በየታላላቁ አድባራት በመዘዋወር ያጠናቀቁ ስለመሆናቸው ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ። የተማሩባቸውም መፃሕፍት ተጽፈው ይገኙ የነበረበትን የግዕዝ ቋንቋ አጣርተው ያውቁ ነበር። እናታቸው ወይዘሮ የውብዳር ከባለቤታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም ከሞቱ በኋላ በጅሮንድ መዩ የተባሉትን የዓፄ ቴዎድሮስን ባለሟል አግብተው ነበር። እሳቸውም ጣይቱ ብጡል ትምህርት እንዲቀስሙ ለማድረግ ልዩ መምህር ቀጥረውላቸው እንደነበር ይታወቃል። እቴጌ ጣይቱ በማኅደረ ማርያም ሆነው ሲማሩና መፃሕፍትን ይቀጽሉ በነበሩበት ጊዜ ለቤተክርስቲያን መጋረጃ መሥሪያ በትርፍ ጊዜያቸው ፈትል እየፈተሉ ያቀርቡ ነበር። በበገና ቅኝትና ድርደራም በኩል የታወቁ ባለሙያ እንደነበሩ ይተረክላቸዋል።
ከንጉሥ ምኒልክ ጋር ጋብቻ
የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በሸዋ የዓፄ ቴዎድሮስ እንደራሴ ከነበሩት አቶ በዛብህ ጋር ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፰፻፶፯ / በጋዲሎ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ድል አድርገው ወደ አንኮበር ገብተው በነሐሴ ፳፬ ቀን ነገሡ። በነገሡም በአሥራ ሁለት ዓመታቸው የፋሲካን በዓል በባሕር ዳር አቅራቢያ ሱሉልታ ላይ ዋሉና ደብረ መይ በጣይቱ ብጡል እናት በወይዘሮ የውብዳር ቤት ከጣይቱ ብጡል ጋር ተጫጭተው ስለጋብቻቸው ተነጋገሩ። ከዚያም ዋና ከተማቸው ወደነበረችው ደብረ ብርሃን ተመልሰው መጡ።
ከተጫጩ ከሁለት ዓመት በኋላ ወይዘሮ ጣይቱን ለማስመጣት በቤተ መንግሥቱ በተደረገው ምክር መሠረት አለቃ ተክለማርያም ወልደ ሚካኤል ደብዳቤ ተሰጥቷቸው ተላኩ። በዚያም አስፈላጊው ሁሉ በተፋጠነ ሁኔታ ተሟልቶ በጐጃም በኩል ደንገጡሮችና አሽከሮች አስከትለው ጉዞውን ጀመሩ። ደብረ ብርሃንም በገቡ ጊዜ ንጉሡ /ምኒልክ/ ታላቅ አቀባበል አደረጉላቸው። ከዚያም ጣይቱ ወንድማቸው ራስ ወሌ ብጡል ዘንድ ለጥቂት ዓመታት ተቀምጠው ከቆዩ በኋላ የጋብቻቸው ስነ-ሥርዓት የፋሲካ ዕለት ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፲፰፻፸፭ / በአንኮበር መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለው ተጋቡ።
አፈወርቅ ገብረ ጊዮርጊስዳግማዊ አጤ ምኒልክበተባለው መጽሐፋቸው ገጽ ፴፱--፵፩ ላይከልዢነት ጀምረው ሲመኟት እንደ ህልም ሲአልሟት ትኖር የነብረችው ጣይቱ ብጡል በ፲፰፻፸፭ / ደብረ ብርሃን ገባች ንግሥተ ሸዋ ሆነች ወዲያው የፋሲካ ለት አንኮበር መድኃኔ ዓለም ቆርበው ሁለቱ ተጋቡ።ፀሐይቱ ለማለት ጣይቱ ተባለች ነገር ግን ከጣይቱ እጣይቱ ለመባል ይገባታል።ይላሉ

Tuesday, July 24, 2012

አቢሲኒያ የሚለውን ስም ከእኛ ይልቅ ነጮቹ ይጠቀሙበታል!


