Wednesday, April 4, 2012

ኑሮ በአገርኛ፤ ጾም ይበዛበታል!

 በፍቄ ከአዲስ አበባ፣

ባሕር ማዶ ካሉ ሰዎችጋ ስናወራ አንዳንድ የማይገቡን ወሬዎችን እየሰማን ጭንቅላታችንን እየናጥንወቸ ጉድ!” ማለታችን አይቀሬ ነው፡፡ ለኛ ባዳ ከሆነው ከቀላሉ “GPS” ጀምሮ፣ credit card ቢሉ፣ ምን ቢሉ ሁሉም ለኛ እንቆቅልሾች ናቸው፡፡ ወጉ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ እንዲሉ “GPS” ቀርቶብኝ እበላው ባገኘሁ የሚለው እስኪታወሰን ድረስ እንደመማለን፡፡ እዚህ GPS የለም፣ credit card የለም፣ ባቡር (ወይም subway station ብሎ ቋንቋ) የለም፣ smart phone የለም፣ wi-fi የለም (አለ እንዴ?) ለነገሩ የዚህ ጫወታ ጉዳዮች እነዚህ ሁሉ ስላልሆኑ እንኳን ደስ ያላችሁ፡፡ በርግጥ ግን ወደጫወታው አጀንዳ ለመድረስ አሁንም ዳር፣ ዳሩን መነካካት የግድ ነው፡፡አሜሪካኖች ለምን ወፋፍራም ሆኑ? ኢትዮጵያውያኖች ለምን ቀጫጭን ሆኑ?› ብለን ብንጀምርስ!
ያልተመጣጠነ ውፍረት 75 በመቶ አሜሪካውያን የጤና እክል እየፈጠረ ነው፤ 75 በመቶ ኢትዮጵያውያን ደግሞ (ይህ ቁጥር በጥናት አልተረጋገጠም እንጂ፣) ችግራችን ቅጥነት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ obesity ሳይሆን በምግብ እጥረት፣ በጨጓራ ሕመም የሚሰቃዩ ሰዎችን ነው ማግኘት የሚቻለው፡፡ ለምን ብለን የጠየቅን እንደሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስልጣናቸው አፍላ ዘመን ቃል በገቡት መሠረትበቀን ሦስቴ መብላትባለመቻላችን ነው፡፡ በቀን ሦስቴ መብላት ማለት አሰሱን ገሰሱን ማግበስበስ ማለት አይደለም፡፡ በሦስተኛ ክፍል ሳይንስ ላይ እንደተማርነው የተመጣጠነ ምግብ መብላት ማለት ነው፡፡ የተመጣጠነ ምግብ ደግሞ ፕሮቲን፣ ካርቦሃይድሬት፣ ፋት፣ ቫይታሚኖችና ማዕድኖችን መያዝ አለበት፡፡

የኢትዮጵያውያንን አመጋገብ በጥቅሉ በአንድ መስመር መተረክ ይቻላል፡፡ ቁርስ፤ ዳቦ በሻይ (ሻይ ከተገኘ!) ምሳ፤ እንጀራ በሽሮ ወጥ፣ እራት፤ እንጀራ በሽሮ ወጥ፡፡ በዚህ የአመጋገብ ልምድ ውስጥ የሚካተቱት ጤፍ፣ ስንዴ፣ ባቄላ እና ውሃ ናቸው፡፡ በርግጥ በስንዴ ውስጥ ካርቦሃይድሬት፣ በጤፍ ውስጥ iron (ብረት ነክ ማዕድን) በባቄላ ውስጥ ፕሮቲን አለ፡፡ ፋት ግን ምናልባት እንደሽሮፕ በማንኪያ በምትጨመረው ዘይት ውስጥ ካልሆነ በቀር የለም፤ ስለዚህ የሚያወፍረን ምንም ነገር የለም፡፡ በምግብ ዝርዝራችን ውስጥ የሚያወፍር ነገር አለመኖሩ እሰዬው፣ ነገር ግን በሽታ የመከላከል አቅማችንን የሚያጎለብት÷ የፍራፍሬና የአትክልት dessert እንዳይኖር እርጥብ አገራችንን ያደረቃት ማነው?

