Saturday, March 29, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን የሚፈርሰው በራሱ ተግባር ነው፤ ኢሕአዴግ ላለፉት 22 ዓመታት መቼ ነካው?



ይህ ህንጻ የማነው? የቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን? የመንበረ ፓትርያርክ? የኢንቨስተር? የነጋዴ? የአስመጪና ላኪ?

የሀገሬ ሰው «ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል» ይላል። ይህ አባባል ለሰሞነኛው የማኅበረ ቅዱሳን የጅቡ በላኝ ጩኸት ይስማማል። ኢህአዴግ ሊያጠፋኝ ነው ሲል በየግል ጋዜጣው ማስወራቱ 22 ዓመታት ኢህአዴግ በሚመራት ሀገር ውስጥ ያልነበረ ይመስላል። ሲነግድ፤ ሲያስነግድ፤ ሲሸጥ ሲለውጥ፤ከግብርና ታክስ ተከልሎ በሚሊዮኖች ብር ህንጻ ሲገነባ በሀገሪቱ ኢህአዴግ ያላየው ወይም የማያውቀው ይመስላል። ኢህአዴግ ማኅበረ ቅዱሳንን በአስማት ይሁን በምትሃት እስከዛሬ ሳያየው ቆይቶ አሁን ለማየት ዓይኑን ሲከፍት ማኅበረ ቅዱሳንን አገኘውና ሊበላው ስለሆነ ማኅበረ ቅዱሳን ኢህአዴግ ሊያጠፋኝ ለምን ፈለገ ሲል ለመጠየቅ የተገደደ ይመስላል። በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ያለው ተግባሬ ከማኅበረ ካህናቱ ጋር አጋጨኝ፤ በማያገባኝ አስተዳደር ውስጥ እጄን ሳስገባ ተገኘሁ እንዳይል ከመሬት ተነስቶ ኢህአዴግ ሊውጠኝ ነው ወደሚል ቅስቀሳ መግባቱን  ከመምረጡ በስተቀር በምድር ላይ ያለው እውነታ ግን የምርጫ ዘጠና ሰባት ውጤትና ተከትሎ የመጣው ፖለቲካዊ ቀውስ ስንቱን ፓርቲና የተቃዋሚ መሪዎች እየደፈጠጠ ሲያልፍ ማኅበረ ቅዱሳን ግን በቤተ ክርስቲያኒቱ ታዛ ተጠልሎ አልፏል። ኢህአዴግ ቢያጠፋው ኖሮ ያኔ ባጠፋው ነበር።
ከዚህ በፊት ማኅበሩ እንደጥራጊ አውጥቶ የጣለው ዳንኤል ክብረት ይህን ኢህአዴግ ሊበላኝ ነው የሚለውን የማኅበረ ቅዱሳንን ዘፈን እንዲህ ሲል በደጀሰላም ብሎግ ላይ አውጥቶ ነበር።
«እኔ እንደምገምተው የማኅበሩ አባላት መንግሥትን እንዲፈሩ እና እንዲጠሉ የሚፈልጉ አካላት በአመራሩ ውስጥ ሳይኖሩ አይ ቀርም፡፡ ምንጊዜም አንዳች ከባድ ነገር ሲነሣ መንግሥት እንዲህ ብሎናል፣ በዚህ ስብሰባው እንዲህ ብሏል፣ ሊዘጋን ነው፣ ሊያስረን ነው፣ ሊጨርሰን ነው ከማለት ያለፈ አንድም ቀን በጎ ነገር ስለ መንግሥት የማያነሡ አካላት አሉ»
 ስለዚህ ከዚህ አባባል ተነስተን ልንል የምንችለው ነገር ይህ መንግሥት ሊበላን ነው የሚለው ዜማ እንደስልት የተያዘና መንግሥት በአባላቱ ዘንድ እንዲጠላ የተዘየደ መሆኑ ነው። ከዚያም ባሻገር መሰሪ ስራውን ለመደበቅ ራሱን ጻድቅ አድርጎ በሌሎች ሰዎች ዘንድ ለመሳል የታቀደ ጥበብ ሲሆን ጻድቁ ማኅበረ ቅዱሳንን ኢህአዴግ ሊያጠፋው ስለሆነ ኦርቶዶክሳውያን የሆናችሁ ሁሉ የዚህን መንግሥት መሠሪነት ተመልከቱ ብሎ ክፉ ስዕል ለመስጠት የተፈለገ ብልጠት ነው።
እውነቱ ግን ማኅበረ ቅዱሳን ነጋዴ ድርጅት መሆኑ ማንም ያውቃል። የግል ይሁን የአክሲዮን ማኅበር መሆኑ ያልታወቀና የራሱን ሀብት የፈጠረ ተቋም ስለመሆኑም ስራው ምስክር ነው። ማኅበረ ቅዱሳን ከንግድ ተቋማቱና ከልዩ ልዩ የገቢ ምንጮቹ ባሻገር የራሱ የሆኑ አባላት ያሉትና የአባልነት መዋጮ የሚሰበስብ ድርጅት ነው። ከዋናው ማዕከል ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ ቁመት የራሱ የሆነ መዋቅርና  ራሱን የቻለ አደረጃጀት ያለው ነገር ግን አደረጃጀቱ በየትኛው የሀገሪቱ  የአደረጃጀት ፈቃድ ላይ እንደቆመ ያልታወቀ መሆኑም እርግጥ ነው። ይህንን የራሱ ተቋማዊ ኅልውና ያለውን ማኅበር በሀብቱ፤ በንግድ ተቋማቱ፤ በመዋቅራዊ አካላቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመቆጣጠርና የማዘዝ ምንም ሥልጣን የላትም።  በአንጻሩም ማኅበሩ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስር ተሸፋፍኖ እንደመጠለሉ መጠን ቤተ ክርስቲያኒቱ በማኅበሩ ላይ የመቆጣጠርና የማዘዝ ሥልጣን እንዳላት ግምት ያለው በመሆኑ መንግሥት ይህን ድርጅት ነክቶት አያውቅም። ስለዚህ ይህንን ማኅበር ቤተ ክርስቲያኒቱም፤ መንግሥትም ሳይመለከቱት ከሁለት ወገን ቁጥጥር ነጻ ሆኖ 22 ዓመት ዘልቋል።
 «ለሁሉም ጊዜ አለው» እንዲሉ ሆኖ ማኅበሩን ማነህ? ምንድነህ? የት ነህ? ምን አለህ? ምን አገባህ? የሚሉ ካህናትና የአመራር አካላት ተባብረው በመነሳት መጠየቅ ሲጀምሩ ጥቂት ሟሳኞችና አሟሳኞች ወደሚል ሃሳብ ለመውረድ ተገዷል።  በምንም ደረጃ ያሉ ሰዎች ማኅበረ ቅዱሳንን መክሰስ መቻላቸው የማኅበሩን ማንነት ማሳያው ተግባሩ እንጂ ክሱ አይደለም።  እየተከሰሰ ያለው ማኅበር በተግባሩ ያልታወቀ ማኅበር ባለመሆኑ በሟሳኞችና አሟሳኞች የቃላት ጫወታ እየፈጸመ የቆየውን ሸፍጥ ሸፍኖ ማስቀረት አይቻልም።
ማኅበረ ቅዱሳን በተግባር በሌለው ሥልጣንና መብት መናፍቃን ናቸው ያላቸውን ኢትዮጵያውያንን በራሱ ጥቁር መዝገብ አስፍሮ አስደብድቧል፤ ሰልሏል፤ ስም አጥፍቷል፤ አስፈራርቷል፤ እንዲሰደዱ አድርጓል። ማኅበረ ቅዱሳን በቤተክርስቲያኒቱ ስም መጽሔትና መጻሕፍትን፤ ካሴትና ቪዲዮ፤ አልባሳትና ንዋየ ቅድሳትን ከታክስና ከቀረጥ ነጻ ሆኖ ነግዷል። የማኅበረ ቅዱሳን አቋም የሚቃወሙ ሁሉ ጠላቶቹ ናቸው። የሚደግፉት ደግሞ ጳጳሳቱ ሳይቀሩ ወንጀል ቢኖርባቸው እንኳን የቤተ ክርስቲያኒቱ ታማኝ አገልጋይ ተደርገው ዜና ይሰራላቸዋል፤ ሙገሳ ይሰጣቸዋል። አባ እስጢፋኖስን ማንሳት ይቻላል። ጠላቶቼ ከሚላቸውና ስማቸውን ሌሊትና ቀን ሲያጠፋቸው ከቆዩት ጳጳሳት ውስጥ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ደግሞ የጥላቻ የአፍ መፍቻው ናቸው። ሌሎቹም ፈርተው አንገታቸውን ደፍተውለታል። የተገዳደረውን አንገት ያስደፋል፤ አለያም ቀና ካለ አንገቱን ይሰብራል።  ሌላው ቀርቶ ሲያመሰግናቸው የነበሩትን አዲሱን ፓትርያርክ ጠላቶቼ የሚላቸውን ሰዎች ሲቀጣ በቆየበት መልኩ በስም ማጥፋት ቅጣት ናዳውን እያወረደባቸው ይገኛል። ለራሱ ኅልውና ብቻ የሚጨነቅ፤ ካልመሰለው ደግሞ ሲያወድሳቸው ለነበሩት ሳይቀር ግድ የሌለው ማኅበር ስለመሆኑ ከድርጊቱ ተነስቶ መናገር ይቻላል።  ወትሮውንም ሸፋጭ ነጋዴ ገንዘቡን እንጂ ወዳጅና እውነት በእሱ ዘንድ ዋጋ የሌላቸው ስለሆኑ የሚያስበው ጊዜያዊ ትርፉን ብቻ ነው። በዚህ ዙሪያ ማኅበሩ አሸንቅጥሮ የጣለውና ለተቀበለው የእጅ መንሻ በውጪ እንዳለ የሚለፈልፈው ዳንኤል ክብረት ማኅበሩ ስለግለሰቦችና ስለቤተ ክርስቲያኒቱ ደንታ ቢስ እንደሆነ ያጋለጠው እንዲህ ሲል ነበር።
«ዲያቆን በጋሻው ማስተማር የጀመረው መቼ ነው? ማኅበሩ በነዲያቆን በጋሻው ላይ ሃሳብ ዛሬ መሠንዘር ለምን ጀመረ? በጋሻው ለቤተ ክርስቲያን አደጋ ነው ብሎ ስላሰበ አይደለም፡፡ በጋሻው ማኅበረ ቅዱሳንን በተመለከተ ስለ ተናገረ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ምንም ያልተናገረው ማኅበር ስሙ ሲነሣ ቤተ ክርስቲያን ተነካች ብሎ ተነሣ፡፡ ማኅበሩ አቡነ ጳውሎስን በተመለከተ የተለየ አቋም መያዝ የጀመረው መቼ ነው? «እርሳቸው ማኅበሩን ሊያፈርሱ ነው» ብሎ መሥጋት ከጀመረ በኋላ፡፡ አባ ሠረቀንም ቢሆ ንኮ ዛሬ ዛሬ በእምነት ችግር ይከሳቸዋል እንጂ፣ ከእርሳቸው ጋር ያለው ዋናው ችግሩ ማኅበሩ መነካቱ ነው፡፡ አባ ሠረቀ ማኅበረ ቅዱሳንን ሳይነኩ የፈለጉትን ቢሆኑ ኖሮ አይናገራቸውም ነበር፡፡ ባለፈው ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ ችግር ሲፈጠር፣ ዝምታን መርጦ የነበረው አመራር የመንግሥት አካላት ከቤተ ክህነቱ ባለሥልጣናት ጋር ሆነው ስለ ማኅበሩ ሲያወያዩት ግን አገር ይያዝልኝ አለ፡፡ የአዋሳ ምእመናንን ችግር በዝምታ ያለፈው አመራር አባ ሠረቀ አንዳች ነገር ተናገሩ ብሎ ድምፁን አሰምቶ ተናገረ፡፡ እነዚህ እና መሰል ሁኔታዎች አመራሩ የሚቆረቁረው ማኅበሩ ሲነካ እንጂ ቤተ ክርስቲያኒቱ ስትነካ አለመሆኑን ያመለክታሉ» ስለዚህ ማኅበረ ቅዱሳን ከራሱ በላይ ማንንም እንደማይወድ እርግጥ ነው።
ማኅበረ ቅዱሳን በፖለቲካው ዙሪያ ከምርጫ 97 በፊትም ሆነ በኋላ ስላለው ሁኔታ መንግሥት በቂ መረጃ እንዳለው ይሰማል። በዚህ ዙሪያ መንግሥት ያለውን መረጃ እስኪያወጣ ድረስ የምንለው ነገር የለም። ነገር ግን ማኅበሩ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲያምሳት መቆየቱን፤ እጁን እያስገባ ሲኖዶሱን ሳይቀር እንደሚጠመዝዝ እናውቃለን። ማኅበሩ ደፋርና የልብ ልብ የተሰማው አንዳንድ የሲኖዶስ አባላት ተጠግቶ የጉባዔ ሃሳብ በራሱ መንገድ እስከመጠምዘዝ የመድረሱን አቅም እየለካ በመሄዱ ነው። ዛሬ ላይ ያ ነገር የለም። ፓትርያርክ ማትያስ ለዚህ የማኅበሩ ሃሳብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ገና አንድ ዓመት ሳይሞላቸው ከኢህአዴግ ጋር ተመሳጥረው ሊያጠፉኝ ነው እያለ ስም ወደማጥፋት ወርዷል። በተቃራኒው ደግሞ ማንም እንደማያጠፋው በሚገልጽ ጀብደኝነቱ ፓትርያርክ ጳውሎስም እንደዚሁ ሊያጠፉኝ ሞክረው እንደማያዋጣቸው አውቀው አጃቸውን ከእኔ ላይ ለማንሳት ተገደዋል በማለት ለፓትርያርክ ማትያስ የማስጠንቀቂያ ማስታወቂያ እየሰራ ይገኛል። እጅዎን ከእኔ ላይ የማንሳትን ጉዳይ ችላ ሳይሉ ከቀድሞው ፓትርያርክ ትምህርት ውሰዱ በማለት ማሳሰቢያ እየሰጠ መሆኑ ነው። የሚፈራው ከተገኘ ጥሩ ጀብደኝነት ነው፤ ነገር ግን ባለቀ ጊዜ ማላዘን ዋጋ የለውም። ማኅበረ ቅዱሳን ቤተክርስቲያኒቱ ስንት ችግር ባለባት ሰዓት ራሱ ችግር ፈጣሪ ሆኖ ካለቦታው የተገኘ ማኅበር ስለሆነ ተገቢ ቦታውን መያዝ ካለበት ሰዓቱ አሁን ነው። ማኅበረ ካህናቱና የቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር አባላት ጠንክሮ መታገል የሚገባችሁ ወቅት ቢኖር ዛሬ ነው። ማኅበሩ ቁጭ ብሎ አዋጭ የሆነውን መንገድ መቅረጽ ካለበት ቶሎ ብሎ ይህንኑ እንዲፈጽም ምክር እንለግሰዋለን። የአክሲዮን ማኅበር፤ የሃይማኖት ተቋም፤ በጎ አድራጊ ድርጅት ወይም የተሻለ ነው ብሎ የደረሰበትን ውሳኔ ወደተግባር መቀየር ካለበት ቀኑ ሳይመሽ በብርሃኑ ይሆን ዘንድ ልናሳስበው እንወዳለን። ሲሆን ዘንድሮ፤ ካልሆነም በቀጣዩ ዓመት፤ ቢረዝም፤ ቢረዝም አንድ ቀን ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተ ክርስቲያኒቱ ጉያ እንደመዥገር የተጣበቀበት ቀን እንደሚያበቃ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ምክንያቱም ማኅበሩና ተግባሩ፤ ካህናቱና አስተዳደሩ መቼም ቢሆን አሁን ባለው መንገድ አብረው መጓዝ አይችሉምና ነው።  ከዚህ ሁሉ ፓትርያርኩም፤ ካህናቱም፤ አመራሮችም፤ መንግሥትም ይህንን ማኅበር ቦታ የማስያዙን ጉዳይ ችላ ሊሉት አይገባም። ማኅበረ ቅዱሳን ሳይኖር ቤተ ክርስቲያን ነበረች፤ ማኅበረ ቅዱሳን ሳይኖርም ትኖራለች!!!  «ማኅበረ ቅዱሳን ከሌለ ቤተ ክርስቲያን ትጠፋለች» የሚለው ራሱ ማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ነው።

Monday, March 24, 2014

አዲሱ ፓትርያርክ ብዙ ሥራ ይጠብቃቸዋል! ( በድጋሚ የቀረበ )

ይህንን ጽሁፍ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በተሾሙ ማግስት በመካነ ጦማራችን ላይ አውጥተነው ነበር፤ እነሆ አንድ ዓመት አለፈው። ከተናገርናቸውና ይፈጸሙ ዘንድ ከምንጠብቃቸው ተስፋዎች ውስጥ ምን ያህሉ ተግባራዊ ተደርጓል የሚለውን ወደኋላ መለስ ብለን ለማየት እንዲቻል ደግመን አቀረብነው። ቤተ ክርስቲያኒቱ እንደጥንቱ ዛሬም በልምድና በግምት እየተጓዘች ነው ወይስ የተሻለ የአስተዳደር ማዕከል መገንባት ችላለች? የሚለውን ጥያቄ አሁንም ማንሳታችንን አልተውንም። ከወቅቱ ሰሞነኛ ዜናዎች መካከል በማኅበረ ቅዱሳን ላይ እየቀረቡ የሚገኙት የማኅበረ ካህናቱ አቤቱታዎች (በማኅበሩ ዘንድ በጣት የሚቆጠሩ እየተባሉ ይናቃሉ) እንዲሁም ፓትርያርኩም እያመረሩ የመገኘታቸው ጉዳይ ብዙ እየተባለለት ነው። ( የፓትርያርኩ ለመታዘዝ ፈቃደኛ አለመሆንም ማኅበሩ እያናደደው ነው)  በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ማኅበሩን ቦታ ካላስያዙት የፓትርያርኩ የስራ ሂደት አስቸጋሪ እንደሚሆን የዛሬ ዓመት ጠቁመን ነበር። አጠቃላይ የመዋቅር ለውጥና የአዲስ ሕግ አወጣጥ የፓትርያርኩ አዲስ የስራ ጅማሮ እንዲሆን አሳስበን የነበረ ቢሆንም ማኅበሩ ግን ፓትርያርኩን አስቀምጦ በአባ እስጢፋኖስ በኩል ራሱ ፓትርያርክ የሆነበትን ሂደት ለመታዘብ መገደዳችንንም እንድናስታውስ አድርጎናል። ለሁሉም ሊሆን ይገባል ብለን በግላችን ያሳየንበትን ሁኔታ መታዘብ እንዲቻል ለአንባብያን በድጋሚ አቅርበናል። መልካም ንባብ!!

