የዐረብ ሊግ ሀገራት ካርታ
(ክፍል አንድ )
(ክፍል አንድ )
ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ ከፊውዳላዊ ወደ ሶሻሊስታዊ፤ ከዚያም የአብዮታዊ
ዲሞክራሲ መርህ በመረከቡ ሀገሪቱ በአዙሪት ቅብብሎሽ እየተናጠች በመዝለቋ የተነሳ ሕዝቡ የኖረበትን የዝብርቅርቅ
ፖለቲካ አመለካከት ባለቤት ሆኖ መገኘቱ የሚካድ አይደለም። ከዚህም ውስጥ አሁን በሥልጣን ላይ ያለውን የኢህአዴግ «የአብዮታዊ ዴሞክራሲን»
ጽንሰ ሃሳብ ብዙዎች የማይቀበሉት ፍልስፍና መሆኑም እውነት ነው።
ይህ ሲባል አብዮታዊ ዲሞክራሲ ለራሱ ጥቅም ይሁን ተጨቁኗል ለተባለው ወገን ዘላቂ ጥቅም ለማስገኘት የፖለቲካ ትረካው ለጊዜው ይቆየንና
በዚህ በአብዮታዊ ፍልስፍና ተጠቃሚ የሆኑ ክፍሎች መኖራቸውን ግን አሌ ልንለው የማንችለው ሐቅ ነው። ከእነዚህ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ፍልስፍና ግንባር ቀደም ተጠቃሚ ከሆኑት የሀገሪቱ
ዜጎች መካከል የእስልምና ሃይማኖት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። ይህ መብትን የመጠቀም መርህ መልካምነቱ እንዳለ ሆኖ የመብት አጠቃቀም
ልዩነቱ የሚነሳው አብዮታዊ ዲሞክራሲ ይህን በሃይማኖት የመጠቀም መብትን ለእስላሞቹ የሰጠበት ስልትና ጥበብ፤ መብታቸውን ገቢር ለማድረግ
አጋጣሚውን ከተጠቀሙበት ከእስላሞቹ ዓላማና ግብ ጋር ሰፊ ልዩነት ያለው የመሆኑ ጉዳይ ነው። የአብዮታዊው ዲሞክራሲ ስልት በተረጋገጠው
የእስላሞች መብት የተነሳ እስላሞቹን በዚህ ፍልስፍና በማጥመቅ የኃይል ድጋፍ የማግኘት ጥበብ ሲሆን እስላሞቹ ደግሞ በአብዮታዊ ዴሞክራሲ
ፍልስፍና ውስጥ መብትን እየተጠቀሙ የሚገኙት አብዮታዊውን ወደ እስልምናዊ ፍልስፍና የመቀየር መንገድ እንደነበራቸው የተጓዙባቸው
የሁለት አሥርት ዓመታት ጉዞዎች ፍንትው አድርጎ የሚያሳየን ሁለቱም ሄደው ሄደው አሁን የደረሱበት የመጠጋገብ የእድገት ደረጃ ነው።
ዛሬ እየታየ ያለው የአክራሪዎችና የመንግሥት እሰጥ አገባ መሠረቱ የሁለቱ ፈላስፋዎች የጉዞ መቋጫ «የደረስኩብህና የነቃህብኝ» ዓይነት
ድብብቆሽ ከመነሻው ዲሞክራሲን በመስጠትና ዲሞክራሲን በመተግበር ሁለት የተለያዩ ቡድኖች እንደነበሩ የሚያረጋግጥልን ነው።
ሌላው ነጥብ ፖለቲካዊ ጥቅሙን በማስላት ይሁን ለሃይማኖቶች
መከበር ከሃይማኖተኞቹ በላይ ሃይማኖተኛ
የመሆን ያለመሆኑ የመንግሥት አቋሙ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የማይካደው
ነገር ቢኖር ኢህአዴግ እንደማንኛውም እምነት ለእስልምናው ሃይማኖት መከበር ትልቅ መብት የመስጠቱ ነገር ጉዳይ ነው። እንዲያውም እስልምናውን
ከማንም በላይ በመሸከም በአክራሪዎች የግድያ፤ የማቃጠልና የማሳደድ እርምጃ በኦርቶዶክሱና በሌላው ላይ ሲወሰድ ዝምታን የመረጠበትና
ጉዳዩን በማለዘብ ሌሎቹን ዝም እያሰኘ ሲያረግብ መቆየቱም መንግሥት ሲነቀፍበት ቆይቷል። ሌላው ቀርቶ የመንግሥት ሹመኛው አሊ አብዶ የተባለው የእስልምና አክራሪዎች
አባት በአዲስ አበባ ከንቲባነቱ የሕዝብን የልማት ሥራ ወደጎን በመተው በመስጊድ ልማት ላይ ጊዜውን የመፈጸሙ ነገር ኢህአዴግ የእስላሙን
ልብ ለማግኘት የተጓዘበት መንገድ ተደርጎ መቆጠሩም መዘንጋት የለበትም። በአሁኑ ወቅት
በአክራሪዎችና በኢህአዴግ መካከል ያለውን የዓይጥና የድመት ሩጫ ተከትሎ ፤በመግቢያችን ላይ ለመጠቆም እንደወደድነው ለዓመታት
በተለያየ የፖለቲካ አስተሳሰብ የተናጠው ትውልድ የአብዮታዊ ዲሞክራሲን ፍልስፍና በመጥላቱ ብቻ «የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው» ከሚል
ስንኩል እሳቤ የተነሳ እስልምናው እንደተጨቆነና አብዮታዊ ዲሞክራሲ መብቱን እንደጨፈለቀው በመቁጠር ድጋፍን ለማሳየት የመሞከሩን
ነገር ስንመለከት እጅግ ያስገርማል። ያሳዝናልም። ኢህአዴግን መጥላት አንድ ነገር ነው። በእስልምና ፍቅር መቃጠል ደግሞ ሌላ ነገር
ነው። በኢህአዴግ የሥልጣን ዘመናት ሁሉ ከኢህአዴግ ጋር ቆሞ የነበረው የእስልምናው አክራሪ ክፍል የእድገቱን ደረጃ በጨረሰበት ወቅት
ላይ ወደመላተም ሲደርስ በመመልከት «የጠላትህ ጠላት ወዳጄ ነው» የሚለው ያረጀ ፈሊጥ የትም አያደርስም። እውነታውንም አይለውጥም። እውን የእስላሞች የሃይማኖት መብት በአብዮታዊ ዲሞክራሲ ፍልስፍና አልተከበረም?