የልምድ Vegetarians
ኢትዮጵያውያን የኑሮ ነገር ሁኖብን ከጥንትም ጀምሮ የምንመገበው የምግብ ዓይነት vegetarian የሚያሰኘን ነው፡፡ የጤፍና ባቄላ ድምር!!! በርግጥ ብዙዎቻችን የምግብ ምርጫችን ምን እንደሆነ ስንጠየቅ ቁርጥ ወይም ክትፎ ልንል እንችላለን፡፡ የምግብ ምርጫችን ግን አምሮታችን እንጂ÷ ‘የምናዘወትረው የምግብ ዓይነት ነውየሚል ትርጉም እንደሌለው ሁላችንም ይገባናል፡፡

ቬጂቴሪያንነትም ሆነ ቅጥነት ዕድሜን እንደሚቀጥል ምሁራኑ ይናገራሉ፤ ይሁን እንጂ የወፋፍራሞቹ አሜሪካውያን አማካይ ዕድሜ 70 ሲዘልቅ፣ የቀጫጭኖቹና የልምድ ቬጂቴሪያኖቹ ኢትዮጵያውያን ዕድሜ ግን ሃምሳ መድረስ አቅቶታል፡፡የዘመኑ ምርጫ፣ ምን እና ቀጫጫየተባለውን እውነታ አፈርድሜ አስበልቶ፣ ውፍረትን እንደምቾትና እንደጤነኝነት ባገራችን እንዲቆጠር ያደረገው ማነው?

ምግብ አጥቂውን ነው የሚያጠቃው
ይህች አባባል አገልግሎት ላይ የምትውለው ብዙ በሊታ ከሲታዎችን ለመተቸት ነው፡፡ ይሁን እንጂእውን በሊታ ከሲታዎች አሉ?› ብለን ከጠየቅን ውዥንብር ውስጥ መውደቃችን አይቀሬ ነው፡፡ አንዳንዴ አሰሱን ገሰሱን ማግበስበስ ሆድን ከመቆዘርና፣ ጨጓራን ለበሽታ ከመዳረግ ያለፈ ፋይዳ የለውም፡፡

ምግብ አጥቂውን ነው የሚያጠቃውየሚለው አባባል እንደየሃገሩ የተለያየ ትርጉም ይኖረዋል፡፡ ምንም እንኳን እኛጋ ብዙ የሚበሉት ናቸው የሚከሱት ብሎ ለመሳለቅ ቢያገለግልም፤ ወፋፍራሞቹ ዓለም ግን ብዙ መብላት ለውፍረት፤ ውፍረት ደግሞ ለበሽታ ወይም ሞት ይዳርጋል የሚል አንድምታ አለው፡፡ ዞሮ ዞሮ ምግብ አጥቂውን ነው የሚያጠቃው፡፡

እኛ አገር ግን ምግብ ይከበራል፡፡ገበታ ንጉሥ ነውነው ከነአባባሉ፡፡ ሁሉም ንጉሥ ከሚሊዮን አንድ ነው፤ ታዲያ ገበታን ከንጉሥ እኩል ምን አደረገው ብለን ስንጠይቅ መልስ ሊሆን የሚችለውገበታ በሃገራችን ከሚሊዮን አንድ ነውየሚል ይሆናል፡፡ ሌላው ዓለም በሌለ መልኩ ኢትዮጵያ ውስጥ ምግብ ከንጉሥ እኩል ይከበራል፣ ይዘፈንለታል፡፡ በዘፈን ክሊፖቻችን ሳይቀር ለእንቁልልጭ ይቀርባል፡፡ ለምን? ምግብ ብርቅ ነዋ! ምግብን ከጥንት እስከዛሬ በሃገራችን ብርቅ ሆኖ እንዲቀር ያደረገው ማነው?