በዚህም ተባለ፤ በዚያ አቡነ ማትያስ ፮ኛው ፓትርያርክ ሆነው ተሹመዋል። ባለፈው ግድፈትና እውነት ላይ  እያነሳንና እየጣልን ጊዜ አናጠፋም። ይልቅስ ብዙዎች የታገሉለት የምርጫው ስኬት እንዳሰቡት ጥሩ የሥራ ጊዜ ይዞ ይመጣላቸው  እንደሆነ የምናይበት፤  ገሚሶቻችንም የምናያቸው የቤተ ክህነት ተግዳሮቶች የሚቀረፉበት፤ ሰናይ የአስተዳደርና መንፈሳዊ ዘመን ናፍቆታችንን ተስፋ በማድረግ እንደዚህ በፊቱ አስቀድመን አንዳንድ ነገሮችን ለማመልከት ወደድን።
የአዲሱ ፓትርያርክ አዲስ የሥራ ዘመን ቀላል እንደማይሆን ይገመታል። የተጠራቀሙ የቤተ ክህነቱ ችግሮችና ብዙ እንከኖች  ከፊታቸው ይጠብቋቸዋል። የችግሮቹ ዓይነቶች፤ ደረጃና ጥልቀት የተለያዩ እንደመሆናቸው መጠን የተለያየ ውሳኔና እርምጃንም የሚጠይቁ ናቸው። ለዚህ የተዘጋጀ የአእምሮ ዝግጁነት፤ የእውቀት በሊህነት፤ ድፍረትና ማስተዋል እንደሚጠይቁም አይጠረጠርም።  ያንን ዓይነት ሰው ከየት እናገኛለን ብለን አናሳብም። ምክንያቱም ምርጫው /ከተባለ/ ትልቅ አባት ሰጥቶናልና። ስለዚህ ወደችግሮቹ እንንደርደር።

1/ የቤተ ክህነቱ ላዕላይና ታህታይ መዋቅር ማሻሻል

የቤተ ክህነቱ ቀዳሚው ችግር ሥራና ሠራተኛ የተገናኘበት ተቋም አለመሆኑ ነው። ሥራና ሠራተኛ ካልተገናኘ ደግሞ  በየትኛውም መልኩ የቤተ ክህነቱ የሥራ አፈጻጸም «ከርሞ ጥጃ» መሆኑ አይቀርም። ሥራና ሠራተኛ ማለት ለተገቢው ሥራ ተገቢ ባለሙያ ወይም ተቀራራቢ ችሎታ ያለው ሰው ማለት ነው። እንደዚህ ባለው ሰው ላይ የተቋሙን ዓላማና ግብ በደንብ ካስጨበጡት ከችግሮቹ ብዛት አንጻር ባንድ ጊዜ ፈጽሞ ባይወገድም፤ ከየትኛውም ጊዜ የተሻለ ለውጥ ሊመጣ ይችላል። በዘመድ አዝማድ የተለጣጠፉና የተደረቱ ክፍሎችን ይዞ መቀጠል ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ ይሆናልና አሁን ያለን የሥራና ሠራተኛ አቋም የችግሩ ዋና ምንጭ ነው ባይባልም የችግሩ አካል ነውና ከጥገናዊ ለውጥ ወይም ከማስመሰል /pseudo/ የራቀ ለውጥ ያስፈልገዋል። ከአቅም በታች ለመሥራት የእድሜ ጣሪያ የገደባቸውም  በየመልኩ ቦታቸውን መያዝ  ካልቻሉ ቤተ ክህነት የዘመዳ ዘመዶች የጡረታ ተቋም ሆኖ ይቀጥላል እንጂ የሥራ ብቃት መለኪያ ስፍራ ሊሆን አይችልም። 

ሀገር አቀፍ ተቋም የሆነው ቤተ ክህነት ሀገር አቀፍ አደረጃጀት ሊኖረው የግድ ነው። ከላይ እስከታች አደረጃጀቱ መሻሻል አስፈላጊ ከሚባልበት ጊዜ ላይ ተደርሷል ብለን እናምናለን። በአንድ ወቅት በአሁኑ ሰዓት የአንበሳ አውቶቡስ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ በድሉ አሰፋ የቤተ ክህነቱን የአቅም ግንባታ ክፍል ሆነው ጥናት አቅርበው እንደነበር አስታውሳለሁ። ቤተ ክህነትና የዘመኑ ጥናት ሊግባቡ ባለመቻላቸው ቤተ ክህነትም በአሮጌ ልምዷ ስትቀጥል፤ አቶ በድሉም አሮጌው ጎዳና አላሰራ ስላላቸው ትተውት የተሻለ ቦታ ሄደዋል። ስለዚህ ቤተ ክህነትን ከአሮጌ መዋቅር ወደዘመነ ሥርዓት ለማስገባት አዲሱ ፓትርያርክ ትልቁ ሥራቸው መሆን አለበት  እንላለን። የተደረተውን በመጠገን  ላይ ካተኮሩ ግን ልባቸው ወልቆ እርጅናቸውን ከማፋጠን በስተቀር ለእርሳቸውም ይሁን ለቤተ ክህነቱ ቀጣይ አስተዳደር አንዳችም  ነገር ጠብ ሳይል ይቀጥላል ማለት ነው። ይህን ማስተካከል የአዲሱ ፓትርያርክ ፈታኝ ሥራ ነው ብለን እናስባለን።


2/  እርምጃ አወሳሰድ፤ የሥራ ብቃት መለኪያና አፈጻጸሙን የመቆጣጠሪያ ስልት፤

 ቤተክህነትን በብቃት የሚመራ ሕግ፤ መመሪያና ደንብ የለውም። ያለውንም በሥራ የሚያውል አካል አልነበረም። ነገሮች ሁሉ በልምድና በስምምነት የሚሰራበት ሆኖ ቆይቷል። ሥልጣንና ተግባር ለክቶ የሚሰጥ መመሪያ ባለመኖሩ ሥራና ኃላፊነት ተደበላልቀው በባለሥልጣን ይጣሳል፤ ወይም በመሞማዳሞድ ይሸፈናል።  መመሪያው ሕግ ሳይሆን ሹመኛው ራሱ ሕግ ሆኖ ያገለግላል። የአድርግና አታድርግ፤ የጌታና የሎሌ አስተዳደር እንጂ የ21ኛው ክ/ዘመን የተጠያቂነት አሠራር በቤተ ክህነት  የለም። ባለሥልጣናቱ ከፈለጉ ከአፈር ይቀላቅሉሃል፤ ከወደዱም ጣሪያ ላይ ይሰቅሉሃል። ሰው  የሚያድገውም  ይሁን  ድባቅ የሚመታው ተጠያቂነት በሌለው ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ቆይቷል።  ለሠራው ሥራ ብቃትና ጉድለት መለኪያ  ሚዛን የለም። ሌላው ይቅርና የፓትርያርክ የምርጫ ሕግ እንኳን ከእንከን የጸዳ ባለመሆኑ በነቶሎ ቶሎ ቤት ጥበብ  ተለክቶ የተሰፋው በቅርቡ መሆኑን ልብ ይሏል።  እንግዳነቱ ብዙ ጭቅጭቅና ክርክር ማስነሳቱም  አንዱ የቅርብ ጊዜ ትዝታ መሆኑ አይዘነጋም።  ነገም ይህ ችግር ላለመደገሙ ዋስትና የለም። ስለዚህ ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ  ወጥነት ያለው ሕግ፤ መመሪያና ደንብ ሊኖር ይገባል።  ይህንን ችግር አጥንቶ የተሻለ መፍትሄ በማምጣት ላይ አዲሱ ፓትርያርክ ትልቅ ሥራ ይጠብቃቸዋል።

3/ መንፈሳዊ ሲመት/ሹመት/ በተገቢው መለኪያ ማከናወን

ከጵጵስናው ጀምሮ እስከ እልቅና ድረስ ያለው የሲመት አሰጣጥ ሲባል እንደቆየውና እንደምናውቀው ወይ ገንዘብ ያለው፤ ወይ ዘመድ ያለው እንጂ በችሎታና በብቃት ልኬት የሚገኝ አልነበረም።  ጉልበት ስር መንበርከክን ዝቅ ሲልም ትቢያ መላስን እንደመስፈርት ሲሰራበት ቆይቷል። መከባበር ተገቢ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ትሕትናን ገንዘብ በማድረግ ያይደለ ሥጋዊ ክብርን ከመፈለግና ለሹመት ሲባል ወደአምልኮ የተቀየረ ስግደት የመስጠት ትእቢታዊ  ግብር ማላቀቅ ተገቢ ነው። ጵጵስናውንም እንደሲሞን መሰርይ ሽጡልኝ ወደሚባልበት ደረጃ ማውረድ ወይም በአማላጅና በሽማግሌ የሚረከቡት ንብረት መሆኑ መቆም አለበት።   መሪው በተመሪው የተመሠከረለት ቢሆን እንዴት ባማረ ነበር? ጳውሎስም የመከረን ይህንኑ እንድናደርግ ነበር።  ብዙ ጊዜ እንደሚታየው መሪውን ገንዘብ ይመርጥና ወደተመሪው ሕዝብ ይላካል። እዚያም እንደደረሰ መሪው ለሚመራው ሕዝብ ሳይሆን አገልጋይነቱ ለመደቡት ክፍሎች ይሆናል። ሕዝቡም በሚወርድበት የዐመጻ ሥራ የተነሳ እምነቱን እንዲጠላ፤ እንዲያፍርና እንዲሸማቀቅ ብሎም እንዲኮበልል ይገደዳል። ሕገ ወጥነት የሰለጠነበት የቤተ ክህነት ሥልጣን እንደገና መበጠር ይገባዋል።  ሕዝቡ መጣብን ሳይሆን መጣልን የሚል መንፈሳዊ መሪ ይፈልጋል። በመጡበት ተላላኪዎች እስከዛሬ መሮታል። እናም አዲሱ ፓትርያርክ ይህንን ሁሉ ችግር ተረክበው የጣፈጠ ሥራን ሊያሳዩት ይጠበቃል።  ያለፈውን ችግር ተሸክመው በምን ቸገረኝነት ይቀጥላሉ ወይስ ይህንን የሚሸከም ጀርባ የለኝም ይሉ ይሆን? እሳቸውንና ደጋፊዎቻቸውን የምንጠይቃቸው  መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ ትልቁ ፈታኝ ሥራቸው እንደሆነ ግን በበኩላችን አስምረንበት እናልፋለን።


4/  የመንፈሳዊ ሀብት ጥበቃና ልማት አንጻር፤

ቤተክህነት ጥንታዊ የመንፈሳዊ ሀብት ባለቤት ብትሆንም አሁን ያለችበት ደረጃ ግን በተገቢ ሥፍራዋ ላይ አይደለም።  ግእዝ ቋንቋ የሀገሪቱ ሀብት መሆኑ ቀርቶ ዛሬ በዱርና በበረሃ ተደብቆ የሚገኝ በመጥፋት ላይ ቅርስ ሆኗል። ይህንን ቋንቋ በሕይወት ለማቆየት የአብነት መምህራን ግሱን እያስገሰሱ፤ ቅኔውን እያስዘረፉ በጥቂቶች እጅ ብቻ የሚገኝ ቋንቋ ሀብት ከማድረግ ባሻገር የብዙዎች ለማድረግ ቤተ ክህነት አቅሟ ተሰልቧል።  ሐምቡርግ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋዎች ኢንስቲቲዩት ግእዝን ሲያስተምር የቋንቋው ባለቤት ግን ለዚህ ነገር እንግዳ ናት።  መምህራኖቹ ከውሻ ጋር እየታገሉ ከተማሩት ውጪ ቤተ ክርስቲያኒቱ በወጥ የትምህርት ሥርዓት ለማስተማር ጊዜ አላገኘችም። ወይም ጊዜውን ለመጠቀም አልፈለገችም።  ትውልዱ እንግሊዝኛ፤ ዐረቢኛና ፈረንሳይኛ ሲማር የራሱ የሆነውን ግእዝን እየፈለገ አላገኘውም። ከመንፈሳዊ ቀጣይ ልማት ውስጥ የግእዝ ቋንቋን እንደሙሉ ቋንቋ ለትውልድ ማስተላለፍ ይጠበቅባታል። ከጥቂት የአብነት መምህራን እጅ ወደ ሁሉን አቀፍ ቋንቋ እንዲቀየር በኮሌጅ ደረጃ ማስተማር ይጠበቅባታል።  ሌሎቹንም የአብነት ትምህርቶች ደረጃና ብቃት በማሻሻል ቀጣይነቱን ማረጋገጥ የቤተክህነቱ ድርሻ ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ የቴኦሎጂ ኮሌጆችም ካለው የቤተ ክርስቲያኒቱ የሰው ኃይል ብዛት ጋር ፈጽሞ እንደማይመጣጠን  ይታወቃል። ሁለት ጡት ሆኖ መቅረቱ ያሳዝናል።/እንደምን?/ ሌላው ቢቀር የላምን ጡት ቁጥር ሞልቶ የምሁራን ወተት የሚታለበው መቼ ይሆን?  እያንዳንዱ ሀገረ ስብከት የኮሌጅ ባለቤት መሆን በሚገባው ሰዓት፤ አንድም የሴሚናሪ/ ት/ቤት የሌለው መሆኑ ያስከፋል።  ጳውሎስ መንፈሳዊ ት/ቤት እንኳን ባለበት መርገጥ ከጀምረ ሦስት መንግሥታት አለፉት። ለዚያውም እስከነ ግዙፍ ችግሩ። እያንዳንዱ ሀገረ ስብከት የካህናቱን ብቃትና ችሎታ ማሳደግ  በሚገባው ወቅት በዲያቆን ቅጥርና ማባረር ጊዜውን ማጥፋቱ አሳዛኝ ነገር ነው። የአጫጭር፤ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የትምህርትና የስልጠና መስኮች መከፈት ይኖርባቸው ነበር። የእድሜአችንና የስፍራችንን  መራራቅ ቢያንስ ማቀራረብ ተገቢ ነው።

