መነሻ ሃሳብ «ገመና ዘ81ዱ» መጽሐፍ
ርእስ፤ እውነቱ የቱ ነው?
ሀተታ፤
በኦርቶዶክሳውያን ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውስጥ ከታች ጀምሮ እስከላይኛው እርከን ድረስ ያለው
ሰው ስህተት ይኖርብናል ወይም ልንሳሳት እንችላለን ብሎ የሚያስብ ማግኘት አዳጋች ነው። በክርስቶስ ደም የተመሰረተችው ቤተክርስቲያን
ፍጽምትና ንጽሕት መሆኗን በመቀበል እንዳለ መሪውና ተመሪው ራሱንም በዚያው ዓይን እያየ እኛ ፍጹማንና ንጹሐን ነን በሚል ከለላ
ስር ራሱን በማስጠለል፤ ስህተትን አምኖ ለመቀበል አይፈልግም። የስህተት አስተምህሮ አለ፤ በእግዚአብሔር ቃል ሲመረመር አደጋው የከፋ
ነው፤ የክፉ መንፈስ አሰራር ወደማወቅ እንዳንደርስ ቃሉን በክሏል ሲባል የሚሰጠው ምላሽ፤ 2000 ሺህ ዘመን የኖረችን ቤተክርስቲያን
ዛሬ የተነሱ አፍቃሬ ተሐድሶ መናፍቃን ሊያርሟትና ሊበርዟት ይፈልጋሉ በማለት ታፔላ መለጠፍ ይቀናቸዋል። የስም ታፔላ መለጠፍ ብቻ
ሳይሆን ሽልማት የሚያሰጥ ቢሆን ኖሮ የተመረጡና ለመስማት የሚዘገንኑ ስድቦችና ዛቻዎች ይዥጎደጎዳሉ።
በእርግጥ የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ፍጽምትና ንጽሕት
መሆኗ አያጠራጥርም። ምክንያቱም የመሠረታት በዓለቱ ላይ በፈሰሰው ደሙ ነውና። ይህ እውነት ቢሆንም በክርስቶስ ቤተክርስቲያን ውስጥ
አባል ሆነው የሚኖሩት የአዳም ልጆች መሆናቸውንም በመዘንጋት የቤተክርስቲያኗን መንፈስና ባህርይ እንዳለ ወደሰዋዊ ማንነት በመውሰድ
እኛ ፍጹማንና ንጹሐን ነን በማለት ከስህተት አልባነት የቤተክርስቲያን ማንነት ጋር ራስን መቁጠር ትኩረት የሚያሻው መሆኑን ልናሰምርበት
ይገባል። በእርግጥም የተጠራነው ፍጽምት በሆነች ቤተክርስቲያን ውስጥ ፍጹማን እንድንሆን ነው። ነገር ግን ሰው ከተፈጠረበት ማንነት
የተነሳ በፍጽምቷ ቤተክርስቲያን ውስጥ ፍጹም ሆኖ መኖር የሚችል ማንነት የለውም።
ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑን የሚችሉት የገላትያ ሰዎች
ማንነት ነው። የገላትያ ሰዎች በክርስቶስ አዳኝነት አምነው ወደ ሕይወት መንገድ የተመለሱ ሕዝቦች ነበሩ። ፍጽምትና ንጽሕት በሆነች
የክርስቶስ ቤተክርስቲያን ተጨምረው የቆዩ ሆነው ሳለ ሰብአዊ ማንነታቸው አሸንፎአቸው ወደስህተት መንገድ በመግባታቸው በሐዋርያው
ጳውሎስ እጅግ የተወቀሱ ሕዝቦች ሆነዋል።
«የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ
ነበር፤ ለእውነት እንዳትታዘዙ አዚም ያደረገባችሁ ማን ነው?» ገላ 3፤1
ክርስቶስ ኢየሱስ በፊታቸው የተሰቀለ ሆኖ በእምነት
ይታያቸው የነበሩት ሕዝቦች ከዚያ የቅድስና ማንነት ወርደውና እውነትን በመተው፤ የጠላት አዚም የወረደባቸው ሕዝቦች እስከመሆን መድረሳቸውን ሲናገር እናያለን። ሥራቸውን ሁሉ በመንፈስ
ቅዱስ ኃይል የጀመሩ ሆነው ሳለ ቁልቁል ተመልሰው የሥጋን ሃሳብና እውቀት ወደማመን መመለሳቸው በእርግጥም አሳዛኝ የሰው ልጆች ማንነት
ማሳያዎች እንደሆኑ የሚያስገነዝበን ነገር ነው።
«እንዲህን የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ
አሁን በሥጋ ትፈጽማላችሁን?» ገላ 3፤3 ይላል።
