Wednesday, March 13, 2013

እቴጌ ጣይቱ ብጡል

                                                                          (ምንጭ፤wikipedia)
                                                                      
ባለቤት             ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ
አባት    ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም
እናት    ወይዘሮ የውብዳር
የተወለዱት       ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፪ / በደብረ ታቦር
የሞቱት             የካቲት ቀን ፲፱፻፲ ..
የተቀበሩት        ታዕካ ነገሥት በዓታ /ክርስቲያን
ሀይማኖት         የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና

«ብርሃን ኢትዮጵያ» በሚል ቅፅል ስም የታወቁት እቴጌ ጣይቱ ከአባታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም እና ከእናታቸው ወይዘሮ የውብ ዳር ነሐሴ ፲፪ ቀን ፲፰፻፴፪ / በጌምድር ውስጥ ደብረ ታቦር ከተማ ተወለዱ። በየኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት መሠረት በተወለዱ ቀናቸው ጥቅምት ፳፯ ቀን ፲፰፻፴፫ / በደብረ ታቦር ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ክርስትና ተነሡ። በልጅነት ዘመናቸው በዚሁ ደብር ውስጥ ዳዊትን ሲከታተሉ ከቆዩ በኋላ በጊዜው ይሰጡ የነበሩትን ሌሎች የሃይማኖት ትምህርቶች በየታላላቁ አድባራት በመዘዋወር ያጠናቀቁ ስለመሆናቸው ታሪክ አዋቂዎች ይናገራሉ። የተማሩባቸውም መፃሕፍት ተጽፈው ይገኙ የነበረበትን የግዕዝ ቋንቋ አጣርተው ያውቁ ነበር። እናታቸው ወይዘሮ የውብዳር ከባለቤታቸው ደጃዝማች ብጡል ኃይለ ማርያም ከሞቱ በኋላ በጅሮንድ መዩ የተባሉትን የዓፄ ቴዎድሮስን ባለሟል አግብተው ነበር። እሳቸውም ጣይቱ ብጡል ትምህርት እንዲቀስሙ ለማድረግ ልዩ መምህር ቀጥረውላቸው እንደነበር ይታወቃል። እቴጌ ጣይቱ በማኅደረ ማርያም ሆነው ሲማሩና መፃሕፍትን ይቀጽሉ በነበሩበት ጊዜ ለቤተክርስቲያን መጋረጃ መሥሪያ በትርፍ ጊዜያቸው ፈትል እየፈተሉ ያቀርቡ ነበር። በበገና ቅኝትና ድርደራም በኩል የታወቁ ባለሙያ እንደነበሩ ይተረክላቸዋል።
ከንጉሥ ምኒልክ ጋር ጋብቻ
የሸዋው ንጉሥ ምኒልክ በሸዋ የዓፄ ቴዎድሮስ እንደራሴ ከነበሩት አቶ በዛብህ ጋር ነሐሴ ፲፯ ቀን ፲፰፻፶፯ / በጋዲሎ አካባቢ በተደረገው ጦርነት ድል አድርገው ወደ አንኮበር ገብተው በነሐሴ ፳፬ ቀን ነገሡ። በነገሡም በአሥራ ሁለት ዓመታቸው የፋሲካን በዓል በባሕር ዳር አቅራቢያ ሱሉልታ ላይ ዋሉና ደብረ መይ በጣይቱ ብጡል እናት በወይዘሮ የውብዳር ቤት ከጣይቱ ብጡል ጋር ተጫጭተው ስለጋብቻቸው ተነጋገሩ። ከዚያም ዋና ከተማቸው ወደነበረችው ደብረ ብርሃን ተመልሰው መጡ።
ከተጫጩ ከሁለት ዓመት በኋላ ወይዘሮ ጣይቱን ለማስመጣት በቤተ መንግሥቱ በተደረገው ምክር መሠረት አለቃ ተክለማርያም ወልደ ሚካኤል ደብዳቤ ተሰጥቷቸው ተላኩ። በዚያም አስፈላጊው ሁሉ በተፋጠነ ሁኔታ ተሟልቶ በጐጃም በኩል ደንገጡሮችና አሽከሮች አስከትለው ጉዞውን ጀመሩ። ደብረ ብርሃንም በገቡ ጊዜ ንጉሡ /ምኒልክ/ ታላቅ አቀባበል አደረጉላቸው። ከዚያም ጣይቱ ወንድማቸው ራስ ወሌ ብጡል ዘንድ ለጥቂት ዓመታት ተቀምጠው ከቆዩ በኋላ የጋብቻቸው ስነ-ሥርዓት የፋሲካ ዕለት ሚያዝያ ፳፭ ቀን ፲፰፻፸፭ / በአንኮበር መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ቁርባን ተቀብለው ተጋቡ።
አፈወርቅ ገብረ ጊዮርጊስዳግማዊ አጤ ምኒልክበተባለው መጽሐፋቸው ገጽ ፴፱--፵፩ ላይከልዢነት ጀምረው ሲመኟት እንደ ህልም ሲአልሟት ትኖር የነብረችው ጣይቱ ብጡል በ፲፰፻፸፭ / ደብረ ብርሃን ገባች ንግሥተ ሸዋ ሆነች ወዲያው የፋሲካ ለት አንኮበር መድኃኔ ዓለም ቆርበው ሁለቱ ተጋቡ።ፀሐይቱ ለማለት ጣይቱ ተባለች ነገር ግን ከጣይቱ እጣይቱ ለመባል ይገባታል።ይላሉ