 በመንፈሳዊ ሃብት ጥበቃና ልማት አንጻር ሌላው የሚነሳው ነገር ማን እንደጻፋቸው የማይታወቁ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተምህሮ የሚጻረሩ፤ ተረት፤ ቧልት፤ ቀልድና ክህደት የሚያስፋፉ መጻሕፍትና ትምህርቶች ሁሉ በሊቃውንቱ እንዲታረሙና እንዲመረመሩ መደረግ ይገባዋል።  በተሀድሶ መጣና በመናፍቃን በላህ ዘመቻ እንከኖቻችንን ተሽከመን መዝለቅ ችግሩን ከሚያባብስ በስተቀር መፍትሄ አይሆንም። ገሚሱም ከእውቀት ማነስ የተነሳ ሲመቸው ከሚነቅፍ፤ ገሚሱም ባልዋለበት ቦታ ሊቅ ሆኖ ጠበቃና ተከራካሪ ከሚመስል ምሁራኑ የተሳሳተውን አርመው፤ የጎደለውን መልተው ሊያስተካክሉ ይገባል።  ቤተ ክህነት የማታውቀውን ጠልሰም ሁሉ በይፋ ማውገዝ ይገባታል። ዝምታ በራሱ ወዶ እንደመቀበል ይቆጠራልና።  የተሻለ የህትመትና የሚዲያ ዘመን ላይ ብንገኝም ማንም ተነስቶ እኔ ጠበቃ ነኝ በሚል ዲስኩር ኑፋቄን ሲያሰራጭ፤ ሲያሳትም፤ ሲዘፍን/ ሲዘምር?/ ቤተ ክርስቲያኒቱ ዝምታዋ አስገራሚ ሆኗል። የቤተ ክርስቲያኒቱን ስርዓትና ደንብ  የተከተለ በሚል ሽፋን መድረኳን  የርግብ ለዋጮች ገበያ ሲያስመስለው ዝምታው ያስገርማል። ይህ ሁሉ የሚሆነው ሊቃውንት ጉባዔውን ሊቃውንት ስላልመሩት ወይም ሊቃውንት መሰኘት በምንም ልኬታ እንደሆነ ትርጉሙ ጠፍቷል ማለት ነው። እነዚህን  ሁሉ ችግሮች የመለየት፤ የማስወገድና የማረም መንፈሳዊ ልማት ከአዲሱ ፓትርያርክ የሚጠበቅ ሥራ ነው።
እንደዚሁም ሁሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ያላትን ቅርስና ሀብት በአግባቡ መዝግባ፤ በዘመነ የመረጃዋ ቋት አስገብታ መያዝ ይገባታል። የፈረሰውን በመጠገን፤ ያረጀውን በማደስ ልትሰራው የሚገባት አንገብጋቢ ጉዳይ ሞልቷታል። በጉብኝትና ጎብኚ /Tour & Tourism operation / ረገድ የሰራችው ምንም ነገር የለም። በሀብቷ የሚበለጽጉት ሌሎች ናቸው። «ከሞኝ በራፍ፤ ይቆረጣል እርፍ» እንዲሉ አስጎብኚዎች በቤተ ክርስቲያኒቱ ስንፍና፤ ጉብዝናቸውን በቤቷ ውስጥ እያሳዩ ያሉት ያተርፉባታል ። ስለሆነም በመንፈሳዊ ሀብት ልማትና ጥበቃ አዲሱ ፓትርያርክ ብዙ ይጠበቅባቸዋል።

5/ ማኅበራዊ ልማትና እንቅስቃሴ

ከኋላዋ የመጡ አብያተ እምነቶች በተሻለ ደረጃ በሕብረተሰብና በመንግሥታዊ የልማት ተሳትፎ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ አላቸው። እያንዳንዷን የምጽዋት ገንዘብ በልማትና ልማቱን ተከትሎ በሚደረገው ስብከት ላይ ያውላሉ። የቤተ ክህነት ሙዳየ ምጽዋት ግን ሌላ የልማት ገቢ ስለሌለ የካህናት ደመወዝ ከመሆን ወጥቶ የሕብረተሰብ ልማት ላይ መዋል አልቻለም። ለኃጢአት ማስተስረያ የሚሰጥ ገንዘብ ተመልሶ ሕይወት ወዳለው ልማት የመዋል እድል አላገኘም። አድባራትና ገዳማት በልማት ሥራ ላይ ጉልበታቸውን እንዲያውሉ ማስቻልና  ይህንንም በገንዘብና በሙያ ቤተ ክህነት ማገዝ ሲገባት የልመና ደብዳቤ በመስጠት ወደጎዳና ትልካቸዋለች። በየአድባራቱ የልማት ክፍል እንዲስፋፋ የገንዘብ ዘረፋንና ብክነትን መቆጣጠር መቻል በራሱ ልማት ነበር። ይሁን እንጂ ያንን ገንዘብ ወደተሻለ  ልማት ማዋል በሚል ሰበብ  ገንዘብ የሚዘረፍበት ዘዴ ሆኖ ቆይቷል። ይህንን ማስቆም ካልተቻለ አዲሱ ፓትርያርክ ስኬታማ እንዳይሆኑ ያደርጋቸዋል። መራጮቻቸውንም በመምረጣቸው መመካት የማይችሉ ድኩማን ሆነው ያፍራሉ። ስለዚህም ሁሉም ወገን የሚጠብቀው ልማት በሰው ኃይል ብቻ ሳይሆን በገንዘብ አጠቃቀም፤ በማኅበራዊ እንቅስቃሴ፤ በሕብረተሰብ አቀፍ ልማት ውስጥ ተሳትፎ ማድረግን ያጠቃልላል። እነአቡነ ቴዎፍሎስ ያስገነቡትን ህንጻዎች እያከራዩ የጳጳሳት ደመወዝ በየሁለት ዓመቱ መጨመር ሳይሆን በየሁለት ዓመቱ ደመወዝ የሚያስጨምር ልማት ሰርቶ ማስረከብ ይጠበቃል። የተሻለ ደመወዝና ሥራ ፍለጋ የሚጎርፈው ቄስና አባ የትየለሌ ነው። ቤተ ክህነት ሁሉንም ማርካት የሚችል ቅጥር በመፈጸም ጊዜዋን ማጥፋት የለባትም። ሥራ በመፍጠር የተጨማሪ ባለሙያ ባለቤት ማድረግም ትችላለች። አድባራት /በተለይም/ አዲስ አበባ የቅጥር ሁኔታ ሞልቶ ወደመፍሰስ/ saturated/ ወደ መሆን ደረጃ ደርሷል። ካህን ሁሉ የግድ መቀደስ ወይም ማኅሌት ብቻ ካልቆመ መኖር አይችልም የሚል ህግ የለም። ስለዚህ በልዩ ልዩ ሙያ ማሰልጠን፤ ትርፋማ ልማትን መፍጠር ይጠበቅባታል። በመቅጠርና በማዘዋወር ዘመኗን መፈጸም የለባትም።

በሌላ መልኩም ቤተ ክህነት  እመራዋለሁ በምትለው ሕዝብ ውስጥ በጤና፤ በአካባቢ ጥበቃ፤ በንጹህ የመጠጥ ውሃ፤ ወዘተ ልማት ውስጥ መኖሯን ማሳየት አለባት።  የአባልነት መዋጮ እያለች  ከተከታዮቿ ላይ በፐርሰንት መልቀም ብቻ ሳይሆን  የተለቀመውን ገንዘብ መልሳ በልማት ውስጥ ለተከታዮቿ ማፍሰስ ይገባታል።  የቤተ ክህነቱ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በስሩ እስካሉት መምሪያዎች ጭምር ባለፉት ዓመታት ያልተወራረደ የእርዳታ ገንዘብ ተሸክሞ መቆየቱ ይነገራል። ቀጣዩ የልማት ኮሚሽኑ የቡድን ተሿሚው አባት ይህንን ያብሱት ይሆን ወይስ ያርሙት?  ጊዜው ሲደርስ የምናየው ሆኖ ለአሁኑ ግን አዲሱ ፓትርያርክ ቀጣይ ብዙ ሥራ እንደሚጠብቃቸው እንጠቁማለን።

5/  ማኅበራት፤ ቡድኖችና ግለሰቦች እንደ ቅልጥም ሰባሪ አሞራ ማኮብኮባቸውን ማስቆም፤

ቤተ ክህነት ከቅዱስ ሲኖዶስ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ድረስ አንድ ወጥ መዋቅር አላት።  በዚህ መዋቅር ውስጥ ሥፍራ የሌለው ነገር ግን የሚጠጋበትን ጥግ እየቀደዱ ወይም እየቦረቦሩ ባዘጋጁለት ቦታ ሆኖ በእንቅስቃሴው፤ ቤተ ክርስቲያኗን አክሎ፤ እሷን መስሎ የራሱን  የሀገረ ስብከት ተቋም በሀገር ውስጥና በውጪው ያደራጀው ራሱን «ማኅበረ ቅዱሳን» እያለ የሚጠራውን ክፍል አዲሱ ፓትርያርክ ተገቢውን ቦታ ሊሰጡት ይገባል። በሲኖዶሱ፤ በሀገረ ስብከቱ፤ በአድባራትና ገዳማቱ ሁሉ ያልታጠበ እጁን እያስገባ መቀጠል የለበትም። ሰንበት ተማሪ ነኝ የሚል ከሆነም የሰንበት ተማሪዎችን ሕግና ደንብ አጥብቆ የሚይዝበት ምክር ሊሰጠው ተገቢ ነው። ራሴን የቻልኩ ማኅበር ነኝ ካለም ራሱን የቻለ ተቋም ሆኖ  ይኑር እንጂ ከቤተ ክህነት ጀርባ ላይ እንደትኋን ተጣብቆ ሲመቸው አዛዥና ናዛዥ፤ ሳይመቸው ደግሞ ትሁት መስሎ ነጣላውን እያጣፋ ከበሮ መደብደቡን ያቁም።  ከእሱ ጋር ሲነፍስ የሚነፍሱ ጳጳሳትም ያሉበትን ተቋምና ደረጃ እንጂ የቡድን ዋሻ አድርገው መጠቀማቸውን ማቆም አለባቸው። ይህ ሃሳብ የብዙዎች ሃሳብ ስለሆነ እንደቀላል ነገር መታየት የለበትም። ከሁሉም በላይ የአዲሱ ፓትርያርክ የሥራ እንቅፋት አንዱ ይኸው በቅዱሳን ስም የተሰባሰበው ማኅበር ነው። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቤተ ክህነቱን የወረሩ የቀን ጅቦችና ወሮ በሎች የቤተ ክህነቱን ዓርማና መለያ ለብሰው በጨዋ ደንብ ተቀምጠዋል። እነዚህም ቤተ ክህነቱን እንደቅንቅን የበሉ ምንደኞች ቦታ ቦታቸውን መያዝ ይገባቸዋል። ትዳር አልሆን ያላቸው፤ እድሜአቸውን ለንስሐ ያልተጠቀሙ አሞራዎችም ሲኖዶስን እስከመበጥበጥ ልምድና ችሎታ ያላቸው ስለሆኑ ከአዲሱ ፓትርያርክ ጋር ክንፋቸውን እያማቱ ሰላማዊ ርግብ ለመመስል መሞከራቸው አይቀርምና ለእንደዚህ ዓይነቶቹም ቤተ ክህነት ሥፍራ እንደሌላት ማሳየት የአዲሱ ፓትርያርክ ሌላው ፈታኝ ሥራ ነው። እንዳለፈው  ሁሉ አዲሱም ተመሳሳይ ድርጊትን ካራመዱ  ራስን ወደእሳት ውስጥ ማስገባት ይሆንባቸዋል። እኛም ብለን ነበር፤ የሚሰማን ጠፋ እንጂ ማለታችንን አንተውም።  ችግሮች ተባባሱ ከማለት ይልቅ መፍትሄ አገኙ የሚል የምስራች የምናወራ እንድንሆን እንሻለን።  አሁንም የሦስት ረድፍ ቡድኖች ይታዩናል። ራሳቸውን አሸዋ ውስጥ ከተው የተደበቁ ቢመስሉም ዓመላቸው ስለማያስችላቸው ብቅ ብለው በቅርቡ ቦታ ቦታቸውን ሲይዙ እናገኛቸዋለን።   የሆኖ ሆኖ  ቤተ ክርስቲያኗን ብቻ ማዕከል አድርገው የመሥራት ድርሻው በአዲሱ ፓትርያርክ ጫንቃ ላይ ወድቋል።

6/ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጋር ኅብረትና ስምምነት ማድረግ

ይህንን ሁሉ ሥራ ለመሥራት የሲኖዶሱ ኅብረትና ስምምነት አስፈላጊ ስለመሆኑ ምንም ጥርጣሬ የለንም። አንዱን በማቅረብና ሌላውን በማራቅ የሚሰራ ሥራ ውጤታማ አይሆንም። በሁሉ ነገር ነገር ሙሉ ስምምነት መኖር ባይችል እንኳን ሰፊ ውይይትና አብላጫ ድምጽ መኖሩ በራሱ እንደሙሉ ስምምነት ያስቆጥራልና ይህንን ማዳበር ካለፉት የሲኖዶስ ጉባዔዎች እንደተሻለ ተሞክሮ መጠቀም ተገቢ ነው እንላለን። መከፋፈል፤ መምታት፤ መነጠል፤ ማሳደም፤ መግፋት የመሳሰሉት ከዚህ በፊት ተሞክረው የትም አላደረሱምና ከዚህ ዓይነቱ ጥቃቅን የሚመስል ግን አደገኛ አካሄድ መጠበቅ ይበጃልም ጥቆማችን ነው። ሥልጣንን ሰብስቦ ሳይሆን በየደረጃው ከፋፍሎ  ነገር ግን አስረክቦ ያይደለ ጠብቆ የመሥራት ጥበብ ጠቃሚ ነው።  ወደታች ወርዶ ቄስ እስከመቅጠርና እስከማዛወር መሄድ ግን የፓትርያርክ አንባ ገነንነት መገለጫ ነው። አሞራዎች  ማንዣበባቸው የፍቅራቸው ጥግ ሰማይ ስለደረሰ ሳይሆን የሹመት ጥንብ የት እንዳለ ለማየት ሲሉ እንደሆነ ወደ ላይ መሰቀላቸውን ማጤን ይገባል።  ጣል ጣል ይደረግልን ማለታቸው እንደማይቀር ከዓመላቸው ተነስተን ብንገምት ግምታችን ከእውነታው የራቀ አይደለም። ይህንን ይፈልጋሉና አዲሱ ፓትርያርክ በቅጥር ላይ ተጠምደው እጃቸውን ማድከም የለባቸውም።  መንፈሳዊ የተባለው ሥልጣን ወዳጅ መጥቀሚያ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኗን ችግር መፍቻ ማድረጉ ይበጃል። የቀድሞውን በነቀፉበት አፍ ራስን እዚያው ውስጥ ማስገባት በሰውም ያስተዛዝባል፤ ፈጣሪንም ያስቀይማል።  ቢሞቱ ምን የመሰለ አባት ሞተብን እንጂ እንኳንም ተቀሰፈልን ከሚል ክፉ ስም ለመጠበቅ ቢያንስ ራስንና የተናገሩትን ቃል መጠበቅ መልካም ነው።  ጠቢቡ በመጽሐፉ «ከመልካም ሽቱ መልካም ስም፥ ከመወለድ ቀንም የሞት ቀን ይሻላል» እንዳለው።  በተቻለ መጠን ከመልካም ሽቱ ለተሻለው መልካም ስም መሥራት ብልኅነት ነው።  ስለዚህ ከሲኖዶስ አባላት ጋር ተስማምቶ መሥራት ለሁለንተናዊ የቤተ ክርስቲያን እድገት ጠቃሚ መሆኑን እየገለጽን ሲኖዶሱን ለመጠምዘዝ ወይም ለማሽከርከር የሚፈልጉ ሰንጎ ያዢዎችንም  እያስታገሱ  መጓዝ ተገቢ መሆኑንም ሳንዘነጋ ነው።