እንግዲህ ክርስቲያኖች ፍጽምትና ንጽሕት በሆነች ቤተክርስቲያን ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እምነታቸውን ሊጀምሩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ይህንን ፍጽምና ወደአለማወቅ መመለስም ሊታይባቸው ይችላል። ምን ጊዜም ቢሆን የስህተት መንፈስ አገልግሎቱ፤ የእውነቱን መንፈስ ከሰው ልቡና ላይ በመውሰድ ወደስህተት መንገድ መምራት ስለሆነ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ውስጥ የስህተት አስተምህሮ እንደሚገባ እናረጋግጣለን።
እንግዲህ ክርስቲያኖች ፍጽምትና ንጽሕት በሆነች ቤተክርስቲያን ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እምነታቸውን ሊጀምሩ ይችላሉ። ይሁን እንጂ ይህንን ፍጽምና ወደአለማወቅ መመለስም ሊታይባቸው ይችላል። ምን ጊዜም ቢሆን የስህተት መንፈስ አገልግሎቱ፤ የእውነቱን መንፈስ ከሰው ልቡና ላይ በመውሰድ ወደስህተት መንገድ መምራት ስለሆነ በቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ውስጥ የስህተት አስተምህሮ እንደሚገባ እናረጋግጣለን።
ብዙዎች የአብያተ ክርስቲያናት አባላት በክርስቶስ
ፍቅር ላይ ጸንተው ከመቆም ይልቅ ወደ ምድራውያንና ሰማያውያን ፍጥረቶች ፍቅራቸውን ስለለወጡ የሕይወት መንገድን ስተው መገኘታቸው
እውነት ነው።
ጳውሎስ ጢሞቴዎስ ልጁን ወደ ተሰሎንቄ የላከበት
ዋናው ምክንያትም ተሰሎንቄዎች ከእምነት ጽናታቸው ወደኋላ እንዳይመለሱ
በመንፈስ ያበረታታቸው ዘንድ ነበር። ምክንያቱም ፈታኝ የምንጊዜም አዚሙን የሚያፈሰው የአማኞችን ልቡና በማደንዘዝ ወደ አልሆነ አቅጣጫ መመለስ ሥራው ስለሆነ ከዚህ ፈታኝ ይጠበቁ ዘንድ እንደላከላቸው ቅዱሱ ወንጌል ይነግረናል።
«ስለዚህ እኔ ደግሞ ወደ ፊት እታገሥ ዘንድ ባልተቻለኝ ጊዜ። ፈታኝ ምናልባት ፈትኖአቸዋል ድካማችንም
ከንቱ ሆኖአል ብዬ እምነታችሁን ለማወቅ ላክሁ» 1ኛ ተሰ 3፤5
ከከሳቴ ብርሃን አባ ሰላማ ወዲህ ወደ ኢትዮጵያ
መጥተዋል ተብለው የሚጠሩ መነኮሳት በዋሻና በፍርክታ ገዳም መስርተው ሰው ሁሉ ወደዚያው እንዲከትም ከማድረግ ውጪ ሀገር ላገር ዞረው፤
እንደሐዋርያቱ ወንጌል ላልበራለት ሕዝብ ወንጌልን ስለማስተማራቸው የሚታወቅ ነገር የለም። ወንጌል ለሕዝቡ የበራ ቢሆንማ ኖሮ እስከዛሬ
በዛፍ ስር ቡና የሚደፉ፤ ደም የሚያፈሱ፤ቅቤ የሚቀቡ፤በጨሌ፤ ቆሌና የቤት ጣጣ አምልኮ ሰርጾባቸው የሚኖሩ ባልኖሩ ነበር። እምነት አለን፤ አውቀናል የሚሉት እንኳን እስከፕሮቴስታንት መምጣት ድረስ
መጽሐፍ ቅዱስን አያውቁትም። ደረትን ነፍቶ ኦርቶዶክሳዊ ስለመሆን አረጋጋጭ ከሆኑት ከድርሳናት ውጪ መጽሐፍ ቅዱስን ይዞ መገኘት
በራሱ ኮትልኳል ወይም ጰንጥጧል የሚያሰኝ በመሆኑ ይዞ መገኘት ያሳፍር ነበር። ይህ በእድሜአችን ያየነው እውነት ነው። አንዳንዶች
«ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው» የሚለውን ቃል ጠምዝዘው ራሳቸው ለመሸንገያነት በመጠቀም አንድም ሐዋርያ ሳይመጣ ያመንን ስለሆንን
ቃሉ እኛን ኢትዮጵያውያንን ያመለከታል ለማለት ቢፈልጉም የሐዋርያ ወይም የሰባኪ አለመምጣት እንደ ጉዳት እንጂ እንደጠቃሚ ነገር