Sunday, April 1, 2012

የአቡኑ ገዳም



ቡኑ ገዳም
ተራራ ወጥቼ፣ ቡኑ ዘንድ ሄጀ መስቀል ለመሳለም
ክረምቱ በረታ፣ ምንም  ልተቻለ፣ ያሰብኩት ሳይሞላ፣ ሳይሆንልኝ ቀረ
ዳመናው ዝናቡ፣ ጉምና ጭጋጉ፣ ይህ የዛሬ ክረምት መች ያነቃንቃል!
ደጁን ጨቀይቶት፣ ወንዙም ጐርፍ ሞልቶት፣ ጅጉን ስፈሪ፣ በጣም ያስጨንቃል
በታምር በፀሎት፣ ከተራራው ፋፍ፣ ከዳመናው በላይ የገደሙት ገዳም
ደካማው ጉልበቴ፣ ንደምን ይቻለው፣ ጭቃውን ሸርተቴ፣ የኖኁን ዝናም
ዛሬ፣ ነገ ያልኩ ሰማዩና ምድሩን ሳስስ ስመለከት፣ ስቃኝ ድማሱን
ዓይኖቼም ደከሙ፣ ለቀ ጉልበቴ፣ መቃብር ቁፋሮ፣ ሰርክ መማሱን!
ማለዳ-ማለዳ ደረትዋን ገልብጣ፣ ድምጿንም ከፍ ደርጋ የምትጮኸው ወፍ
የቀሰቀሰች  ንቅልፍ ነሳችኝ፣ ሽፍንፍን ብዬ፣ ተኝቼ በሰላም በደህና ንዳላርፍ!
ምድር-ዓለሙ ክዶኝ፣ ሁሉም ጥሎኝ ሄዷል፣ ጠያቂም የለኝም ከቶ ሚያጽናናኝ
ወፊቱስ የት ሄደች? ከጠፋች ቆይታለች፣ ድምጿንም ልሰማሁ፣ ንዳታዝናናኝ
ደጋግሞ የቆየ የሚነፍሰው ነፋስ ለው መጥፎ ጠባይ፣ ኃይለኛ ዙሪት
የጐጆየን ክዳን በትኖ ያነሳ፣ ምን ዓይነት ተንኮል ነው፣ ምን ዓይነት ብሪት!
መቸ ይኸ ብቻ! ሰማዩን ተርትሮ ስደንጋጭ ብልጭታ መብረቅ ሲፈነጥቅ
ከታትሎ ይሏል የሰማይ ነጐድጓድ ቤቱን ንቀጥቅጦ ጆሮ ስኪሰነጥቅ
ተራራ ልወጣህ፣ ታቡን ዘንድ ልደረስኽ፣ መስቀል ልተሳለምክ ብሎ ነው መሰለኝ
ከዚያ ላይ ስወጣ ገደል ከምገባ፣ ወድቄ ከምሞት፣ ወይም ንሸራትቶኝ ከሚሰባብረኝ
ከዚሁ ከቤቴ ካልጋዬ ተኝቼ፣ በንፋስ፣ በመብረቅ ነጉዶ ንጐዳጉዶ እንዳሻው ያድርገኝ!
                              
 ገ/ኢ ጎርፉ

ኢትዮጵያ የሥልጣኔ ምንጭ

‹የዓለም የሥልጣኔ ምንጭ ኢትዮጵያ ናት›፤ ማንስ ነው አይደለችም የሚል?