የዛሬዋ ኢትዮጵያ በአንድ ወቅት ታላቅ ሀገር እንደነበረች ታሪክ ይናገራል።  በግዛት ስፋት፤ በጦር ኃይል ብዛት፤ በሥነ ሕንጻና በሥነ ጽሁፍ ገናና ሆና መቆየቷን የሚናገሩ ብዙ የታሪክ ድርሳናት አሉ። በእርግጥ ብዙዎቹም ድርሳናት የተጻፉትና በሰነድነትም የሚገኙት በውጪው ዓለም ነው። አቢሲኒያ የሚለው ስም የትመጣነት ለታሪክ ሀተታ ይቆየንና ኢትዮጵያ የሚለው / ጥቁር መልክ/ ስያሜ ከመሰጠቱ በፊት አቢሲኒያ የምትባለው ሀገራችንን ታሪክ አብዛኛው የምናውቀው « የኢትዮጵያ የቀድሞ ስም» የሚለውን ጥሪ ብቻ ነው። ግፋ ቢልም «አቢሲኒያ ባንክን» !!!
ታሪካዊነቱን የሚገልጽ መታሰቢያ ዩኒቨርሲቲ፤ የጎዳና ስም፤ ሆስፒታል ወይም ሌላ ተመሳሳይ መጠሪያ እስከምናውቀው ድረስ የለንም። ምናልባት ያልሰማነው ካለ ይታረማል። ታሪክና ቅርስ ለአንድ ሀገር ሕዝብ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ማንነት ወሳኝ ነው።  በዘመናት ያለፈባቸውን የጥንካሬና የድክመት ጉዞዎቹን ይቃኝበታል። መጻዒውንም ያማትርበታል።
እስራኤሎች ታሪካቸውን እየጻፉ ለመጪው ትውልድ የሚያኖሩላቸው ጸሐፊያን በየዘመኑ ነበራቸው። በሕይወታቸው ያለፈውን፤ ያደረጉትንና የተደረገላቸውን እየከተቡ ያኖሩ ነበር።
1ኛ ነገ 43
«ጸሐፊዎቹም የሴባ ልጆች ኤልያፍና አኪያ፥ ታሪክ ጸሐፊም የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ»
የእያንዳንዱ ነጋሲ ታሪክና ሥራ እየተጻፈም ይቀመጥ ነበር። ይህም ለልጅ ልጆች የሚቀመጥ ውርስ ነበርና ነው።
1ኛ ነገ 1532
በእስራኤል ነገሥታት ታሪክ መጽሐፍ የተጻፈ አይደለምን?
እኛ ለዚህ አልታደልንም።

 እንኳን እንደዚህ ዓይነት ታሪክ ጽፈን ለማቆየት ይቅርና በዘልማድ  ስለምናውቀው «አቢሲኒያ» ስለሚለው የሀገራችን ስም መታሰቢያ የሚሆን ነገር የለንም። ይሁን እንጂ ፈረንጆቹ በመጽሐፍ ቅዱስ «ኩሽ» በታሪክ አቢሲኒያ፤ በመጠሪያ ደግሞ ዛሬ ኢትዮጵያ ስለምትባለው ሀገራችን የእምነት፤ የጀግንነት፤የታሪክ፤ የቅርስና የመልክዓ ምድር ወዘተ ሰፊ ጥናት አድርገዋል። መጻሕፍትንም ጽፈዋል።
ፈረንሳዊው የታሪክ ጸሐፊ  ጂን ክሪስቶፍ ሩፊን/Jean-Christophe Rufin/ ዘ አቢሲኒያን፤ ሳሙኤል ጆንሰን፤ ጀምስ ብሩስ፤ሪቻርድ በርተን፤ ኢቭሊን  ዎግ፣ ዴርቭላ መርፊ፤ ሲልቪያ ፓንክረስት፤ ኸርበት ቪቪያን፤  ሮማን ፕሮቼስካ ፤ ጆንስ እና ኤልሳቤጥ/ መጽሐፉን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ /  ወዘተ እና ሌሎች ብዙዎች ጸሐፊያን ስለአቢሲኒያ ጽፈዋል።