7/ አቤቱታዎችን፤ እሮሮዎችንና  ጩኸቶችን መስማት መቻል፤

ቤተ ክህነት የእሮሮና የአቤቱታ ፋብሪካ መሆኗ ይታወቃል። በአንድ ወቅት ምሬት ያንገሸገሸው የልጆች አባት፤ አንዱን ጳጳስ በሽጉጥ እስከማስፈራራትና አንዱን ሹም  እስከ መግደል ያደረሰው ጉዳይ ምሬትና እሮሮን የሚሰማ ሰው በመጥፋቱ የተነሳ ነው። ይህ እሮሮና የምሬት ጩኸት እስከዛሬም ከቤተ ክህነቱ ግቢ አላባራም። የቤተ ክህነቱ ቢሮ ይዘጋል። ባለሥልጣኑ ጩኸት አልሰማ  ይላል። በዘመድ ወይም በገንዘብ ድምጹ የሚታፈን ወገን ብዙ ነው።  ልቅሶ እና ወይኔን ይዞ እንዲመለስ ይደረጋል። የፓትርያርክ ቢሮ ለመድረስማ እንዴት ይታሰባል? መንግሥተ ሰማይ በእምነትና በጥቂት ሥራ መግባት ሲቻል ለመንበረ ፓትርያርክ በር ግን እምነትና ምግባር ዋጋ የላቸውም። በእነሱ ፋንታ ገንዘብና ዘመድ በሩን ሁሉ ከፍተው ደንበኛቸውን ይጋብዛሉ። ይህ አባባል የሚያቅለሸልሽ ቢሆንም የተገለጠ እውነት ነው። አዲሱ ፓትርያርክ ከዚህ ጋር ብዙ ትግል ይጠብቃቸዋል። የእሳቸው ቢሮም  ወፍ እንዳያሾልክ ተደርጎ ካልተጠረቀመ በስተቀር ቤተ ክህነት በአቤቱታና በመብት ጥሰት እሮሮ ከመሞላቱ የተነሳ  ባለጉዳይን እንዴት እንደሚያስተናግዱ ስናስበው ግራ ይገባናል።  ከላይ እስከታች ድረስ የአቤቱታ አቀራረብና የመፍትሄ አሰጣጥ መንገድ ካልተዘረጋ በስተቀር አዲሱ ፓትርያርክም ያለፈውን ደግመው በአዳራሻቸው ጥቂት ወፋፍራሞችንና ጉንጫቸው ሊፈነዳ የደረሰውን ብቻ የሚያስተናግዱ የዘመነኞች ፓትርያርክ ሆነው እንዳይቀሩ እንሰጋለን።
ፍርድ የመስጠት ሥልጣኑ የነበራት ቤተ ክህነት በፍርደ ገምድል ሰዎች በመሞላቷ ከደረጃው የወረደ፤ ከሥራ የተባረረ፤ እድገት የተከለከለ፤ ደመወዙን የተቀማ፤ በሀሰት ምስክሮች ወህኒ የማቀቀ ብዙዎች እንዳሉ እናውቃለን። ከዘበኛው ጀምሮ በየደረጃው ባለጉዳይን እንደ ልጅነት ልምሻ በሽታ የሚያማቅቅ ሞልቷል።   ለዓመታት የተከማቸውን ችግር ባንድ ሌሊት ማስወገድ እንደማይቻል ቢታወቅም ችግሩ የት እንዳለ አውቆ ለማስተካከል መነሳቱ በራሱ የፍጻሜው መጀመሪያ ነውና በዚህ ዙሪያ ብዙ እንጠብቃለን። በየፍርድ ቤቱ የቤተ ክህነት የክስ ፋይል እና በየከርቸሌው የቤተ ክህነት ተያያዥ ሰዎች ውሳኔ ዓለማውያኑን ሳይቀር በሚያሳፍር ደረጃ ላይ መገኘቱም የአደባባይ ሐቅ ነው። ይህንን ሁሉ የቆየ እንቅፋት ለማስወገድ አዲሱ ፓትርያርክ ረጅም መንገድ ይጠብቃቸዋል።

የከተማ አወደልዳዩን እና በባህል መድኃኒት ሰበብ በየሰፈሩ ያለውንና  በቤተክህነቱ ዓርማ  የሚዘርፈውን አጭልግ ሁሉ አንድ ፈር ማስያዝ የወቅቱ ተግዳሮት ነው። እንደዚሁም ሁሉ የሴቶች መብት የተከበረ እንደመሆኑ መጠን በተገቢ ሙያቸው ማሰራት አግባብ መሆኑ ባይካድም ባለሙያ ካህናት ሊሰሩ የሚችሉትን ሥራ ሁሉ ምክንያቱ በታወቀና ባልታወቀ መንገድ ቤተ ክህነቱን የሴቶች ማኅበር አድርጎ መሰግሰጉም አንዱ ችግርና ሰሚ ያጣ እሮሮ ነው።  ያዝ ለቀቅና የአንድ ሰሞን ግርግር አድርጎ መተዉ የቤተ ክህነቱን ስምና ክብር ሊጠግን አይችልም። ይህ ሁሉ ውዝፍ ሥራ አዲሱን ፓትርያርክ  የሚጠብቅ ነው። ቀድሶ ማቁረብና ቡራኬ መስጠት አባታዊ ተግባር መሆኑ ባይዘነጋም በየአድባራቱ በዓላትን ጠብቆ በመሄድ ፈጣን ምላሽ የሚያሻቸውን ፋይል ጠረጴዛ ላይ እንዲወዘፍ ያደርጋልና «በሉ ተነሱ»  በሚል ቀጭን ትእዛዝ መሄድ ጠቃሚ አይደለም።  በታቀደና በተያዘ መርሐ ግብር ብቻ መመራትም እሮሮዎች እንዳይበዙ ያግዛልና ይኼም ሊታሰብበት የሚገባ ይመስለናል። 

ይህ ሁሉ የርእሰ መንበሩ ሰርቶ የማሰራት ኃላፊነት ነው። በባሌ ይሁን በቦሌ ስልጣንን በእጅ ማድረጉ ብቻ ለቤተ ክርስቲያን ምንም አይጠቅማትም። ካለፈው ተምሮ፤ ያለበትን የአሁኑን ተንትኖ የወደፊቱን የሚያይ ባለርእይ መሪ እንጂ ቤተ ክህነት የሹመኛ ችግር የለባትም። ስንወቃቀስ ሳይሆን ስንነጋገር ብቻ ነው ለችግራችን መፍትሄ ማምጣት የሚቻለው። አለበለዚያ በመጫጫህ አንድም ነገር ሳንሰራ ዘመናችን ያልፋል። እንግዲህ ቢሰራ የምንመኘው፤ ካለፉት ሂደቶች ወደዚህ የተሻገሩ ናቸው የምንላቸውን ችግሮች በጥቂቱ አንስተናል። አጠቃላይ ጥናት ቢደረግ ደግሞ የገዘፈ ነገር እንደሚኖር ይገመታል። ይህ የግል ምልከታ ነው። ከዚህ የግል ምልከታ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ይሁን በከፊል ደስ የማይላቸው ወገኖች ይኖራሉ። ደስ የማይላቸው ከራሳቸው ጥቅም አንጻር ሊሆን ይችላል ወይም ከማንም የተሻለ ጠቃሚ ርእይ አዘጋጅተው ይሆናል። እኛ ግን እያየን ስንለው የቆየነውን ፤ ያዩትም ሲሉት የኖሩትን፤  ብዙዎችም ሲሉት የደከሙበትን አጠራቅመን  በትንሹ  ማለት ያለብንን እነሆ ብለናል። ወደፊት ችግሮቹ እዚያው ሆነው ስናገኛቸው ደግሞ ዳግመኛ ብለን ነበር እንላለን።ችግሩ  ሲቀረፍ ደግሞ እሰየው ማለታችን የግድ ነው።  ችግሮቹ ካልተቀረፉም  የሁሉም ሃሳብ ወደመሆን መሻገሩ አይቀርም።  ያኔ ደግሞ አዲስ ፊት አይተን ምን አተረፍን፤ ምንስ አጎደልን? ማለታችን አይቀርም። « ለዚሁ ነው በሬዬን ያረድኩት» ማለትም ይመጣል። ከዚያ በፊት ያለንበትን እና የምንሄድበትን ማየት እስካልተቻለ ድረስ «ጉልቻ ቢለዋወጥ….» ከመሆን አይርቅም።

በስተመጨረሻም  ብዙ ሥራ ከፊታቸው ለተደቀነው ለአዲሱ ፓትርያርክ  ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ መጪው ዘመን የሰላም፤ የፍቅር፤ የአንድነት፤ የእድገትና የመንፈሳዊ ብልጽግና ዘመን እንዲሆንላቸው እንመኛለን።

Friday, March 21, 2014

የአቶ ግርማ ወንድሙ የማጭበርበር ጥምቀት የተፈቀደ አይደለም!



  

ግርማ ወንድሙ አጠምቃለሁ፤ ሰይጣንም አስወጣለሁ እያለ ማጭበርበርና ገንዘብ መዝረፍ ከጀመረ ሰነባብቷል። ማታለል በሀገሪቱ ህግ ወንጀል ቢሆንም ይህንን አታላይ የሚዳኝ ህግ እስካሁን አልተገኘም።  ከሁሉም የሚያሳዝነው ደግሞ ሊቃነ ጳጳሳቱም ከእነዚህ ዓይነቶች አጭበርባሪዎች ጋር ግንባር ፈጥረው ቤተ ክርስቲያኒቱ እመራበታለሁ ከምትለው የሥልጣነ ክህነት የአሰጣጥ ሂደት በተቃራኒው ግርማ ወንድሙ ለተባለው ነፍሰ በላ ወታደር  የቅስና ማዕርግ ሰጥተውት «ይፍታህ» እያለ ኃጢአት ሲደመሰስ እንደሚውል መዝጊያ የሚያክል መስቀል ጨብጦ እያየን ነው። ከስጋ ለባሽ መካከል ኃጢአትን የሚያስተሰርይ ቢገኝ ኖሮ የክርስቶስ ሰው መሆን ባላስፈለገም ነበር። 
  ዳሩ ግን እንኳን የሌሎችን ኃጢአት ሊያስተሰርይ ይቅርና ከማጭበርበር ዓለም ወጥቶ ራሱን መግዛት ያልቻለው ግርማ ወንድሙ መውጊያ በሚያክል የብረት መስቀል «ይፍታሽ፣ ይፍታህ» እያለ እንዲደበድብ ጳጳሳቱ ቅስና ሰጥተውታል። ጳጳሳቱ ገንዘብና የሚቀበላቸው ካገኙ እንኳን ቅስና ጵጵስናም ከመስጠት አይመለሱም። የትም ሳይማሩ የክብር ዶክተሬት ዲግሪ እንደሚሰጠው ሁሉ «ፈቀደ እግዚእ» ብለው የሰኞ ውዳሴ ማርያምን መዝለቅ ለማይችሉ ሁሉ የክብር የቅስና ማዕርግ ሲሰጥ እያየን ነው።  እስካሁን በአደባባይ የክብር የቅስና ማዕርግ እንደምትሰጥ ከቤተ ክርስቲያኒቱ በኦፊሴል ባንሰማም በተግባር ግን የማይሰራበት የክብር የቅስና ማዕርግ ይዘው ያሉ እንዳሉ እናውቃለን። ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ በዚህ መልኩ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። የሚያገለግሉበት ወይም ያገለገሉበት ደብርና ገዳም ሳይኖር ወይም ለማገልገል የሚያበቃ ሙያ ወይም ትምህርት ሳይኖራቸው ቅስናና ዲቁና አለን ብለው በእጃቸው ትላልቅ መስቀል ጨብጠው መንገድ የሚያጣብቡ ሁሉ ለወደፊቱ መለየት አለባቸው።
 ይህንን የዲቁና፤ የቅስናና ሌሎች ማዕርጋት ልክ የንግድ ፈቃድ እድሳት እንደሚደረገው የእድሳት ዘመን ተደርጎለት ማዕረጉን ከየት እንዳገኘው? የት እንደሚያገለግልበትና ምን እንደተማረ? እየተመረመረ ተገቢ ሆኖ ያልተገኘው ሁሉ እንዳጭበረበረ ተቆጥሮ ወዳቂ ካልተደረገ በየሜዳው «ቀሲስ» የሚባሉ ጩልሌዎችን አደብ ማስገዛት አይቻልም። ከእነዚህም የክብር የቅስና ማዕርግ ተሸካሚ አንዱ አቶ ግርማ ወንድሙ ነው። ሌሎቹም ቢሆኑ ሙያውና እውቀቱ እያላቸው ነገር ግን ሥነ ምግባርና ለተመደቡበት ማዕርግ የሚያበቃ ማንነት የሌላቸው ዲያቆናት፤ ቀሳውስትና መነኮሳት ከዚሁ ጋር ተያይዞ ካልታየ በስተቀር የዝቅጠትና የውርደት መለያ ሆኖ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ውድቀት አስተዋጽኦ ማድረጉ አይካድም። ምዕመናንና ምዕመናት በእንደዚህ ዓይነቶቹ ተቆጣጣሪ አልባ ባለማዕርጋት ስርዓተ አልበኝነት የተነሳ በሀፍረት ተሸማቀው  እንደሚገኙም ይታወቃል።

   ከእነዚህኞቹ አንዱ የሆነው አቶ ግርማ ወንድሙ በስመ ማጥመቅ የሚሊዮን ብሮች ባለቤት መሆኑ ሳያንስ ከዚህ ዓይነቱ ተግባር እንዲላቀቅ ቤተ ክርስቲያኒቱ ብትመክረውም ለመስማት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ( እሱ ይሁን ወዳጆቹ) ማን እንዳስጻፈው ያልታወቀ የማጥመቅ ፈቃድ አውጥተው እንደነበር አይዘነጋም። ( ደብዳቤውን ለማንበብእዚህ ይጫኑ )

  ይሁን እንጂ በአባ ገሪማ ፊርማ ቅዱስ ፓትርያርኩ የማጥመቅ ፈቃድ ሰጥተውታል የተባለበት ደብዳቤ ከቤተ ክህነቱ ደርሶ ኖሮ ሲመረመር የሀሰትና የማጭበርበር ተግባር መሆኑ በመረጋገጡ ቤተ ክህነት ይህንኑ ለማሳወቅ ተገዷል። በዚሁ መሠረት ለአቶ ግርማ ወንድሙ የማጥመቅ ሥራ ምንም ዓይነት ፈቃድ እንዳልተሰጠና ፈቃድ የተሰጠው በማስመሰል የተበተነው ወረቀት የማጭበርበር ውጤት እንጂ የቤተ ክህነቱን የፕሮቶኮል ቁጥር የያዘ እንዳይደለ በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልጿል። በአባ ገሪማ የተጻፈውን ደብዳቤ ለማንበብ  ( እዚህ ላይ ይጫኑ ) 

አቶ ግርማ ድሮም አጥማቂ አልነበረም፤ አሁንም አጥማቂነት እንዳልተፈቀደለት ተረጋግጧል።  ግርማ ወንድሙ ከእጁ በምን ዓይነት ተአምር ሊለያት በማይፈልጋት መቁጠሪያ ሰይጣናዊ አስማት የሚጠቀም አስመሳይ እንጂ አጥማቂ አይደለም። ስለዚህ አፍቃሬ ግርማ ወንድሙ የሆናችሁ ሁሉ እርማችሁን አውጡ።

 ዳሩ በማስመሰል የሚያጠምቀው ግርማ ወንድሙ ይቅርና «እኔ ጥቁሯ ድንግል ማርያም ነኝ» እያለች ስታጭበረብር የነበረችው ሴት እንኳን ብዙ ተከታዮች ማፍራቷን አይተናል፤ ከእሷ አታላይነትም የበለጠ «ጥቁሯ ድንግል ማርያም» እንደሆነች አምነው የሚከተሏት ሰዎች ያስገረመን ጉዳይ ሆኖ አልፏል። ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክትን እንጂ የወንጌልን ቃል ስለማይመረምር ለእንደዚህ ዓይነት ትንግርቶች ተጋላጭ ነው።  

«በዚያን ጊዜ ማንም እነሆ፥ ክርስቶስ ከዚህ አለ፤ ወይም ከዚያ አለ ቢላችሁ አትመኑ፤ሐሰተኞች ክርስቶሶችና ሐሰተኞች ነቢያት ይነሣሉና፥ ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳ እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ። እነሆ፥ አስቀድሜ ነገርኋችሁ»    ማቴ 24፤23-25

Saturday, March 15, 2014

«ቅዱስ ኤልያስ ይዞት የመጣውን መጽሐፍ” ቤተ ክርስቲያን እንድትቀበል ተጠየቀ»

 (ምንጭ፤አዲስ አድማስ)
መጽሐፉ ለአቡነ ማትያስና ለጠ/ሚ ኃይለማርያም እንዲደርሳቸው ተደርጓል
ደብዳቤው ለእስራኤሉ ጠ/ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታናሁ እና ለተመድ ተልኳል