26 Mar 2012       በካሳሁን ዓለሙ
እንዳውም ‹ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ› ብላችሁ ካልተሳለቃችሁብኝ የዓለም ሥልጣኔ ምንጩ ኢትዮጵያ ናት የሚል አስተሳሰብ ከሰረፀብኝ ውሎ አድሯል፡፡ ምን ላድርግ የግብፅን የጥንት ሥልጣኔ ያጠኑ የግብፅ ጥናት ሊቆች(Egyptologists)  ‹የጥንቱ የዓለም ሥልጣኔ ከግብፅ ተነሥቶ እንደተስፋፋ ሞገቱኝ!› ተስማማሁ፡፡ ስስማማላቸው ነው መሰል ‹ግብፅ የተመሠረተችው እኮ በጥንት ኢትዮጵያውያን ነው› ብለው ማስረጃ አቀረቡ፡፡ አረ ተው ብላቸው ‹የጥንቱን ከአሁኑ ጋር እያነጻጸሩ እመን አሉኝ› እስቲ ቆይ ላስብበት ብዬ የሀገር ውስጡን ትውፊቱን፣ ተረቱንና ባህሉንና መልካችንን ‹የጥንት ግብፅ ሥልጣኔ ነው› ከተባለው ጋር ሳነጻጽር ቁርጥ የራሳችን ሆኖ አገኘሁት፡፡ ከዚያም ባሰብከው መሠረት ‹ውሳኔህ ከምን?› አሉኝ ‹አመንኩ ተጠመቅኩ› አልኳቸው፡፡ እናንተ ጥርጣሬ ይዟችሁ ‹የውሳኔ እጅህ ከምን? አስረዳ!› ብላችሁ ከላዬ ላይ አልወርድ ካለችሁ ‹ግራ ቀኙን ተመልክቼ የውሳኔዬን ማብራሪያ ላቀርብ ነው›!
መቼም እንዳልኳችሁ ዋና የማስረጃ ምንጮቻችን የጥንት ታሪክ ሊቆች ናቸው፡፡ እናንተም በእነዚህ ሊቃውንት ዘገባና ማስረጃ እንደምትስማሙ እገምታለሁ፡፡ ከዚያ ውጭ አምጣ ካችሁኝ ግን ‹እንዴት ብዬ?› ነው መልሴ፡፡ በዚህም ቢሆን መጀመሪያ ልትጠይቁ የምትችሉት ‹ለመሆኑ ዓለም አንድ የጋራ የሥልጣኔ ምጭ አላት ወይ?› የሚል ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ፡፡ ልገምት የቻልኩትም ሊቃውንቱም ይህንን ጥያቄ ስለሚያነሱት ነው፡፡ ሆኖም እነሱ በመጨረሻ የደረሱበት መደምደሚያ ‹የዓለማችን ሥልጣኔ ከአንድ የጋራ መነሻ ፈልቆ ወደ ተለያየ አቅጣጫ ፈሷል› የሚል ነው፡፡ እዚህ መደምደሚያ ላይ ለመድረስም ያስቻሏቸውን የተለያዩ ማስረጃዎችም አስቀምጠዋል፡፡ ከእነዚህ ማሰረጃዎች መካከልም የሥልጣኔ ቅሪቶች፣ የሥነ ተረት ማሳያዎችና የታሪክ ፍሰቶች ወደ አንድ አቅጣጫ በመምራት ቅድሚያውን ይይዛሉ፡፡
በሥነ ምድር ጥናት የዓለማችን ሥልጣኔ ከአንድ ከተወሰነ አካባቢ ከሚኖሩ ማኅበረሰቦች መነሣቱን ማረጋግጥ የሚያስችሉ ብዙ ማስረጃዎች ማግኘት ተችሏል፡፡ በዚህም የጥንት ዘመን ሥልጣኔ ማሳያዎች የሆኑት የሐውልት አሠራር፣ የግብርና አጀማመር፣ የአምልኮ ሥርዓት፣ የጊዜ አቆጣጠር፣ የባህል ውርርስ፣ የልምድ ድርጊት … ተመሳሳይነት የሥልጣኔ መነሻ አንድ ስለመሆኑ መስካሪዎች ሆነው ተገኝተዋል፡፡