 ይህንኑ ገናናውን የአቢሲኒያን ታሪክ ተከትሎና ከጥቁር ምድር ቀዳሚ የክርስትና ሀገር ኢትዮጵያ በመሆኗም ጭምር አሜሪካውን ጥቁሮች ቤተክርስቲያኖቻቸውን ጭምር በምድረ አሜሪካ ውስጥ በአቢሲኒያ ስያሜ ይጠሩ ነበር።  ኮሎራዶ በ516ኛው ክሬስትሞር ጎዳና ላይ የሚገኘው የአቢሲኒያውያን ክርስቲያኖች ቤተክርስቲያን፤  ኒውዮርክ በምእራብ 138ኛው ጎዳና ላይ በ1808 የታነጸው የአቢሲኒያውያን መጥምቅ ቤተክርስቲያን፤ 1828 ዓ/ም በ75 ኒው በሪ ጎዳና የተመሰረተው የፖርት ላንድ አቢሲኒያውያን ቤተክርስቲያን፤ እዚው ፖርት ላንድ የሚገኘው የአቢሲኒያውያን የመሰብሰቢያ አዳራሽ፤  ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ በኢትዮጵያ የቀድሞ ስም በአቢሲኒያ ስም የተጠሩ የአሜሪካ ጥቁሮች የታሪክና እምነት ስያሜ መጠሪያዎች ነበሩ። ዛሬም በዚሁ ስም እየተጠሩበት ይገኛሉ። ብዙዎቹም እናት ምድራችን በሚሏት አቢሲኒያ /ኢትዮጵያ/ ተገኝተው ታሪኳን ቅርሷን፤ ክብሯን ሁሉ በአካል ለማየት ችለዋል። ያ ሁሉ ዝናና ታሪክ ተንኮታኩቶ የድሆች መናኸሪያ፤ የስደተኞች መፍለቂያ መሆኗን ሲያዩ ምን ብለው ይሆን?
አብያተ ክርስቲያኖቻቸውን በአቢሲኒያ ስም ከመጥራት ባሻገር አቢሲኒያን በተለያየ ዘመናት የረገጡ ነጮች ከምድረ አቢሲኒያ ድመት፤ ውሻ፤ ፈረስ፤ ድብ፤ አሳማ፣ እጽዋት በመውሰድ በሀገራቸው አራብተዋል፤ አዳቅለዋል።  
ዛሬ በአሜሪካ የአቢሲኒያ ድመት፤ ውሻ፤ ፈረስ ወዘተ በስም ተለይቶና ተመርጦ የሚገዛበት ትልቅ  ስም ነው። እንዲያውም ተፈላጊ መለያ ነው።
የአበሻ ውሾች ቁጡዎችና ኃይለኞች፤ ድመቶቹ አይጥ አዳኞች፤ ፈረሶቹ የጦር ሜዳ ዘመቻ ጋላቢዎች ስለነበሩ እየወሰዱ ተዳቅለዋል። ሳንዲያጎ በሚገኘው ግዙፉ የእንስሳት ፓርክ ውስጥ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ አእዋፍና አሞራዎች አሉ። የአቢሲኒያ ድመቶች ማደቀያ ማኅበር ራሱን ችሎ በአሜሪካና በእንግሊዝ የተቋቋመ ነው።  እንስሳዎቹም በአቢሲኒያ ስም እስከዛሬ ይጠራሉ።
ከታች የሚታዩት ስእሎች በ«አቢሲኒያ» ስም ከሚጠሩ መካከል ጥቂቶቹ  ናቸው።