       ከተፃፈ ከ2 ሺህ ዓመታት በላይ አስቆጥሯል የተባለውንና ስለ ቅዱስ ኤልያስ መምጣት ምስጢር የሚተነትነውን መጽሐፍ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተቀብላ ወደተለያዩ ቋንቋዎች በማስተርጎም ምዕመናኖችን እንድታስተምር፣ “ማህበረ ሥላሴ ዘደቂቀ ኤልያስ” ለቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በጻፈው ደብዳቤ ጠየቀ፡፡
ማህበሩ፤የመጽሐፉን ኮፒዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሣለኝ እና ለብፁዕ አቡነ ማትያስ  ህዝቡን እንዲያስተምሩበት ከሚያሳስብ ደብዳቤ ጋር መላኩን አስታውቋል፡፡
አርቲስት ጀማነሽ ሰለሞን አባል የሆነችበት ማህበረ ሥላሴ፤“ቅድስት ቤተ-ክርስቲያን ለሁለት ሺህ ዘመን ስትጠብቀው የቆየችውን ምስጢራዊ መጽሐፍ በአደራ የመረከብና ለዓለም ሁሉ የማሳወቅ ፅኑ ኃላፊነትን ይመለከታል” በሚል ርዕስ ለፓትርያርኩ፣ በግልባጭ ደግሞ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እንዲሁም ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔትናሁ እና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት በፃፈው  ደብዳቤ “ማህፈድ ብርህት ዘዲዮስቆሮስ አንበሳ” በሚል ርዕስ በግዕዝ ቋንቋ የተፃፈውን መጽሀፍ፣ የቤተ-ክርስቲያኗ ሊቃውንት ተቀብለው ምእመናኑን ስለ ቅዱስ ኤልያስ እና ትክክለኛይቱ ሰንበት እንዲያስተምሩበት አሳስቧል፡፡
ደብዳቤው ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር የተላከው ኢትዮጵያና እስራኤል በመንፈሣዊ አሰራር አንድ ስለሚሆኑበት ሁኔታ ለማመልከት ነው ያሉት የማህበሩ አመራሮች፤ለተባበሩት መንግሥታት የተላከውም መልእክቱ ለዓለም ሁሉ እንዲዳረስ ስለሚፈለግ ነው ብለዋል፡፡
ከ2 ሺህ ዓመታት በፊት እንደተፃፈ የሚነገርለት መጽሐፉ፤ ስለ ቀዳሚት ሰንበት ምንነትና ዘለዓለማዊነት በግልፅ እንደሚያብራራ እንዲሁም የኢትዮጵያና የእስራኤልን አንድነትና ትንሳኤ ምስጢር ተንትኖ እንደሚያስረዳ ተጠቁሟል፡፡
ማህበሩ በላከው መልዕክት፣ ቅዱስ ኤልያስ ከብሄረ ህያዋን ይዞት የመጣውን መጽሀፍ፣ የቤተ-ክርስቲያኒቱ ሊቃውንት እንዲመረምሩት፣ በተለያዩ ቋንቋዎች እንዲተረጎምና እንዲታተም፣ ምዕመናንም እንዲያነቡት የማድረግ ግዴታ ፓትርያርኩ እንዳለባቸው ያሳስባል፡፡ “ይህ ሳይሆን በእንቢተኝነትና በቸልታ ለዘመናት በተስፋ የተጠበቀውን ይህን መጽሀፍ እንዳይቀርብ ቢያደርጉ፣ ከብሄረ ህያዋን የመጣው ቀናኢ ነቢይ ዓለምን ሁሉ እየገሰፀ ባለበት ኃያል፣ ስልጣኑ ፅኑ ፈራጅነቱና ቁጣው የሚፈርድ መሆኑን አረጋግጠን እንነግርዎታለን” ብሏል፡፡ “ለቤተ-ክርስቲያኒቱ ሲኖዶስ እና ካህናት ጥፋትና የመጨረሻው ውድቀት ነው” ሲልም ለመፅሃፉ ትኩረት እንዲሰጥ ማህበሩ  አበክሮ አሳስቧል፡፡
በጉዳዩ ዙሪያ የፓትርያርኩን ጽ/ቤት እና የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጽ/ቤት በስልክ አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ሳይሳካ ቀርቷል፡፡

Wednesday, March 12, 2014

የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል የሰንበቴ ማኅበራት ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተወከለውን ኦዲተር የኦዲት መርኃ ግብር በመቃወም ህገወጥ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

በአዲስ አበባ የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል የሰንበቴ ማኅበራት ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተወከለውን ኦዲተር የኦዲት መርኃ ግብር በመቃወም ህገወጥ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ፡፡ በተለያየ መጥፎ ሥነ ምግባርና ድርጊት ከካቴድራሉ ሰንበት ትምህርት ቤት የተባረሩ ሁለት አባላትን ይዘው በካቴድራሉ ሁለተኛ ሰንበት ትምህርት ቤት ለማቋቋም ከጉርድ ሾላ እና አካባቢ የሰበሰቧቸው ወጣቶች ስለ ሰንበት ትምህርት ቤት አመሰራረት ግንዛቤ የሌላቸው በመሆናቸው የአዲሱ ሰንበት ትምህርት ቤት ምስረታ አልተሳካም፡፡  ቀደም ሲል የሰንበቴ ማኅበራቱ ከሀገረ ስብከቱም ሆነ ከካቴድራሉ አስተዳደር እውቅና ውጪ የሚሸጡትንና በወር እስከ 300.000.00 (ሦስት መቶ ሺህ ብር) ገቢ የሚያገኙበት የቀብር ፉካ ሽያጭ እና የአዳራሽ ኪራይ ንግድ ወይ ለቤተክህነቱ ፈሰስ እንዲያደርጉ አልያም ንግድ ፈቃድ አውጥተው ለመንግሥት ግብር እንዲከፍሉ በሀገረ ስብከቱ የቀረበውን ሐሳብ አልተቀበሉትም፡፡ እናም በመስከረም ወር 2006 ዓ.ም ከጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጁ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ፤ የቅዱ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ በተገኙበት ተመርጦ ሥራ የጀመረውን ሰበካ ጉባዔ አይመራንም፤ እነርሱ ባቀረቡት ጥቆማ መነሻነት ከመንግሥት እና ከገለልተኛ አካላት የተዋቀረው የኦዲት  ኮሚቴ እኛን (የሰንበቴ ማኅበራቱን እና እንደ አቶ ወልዴ የሺጥላ አይነት በሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ ገንዘብ ጉድለት የተገኘባቸውንና በቤተክርስቲያኑ ግቢ በቤተልሔሙ ጎን 26 ፉካ በመስራት መናፍቅ ልጆቻቸውን ወራሽ በማድረግ ሕገ ወጥ ሰነድ ያዘጋጁትን) ኦዲት ሊያደርጉ አይገባም በሚል ነጻና ገለልተኛ ቤተክርስቲያን እንመሰርታለን የሚል ፖስተር በመያዝ  እሑድ የካቲት 2 ቀን ጠዋት በቅዳሴ ሰዓት የቅዳሴ ሥነ ሥርዓቱን ለማስተጓጎል ሞክረዋል፡፡
በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የሴት ሰባኪ የሆነችውና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሕጋዊ ባሏን ጥላ   ወልዴ የሺጥላ የተባለውን የቀድሞ የህንጻ ኮሚቴ ሊቀ መንበር የወሸመችው እራሷን የዘመኑ የወንጌል አብሳሪ በመንፈስ ቅዱስ የተቀባሁ ጳውሎሳዊት ነኝ በማለት ጸሎተ ፍትሐት አያስፈልግም እኔ በፍትሀቱ ፋንታ ጸሎት አድጋለሁ አስተምራለሁ በማለት ምንፍቅና የምታስፋፋው  ቅድስት አሳልፍ ወደ ቤተክርስቲያኑ ድንጋይ እንዲወረውሩ ተሰብሳቢዎቹን ስታግባባ ነበር፡፡
ከካቴድራሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ሴት አባላትን በመተናኮልና ወሲባዊ ጥቃት በማድረስ በሕግ ተከሶ የተቀጣውና ከሰንበት ትምህርት ቤት በዚህ ቅሌት የተባረረው ሰለሞን አጥሌ የተባለው የታክሲ ሾፌርና የሰንበት ትምህርት ቤቱን ገንዘብ በተለያየ ወቅት በመውሰድ በሌብነት ወንጀል ተከሶ ከሰንበት ትምህርት ቤት የተባረረውና ዲቃላ ልጁን ደብቆ ሁለተኛ ሚስት በተክሊል ያገባው የሰለሞን አጥሌ ወያላ የሆነው ሲሳይ አፈወርቅ የተባሉት ሁለት ግለሰቦች መናፍቃንን በማሰባሰብ ሁለተኛ ሰንበት ትምህርት ቤት ለማቋቋም ያደረጉት እንቅስቃሴ አልተሳካላቸውም፡፡
ከዚህ ቀደም በዋነኛነት የሰንበቴ ማኅበራቱንና በመንግሥት ላይ ያኮረፉትን እንደነ ታዋቂውና ጨካኙ የደርግ የምስራቅ  ጎጃም ክፍለ ሀገር አስተዳዳሪና የደርጉ አባል አንሙት ክንዴን አይነት ሰዎችን በማሰባሰብ የደርግ ሥርዓተ ማኅበርን በቤተክርስቲያን ለመመስረት የሚታገለው የደርግ የስለላ ሹም የመቶ አለቃ አባቡ ታከለው በአጣዳፊ ህመም ከሰልፉ ላይ ወጥቶ ወደ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን ህመሙ ጊዜ የማይሰጥ በመሆኑ እለቱን ኦፕራሲዎን መደረጉንና እስካሁን ከሰመመን እንዳልነቃ ታውቋል፡፡
የካቴድራሉ አስተዳደር በሰንበቴ ማኅበር ስም ተደራጅተው የሚነግዱትን አንዳንድ የደርግ ጡረተኞችና የሰንበቴ አላማ ጠላ ማንቃረርና ቆሎ ማሸርደም የሚመስላቸው ሥራ ፈት አባወራዎችንና የሚገስጻቸው ያጡ ባሎቻቸው የዘነጓዋቸውን እንደነ ቅድስት አይነት መናፍቃንን በቅጡ በመቃወሙና በፍርድ ቤት በተወሰነ ቤተክርስቲያኒቱ  ባወጣችው ሕግ ሕገወጥ ንግድ እና የቦታ ወረራ በመቃወሙ በመረጃ ባልተረጋገጠ ሙስና እና ስም ማጥፋት ሆ ብለን በመጮህ  ከሰን እናስወግዳለን ከሚመጣውም ጋር በመደራደር የፉካ ንግዳችንን እንቀጥላለን በማለት  ለሀገረ ስብከቱ ቅሬታቸውን በሕጋዊ ሽፋን ቢያቀርቡም ሀገረ ስብከቱ በቦታው ያለውን ችግር በዘላቂ ሁኔታ ለመፍታት ከመንግሥትና ከገለልተኛ አካላት  የተመደበው አጣሪ ግን በተጨባጭ በደረሰው መረጃ  እና በተለያዩ ጊዜያት በሰንበቴ ማኅበራቱ በቤተክርስቲኗ የድንጋይ  መአድን ሽያጭ  ባገኙት ገንዘብ በገዟቸው የቢራ አክስዮኖች ባለቤትነት ጉዳይ እንዲሁም እነ ወልዴ የሺጥላ የህንጻ ኮሚቴ ሊቀመንበር መሆናቸውን ሽፋን በማድረግ በሌሎች አብበያተክርስቲያናት ባልተለመደ መልኩ በቤተክርስቲያኗ ግቢ መኖሪያ ቤት በመገንባት እና ለግላቸው 26 ፉካ በመገንባት ለፈጸሙት ምዝበራ ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ ኦዲት ለማድረግ በማሰብ ያዘጋጀውን የጊዜ አጠቃቀም መመሪያ በመቃወም ሰልፉን አደራጅተዋል፡፡
 ቁጥራቸው 60 የሚደርሱት እነዚሁ ሰልፈኞች ከያዟቸው መፈክሮች መካከል መንግሥትን የሚተቹ እና አመጹን በማስፋፋት ልክ በእስልምና እምነት በመስኪዶች አካባቢ እንዳለው አይነት ውጥረት ለመፍጠር ቢያስቡም ፖሊስ ደርሶ ሰልፉ እንዲበተን አድርጓል፡፡ በቅርቡ ከአሜሪካ የመጣውና የደህንነት አባል ነኝ በማለት አመጹን የሚያስተባብረው አለማየሁ ከልል  ክሰ ቢመጣ አዘጋላችኋለሁ በማለት ቃል እንደገባላቸው የሰንበቴ ማኅበራቱ አመራሮች አስታውቀዋል፡፡ በዚህ ድርጊት ውስጥ የተሳተፉት ዋናዎቹ ግለሰቦች የተለያየ ችግር ያለባቸው ሲሆኑ አንዳንዶቹ በአጫሽነት ፤ ሰካራምነት ፤ በቃሚነት የሚታወቁ እና በአካባቢ ማኅበረሰብ የእንጨት ሽበት ተብለው የተናቁ ሽማግሌዎች ናቸው፡፡ ይህን አጋጣሚ እንደ መልካም የቆጠሩት አንዳድ ፖለቲካ ኃይሎች ሰልፉን ለማጠናከርና ወደ ውጪ በመውጣት ህዝብን ቀልብ ለመሳብ ቢያስቡም ፖሊስ ግን ይህንን ሊፈቅድ አልቻለም፡፡ ከትግራይ የተመረጠ ፓትርያርክ ቤተክርስቲያኗን ሊመራ አይችልም መንግሥት እጁን ከቤተክርስቲያናችን ላይ ያንሳ ትግሬ ተወላጅ ሰራተኞች ይውጡ በማለት በዋናነት መፈክር ሲያሰሙ የዋሉት አንሙት ክንዴ፤ አስማረ ዋሴ ፤ ባዬ ባዘዘው፤ወልሴ የሺጥላ፤ አበበ ደስታ ፤ መልአከ ኃይሌ ፤ ታደሰ  ፤ ቅድስት አሳልፍ፤ ደሳለኝ ፋንታቢል፤ ወልደኢየሱስ በሻህ ፤ሙሉ በለጠ ሲሆኑ ከወጣቶቹ ደግሞ ሴሰኛው ታክሲ ሾፌር  ሰለሞን አጥሌ እና ሌባው ሲሳይ አፈወርቅ ሲሆኑ እነዚህ የግል ጥቅም ያሳወራቸውና እምነትና ፖለቲካ የተቀላቀለባቸው ግለሰቦች በፖሊስ ክስ እንደተመሰረተባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡
በሰአሊተ ምህረት ያለው የሰንበቴ አካሄድ ገና ከጅምሩ በ34ኛው አጠቃላይ መንፈሳዊ ሰበበካ ጉባዔ ታላቅ ተቃውሞ የገጠምውና ሲኖዶሱ እልባት እንዲሰጠው በተሰብሳቢዎቹ አቋም የተያዘበትቤተክርስቲያን የምትመዘበርበት መንገድ ነው፡፡ የሰንበቴ ማኅበራቱ ወደ እድርነትና እክስዮን ማኅበርነት በመለወጣቸው እና ከቀብር ፉካና ከአዳራሽ ኪራይ ያገኙትን ገቢ የቢራ አክስዮኖችን በመግዛት ከመንፈሳዊ ተግባት ውጪ የሚያውሉት ሲሆን ለረፈደበት የፖለቲካ ዓላማ ከፍተኛ ገንዘብ እንደሚያንቀሳቅሱ ማወቅ ተችሏል፡፡ የዚህ ድርጊት ዋነኛ መሪ ወልዴ የሺጥላ በኢትዮ ቴሌኮም ሲሰራ በጽዳት ሰራተኞች ላይ በፈጸመው የወሲብ ትንኮሳ በአስተዳደር ተከሶ ከቅርንጫፍሥ አስኪጅነት ወደ ሽያጭ ሰራተኛነት የወረደ ግለሰብ መሆኑ ስለርሱ የሚያውቁት ሁሉ ይመሰክራሉ፡፡
በካቴድራሉ ጉብኝት ያደረጉት ቅዱስ ፓትርያርኩ እና ብፁአን ሊቃነጳጳሳት በሰንበቴ ማኅበራ የተወረረውንና ለብዝኃኑ ጥቅም መስጠት ያለበትን ቦታ እና ግንባታ ተመልክተው ማዘናቸው ታውቋል፡፡ የደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምህረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ሰፊ የልማት ቦታና በሰንበቴ የተወረረ የቀብር ስፍራ እንዲሁም በሰንበቴ ማኅበራ ቁጥጥር ሥር የሆነ በብዙ ሚሊዮን ብር የሚገመት የድንጋይ ማእድን ሐብት እና ከ100.000 በላይ አማንያን ያሉበት ሲሆን በሰንበቴ የጥቅም ሰንሰለት የተደራጁ ከ60 የማይበልጡ ግለሰቦች ምክንያት ሰላሙን አጥቶ የቆየ ደብር ነው፡፡

Monday, March 10, 2014

ማኅበረ ቅዱሳን የፓትርያርኩን እጅ የመጠምዘዝ፤ እምቢ ካሉም የማስወገድ ትግሉን አጠናክሮ ቀጥሏል!! (ከማን ጋር ሊሰሩ ነው? » አባ ኤልሳዕ


