(የጽሁፍ ምንጭ፤ ዘሐበሻ)
ደብረሰላም መድሃኔዓለም ከተመሠረተ ጊዜ ጀምሮ በብዙ ውስብስብ ችግሮች ያለፈ ሲሆን ከዓመታት በፊት በማን ሥር መሆን አለበት ተብሎ 3 ምርጫ ቀርቦ ነበር። ይኸውም ሃገር ቤት በወያኔ ሥር በሚገኘው ሲኖዶስ፣ ኒውዮርክ በነበሩት አቡነ ይስሃቅ እና 3ኛው ገለልተኛ እንዲሆን ሲሆን በጊዜው በስብሰባው ቦታ በነበርነው አባላት በውጭ የሚገኘው ሲኖዶስም በደንብ ባለመጠናክሩ ገለልተኛ ሆኖ እንዲቆይ ተስማምተን ቤተክርስቲያኑ ለተወሰኑ ዓመታት ገለልተኛ ሆኖ ቆይቷል። ሆኖም ለቤተከርስቲያኑ ምስረታና ዕድገት በጊዜው ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉት አባ ፍቅረማርያም የአሁኑ (አቡነ ዳንኤል) ወደ ሃገር ቤት ተመልሰው ጳጳስ ከሆኑ በኋላ የደብረ ሠላም መድሃኔዓለም ገለልተኛ ሆኖ መቀጠል አጠያያቂ ሆኗል።
ፕሮፌሰር መሥፍን ወ/ማርያም
(ክፍል ሁለት)
የዛሬዎቹ ባለሥልጣኖች በደርግ ጊዜ አልነበሩም፤ የደርግን ስሕተት
በማየት አልተማሩም፤ ትምህርታን አቋርጠው ወደጫካ የገቡት ከትምህርት የሚበልጥባቸው ምኞት አጋጥሟቸው ነው፤
የትምህርት ገዜያቸውን በጫካ ባለሥልጣን በመሆን፣ እነሱው ሕግ አውጪና ዳኛ፣ እነሱው የጫካ አስፈጻሚ ሆነው ቀዩ፤
ደርግ በጠራራ ጸሐይ የሚሠራውን እነሱ በጫካ ጭለማ ሲሠሩ ቆዩ፤ በሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላም በጣም ቆይተው ትምህርት
አስፈላጊ መሆኑን በትንሹ ተገነዘቡ፤ በጣም የተማሩ ሰዎች ጋር ሲገናኙ ማፈር አስጨነቃቸው፤ ስለዚህም ቀላሉ ነገር
የተማሩ ሰዎችን አለማቅረብ፣ ትምህርታቸውን በጠባያቸው ካላጠቡ የተማሩ ሰዎች ጋር በቀር አለመገናኘት፣ እንዲያውም
የትምህርትን ዋጋና ጥራት በማዋረድ አዲስ የሚመረቁት ሁሉ ለባለሥልጣኖች አንገታቸውን የሚደፉ ዓይነት እንዲሆኑ
ማድረግ ዓላማ ሆነ።
የተማሩና የሠለጠኑ የጦር መኮንኖችም ተሸናፊዎች በመሆናቸው ትምህርታቸው ዋጋ
እንደሌለው ማረጋጋጫ እያደረጉ የወያኔ መሪዎች በአደባባይ ተናገሩ፤ ትንሽዋ ቢምቢ ሰውን መግደል እንደምትችል
ያልተገነዘቡት ከጫካ የመጡ ሰዎች በመግደል ማሸነፍን የትምህርትን ዋጋ-ቢስነት ማረጋጋጫ አደረጉት፤ የተማሩ ሰላማዊም
የጦር መኮንኖችም ዋጋ-ቢስነታቸው ኑሮአቸውን በማናጋቱ በችግር ወደሌላ ሥራ ተሰማሩ፤ ወይም አገር ጥለው ተሰደዱ፤
በሰላማዊውም ሆነ በፖሊስና በጦር ሠራዊቱ የተማረ ሰው እጥረት መፈጠሩ ለወያኔ መግቢያና መደላደያ ምቹ ሁኔታን
ፈጠረ።
መስፍን ወልደማርያም
ጥር 2005
ክፍል አንድ
በአለፉት አርባ ዓመታት ውስጥ አንድ ልብ ያላልነው መሠረታዊ ለውጥ አለ፤ እንዲያውም የመከራችን ሁሉ ምንጭ ነው ለማለት ይቻላል፤ የመሪዎቻችን አለመማር ብቻ ሳይሆን ትምህርትን መናቅ ወይም ጭራሹኑ መጥላት ዋና ባሕርያቸው ሆነ፤ እስከደርግ ዘመን የነበሩት የአገር መሪዎች ቢያንስ የአንደኛ ደረጃውን (ዳዊት መድገም) የአገሩን ባህላዊ ትምህርት ያከናወኑ ነበሩ፤ ከዚያ በኋላ ለጨዋ ቤተሰብ ልጆች ትምህርት ማለት በቤተ መንግሥት በመዋል የሚገኝ ልምድ ነበር፤ ተፈሪ መኮንን በአሥራ ሦስት ዓመቱ ደጃዝማች የሆነውና ሥልጣን ላይ የወጣው በመወለድ ያገኘውን ዕድል በልምድ እንዲያዳብረው ነበር፤ ተክለ ሐዋርያት ከአሥር ዓመታት በላይ ሩስያ ተምሮ ሲመለስ ተፈሪ ያገኘውን አላገኘም።
በአጼ ኃይለ ሥላሴ ዘመን ትውልድ ለሥልጣን መነሻ አይሆንም ነበር ባይባልም፣ ለእድገት ትምህርት አስፈላጊ መሆኑ በመታመኑ የዓየር ኃይል እጩ መኮንኖችም ሆኑ መኮንኖቹ ከደብረ ዘይት እየተመላለሱ ይማሩ ነበር፤ በማታው ትምህርት ብዙ የፖሊስና የጦር ሠራዊት መኮንኖች (ኮሎኔል ሚካኤል አንዶም ጭምር) ይማሩ ነበር፤ ማታ ከተማሩት የፖሊስ መኮንኖች ውስጥ ሁለቱ አምባሳደሮችም ሚኒስትሮችም ሆነው ነበር፤ ከሐረር አካደሚ የወጣ መኮንንም አምባሳደር ሆኖ ነበር፤ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አገዛዝ የደሀ ልጆች ወደሥልጣን ወንበሩ አልተጠጉም የሚሉ ካሉ የማያውቁ ናቸው፤ ትምህርታቸውን በታማኝነት ከፍነው ቀብረው ሚኒስትርና ሌላም ሹመት ያገኙ የደሀ ልጆች ብዙዎች ናቸው።