Sunday, July 1, 2012

አፄ ዓምደ ጽዮንና የኢትዮጵያ አንድነት

ፀሐፊ፤ ሔኖክ ጌትነት

አፄ ዓምደ ጽዮን ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ

ግዛት      ከ1314-1344 ፤  ቀዳሚ ንጉሥ  አፄ ውድም አርእድ(አባት)
ተከታይ ንጉሥ፤  አፄ ነዋየ ክርስቶስ/ ሰይፈ አርእድ ልጅ/
ባለቤት ብሌን  ሳባ/ የባሕረ ነጋሲ ንግሥት/
ሙሉ ስም፤  ገብረ መስቀል
ሥርወ-መንግሥት፤   ሰሎሞናዊ
አባት ፤     ውድም አርእድ
ሀይማኖት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና
ቀዳማዊ አጼ ዐምደ፡ጽዮን (የዙፋን ስም ገብረ መስቀል) ከ1314 እስከ 1344 ዓ.ም. የነገሡ ሲሆን በጥንቱ ዘመን ከተነሱ ነገሥታት ውስጥ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ሰፋ ያለ አሻራ ትተው ካለፉት (ለምሳሌ፦ ዘርአ ያዕቆብ ) ጎን ወይም በላይ ስማቸው ይጠቀሳል። አጼ ዐምደ ጽዮን የአጼ ይኩኖ አምላክ የልጅ ልጅና የአጼ ውድም አርእድ ልጅ እንደሆኑ ይታመናል፡፡ ይኩኖ አምላክ አዲሱን የሰሎሞን ስርወ መንግስት ቢመሰርቱም፣ በልጅ ልጆቻቸው የነበረው ፉክክርና አዲስ ከሚስፋፋው የእስልምና ሃይማኖት የሚሰነዘረው ጥቃት ስርዓቱን ስጋት ላይ የጣለ ነበር። አጼ አምደ ጽዮን ይህን ፉክክር በማስቆምና በዘመናት በማይደበዝዘው ጀግንነታቸው የኢትዮጵያን ድንበር ከሞላ ጎደል አሁን በሚታወቀው መልኩ በማስቀመጥ፣ የአዲሱን ስርወ መንግስት መሰረት በማጽናት እንዲሁም በማረጋጋት ዝናቸው በጥንቱ አለም ክአፍሪቃ ቀንድ እስከ አውሮጳ የተንሰራፋ ነበር።
1/ የአጼ ዐምደ ጽዮን ዘመንና ዘመቻዎች
ዘመቻ ወደ ደቡብ ምዕራብና ሰሜን ኢትዮጵያ
ዓምደ ጽዮን በእንዴት መንገድ ወደ ስልጣን እንደመጡ መረጃ የለም፣ ስለሆነም ታሪክ አጥኝው ታደሰ ታምራት ንጉሱ ከአባታቸው ጋር ትግል ገጥመው ዘውድ ላይ እንደወጡ መላ ምት ያቀርባል ። ንጉሱ በመንግስታቸው መጀመሪያ (፲፫፻፲፮ ዓ.ም. ) የተሳካላቸው ዘመቻዎች በጎጃም፣ ዳሞትና ሐድያ በማድረግ እኒህ አካባቢወች እንዲገብሩ ሆነ[5]። ሆኖም በኒህ ዘመቻወች ትኩረታቸው ስለተሳበ በተገኘው ክፍተት የእንደርታ ገዢ የነበረው ይብቃ እግዚ የአምባ ሰናይት፣ ብልሃትንና ተምቤን ሰራዊትን በማደራጀት በንጉሱ ላይ ተነሳ ። በ1320ዓ.ም ንጉሱ የይብቃ እግዚን አመጽ ከደመሰሱ በኋላ በአምባ ሰናይት የጦር ዕዝ አቋቋመው ወደ ስሜን በመዝመት እስከ ቀይ ባህር ድረስ ያለውን ክፍል ለመቆጣጠር ቻሉ። በዚህ ወቅት እንደርታን እንድታስተዳድር የተሰየመችው የትግሬ ተወላጅ የነበረችው የንጉሱ ሚስት ንግስት ብሌን ሳባ ነበረች። ስልጣኗም ባልታ ብሃት በመባል ይታወቅ ነበር። ቆይቶ እንደርታን እንዲያስተዳድር የተደረገው የንጉሱ ሦሥተኛ ልጅ ባህር አሰገድ በማዕከለ ባህር ማእረግ ነበር፣ ግዛቱም እስከ ቀይ ባህር ወደብ ድረስ የተንሰራፋ ነበር ።