የእስልምና መብቶች ከሌሎች ሃይማኖቶች መብት ያነሰ ነበር? ኢህአዴግን ከሌሎቹ በተለይም ከኦርቶዶክሶች በላይ በተለጠጠ መብት ሲያባልገው አልቆየም? ኢህአዴግ ለእስላም ኢትዮጵያውያን የሰጠው ወሰን አልባ መብት ከሚያስነቅፈው በቀር የእስላሞችን መብት በመደፍጠጥ እንደጨቆነ አድርጎ መናገር ያስተዛዝባል። ኢህአዴግ አንባገነን ይሁን ወይም በእስላሞች ጉዳይ እጁን ያስገባ፤ አያስገባ
አንድ ነገር ሆኖ ከሌላው ሃይማኖቶች በተለየ እስልምና ተጨቁኗል የሚለው
አባባል ሚዛን የሚደፋ አይደለም። እንደእውነቱ ከሆነ ምዕራብ አፍሪካን እያመሰሰ ያለው አክራሪ እስልምና በኢትዮጵያ ውስጥ የጦርነት ዘመቻውን አልጀመረም ካልሆነ በስተቀር ሃይማኖታዊ መብቱ ተረግጧል በማለት የፖለቲካ ኅብረት ለማድረግ መስማማት የሚያሳየው የኢህአዴግን ብልግና ሳይሆን ፖለቲካ የሚባለው የሀሰት ፍልስፍና እየቆሸሸ መምጣቱን ነው። በምድር ላይ ያለው እውነታ ግን ከዐረብ ሀገራት እስከ ኢትዮጵያውያ ድረስ የአክራሪ ሙስሊሞች እንቅስቃሴውና
የትስስሩ ዘመቻ ዋና ዓላማ ኢትዮጵያን የ«ዲን አልኢስላም» ሀገር ለማድረግ እርግጥ የመሆኑ ጉዳይ ብዙ የተባለለት ስለሆነ ፖለቲካ ሀቁን አይለውጠውም።
በኢትዮጵያ ውስጥ ኢስላማይዜሽን እየተገለጠባቸው ያሉትን መንገዶች መመልከት ይቻላል፤ ዋና ዋናዎቹ፤
1/ የክርስትናውን ሃይማኖት በመንቀፍ፤ በማንቋሸሽ፤ በመተች መጻሕፍትን ማሳተም፤ ማሰራጨት
2/ የወሀቢዝም መፈልፈያ መድረሳዎችን በሀገር ውስጥ መክፈትና ማሰልጠን
3/ በአክራሪ ሀገራት በሚሰጠው የአክራሪነት ትምህርት መጠመቅ፤ የማስፋፊያ የወታደራዊ ስልትን መማር፤
4/ በተለያዩ ስፍራዎች ትንኮሳዎችን በመፍጠር፤ አጋጣሚዎችን መጠቀም
5/ ባያምኑበትም ባለው ፖለቲካዊ ተቋም ውስጥ አማኞቻቸውን በመሰግሰግ መብትና ጥቅምን ለማስከበር ስልጣን መቆጣጠር
6/ ኢኮኖሚያዊ አቅም የሌላቸውን የሌላ እምነት ሰዎችን በጥቅም መለወጥ ወይም በጋብቻ ምክንያት ማስለም
7/ ግልጽ የሆነ ጫና እስካልመጣ ድረስ መንግሥትን በመደገፍ ስልታዊ እንቅስቃሴን ማስፋፋት
8/ የእስልምናው ቁጥር ከክርስቲያኑ እንደሚበልጥ የተሳሳተ መረጃ በማውጣት፤ ሸሪአን ለኢትዮጵያ ማወጅ
የመሳሰሉትን መንገዶችን በመተግበር በዲሞክራሲው ሽፋን ኢትዮጵያ ውስጥ ሲሰራ ቆይቷል።