የአሀዳዊ መዋቅር ምንጭ በሆነው ሲኖዶስ የምትተዳደር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን ምኗ ነው? 
በአንድ ወቅት ሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ «በመንግሥት ሌቦች እጃችን ታስሯል» ማለታቸው አይዘነጋም። ከትንሹ በቀቀን ካድሬ አንስቶ እስከ ትልቁ ዓሳ ነባሪ/አንበሪ/ ሹመኛ ድረስ የመዋጥ፤ የመሰልቀጥ ተግባሩን ተመልክተው «የመንግሥት ሌባ እጃችንን አስሯል» ማለታቸው ይህንን ሁሉ በአንዴ ለማስቆም አለመቻላቸውን መግለጻቸው ብቻ ሳይሆን ከስፋቱ አንጻር ለማስቆም መሞከር ውጤቱ አደገኛ ሊሆን መቻሉን ለማመልከት« እጃችን ታስሯል» በማለት የችግሩን ስር መስደድ በአጭር ዐረፍተ ነገር ለመግለጽ ሞክረዋል። እዚያ አደገኛ ደረጃ ላይ የተደረሰው ግን በአንድ ጀምበር ሳይሆን ቀስ በቀስ አንዱ አንዱን እየዋጠና እየፋፋ እንደመሆኑ መጠን እጅ ከመታሰሩ በፊት አስቀድሞ ትንሽ በትንሹ እርምጃ ቢወሰድ ኖሮ አስጊነቱ ያን ያህል ባላሳሰበ ነበር።  ስርቆት ምንጊዜም ከክፉ ሰዎች ልቡና በሚመነጭ ሃሳብ የሚፈጸም ተግባር ነው። ክፉ ሰዎች ደግሞ ሰውን ከመግደል ወደኋላ አይመለሱም። እግዚአብሔርን ማወቅ ከሰዎች ኅሊና ውስጥ ሲጠፋ ጭካኔ ይስፋፋል። እርግማን፤ ግዳይ፣ ስርቆት፤ ደም ማፍሰስ ይበዛል።
በአንድ ወቅት የእስራኤል ልጆች ኃጢአት በመብዛቱና የካህናቱ ርኩሰት መጠን ከማጣቱ የተነሳ እግዚአብሔር አዝኖ የሥራቸውን ዋጋ ይቀበሉ ዘንድ ጥፋት እንደተዘጋጀባቸው መጽሐፍ ቅዱሳችን ይነግረናል።( ሆሴዕ ምዕ 4 እና 5) ሌብነትን መዋጋት ህግን እንደማስከበር ብቻ ሳይሆን መታየት ያለበት ደም ለማፍሰስ የማይመለሱ ሰዎችን ከኅብረተሰቡ ውስጥ እንደማውጣት ይቆጠራል።
እንደዚሁ ሁሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከፓትርያርኩ ጀምሮ እስከ አጥቢያው አገልጋይ ካህን ድረስ እጃቸውን ወደኋላ አስሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እየነገደ የፈረጠመውና በመዋቅሩ የዓሳ ነባሪ ያህል የገዘፈው ማኅበረ ቅዱሳን መሠረታዊ ጥቅሙን ለማስከበር ሲል ብቻ ከዚህ በፊት ለፓትርያርኩ ይሰጥ የነበረውን የምስጋና ካባ አውልቆ እጃቸውን ወደመጠምዘዝ ተግባር መሸጋገሩን እየተመለከትን እንገኛለን። የዚህ ሁሉ ዋናው ምክንያት በጥቅሙ መስመር ላይ የሚቆም ማንም ሰው የጥቅሙ ጠላት በመሆኑ አስቀድሞ እጁን በመጠምዘዝ ወደቀድሞ አስተሳሰቡ ለመመለስ በየትኛውም መልኩ መታገል፤ ካልተቻለ ደግሞ ከቆመበት የጥቅሙ መስመር ላይ ማጥፋትና ማስወገድ የጥቅመኛ መዳረሻ ግቡ ነው። ምን ጊዜም በማግበስበስ የበለጸጉ ሰዎች ጥቅማቸውን የማያስጠብቀውን አመራር ለማስወገድ እረፍት የሌላቸው መሆኑ ታሪክ ያስተምረናል። ሰሞኑን  የማኅበረ ቅዱሳንና የተባባሪ ጳጳሳቱ ጩኸት አቶ መለስ እንዳሉት የፓትርያርኩን እጅ የመጠምዘዝና ወደኋላ በማሰር ወደቀድሞ የማኅበሩን ጥቅም የማስከበር መስመር የመመለስ ትግል ተጠናክሮ መቀጠሉን እያየን ሲሆን ችግሩ በዚህ የማይፈታ ከሆነና ከቀጠለ ፓትርያርኩን የማስወገድ እርምጃ እንደሚከተል ሳይታለም የተፈታ ነው። እንዴት ይፈጸማል? የሚለውን ወደፊት የምናየው ሆኖ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ግን ክፉ ሰዎች / ክፉ መሪዎች/ ክፉ ሀገራት/ ወዘተ ምን ጊዜም የማይስማማቸውን ከመግደል እንደማይመለሱ በእርግጠኝነት ልንናገር እንችላለን።
«ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፤ ካላሰናከሉም እንቅልፋቸው ይወገዳልና» ምሳሌ 4፤16
በዚሁ አጋጣሚ የምናሳስበው ነገር እውነተኛን የሚጠብቅ እግዚአብሔር እንደማያንቀላፋ ቢታወቅም  በተሰጠን ልቡና ራሳቸንን እንዳንጠብቅ የሚያዘናጋን ባለመሆኑ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በሚበሉት፤ በሚጠጡትና በሚለብሱት ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ማስገንዘብ እንወዳለን።  እውነት ነው! «ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ» ማቴ 10፤28 በማለት እንደተናገረው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ብቻ በሕይወታችን በማስቀደም ማገልገል እንደሚገባ እንጂ የሚያሳስበን በስጋ መሞት እንደማያስፈራን ይታወቃል።
ፓትርያርክ ማትያስ ከማኅበረ ቅዱሳን እስራት ነጻ ሰው መሆናቸውን መግለጽ በጀመሩ ማግስት፤ እስራታቸውን አምነው እንዲቀበሉ የማኅበሩ እስረኝነታቸውን ያረጋገጡ ጳጳሳት ቢቻል በምክር ሽፋን እጃቸውን እንዲሰጡ አለሳልሰው በማባበል፤ ፓትርያርኩ የአቋም ሰው በመሆን ከቀጠሉ ግፋ ሲል ደግሞ ወደፊት በማስፈራራት፤ አድማ በመምታትና በስመ ድምጽ ብልጫ የፓትርያርክነቱን ሥልጣን በመቀማት እግር ተወርች የማሰሩ ዘመቻ በእርግጥ ይቀጥላል። አባ ጳውሎስንም እንዲሁ ነበር ያዋከቡት።
ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ እንጂ የማኅበረ ቅዱሳን ፓትርያርክ የመሆን ግዴታና ውል የለባቸውም። እኛም እንደተለመደው የምንጠይቀው ነገር ቢኖር አንድና አንድ ብቻ ነው።
የአሀዳዊ መዋቅር ምንጭ በሆነው ሲኖዶስ የምትተዳደር ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን ምኗ ነው? የሲኖዶስ አባላት ጳጳሳቱ የሚያገለግሉት ለማኅበረ ቅዱሳን ወይስ ለቤተ ክርስቲያን?

Saturday, March 8, 2014

«እውነትንም ታውቃላችሁ እውነትም አርነት ያወጣችኋል» ዮሐ 8፤32


ሐዋርያቱ ጌታችንን ከጠየቁት አስደናቂ ጥያቄዎች አንዱ «የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱስ ምንድር ነው?» በማለት ያቀረቡለት ጥያቄ ነው። ከክርስቶስ ዳግም መምጣት በፊት የሚሆነውን የዓለሙን ነገር ከተናገራቸው መካከል አንዱ ደግሞ የመንግሥት ወንጌል በዓለሙ ሁሉ እንደሚሰበክ የተናገረው ይገኝበታል። ማቴ 24፤14
መንግሥተ ሰማያት የሚያስገባውና ዳኝነት የሚያሰጠው የሕግ መጽሐፍ ወንጌል በመሆኑ ማንም ቢሆን ይህንን ቃል እንዲሰማ በመጨረሻውና በክርስቶስ መምጫው መዳረሻ ላይ ወንጌል በዓለሙ ሁሉ እንደሚሰበክ የተናገረው ምልክት እነሆ በዓለሙ ሁሉ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ እየተሰበከ መገኘቱ እውነት ነው። በንግግር፤ በጽሑፍ፤ በምስል፤ በድምጽ፤ በምልክትና የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ወንጌል እየተሰበከ ይገኛል። በእርግጥ ወንጌልን የሚሰብኩ ሁሉ እውነተኞች፤ እንዲሁም ወንጌል የሰማ ሁሉ ይድናል ማለት አይደለም። የተጠሩ ብዙዎች፤ የተመረጡት ግን ጥቂቶች በመሆናቸው ለመዳንም ይሁን በፍርድ ለመውደቅ ድርሻው የእያንዳንዱ ሕይወት ከወንጌል ቃል መስማማቱ ነው። ወንጌል ሕጋችን ነው የሚሉ እነዚህ በሁለት ይመደባሉ።
1/ ወንጌል የሚናገረውን የእውነት ቃል አምነው እንደቃሉ የሚኖሩ
2/ ወንጌል የሚናገረውን የእውነት ቃል አምነው እንደራሳቸው የሚኖሩ ናቸው።
ወንጌል የሚናገረውን የእውነት ቃል አምነው እንደቃሉ የሚኖሩ በመልካም መሬት ላይ እንደተዘራ ዘር የወንጌልን ቃል አፍርተው ለብዙዎች መዳንና ወደእውነት መድረስ መንገድ የሚሆኑ ናቸው። ለዚህ አብነት ሆኖ የሚጠቀስ የመልካም መሬት ዘር ሐዋርያው ጳውሎስ ነው። ሐዋርያው መንፈሳዊ ትግሉ ምንጊዜም ሰዎች የክርስቶስ ብቻ ሆነው መልካም ፍሬ ያፈሩ ዘንድ ይተጋ ነበር።
«እንዲሁ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል፤ ለእግዚአብሔር ፍሬ እንድናፈራ፥ እናንተ ለሌላው፥ ከሙታን ለተነሣው፥ ለእርሱ ትሆኑ ዘንድ» ሮሜ 7፤4
እኛ በወንጌል አምነን በቃሉም የምንኖር ለሕግ ሞተን፤ ለክርስቶስ የሆንን የሌላ የማንም ፍሬ አይደለንም። የተክልዬም አይደለንም። የአቦዬም አይደለንም። የሚካኤልም አይደለንም። የማርያምም አይደለንም። የማንም ጻድቅ አይደለንም። የየትኛውም ቅዱሳን አይደለንም ማለት ቅዱሳንን እንደማቃለል አድርገው የሚመለከቱ አሉ። ከክርስቶስ በቀር የሞተልን፤ ከሞት የታደገንና ያዳነን ማንም የለም ማለት ነው። ጳውሎስ እንደተናገረው «ከሙታን ለተነሳው ለእሱ ትሆኑ ዘንድ» እንዳለው የእግዚአብሔር ብቻ እንደሆንን ይነግረናል። ወንጌል በክርስቶስ ብቻ ድነን የክርስቶስ እንሆን ዘንድ ሲያዘን ለቅዱሳን ያለንን ክብር የገለጽን እየመሰለን በማኅበራዊ ድረ ገጾችና በመረጃ መረቦች ላይ «እኔ የማርያም ነኝ፤ እናንተስ? እኔ የተክልዬ ነኝ፤ እናንተስ? ያለድንግል ማርያም አማላጅነት ዓለም አይድንም! የሚል ጥሪ ወንጌልን አመንን ከሚሉ ነገር ግን የወንጌል ቃል ተቃራኒ ድምጾች ይስተጋባሉ።  እውነቱን ስንነጋገር ዓለም የዳነው መቼ ነው? ዓለሙን ሁሉ ያዳነው ማነው? እግዚአብሔር አብ ዓለሙን ለማዳን አንድያ ልጁን ሲልክ የማን አማላጅነት እረፍት ስለነሳው ነው?
በጣም አሳዛኝና ወንጌልን የሚጻረር ድምጽ እየሰማን እንገኛለን። ቅዱሳንን በማክበር ሽፋንና ቅዱሳን በመቀበል ከለላ «ዓለም ያለቅዱሳኑ አማላጅነት አይድንም» ማለት ፈጽሞ ክህደት ነው ።  የእግዚአብሔር ፍርዱን ማን ሊመረምር ይችላል? ጳውሎስ እንዳለው።
«የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም።የጌታን ልብ ያወቀው ማን ነው?ወይስ አማካሪው ማን ነበር? ወይስ ብድራቱን ይመልስ ዘንድ ለእርሱ አስቀድሞ የሰጠው ማን ነው?ሁሉ ከእርሱና በእርሱ ለእርሱም ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን» ሮሜ 11፤33-36
ወንጌልን አምነው ነገር ግን  እንደራሳቸው ቃል የሚኖሩት ደግሞ የራሳቸው የሆነ ፍሬ አላቸው። ፍሬአቸው ከወንጌል ቃል ጋር ፈጽሞ አይስማማም።  ለአብነትም ይህንን እውነት ከታችኛው ምስለ ድምጽ በማስረጃ ያመሳክሩ!!







Monday, March 3, 2014

ግብፅ ስትደነፋ መለስ ዜናዊ ናፈቁኝ!! When I hear Egypt's Rhetoric over Nile, I miss Meles Zenawi


ፎቶ፦ ናሳ ሳተላይት    
  ጽሁፍ በአማኑኤል ዊንታ
በሌሊት የተነሱ የግብፅ የሳተላይት ፎቶዎችን በአትኩሮት ብታዩ ፍንትው ያለና የማያወላዳ እውነትን ይጋፈጣሉ ከታላቁ የአስዋን ግድብ በካይሮ አድርጐ እስከ ሜዲትራንያን ባህር ድረስ 84 ሚሊዮን የሚጠጋው አጠቃላይ የግብፅ ህዝብ በጣም በሚገርም ሁኔታ የአባይን ዳር ለዳር ተጠግቶ ይኖራል፡፡ ይህም ግብፅን በአለም ላይ ካሉ ሀገራት ሁሉ እራሷን ሙሉ በሙሉ ለጥፋት አደጋ ያመቻቸች ብቸኛ ሐገር ያሰኛታል፡፡
ታላቁ የአስዋን ግድብ ያቋተው ውሃ የናስር ሐይቅ የሚባለውን ሰው ሰራሽ ሐይቅ ለመፍጠር ምክንያት ሆኗል፡፡ የናስር ሰው ሰራሽ ሐይቅ 547 ኪ.ሜ ርዝመት 35 ኪ.ሜ ስፋትና 110 ሜ ከፍታ አለው፡፡ ይህ የተፈጥሮ ሐይቅ ቢመታና ውሃው ቢፈስ በሰዓታት ውስጥ ግብፅ ያለምንም ጥርጥር ከጫፍ እስከ ጫፍ ተጥለቅልቃ ትጠፋለች ይህ ሳይንሳዊ ሐቅ ነው፡፡