Saturday, June 9, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህም ነበር! በቀሲስ መልአኩ


ካለፈው የቀጠለ.................ክፍል 4
በድንጋይ መስታወቱን አንዴ ሲያደቁት በበሩ የነበረው ታጣቂ (ቦታው የአስተዳደር አዳራሽ ሰለነበር ነው ) ወደ ሰማይ ለመተኮስ ቢሞክርም አልቻለም።  መጨረሻ ላይ ነፍስ አውጭኝ ብሎ ሸሸ።  ከዚያ በኋላ መራኮት ሆነ።  «ዋናው እሱ ነው፤ እርሱን ያዙት!  የሚል ጩኸት ብሰማም የማላውቃቸው ሰዎች መጥተው ስለሸፋፈኑኝ እኔን ለመግደል ለሞከሩት ሰዎች አልሆነላቸውም ነበር።  «ስለ እመ አምላክ ተዉኝ» ከምትለው ነፍሰ ጡር ጀምሮ «እማዬ የት ነሽ»  እያለ እስከሚያለቅሰው ሕጻን ድረስ ታላቅ ጩኸት በአዳራሹ ውስጥ ሞላ።

መግቢያና መውጫውን እነርሱ ስለያዙት በየትም መውጫ አልነበረም። የአካባቢው ጸጥታ ኃይሎች እስኪመጡ ድረስ ሰዎቹ ይዘዉት በመጡት መምቻ ሁሉ መቱት።  ማን  ምን እንደሆነ ለማወቅ ግን አልቻልንም ነበር። በመጨረሻ የጸጥታ ሰዎች በመጡ ወቅት ግን የተወሰነው እነርሱን ጥግ አድርገን ለማምለጥ ቻልን።  ከአካባቢው እየሮጥኩ ስወጣ ታክሲ ስላገኘሁ የማልረሳውን ቃል ተናገርኩ «ከዚህ ቦታ ወደ ፈለግህበት ውሰደኝ» ምንም እንኳን ለጊዜው ለባለ ታክሲው የተናገርኩት ቢሆንም በዚያ ወቅት ግን ለአምላኬም የተናገርኩት ነበር።  «ብቻ ከዚህ ቦታ ወደ ፈልግህበት ውሰደኝ»  ወንድሞቼ በምላቸው የገዛ ወገኖቼ የአንዲት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ስንደበደብ ምን ልበል ? ካሳደገችኝ ቤተ ክርስቲያን ሽሚዜ በደም ጨቅይቶ እንደሌባ በገዛ ሀገሬ ወገኔ ፊት ስሸሽ  ምን ልበል ? (ከልለው ባወጡኝ ሰዎች ደም ጭምር ነበር የዳንኩት! እኔ ብቻ ሳልሆን  እነርሱ ለኔ ደሙልኝ ) የደማሁት ቀላል ቢሆንም  በታክሲ የተቻልኝን ያህል ራቅሁ።  የራቅሁት ግን ሕይወቴን በሙሉ ከሰጠሁበትም ቦታ ነበር።
 
ከድሬዳዋ ድብደባ በኋላ ወዲያው ሐረር ነበር የተመለስኩት። በሐረር ሁኔታው ተሰምቶ ስለነበር ሕዝቡ ሁል አንድ ነገር የሆንን መስሎት ነበር።  በሰላም መመለሳችን ደስታ ቢሆንም የእኛን እግር ተከትሎ አንድ አስደንጋጭ ዜና ደረሰ።  ከተደበደቡት መካከል ሦስቱ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙና በተለይም አንደኛው በኮማ ውስጥ እንዳለ ተነገረን።  ሁላችንም አለቀስን።

