በቤተ ክርስቲያን ትልቁ ችግር ከአናቱ እስከ እግሩ ጥፍሩ ያለው መዋቅር በበሰበሰ አስተዳደር መተብተቡ ነው። 2 ሺህ ዘመናትን በመከራና በወጀብ ስትናጥ፤ የደም አበላ ግብሯን ጠያይም ልጆችዋን እየሰጠች፤ ከጉዲት እስከ ግራኝ፤ ከድርቡሽ እስከጣሊያን ድረስ ከልጆቿ እስከ ንብረቷ ስትገብር የቆየችና እዚህ 21ኛው ክ/ዘመን ላይ የደረሰች ቤተክርስቲያን ሉላዊ እውቀትና አስተዳደር በዘመነበት ዘመን ላይ ምን እንደነካት ሳይታወቅ የገዛ ልጆቿ የስልጣንና የሀብት ክምሯ ላይ ሰፍረው እንደ ዳልጋ ዝንጀሮ እየፈነጩ ሲንዷት ማየቱ ውሎ ያደረ ከመሆኑም በላይ ሁሉም እየተባበሩ በአንድ ድምጽ ውድቀቷን እናፋጥን የሚሉ እስኪመስል ድረስ በጥፋት እድምተኞች መሞላትዋ ግልጽ ነው።
ሙዳየ ምጽዋት የሚገለብጡ ይሁዳዎች፤ አፍኒንና ፊንሐስ አመንዝራዎች፤ በነጻ የተሰጣቸውን የሚሸጡና በእናጸድቃለን ካባ የመበለት ቤቶችን የሚመዘብሩ ግብረ በላዎች፤ ስመ ብጽእናን ለምግባረ ብልሹ ስራቸው የደረቱ አባዎች ሞልተው የጋራ ክንዳቸውን በዐመጽና በጥፋት «አንስእ ኃይለከ» ተባብለው የተማማሉ የግብረ እከይ ሰዎችን ማንነትና አድራጎት መመልከቱም እንግዳ ነገር አይደለም። ሆዳቸው ከሞላ የበሻሻ አቦ ምእመናን ሰይፍ በአንገታቸው ቢያልፍ አፋቸው በስብ የተዘጋ ይመስል የማይናገሩ አፈ ዲዳዎች መሪ በሞላባት ዘመን ላይ ቤተክርስቲያን መድረሷ አጥፊዎቿ የውጪ ጉዲት ሳይሆን የራሷ እሬቶዎች መሆኑንም ብዙ ታዝበናል። በአዲስ አበባ ከተማችን የ2000 ብር ደመወዝ እየበላ የሁለት መቶ ሺህ ብር መኪና የሚነዳ የመሪነት ስምን የተሸከመ ሙዳየ ምጽዋት ገልባጭ ማየት የተለመደ ሆኗል። የዘረፋ መዋቅር ዘርግተው የቤተክርስቲያኒቱን ጡት ያለርኅራኄ የሚመጠምጡ አይጠ መጎጦች ተንሰራፍተው ይገኛሉ። ገንዘብ የሚገኝበትን ቤተክርስቲያን ለመምራት ከላይ እስከታች በሚደረገው መቆላለፍ ጅቦቹ አፋቸውን ከፍተው ሲያሰፈስፉ መስማትም ዛሬ ዛሬ እንደተገቢ እየተቆጠረ ይገኛል። በአንድ ወቅት የወይብላ ማርያም ቤተክርስቲያን ከነበራት የ400,000 ብር ካዝና ውስጥ በወራት ልዩነት ወደ 20 ሺህ ደርሶ ለካህናት ደመወዝ መክፈል እስኪያቅት መደረሱን አይተን እነሆ እስከዛሬ በአስገራሚነቱ መዝግበነዋል። ከማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም እስከ ዑራኤል ቤተክርስቲያን፤ ከመርካቶ ሚካኤል እስከ ግቢ ገብርኤል የጅብ መንጋ ሲግጥ ማየት እንግዳ መሆኑ ቀርቷል። በየደረጃው የእያንዳንዱን አብያተ ክርስቲያን ካዝና ገልብጠው ባዶ ካደረጉ በኋላ ወደተረኛው ቤተክርስቲያን የሚዛወሩ ወሮ በሎች በዚህ አጭር ጽሁፍ ዘርዝሮ የሚዘለቅ አይደለም።
የሚያስደንቀው ደግሞ ቤተክርስቲያኒቱ ምን ዓይነት ቁጣ ወረደባት እስኪያሰኝ ድረስ ከሀገር ቤት አንስቶ እስከባህር ማዶ ድረስ የአበሻ ጅቦች የሰፈሩባት መሆኑ ያስገርማል። ከቦርድ እስከ ሰበካ ጉባዔ ከተገንጣይ እስከ ገለልተኛ፤ ከግለሰብ ቤተክርስቲያን እስከ ሁለ ገብ ድረስ እየተቧደኑ መዝረፍና ማስዘረፍ፤ የየሀገራቱን ፍርድ ቤቶች ፋይል እስከማጨናነቅ ያደረሰ የዘረፋ ስልጣኔ መንገሱም ፀሐይ የሞቀው፤ አገር ያወቀው ጉዳይ ነው።
የክህነቱና የመሪነቱ መስፈርት የማንነት ሚዛንስ ምኑ ተነግሮ? እንዲያው ተከድኖ ይብሰል! ይህ ሁሉ ሲሆን ቤተክርስቲያንን በመንፈስ ቅዱስ እመራለሁ የሚል ከፍተኛው የሥልጣን እርከን ሲኖዶስ ነበራት። ለመብላትና ለመናገር ካልሆነ ለመሥራት አቅሙና ፍላጎቱ የሌለው፤ ቤተክርስቲያን ብትሞት እንጂ ለእሷ ሞት ራሳቸውን ለማስቀደም የሚደፍሩ የመሪ ቁርጠኞች በሌለበት ሁኔታ ውስጥ መገኘቷ ችግሯ እንዲባባስና ከልካይ የሌለበት እንድትመስል አድርጓታል። ወጉ ደርሶ ማስቆም ባይችሉ ራሳቸውም አብረው ወራሪና አስወራሪ መሆናቸውን ቢያቆሙ እንኳን እሰየው ባልን ነበር! ነገሩ ግን የተገላቦጦሽ ነው። ሕዝቡ በG ማይነስ ቤት ውስጥ እየኖረ እነሱ በG ፕላስ ውስጥ መኖራቸው ነገሩን ሁሉ አስከፊ ያደርገዋል።