በቅርቡ የካይሮና የአዲስ አበባ መሪዎች የተለያዩ የተካረሩ ቃላቶችን ሲወራወሩ አይተናል ሰምተናል፡፡ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ውስጤን ቆፍጠን! በሸቅ! ነደድ! የሚያደርግ ነገር ወረረኝ፡፡ አይ ወይኔ ይሄኔ ነበር የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ በኖሩልን ብዬ  የተመኘሁት በደንብ አርገው ግብፅን ያቀምሱልኝ ነበራ፡፡ አሐ እሳቸው እንዲሁ ነብሳቸውን ይማርና እንኳን የግብፅን የአሜሪካና የአውሮፓ ድንፋታንም ከቁብ አይቆጥሩት እኔ በግሌ የእሳቸው ፓርቲ አባል አይደለሁም ፓለቲካም አልወድም አባቴ ይሙት! ጀግና ናቸው እረ በጣም አዋቂም ናቸው፡፡ ናፈቁኝ ከምር ናፈቁኝ፡፡ ምን ዋጋ አለው “የማንም ልቅምቅም የሰው ልክ አያውቅም!” አለ ያገሬ ሰው፡፡ ግብፆች ደነፋብን የግብፅ ኘሬዝዳንት ሙሐመድ ሙሪሲ ለህዝባቸው የሚከተለውን ድስኩር አሰሙ፡፡
“በእውነቱ እኔ ጦርነት ይጀመር እያልኩ አይደለም ግን በእርግጠኝነት ቃል እገባላችኋለው የግብፅ የውሃ ፍላጐት በማንም በምንም አደጋ ላይ አይወድቅም! አሉ ቀጠሉናም
“የግብፅ የውሃ ፍላጐትና ደህንነት መቸም ቢሆን ጥያቄ ውስጥ አይገባም በማንም አይሞከርም እንደ ግብፅ ኘሬዝዳንትነቴ እማረጋግጥላችሁ ነገር ቢኖር ሁሉም አማራጮች ክፍት ናቸው ይተገበራሉም!” አሉ
ከዛም ቀጠሉና ተረት ተረት የሚመስለውን ግን እርር ድብን ያረገኝን ቀጣዮቹን ሁለት ንግግሮች ቀጠሉ “ግብፅ የአባይ ስጦታ ናት ካልን አባይም የግብፅ ስጦታ ነው!” በማለት ከድሮ ጀምሮ ሲባል የነበረውን አባባል በቴሌቪዥን ሕዝባቸውን ሆ አስባሉበት ቀጠሉናም ደነፉ፡፡
“የግብፃውያን ሕይወት ከአባይ ጋር ብቻ የተያያዘ ነው…. እንደ አንድ ታላቅ ህዝብ ደግሞ አንዲት ጠብታ ውሃ ከአባይ ላይ ሳትመጣ ብትቀር አማራጫችን አንድና አንድ ነው ደማችን ይፈሳል!” አሉና ፈገግ ጀነን ደንደን አሉ፡፡
እኔም እርር ድብን! ቆጣ! በስጨት! አልኩና ለማን ልተንፍሰው? ኮከቤ ደግሞ ታውረስ በሬው ነውና ለመዋጋትም፣ ይለይልን ኑ ውጡ! ለማለትም አማረኝ ግን አንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ መሆኔ ሁሉንም አገደኝ ግን ከምር አንድ ግብፃዊ መንገድ ዳር ላይ ባገኝ ያን ቀን በስሱ በቴስታ ነበር አፍንጫውን ብየ ደም እያሉ ኘሬዝዳንት ሙርሲ የደነፉበትን ደም የማየው በእውነት ምን ችግር አለው በስሱ አንድ ቴስታ ባቀምሰው? ምንም፡፡
ኘሬዝዳንት ሙርሲም ሲያጠቃልሉ “ግብፅ ሁሉንም የአባይ ተፋሰስ ሐገራት ኢትዮጵያንም ጨምሮ በወንዙ ላይ ለሚሰሩት የልማት ኘሮጀክቶች ተቃውሞ የላትም፡፡ ነገር ግን የልማት ኘሮጀክቶች የግብፅን ህጋዊም ሆነ ታሪካዊ መብቶች የሚነኩም የሚያስተጓጉሉም መሆን የለባቸውም፡፡” አሉና ፖለቲካቸውን ቦተለኩ፡፡
የግብፅ የተለያዩ ፖለቲከኞችም የሙርሲን አባባል እያነሱ እያወደሱ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብቅ እያሉ እንዳውም ታላቁን የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ከፍ ሳይል ባጭር እንቅጨው የጦር እርምጃ እንውሰድበት እያሉ ቀባጠሩ፡፡
ታዲያ መለስ ዜናዊ ቢናፍቁኝ ትፈርዱብኛላችሁ? አሃ ሌሎችንማ አየናቸው እኛ ላይ ሲሏችሁ ነው እንጂ የምትደነፉት ጠላት ሲመጣማ ጭጭ ምጭጭ፡፡ ባይሆን በኢቲቪ ወጣ ብላችሁ “ግብፅ ብትደነፋም በኩርኩም ነው የምንላት!” ምናምን እያላችሁ አታፅናኑንም? ድንቄም ፖለቲከኛ! እኔ በእውነት በጣም ተሰምቶኛል ወይ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ፖለቲከኞቻችን መድረሱን ለጀግኖች ለመከላከያ ሰራዊታችን ለቀቅ አድርጉላቸውና በሚዲያችን ዛቻና ድንፋታ እንስማበትና ወንዱ! አንበሳው! እንባባል፡
እውነቱን እንነጋገር ከተባለ ይህንን ሁሉ ችግር የፈጠረው የእኛ የፖለቲከኞች ችግርና ጥበብ ማነስ ነው ግድቡ የኢህአዴግ ብቻ ይመስል ለግንቦት 20 በአል አከባበር ታላቅ ድምቀት ብላችሁ የልደት ኬክ ይመስል አባይን ቦታውን አስቀይሳችሁ በሌላ አቅጣጫ እንዲፈስ አደረጋችሁ ወይም በሳይንሳዊ አገላለፁ (Diversion) ተሰራ፡፡ ግን ይሄ መሆን ያለበት የግብፅም ሆነ ሌሎች የአባይ ተፋሰስ ሐገራት ቅድሚያ አውቀውትና ተስማምተው መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ግድቡ ሲጀመርም እኮ አብዛኞቹ ሐገራት ተስማምተዋል፡፡ መመካከር ማንን ይጐዳል? ነው ወይስ አባይን ለፖለቲካ ቅስቀሳ ጥቅም ብቻ ነው የገነባችሁት? አባይ የዚህ ወይም የዛ ፓርቲ አባል ነው የሚል ፓርቲ ካለ ከግብፅ ጐን መሰለፍ ይችላል፡፡ አባይ በተለይም ጥቁር አባይ የኢትዮጵያዊያን በሙሉ ነው፡፡ ለዛም ነው ህዝቡ በጉልበቱም በገንዘቡም ሆ ብሎ እየገነባው ያለው የሚገነባውም! እና እንደ ምክር ወይ እንደተግሳፅ ፖለቲከኞቻችን እዩትና እባካችሁ ለሐገራችን የሚጠቅመውን አድርጉ አዋቂና ጥበበኞችም ሁኑ አንብቡ ተማሩ ተመራመሩ፡፡ መለስ የናፈቁኝ አንባቢ መሪና ተመራማሪ ስለነበሩ ነው፡፡ እንደውም አሁን አሁን በየቀበሌው በየቢሮው የመለስን ራዕይ እናሳካለን እያላችሁ በለጠፋችሁት ወረቀት ስር ይህንንም የምንተገብረው እንደሳቸው በማንበብና በመፃፍ በመማርና በመመራመር ነው በሉበት፡፡ በእውነት እውነቴን ነው፡፡ እኔ ይህንን ጽሑፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ የፖለቲካ ፓርቲ አባል ወይም ስልጣን ፈላጊ ሆኘ አይደለም ሐገሬን አንድ ግብፃዊ ስነ-ህዝቡ በአደባባይ ሲዘልፋት ሰምቸ ተናድጀና ተቆጥቸ እንጅ አንድ ተራ ሰላማዊ ዜጋ ነኝ ግን እንደኔ ይህንን ስሜት የሚጋሩ ብዙ ኢትዮጵያዊያን አይጠፉምና አስቡበት፡፡
ከዚህ ቀጥሎ ግብፅ በ2011 ላይ ደርሶባት ስለነበረው የእርስ በእርስ ግጭትና የግብፅን የአሁን ሁኔታ በመላው አለም ላይ ተሰራጭቶ የተለያዩ ኤክስፐርቶች አስተያየት የሰጡበትን መረጃ በመመርኮዝ ለሐገራችን ሕዝቦች ለመንግስታችንና ለሐገር መከላከያ ሰራዊታችን አቀርባለሁ፡፡
ልብ በሉ ግብፅ በታሪኳ ብዙ ጦርነቶችን አድርጋለች ታላላቅ ጦርነቶችን ግን ተሸንፋለች፡፡ በአሁኑ ሰዓት የጦር ኃይሏ በአፍሪካ አንደኛ በአለም አስረኛ ነው፡፡ በአሜሪካ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ከሚያገኙ ሐገራት ከእስራኤል ቀጥሎ ሁለተኛ ናት፡፡ አሜሪካ የእኔ ብቻ ናቸው ሌላ ሐገራት ቴክኖሎጂውን እንዳይሸጡት በሽያጭ አላቀርባቸውም የምትላቸው የብቻዋ ቴክኖሎጂ የሆኑ የተለያዩ ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያዎች ሄልኮኘተርና ጀቶችን ጨምሮ ግብፅን አስታጥቃታለች፡፡ በአጭሩ ግብፅ በአፍሪካ ቁንጮ ላይ ከአቅሟ በላይ የታጠቀች ጉረኛ ሐገር ናት ማለት ይቻላል፡፡
በአንድ ቀላል ምሳሌ እንኳን ለማስረዳት እስራኤልን ከምድረ ገፅ አጠፋለሁ ብላ ከሶስት ሐገራት ጋር ተባብራ በታሪክ የ“6 ቀኑ ጦርነት” የሚባለውን ልትተገብር ስትነሳ፣ ገና ሳይነሱ እስራኤል አጋየቻቸው እንጅ 300 የጦር አውሮኘላኖችን ቦምብና ሚሳኤል አስታጥቃ እስራኤልን ልትወርና ልታጠፋ የሞከረች ሐገር ናት፡፡ ይህም ምን ያህል ድንፋታም ነገር ግን ጥበብ የጐደላት ሀገር መሆኗን በቀላሉ ያስረዳል፡፡
ብዙ አወራሁ ወደ ተሰራጨ ያልኳችሁ ፅሑፍ ልግባና በመፅሐፍ ቅዱስ ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ 29 እና 30 ላይ የግብፅን ቅጣት ስለሚያትተው ትንቢት የተሰራጨ አንድ ጽሑፍ ነበር ጽሑፉንም የተለያዩ ታዋቂ ሰዎች አስተያየታቸውን አስፍረውበት ነበር ከአስተያየቶቹ መካከልም አይ ይህ ትንቢት እኮ ድሮ ገና ድሮ ከእየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት በ572 ቅ.ል.ክ አካባቢ በናቡከነፃር ጊዜ ተፈፅሟል ያሉም ነበሩ፡፡ በዚህ አሁንም ድረስ እያነጋገረ ባለ ፅሑፍ ተነስተን እስኪ በደንብ ትንቢቱን በጥሞና እንየው፡፡
በደንብ መታየት ያለበት ነገር የግብፅ የቅርብ ጊዜ እርስ በእርስ መባላት በየአደባባዩ ጐራ ለይቶ መወራወር ከቱኒዚያ በተነሳው የጐዳና ላይ ግጭት ቀጥሎ የአለምን ትኩረት የሳበ ነበር፡፡ የግብፃዊያኑ አመፅ ዋናው አላማም ለ30 አመት ግብፅን አንቀጥቅጦ የገዛውን የሆስኒ ሙባረክን መንግስት መገልበጥ ነበር፡፡ በአሜሪካ መንግስትና በአንዳንድ የምዕራቡ ሐገራት ባለስልጣናት ግፊትም ሆስኒ ሙባረክ ስልጣናቸውን በፌቡራሪ 12 ቀን መልቀቂያ ጠይቀው ለግብፅ ጦር ሰራዊት አስረከቡ፡፡ ከዛ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ በግብፅ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የስልጣን ሽኩቻና ብጥብጥ ተፋፍሟል ዋናው ግፊትም ያለው ግብፅ በሐይማኖት መሪዎች የምትመራ ጠንካራና እስላማዊ ሐገር ሆና እንድትቀጥል ለማድረግ የሚደረግ ጥረት ነው፡፡
ተራማጅ እስላም በሚል መፈክር ስርም ከጀርባ ሁኖ ማርሹን በመቀያየር የሚገኘው “ሙስሊሞቹ ወንድማማቾች” (Muslim brotherhood) የሚባለው ድርጅት እንደሆነ የአደባባይ ሐቅ ነው፡፡ ቀስ በቀስም በጥበብ ቁልፍ የስልጣን ቦታዎችን እየያዘ ገና እየወጣ የሚገኝ ፓርቲ ነው ዋናው አላማውም ግብፅን ጠንካራ የሙስሊሞች ሐገር እንድትሆን ማስቻል ነው፡፡ በቅርቡ የሚታየው ሁኔታ እንደሚያመለክተውም የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ በግብፅ ጦር ውስጥ ያሉ ቁልፍ ሰዎችን እያዳከመና ወደ ፓርቲው እየቀላቀለ ስልጣኑን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ቀን ከሌት እየሰራ ይገኛል፡፡
ባጭሩ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚገልፁት በጣም የጦፈ የስልጣን መያዝ ፉክክር እንደሚደረግና የሙስሊም ወንድማማቾች ፓርቲ እንደሚያሸንፍና ተራማጅ እስላም ስልጣን ላይ እንደሚሆን ይገልፃሉ፡፡
ሙባረክ ስልጣኑን ባስረከቡ ማግስት ነው እንግዲህ እስራኤላውያን ነቃ ብለው የግብፅን ሁኔታ በጥሞና ማዳመጥ የጀመሩት የስለላ ኤክስፐርቶቻቸውንም ያሰማሩት፡፡ ምክንያቱም እ.ኤ.አ ማርች 31,1979 ጀምሮ ከ30 አመታት በላይ ያስቆጠረ የሰላም ስምምነት ከሙባረክ ጋር እስራኤል አድርጋ ነበር ሙባረክ ሲወድቅም ስምምነቱ ተቋረጠ፡፡ ባለፉት 30 አመታት ምንም እንኳ ግብፅ በጨቋኙ የሆስኒ ሙባረክ አገዛዝ ስር ብትሆንም እንኳ ግብፅ ለእስራኤል ደቡባዊ ድንበር መጋጋት የሆስኒ ሙባረክ ወታደሮች ከፍተኛ ጥበቃ ያደረጉ ነበርና ነው፡፡ ነገር ግን አሁን ያ አስተማማኝ ጥበቃ የለም ስለዚህ እስራኤል ሆየ ነቃ! ብላ ነገሩን መከታተል ጀመረች፡፡
ይህ የእስራኤል ስጋትም ሳይውል ሳያድር እውን መሆኑ ተረጋገጠ ሁለቱ በተባበሩት መንግስታት አሸባሪ ተብለው የተፈረጁትና እስራኤልን ከምድረ ገፅ ለማጥፋት ሙሉ ጊዜአቸውን ሰውተው የሚንቀሳቀሱት የአሸባሪ ቡድኖቹ የሐማስና የፋታህ መሪዎች ሳይውል ሳያድር ግብፅ ካይሮ ላይ በሚያዚያ 26 ተገናኙና ጦራቸውን አንድ በማድረግ እስራኤልን ለመዋጋት ተፈራረሙ፡፡
የአሸባሪ ቡድኑ ፋታህ ኘሬዝዳንት ሞሐመድ አባስም ንግግራቸውን አሰሙ፡፡
“እኛ ፍልስጤማውያን ከዛሬ ጀምሮ ያንን ጥቁር የልዩነት ዘመናችንን አጠናቀናል! ሐማስ የፍልስጤም ሕዝብ አባልና አካል መሆኑን አውጀናል፡፡ እንግዲህ እስራኤል ከሰፈራ ኘሮግራም ወይም ከሰላም አንዱን መምረጥ አለባት!” ሲሉ ተኮፈሱ፡፡
አሁን በእርግጠኝነት ለመናገር ከዚህ በኋላ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የሚደረግ የሰላም ስምምነት ሊኖር አይችልም፡፡ ቀዩ መስመር ይሉሐል ይሄኔ ነው! ፍልስጤም የምትባል ሐገርን ለማቋቋምና እውቅናን ለመስጠት ፋታህ እና ሐማስ መሞከራቸው አይቀሬ ነው ከዚች ቀን ደቂቃና ሰከንድ ጀምሮም ነበር እስላሞቹ ወንድማማቾችና እስራኤል አይጥና ድመት የሆኑት፡፡
እንግዲህ ቅድም የገለፅኩት የግብፃዊያን ትንቢት በትንቢተ ሕዝቅኤል ላይ ቁልጭ ብሎ ተቀምጧል ያልኩት ከፅሑፉ ተነስቸ ነው፡፡ ምክንያቱም ሕዝቅኤል በግልፅ ግብፆች የሚቀጡት ከእስራኤል ጋር አልተባበርም በማለታቸው ነው ይላል፡፡ “ግብፅ ለወደፊቱ አይቀጡ ቅጣት ነው የሚደርስባት ፍርዱም የቆሻሻ መጣያ ቦታ እስክትመስል በግብፅ ይታያል እያለ ቃል በቃል የሚከተሉትን የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ያትታል፡፡