Monday, June 4, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህም ነበር! በቀሲስ መልአኩ


 ካለፈው የቀጠለ.................ክፍል 3

ፕሮቴስታንቶች አንዳችም ሊያደርጉት ያልተቻላቸውንና በሌሎች ሃይማኖት በተከበበች ምድር አስደናቂ እንቅስቃሴ ያደርግ የነበረውን የሰንበት ትምህርት ትምህርት ቤቶች እንቅስቃሴ በድርጅታዊ ፍቅር ታውሮ የበታተነው ማኅበረ ቅዱሳን በሚል ስም የተቋቋምው ድርጅት ነበር ማኅበረ ቅዱሳን ሐረር ላይ ያለውን የሰንበት ትማህርት ቤቶች እንቅስቃሴ በክፉ ዓይን ማየት የጀመረው  ዓለማያ ግብርና ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ገና እግሩን በተከለበት ወቅት ነው በዚህ ወቅት ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል ማኅበር በሐረር ስሙም  የማይታወቅ ስለነበረ በሐረር ያሉ ካህናትም ሆኑ ምእመናን ቦታ አልሰጡትም ነበርነገር ግን ጥቂት ቆይቶ ማኅበረ ቅዱሳን ለጠቅላይ ቤተ ክህነትና ለሐረርጌ ሀገረ ስብከት አቤቱታ አስገባ አቤቱታውም ሐረር ውስጥ ያሉት ሰንበት ትማህርት ቤቶች በሙሉ ተሐድሶ ናቸው የሚል ነበር።  ለጊዜው የሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት የማኅበሩን ክስ አጥብቆ ተቃወመ የሐረር ሕዝበ ክርስቲያንም ሁኔታውን ሲስማ አጥብቆ ተቃወመ።
ማኅበረ ቅዱሳንን ሐረር ምድር ላይ ላለማስገባት ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ተጀመረ።  ሁኔታው ያላመረው ማኅበረ ቅዱሳን የሐረር ሕዝበ ክርስቲያንን የሚከፋፈልብትን አንድ ረቂቅ ተንኮል አርቅቆ አወጣ።  ያም በሐረር የሚገኙ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን የተሐድሶ አባላት የሚያሳይ የሐሰት ሰነድ ነበር።  ሰነዱ በቃለ ጉባኤ መልክ የተዘጋጀ ሲሆን የተሐድሶ አባላት የሆኑ ከመላው ኢትዮጵያ ተሰብሰበው ለሐረር እንቅስቃሴ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚሰጡ ለሐረርም መሪዎችን እንደሾሙ የሚናገርና ስሞችንም የሚዘረዝር ነበር።

በዚህ የሐሰት ሰነድ ላይ መልአከ  ሰላም ጴጥሮስ አዘነን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ፤ የሀገረ ስብከቱን የመዝገቡ ቤት ኃላፊ፤ ሌሎች ካህናትና ታዋቂ ምእመናን የያዘ ነበር።  በሰነዱ ላይ የተዘረዘሩት ቀንደኛ የሆኑ ማኅበር ቅዱሳንን አላፈናፍንም ያሉ ሰዎች ነበሩ።  በወቅቱ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተሾሙት መምህር ብርሃነ ህይወት (አባ ዜና ማርቆስ የተባሉት በስሜን አሜሪካ ባሉት ታላቅ አባት ምትክ የተሾሙት ) በደስታ ቸኩለው ተሐድሶዎች ቤተክርስቲያኔን ወረዋል በማለት በሸኚ ደብዳቤ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ፤ ካህናቱን፤ የደብር አስተዳዳሪውን ታላቁን ሊቅ መልአከ ሰላም ጴጥሮስ ከስራና ከደሞዝ አገዱአቸው።