ማኅበረ ቅዱሳንን የምንወቅሰው በግብሩ እንጂ ማኅበር ሆኖ ስለቆመ አይደለም!




ብዙዎች ስለማኅበረ ቅዱሳን በምንጽፋቸው ጠጣር መልዕክቶች  በጣም ሲያዝኑ እንመለከታለን።  በኢሜል ወቀሳና ከዚያም ሲያልፍ ስድብ የሚልኩልን አሉ። በጽሁፎቻችን ውስጥ ማኅበሩን ነካ ባደረግን ቁጥር የሚያማቸውና ጸያፍ አስተያየቶችን የሚሰጡንም አጋጥሞናል። አንዳንዶች ስለማኅበረ ቅዱሳን የምንጽፋቸውን  እውነትነት አላቸው  ብለው እንደሚቀበሉን ሁሉ ተቃራኒውን አመለካከት እንደተለየ ሃሳብ ቆጥረን በአክብሮት እኛም ስንቀበላቸው ቆይተናል። ወደፊትም እንደዚሁ! የሃሳብ ልዩነት በዱላ ማስገደድ እስካልተቀላቀለበት ድረስ ለበጎ ነው እንላለን።  እኛ የሚታየንና እውነት ነው ብለን የተቀበልነው ነገር ለእነርሱ እንደስህተት ቢቆጠር አያስገርምም። እኛም ያላየንላቸው የእነርሱ እውነት ሊኖር እንደሚችል አስበንላቸው ተቃራኒ ሃሳባቸውን እናከብራለን። በዚሁ መንገድ የሁለት ወገን እሳቤን ተቀብለን ወደተነሳንበት ርዕሰ ጉዳይ እናምራ።
ማኅበረ ቅዱሳን እንዴት ተመሠረተ? ብለን የዓመታቱን መታሰቢያ የልደት ሻማዎችን ለመለኮስ ወይም አስልቺ የሆነውን የልደት ትረካ በመዘብዘብ ጊዜ ለማባከን አንፈልግም። ግብሩን ለመናገር ጥያቄዎችን እንጠይቅና እንመርምር።

፩/ ማኅበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያኒቱ  የእውቀት ገበታ ነው ወይ?

ማኅበረ ቅዱሳንን እንደምናየው በጠለቀ ደረጃ ባይሆንም በተወሰነ መልኩ በቤተ ክህነቱ የአብነት ትምህርት ቤት ውስጥ ያለፉ ሰዎችን ለመያዝ ሞክሯል። አብዛኛው ግን የቤተ ክርስቲያን ፍቅር ያቃጠላቸው እንደሆኑ የሚናገሩ የሰንበት ት/ቤት አባላትን ያቀፈና ዘግየት ብሎም ከሰንበት ት/ቤትም ሆነ ከፈለገ ሕይወት ት/ቤት ቅርበት ያልነበራቸውን ለመያዝ የሞከረ እንደሆነ ይታወቃል።  ይህንና ይህንን የመሳሰሉ ሰዎችን ይዞ እየተጓዘ እዚህ የደረሰው ማኅበር በነማን ምን ሰራ? ምንስ አበረከተ? የሚለውን  ልክ ስንመለከት ማኅበሩ እንዳዋቀሩት ሰዎች የማንነት ደረጃ አለኝ የሚለውን  የእውቀት ልክ ከነድርጊቶቹ እንመዝናለን እንጂ ዝም ብለን በጥላቻ አንፈርጅም። 