 ሕዝቅኤል 29 (6:12)
በግብፅም የሚኖሩ ሁሉ ለእስራኤል ቤት የሸንበቆ በትር ሆነዋልና እኔ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ”
“በእጅ በያዙህ ጊዜ ተሰበርህ ጫንቃቸውንም ሁሉ አቆሰልህ በተደገፈብህ ጊዜ ተሰበርህ ወገባቸውንም ሁሉ አንቀጠቀጥህ”
“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል እነሆ ሰይፍ አመጣብሃለሁ ሰውንና እንስሳንም ከአንተ ዘንድ አጠፋለሁ፡፡”
“የግብፅ ምድር ባድማና ውድማ ትሆናለች እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ አንተ ወንዙ የእኔ ነው የሰራሁትም እኔ ነኝ ብለሀልና”
“ስለዚህ እነሆ በአንተና በወንዞችህ ላይ ነኝ የግብፅንም ምድር ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔና እስከ ኢትዮጵያ ዳርቻ ድረስ ውድማና ባድማ አደርጋታለሁ፡፡”
“የሰው እግር አያልፍበትም የእንስሳም ኮቴ አያልፍባትም እስከ 40 አመትም ድረስ ማንም አይኖርባትም፡፡”
“ባድማም በሆኑ ምድሮች መካከል የግብፅን ምድር ባድማ አደርጋታለሁ ባፈረሱትም ከተሞች መካከል ከተሞችዋ 40 አመት ፈርሰው ይቀመጣሉ ግብፃውያንንም ወደ አህዛብ እበትናቸዋለሁ በአገሮችም እዘራቸዋለሁ፡፡”

 በአሁኑ ሰአት ያለምንም ጥርጥር ግብፅ እስራኤልን ለማጥፋት ለብዙ አመታት ቀን ከሌሊት ሲማስኑ ከኖሩ ሙስሊም አሸባሪዎች ጋር ህብረት ፈጥራለች፡፡
ይህ የአሸባሪነት ትብብርም በቅርቡ እንደ ሰደድ እሳት መቀጣጠሉና ብዙ አሸባሪዎችን በህብረት አሰባስቦ እስላማዊ ወንድማማቾችን አሁን ጊዜው ደርሷል እስራኤል ትወረር ማስባሉ የማይቀር ሐቅ ነው፡፡
ብዙ ሰዎች ከላይ የጠቀስኩትን የሕዝቅኤል 29 ትንቢት ገና ወደፊት አለም ስትጠፋ የሚፈፀም ትንቢት ነው እንጅ አሁን ጊዜው ገና ነው እያሉ ይቃወማሉ፡፡
አንዳንዶቹ ደግሞ ትንቢቱ እኮ ድሮ ገና ድሮ በባሊሎናዊያን ጊዜ ተፈፅሟል ይላሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ ልብ ያላሉት ነገር ቢኖር የሕዝቅኤል ትንቢት ስለፍፃሜው ሲተነብይ እሚያወራው ሴዌኔ ስለሚባል ቦታ የሚደርስበትን የወደፊት መከራ ነው የሚዘረዝረው፡፡ በዛ ላይ ደግሞ ከላይ የዘረዘርኩት የመፅሐፍ ቅዱስ ቃል እንደሚያትተው ግብፅ በታሪኳ መቸም ቢሆን ለ40 አመታት ያህል ሰው የሌለባት ምድረ በዳ ሆና አታውቅም ይህም ትንቢቱ ገና ወደፊት ለመሆኑ ትልቅ ማስረጃ ነው፡፡
ለብዙ አመታት ስናምንበት የኖርነው የሕዝቅኤል ትንቢት በተፈጥሮው ቅኔያዊ ይዘቱ ያይላል፡፡ ይህንን ለማለት ያስቻለኝ ምክንያትም ሕዝቅኤል ትንቢቱን ሲፅፈው በዛ ጊዜ “የሴዌኔ ማማ” የሚባል ነገር ወይም ቦታ የለም አልነበረም እንደውም እ.ኤ.አ እስከ 1967 ጊዜ ድስ ይህ ቦታ አልተሰራም በ1967 ግን ይህ ቦታ በሚደንቅ ሁኔታ ታላቁ የአስዋን ግድብ ሆኖ ብቅ አለ፡፡ በግብፅ ደቡባዊ በኩል አባይን ተከትሎ ተገነባ፡፡ “ሴዌኔ” የሚለው ስም የመጣው ሲቭኔ ከሚለው የሒብሩ ቃል ሲሆን ትርጓሜውም “መግቢያ” ወይም “ቁልፍ” ማለት ሲሆን ይህም ስም የጥንት ግብፃውያንን መግቢያ ያመላክታል፡፡ ከደቡባዊ ግብፅ ወይም ከኢትዮጵያ ተነስቶ አንድ ሰው ወደ ግብፅ ሲገባ የሚያየውን መግቢያ ወይም ቁልፍ በግልፅ ያትታልና፡፡
በጣም ብዙና የተለያዩ ታሪካዊ መረጃዎችን ብናገላብጥ የመፅሐፍ ቅዱስ ሴዌኔ በእርግጥም አስዋን ግድብ ነው ይላሉ፡፡ ከነዚህ መረጃዎች መካከል አንዱ በ1966 እ.ኤ.አ በኬል እና ዳልሽ የተፃፈው የብሉይ ኪዳን ጥናትና አስተያየት የሚለው መፅሐፍ ይገኝበታል፡፡ ግንኙነቱንም ሲያጠናክረው በግሪኮች “ሴዌኔ ብሩዳሽ” እንደፃፈው “ሴርቱዋጅንት” ወይም የመጨረሻዋ የግብፅ ደቡባዊ ከተማ ከኩሽ ማለትም ኢትዮጵያ አቅጣጫና ጐን ናት ይላል፡፡ አሁንም ድረስ ከአባይ ምስራቃዊ ቦታዎች አካባቢ የሚታዩ ኢትዮጵያዊ የሆኑ አንዳንድ የጥንት ስልጣኔ መገለጫዎች በግብፅ ደቡባዊ አዋሳኝ ከተማ ሴርቱዋጅንት አካባቢ ይገኛሉ፡፡
የሚገርመው ነገር ኬል እና ደልሽ በ1866 የብሉይ ኪዳን ጥናትና አስተያየት ሲፅፉ አስዋን ላይ ምንም አይነት ማማ አልነበረም ሕዝቅኤል ትንቢቱን በ570 ቅ.ክ.ል በፊት ሲፅፈውም ምንም አይነት ማማ አልነበረም፡፡ እውነታው ግን ታላቁ የአስዋን ሐይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ በግብፃውያንና በራሻውያን ተሰርቶ በ1967 እ.ኤ.አ እስከሚጠናቀቅበት ቀንና ደቂቃ ጊዜ ምንም አይነት ማማ በአስዋን ላይ አልነበረም፡፡
አሁን ግን ይህ ግድብ ሲጠናቀቅ በአካባቢው ያለው ብቸኛ ማማና ወደ ላይ የተራራ ያህል ገዝፎ የሚታየው የአስዋን ግድብ እራሱ ነው፡፡ ለዛም ነው ይህ “ሴዌኔ” እየተባለ በትንቢት ሲገለፅ የነበረው ቦታ በአሁኑ ሰአት አስዋን እየተባለ የሚጠራው ቦታ መሆኑን አጋግጠናል የሚሉት፡፡ ግብፃውያኑ የራሽውያንን ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ግድባቸውን በተሳካ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ሲያጠናቅቁም ተኮፈሱና እስከ ዛሬ ድረስ የሚመፃደቁበትን አባባላቸውን ለልጅ ልጅ እንዲወረስ እያደረጉ እንደ ምሳሌያዊ አነጋገር ይጠቀሙበታል፡፡

“ወንዙ የእራሴ ነው የሰራሁትም እኔ ነኝ” ግብፃውያን

 ሕዝቅኤል 29 (2-5)
“የሰው ልጅ ሆይ ፊትህን በግብፅ ንጉስ በፈርኦን ላይ አድርግ በእርሱና በግብፅ ሁሉ ላይም ትንቢት ተናገር፡፡”
“እንዲህም በል - ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላላ በወንዞች መካከል የምትተኛና ወንዙ የእኔ ነው ለራሴም ሰርቸዋለሁ የምትል ታላቅ አዞ የግብፅ ፈርኦን ሆይ እነሆ በአንተ ላይ ነኝ፡፡”
“በመንጋጋህ መቃጥን አገባብሃለሁ የወንዞችህንም አሶች ወደ ቅርፊትህ አጣብቃለሁ ከወንዞችህም መካከል አወጣሀለሁ የወንዞችህም አሶች ሁሉ ወደ ቅርፊትህ ይጣበቃሉ፡፡
“አንተና የወንዞችህን አሶች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥላለሁ በምድርም ፊት ላይ ትወድቃለህ እንጅ አትከማችም አትሰበሰብም መብልም አድርጌ ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች ሰጥቼሃለሁ፡፡”
ትንቢቱ ዝም ብሎ በመጀመያ ሲታይ የሚመስለው ለግብፅ ንጉስ ፈርኦን ፓሮህ የተፃፈ ይመስላል ቀስ እያላችሁ በደንብ መፈተሽ ስትጀምሩ ግን ትንቢቱ የተፃፈው “በባህር ላይ ስለሚኖረው” ታላቅ አዞ መሆኑን ታውቃላችሁ፡፡
ቀጥሎም አንተና የወንዞችህ ወይም የአባይ አሳዎች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥላለሁ ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎችም መብል አደርግሃለሁ እያለ ያትታል፡፡
አባይ በየአመቱ እየተንደረደረ በከፍተኛ ሙላት ነበር ወደ ግብፅ የሚገባው ነገር ግን ግድቡ ከተሰራ በኋላ ሰጥ ለጥ ብሎ ነው ግብፅ ውስጥ የሚጓዘው በትንቢቱ እንደተገለፀው አባይን እንደገና በከፍተኛ ሙላት እያስጋለቡ በግብፅ ውስጥ ለማስጓዝ ብቸኛው መንገድ አንድ እና አንድ ብቻ ነው ግድቡን ማፍረስ፡፡
ሌላው አስደናቂ ነገር ይህ ታላቅ ግድብ የተገነባው በጣም በትልልቅ ብረቶችና ኮንክሪቶች ተጠፍጥፎ ከመሆኑ የነሳ የዘርፉ ባለሙያዎች የአስዋን ግድብ በምንም አይነት ቦምብ ቢመታ ሊፈርስ አይችልም፡፡ ከኒውክሌር ቦምብ በቀር ማለታቸው ትንቢቱን ገና ያልተፈፀመ ስለመሆኑ ያረጋግጣል፡፡ ኒውክሌር ቦምብ የአሁን ቴክኖሎጂ ነውና፡፡

 እስራኤላዊያን ጠበብቶች ምን አሉ?

በ2002 የእስራኤል የፓርላማ አባል የነበረ አቪጐር ሊበርማን የተባለ ሰው ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ይህች በየጊዜው ለእስራኤል ችግር መነሻ እየሆነች ላስቸገረችው ግብፅ የምትባል ሐር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚሆን መፍትሄ አግኝቻለሁ ብሎ ንግግሩን ያሰማው፡፡
“እስራኤል በቀላሉ ግብፅን በአንድ ኒውክሌር ቦምብ ድምጥማጧን ማጥፋት ትችላለች አለ” ልብርማን ስለ ግድቡ በደንብ ነበር ያጠናው ያሰማራቸው ረዳቶችም አስዋን ግድብ በጣም ትልቅና ግዙፍ ከመሆኑ የነሳ በተራ ቦምብ እንደማይፈርስ ተረድቶ ነበርና ኒኩሌየር ቦምብ ብቸኛ አማራጭ መሆኑን ተንትኖ አስረዳ፡፡
ሌላኛው የፓርላማ አባል ይጋል አሎን ቀጠለና ይህንን ጥሩ ዜና የምስራች ለእስራኤላዊያን በአደባባይ አበሰረ፡፡ እነዚህ ሁለት ጀግኖች አብዛኞቹ እስራኤላዊያን የሚያውቁትን ነገር ግን በውስጣቸው አምቀው የያዙትን እውነት በአደባባይ ያበሰሩ ጀግኖች አደረጋቸው፡፡ ሊበርማን ከእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እስከ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴርነት ድረስ፣ ይጋል ደግሞ ለሰባት አመታት በሚኒስቴርነት ሐገራቸውን አገልግለዋል፡፡
ሊበርማንና ይጋል እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ ግብፃውያን አንገታቸውን ደፍተው እድሜልካቸውን መፍትሄ የማያገኙለትን የቤት ስራ ሰጥተዋቸዋል፡፡
እነኚህ ሁለት እስራኤላዊያን ሲናገሩም የእስራኤል የማንነት ጥያቄ በግብፃውያን ወረራ የሚስተጓጐል ከሆነ ጨዋታው የሚሆነው እንደዛ በምትመፃደቁበት ግድባችሁ ላይ ይሆናል በማለት አስረገጡ፡፡
“በኑክሊር ቦምብ አስዋንን እናፈርሰዋለን፡፡ በውሃውም በሰዓታት ሰምጣችሁ ታልቃላችሁ አርፋችሁ ቁጭ በሉ፡፡ “ይኸው እነሱም አርፈው እስከ ዛሬ ቁጭ ብለዋል፡፡

 የሚከተሉት የማጠቃለያ የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች በመጨረሻው ቀን ላይ ያተኩራሉ ልብ ብላችሁም አስተውሉ የሴዌኔ ማማም ተጠቅሷል፡፡

 (ሕዝቅኤል 30 1፡6)
“የእግዚአብሔርም ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ የሰው ልጅ ሆይ ትንቢት ተናገር እንዲህም በል”
“ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል” ዋይ በሉ ለቀኑ ወዮ ቀኑ ቅርብ ነው የእግዚአብሔር ቀን ቅርብ ነው የደመና ቀን የአህዛብ ጊዜ ይሆናል፡፡
“ሰይፍ በግብፅ ላይ ይመጣል ሁከትም በኢትዮጵያ ይሆናል የተገደሉትም በግብፅ ውስጥ ይወድቃሉ ብዛትዋንም ይወስዳሉ መሰረቷም ይፈርሳል፡፡”
“ኢትዮጵያና ፋጥ ሎድም የደባለቀም ሕዝብ ሁሉ ኩብም ቃል ኪዳንም የገባችው ምድር ልጆች ከእነሱ ጋር በሰይፍ ይወድቃሉ፡፡”
“እግዚአብሄር እንዲህ ይላል ግብፅን የሚደግፉ ይወድቃሉ የሐይሏም ትእቢት ይወርዳል ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሴዌኔ ድረስ በእርስዋ ውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ ይላል ጌታ እግዚአብሄር፡፡”

ለዚህም ነው ግብፅ ለመኖሪያ የማትመች የተንኮለኞችና የእግዚአብሔር ቃል ተቃዋሚዎች ሐገር በመሆኗ ለ40 አመት ያህል ማንም የማይኖርባት ምድረ በዳ አደርጋታለሁ ያለው፡፡ የእግዚአብሄር ቃል በሕዝቅኤል 38 ላይ እስራኤልን ተባብረው ከሚያጠቋት የጐግ ሐይሎች ጋር ግብፅ ያልተጠቀሰችውም እኮ ስለማትኖር ነው እንጂ ብትኖርማ የመጀመያ ቋሚ ተሰላፊ ነበር እኮ የምትሆነው፡፡
በራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገር በተበከለ ውሃ የተጥለቀለችን አንድ ሐገር ለማፅዳት የሚፈጀውን ሐይልና ገንዘብ አስቡትና ምን ያህል አስቸጋሪ ነው ብላችሁ እራሳችሁን ጠይቁ፡፡ ወይም ከመጨረሻው ቀን በኋላ በእግዚአብሄርና በተከታዮቹ የሚፀዳው ቦታ ግብፅ ይሆነ ይሆናል፡፡ ማን ያውቃል? እባካችሁ ኢትዮጵያዊያን ጀግኖችም በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ነገር በሉ “ግብፅ ሆይ አርፈሽ ቁጭ በይ! በእሳት አትጫወች! ግድባችንን እንዳንሰራ ወንድ የሆነ ያስቆመናል! አለዛ በደህና ጊዜ የሰራሽውን የአስዋን ግድብ መጥፊያሽ ይሆናል! አሁን ያለው ኢትዮጵያዊ ትውልድ ከምታስቢው በላይ ነቃ ያለ ነው እንኳን ለወደፊቱ ድሮ ለሄደብን አፈርም ካሳ መጠየቁ አይቀርም” እኔስ እችን ፅፌ ትንሽ ንዴቴ ተንፈስ አለልኝ! እናንተስ?

 የምወዳትን ኢትዮጵያ እግዚአብሔር ይባርካት፡፡

                              አመሰግናለሁ፡፡

                       አማኑኤል ዊንታ

                   ባህር ዳር ሰኔ 2005