ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአቡነ አብርሃም ሰሞኑን የንብረት አስረክብ ደብዳቤ መጻፋቸው ይታወሳል። ቅዱስ ፓትርያርኩ ከዚህ ቀደም የተጻፉትንና የተደረጉትን የጽሁፍ ልውውጦች መነሻ በማድረግ ደብዳቤውን ለመጻፍ መቻላቸውን እንጂ በእርሳቸው ደረጃ አቡነ አብርሃም ለምን እስካሁን እንዳላስረከቡ ወይም ለማስረከብም ይሁን ላለማስረከብ ያበቃቸውን ምክንያቶች ምን እንደሆኑ ለማወቅ ያደረጉት ውይይትም ይሁን ንግግር ስለመኖሩ በተጻፈው ደብዳቤ ውስጥ ምንም አልተገለጸም። ደብዳቤውን ለመጻፍ የሚያበቁ አሳማኝ ምክንያቶች መኖራቸው ቢታመንም እንኳን አቡኑን አስጠርቶ በአካል በማወያየት እሺታቸውን ይሁን እምቢታቸውን መረዳቱ የበለጠ ተቀራርቦ የመሥራት ምልክት መሆን በቻለ ነበር። የፓትርያርኩም አዲስ የሥራ መንፈስ መሆኑን ለመረዳትም እድል እናገኝበት ነበር። ከዚህ አንጻር ፓትርያርኩ ነገሮችን በማርገብ ተወያይቶና አወያይቶ ለችግሮች የቅድሚያ መፍትሄ አምጪ መንገዶችን ለመከተል ገና ብዙ ይቀራቸዋል ብለን እንገምታለን።
Saturday, May 4, 2013
Thursday, May 2, 2013
ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአል!
ዕብራውያን פֶּסַח» ፔሳኽ» ይሉታል። ፋሲካ ማለት ነው። በወርኀ ኒሳን በዐሥራ ዐምስተኛው ቀን ይከበራል። ሥርዓቱ የሚጀመረው በዐሥራ
አራተኛው ቀን ዋዜማ ሲሆን በፋሲካው ሳምንት እርሾ የገባበት ምንም ዓይነት ምግብ መመገብ ክልክል ነው።ዕለቱን ተቦክቶ ወዲያው የሚጋገር
እንጂ የኮመጠጠ ወይም የቦካና የዋለ፤ያደረ መመገብ በሕጉ እንደተቀመጠው ከእስራኤል አንድነት ያስወግዳል። ከማንኛውም እርድ ላይ
ጥሬ መብላት ወይም ከበሉትም አስተርፎ ማሳደር አይፈቀድም። ለመስዋዕት የሚቀርበው የበግ ወይም የፍየል መስዋዕትም እድሜው ከአንድ
ዓመት ያልበለጠ ጤናማና የተመረጠ መሆን ይገባዋል። በዐሥራ ዐራተኛው ቀን ምሽት መስዋዕቱ ይታረዳል።ሥጋውን ደግሞ ሌሊት ከመራራ ቅጠል ጋር ቀላልቅለው ይበሉታል።
Tuesday, April 30, 2013
አባ አብርሃም በአሜሪካ ያለውን የሀገረ ስብከት ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ ቋሚ ሲኖዶሱ ወሰነ
http://awdemihreet.blogspot.com/)
በማኅበረ ቅዱሳን አይዞህ ባይነት የአሜሪካውን ሃገረ ስብከት ጽ/ቤት ለብጹዕ አቡነ ፋኑኤል አላስረክብም ብለው የነበሩት አባ አብርሃም የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት እንዲያስረክቡ ቋሚ ሲኖዶሱ ወሰነ፡፡ ይህ በቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ፊርማ የወጣው እና አድራሻውን ለአባ አብርሃም ያደረገው ደብዳቤ እንዳስታወቀው አባ አብርሃም ሀገረ ስብከቱን በዝውውር ለቀው ከወጡ በኃላ የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት አላስረክብም ማለታቸው ህገ ወጥ ድርጊት ነው፡፡
አባ አብርሃም ቤተክርሰቲያን አንዲት መሆንዋን መረዳት ከብዷቸው እና እሳቸውን ለማዘዝ ሙሉ ስልጣን ያለውን ቅዱስ ሲኖዶስ ተጋፍተው ላለፉት ሁለት አመታት የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት አላስረክብም በማለት በሀገረ ስብከቱ ውስጥ የሽፍታ ሠራዊት ማስፈራቸው አስገራሚ ሆኖ ሰንብቷል፡፡ እኚህ ጉድ አያልቅበት የሆኑት ጳጳስ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚሳካው እሺ ብሎ በመታዘዝ መሆኑ ከዲቁና እስከ ጵጵስና ድረስ አለመረዳታቸው በብዙዎች ዘንድ የሚያስተዛዝብ ሆኗል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)