  ከዚህ አንጻር ማኅበሩ ሌላውን የሚመለከትበት ዓይን ራሱን ባዋቀረበት አቅምና ባለው የእውቀት ልክ ሳይሆን ነገሮች እየገጠሙ ስለተጓዙለት ብቻ ራሱን የቤተ ክርስቲያኒቱ የእውቀት ገበታ አድርጎ ማስቀመጡ አስገራሚ ይሆንብናል። በማኅበረ ቅዱሳን ሠፈር ራስን በማሳበጥ የእውቀትና የቤተ ክርስቲያኒቱን ትምህርት አብጠርጥሮ የማወቅ ችግር እንደሌለ ትልቅ ሥዕል አለ። መድረክ ላይ ቆሞ የማስተማር  እድልና  የእውቀት ጥማት ባላቸው ብዙ ምእመናን ጉባዔ ላይ ተገኝቶ የመናገር እድል በመግጠሙ ብቻ ማኅበሩ የእውቀት ርካታ የማካፈል ብቃት እንዳለው አድርጎ ራሱን አግዝፎ  ማየቱን ስናይ ይገርመናል። ብዙዎቹን የማኅበሩ አንጋፋ ተናጋሪዎቹን ትምህርት በአካልና በድምጽ ወምስል መልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች የማየት እድሉ ነበረን። አንዳንዶቹ የእውቀት ሳይሆን የንግግር ችሎታ ያላቸው ናቸው። አንዳንዶቹ የእውቀትም፤ የንግግር ችሎታ የሌላቸው ነገር ግን እድል የከነፈችላቸውና የሰው ወፍ የሚረግፍላቸው  ስለሆኑ ብቻ መምህራን መሆናቸውን ለራሳቸው የነገሩ ናቸው። አንዳንዶቹ እውቀት ያላቸው ቢሆኑም  ነገር ግን እውነቱን በማጣመም ልክፍት የተያዙ ጠማማዎች ሲሆኑ  አረፋ እየደፈቁ ለጉባዔ ሲናገሩ ከማንም በላይ የደረሱበትን እውቀት የሚያስተምሩ ይመስላቸዋል። ሌሎቹም እውቀቱ እያላቸው ለማስተማር የማይፈልጉ  ጥገኞች/Parasitic/ ሆነው ተጎልተዋል። ከምንም ከምኑም  ውስጥ የሌሉ ነገር ግን ክፋትና ሴራ በመጎንጎን የተካኑ የጥፋት መንፈስ ያሰገራቸው ሰዎችንም ተሸክሟል።

 እንግዲህ እነዚህ ሁሉ ባሉበት ማኅበር ውስጥ በተለየ መደብ በቅንነት፤ በየዋህነትና በእምነት የተሰለፉ አያሌዎች ደግሞ የማኅበሩ ቀኝ እጅ ሆነው እያገለገሉ መገኘታቸው እውነት ነው።  አለማወቅ በራሱ ችግር ቢሆንም ቅኖችና የዋሃን ከማኅበሩ ጋር በመቆማቸው የማኅበሩ ድክመት እንደጥንካሬ  በመቆጠሩ ብቻ ቅን ማኅበር ነው ሊሰኝ አይችልም።

Monday, March 11, 2013

የአቡነ ኤልያስና የአርባ ምንጭ ምዕመናን ውዝግብ!




«በአርባምንጭ የመድኃኔዓለም ሕንፃ ቤተክርስቲያን ግንባታ ላይ በብፁዕ አቡነ ኤልያስና በምዕመናን መካከል ተፈጥሮ የነበረው ውዝግብ በዕርቅ ተደመደመ» 
                               ( http://dejeselaam-dejeselaam.blogspot.com)                                                            
በአርባምንጭ ከተማ በመሠራት ላይ የሚገኘው የመድኃኔዓለም ሕንፃ ቤተክርስቲያን ብፁዕ አቡነ ኤልያስ የሰሜን ኦሞ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ሕዝብን ሳያማክሩ የዲዛይን ለውጥ በማድረጋቸው ምክንያት አለመግባባት ተፈጥሮ ግንባታው መቋረጡን ቀደም ሲል November 16, 2012 ባወጣነው ዘገባ መግለጻችን ይታወሳል፡፡
ለውዝግቡ መነሻ የሆነው የዲዛይን ለውጥ የመነጨው "ማኅበረ ቅዱሳን" ሲሆን "ማኅበሩ" አባሉ የሆነ አንድ ኢንጂነርን ከአዲስ አበባ ልኮ የሕንፃ ቤተክርስቲያኑ ዲዛይን ባለ አንድ ጉልላት ክብ ሕንፃ እንዲሆንና ቀደም ሲል በሕዝብ ምርጫና ስምምነት ግንባታው ተጀምሮ የነበረው ባለሦስት ጉልላት ሕንፃ ቤተክርስቲያን እንዲቀር በመወሰኑ ነው፡፡