Wednesday, May 22, 2013
የጤና መረጃ ( በሰውነታችን ከመጠን ያለፈ ስኳር መከማቸት ችግር )
ጣፊያ የተባለው የሰውነታችን ክፍል ለደም ዝውውር የሚያገለግለውን ኢንሱሊን የተባለውን ንጥረ ነገር ማምረት ሳይችል ሲቀር ወደ ደም ሴል መሄድ የሚገባው ስኳር ክምችት ይፈጠራል። ከመጠን በላይ የስኳር መገኘት ችግርም «የስኳር በሽታ» ወይም /Diabetes/ ይባላል። ቁጥር 1 ተብሎ የሚጠራው የስኳር በሽታ በዘር ሊወረስ እንደሚችል ሲነገር፤ ቁጥር 2 ተብሎ የሚጠራው የስኳር ህመም ግን በአብዛኛው ከኑሮ ምቹነትና ከሰውነት እንቅስቃሴ ጉድለት የሚመጣ ነው። ሰዎች በተፈጥሮአችን በመንቀሳቀስ፤ በመውጣት፤ በመውረድ፤ ላብና ወዛችንን አንጠፍጥፈን በመስራት እንድንኖር ተደርገን ወደዚህ ምድር የመጣን ቢሆንም ኑሮአችን ምቹና ድካም በማይጠይቅ ሁኔታ ውስጥ እንድንኖር በሚያደርግ ቅንጦት ውስጥ በዕለታዊ ምግባችን ውስጥ በስብና ቅባት ክምችት የተነሳ የደም ዝውውራችንን እንዲዛነፍ እናደርገዋለን። ስለሆነም ለሰውነታችን ሥርዓተ ዑደት /metabolism/ በስራ ወይም በአካል እንቅስቃሴ እናስተካክል። ከመጠን በላይ በሆነ የሰውነት ግዝፈትና ድሎት ራሳችንን ከምንጎዳ በማጣት ሰው ለተራቡ ያለንን እናካፍል።