መቁጠር አለማወቃችንን የሚያሳይ ነው። መጽሐፍ የሚለን እውነት ይህንን ነው።
«እንግዲህ ያላመኑበትን እንዴት አድርገው ይጠሩታል? ባልሰሙትስ እንዴት ያምናሉ? ያለ ሰባኪስ እንዴት ይሰማሉ?» ሮሜ 10፤14
እንደዚሁ ሁሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
እውነተኛ ወንጌል በማስተማርና ሕዝቡን ከክርስቶስ ወንጌል ጋር በማስማማት እንዲኖር ለማድረግ እስከሞት ድረስ ከታገለው ከአባ እስጢፋኖስ
በቀር ግብጻውያንም ጳጳሳት የሰሩት የወንጌል አገልግሎት አልነበረም። ወንጌል ሥራው በግጻዌ ምድቡ በጥቅስ ደረጃ በየሥርዓተ ቅዳሴው
ላይ ተመርጦ ከሚነበብ ውጪ ከተአምረ ማርያምና ከድርሳናት እኩል መድረክ አልነበረውም። አቡነ ቴዎፍሎስ የወንጌልን አስፈላጊነት በማመን
አዳሪ ት/ቤቶችን በማጠናከር፤ ሰንበት ት/ቤቶች በማቋቋምና በቃለ ዓዋዲ እንዲደነገግ እስኪያደርጉ ድረስ አብያተ ክርስቲያናት በግእዝ
ቀድሰው፤ በግእዝ አንብበው፤ ለዓለመ ዓለም ካሉ በኋላ እግዚኦ መኀረነ ክርስቶስ እንበል 12 ጊዜ ብለው ጣት ከማስቆጠር ባለፈ ህዝቡ
ወንጌልን እንደማያውቅ ጠንቅቀን እናውቃለን።
እንዲያውም ወንጌል እቃ ግምጃ ቤት ገብቶ የሸረሪት፤ የአቧራና የአይጥ ቀለብ ሲሆን በአንጻሩ ልፋፈ ጽድቅ በየአንገት ላይ የሚንጠለጠል ክቡር መጽሐፍ ሆኖ ለዘመናት ኖሯል። ዛሬም እስከመቃብር ድረስ አብሮ የሚወርድ፤ ክቡር አዳኝ መጽሐፍ ሆኖ መቆጠሩን አላቋረጠም። የዲቁናም ይሁን የቅስና ማእርግ የሚሰጠው ሥርዓተ ቅዳሴውንና ኩሳኩሱን ከመልክዓ መልክዑ ጋር መሸምደዱ እንጂ ወንጌልን ተንትኖ ሕይወት የሚገኝበትን ቃል ማስተማር ስለሚችል አይደለም።
እንዲያውም ወንጌል እቃ ግምጃ ቤት ገብቶ የሸረሪት፤ የአቧራና የአይጥ ቀለብ ሲሆን በአንጻሩ ልፋፈ ጽድቅ በየአንገት ላይ የሚንጠለጠል ክቡር መጽሐፍ ሆኖ ለዘመናት ኖሯል። ዛሬም እስከመቃብር ድረስ አብሮ የሚወርድ፤ ክቡር አዳኝ መጽሐፍ ሆኖ መቆጠሩን አላቋረጠም። የዲቁናም ይሁን የቅስና ማእርግ የሚሰጠው ሥርዓተ ቅዳሴውንና ኩሳኩሱን ከመልክዓ መልክዑ ጋር መሸምደዱ እንጂ ወንጌልን ተንትኖ ሕይወት የሚገኝበትን ቃል ማስተማር ስለሚችል አይደለም።
ከዚህ በታች የምናቀርባቸው መጽሐፍ ቅዱሳችን በምንለው
መጽሐፍ ውስጥ የሚገኙ ስህተቶች፤ ነገር ግን እውነት እንደሆኑ ቆጥረን የምንከራከርላቸው ሲሆኑ ችግሩን እንደችግር ያለመቁጠራችን
ዋና ምክንያት ከላይ በሀተታ እንደዘረዘርነው አንድም እኛ ፍጽምትና ንጽሕት በሆነች ቤተክርስቲያን ውስጥ ያለን ስህተት አልባዎች
ነን ከማለት የመነጨ ሰውኛ ማንነትን ካለመቀበል ችግር፤ አንድም- ክርስቶስ ከፊታቸው ተስሎ የነበሩት ገላትያውያን እንደሆኑት የሆነ
አዚም አደንዝዞን እውነትን ለመቀበል ባለመፈለግ፤ አለያም ሳያዩ የሚያምኑ……በሚለው የሽንገላ ቃላት ተሸውደን እውነተኛውን የክርስቶስ
ወንጌል የሚሰብክ እንዲኖረን ባለመፈለግ ራሳችንን ስናሞኝ በመኖራችን ይሆናል።
የስህተት ትምህርት አስረጂዎች፤
ብዙውን ጊዜ «ከእውነተኛ
የወንጌል አስተማሪዎች እጦት የተነሳ» /ከአስተማሪዎች እጦት የተነሳ አላልኩም/ ሕዝቡ እስካሁን ለወንጌል ቃል አዲስ በመሆኑ
አሳማኝ መልስ መስጠት ስለማይችል እንደችግር መፍቻ መፍትሄ የሚጠቀምበት መንገድ በመሳደብ፤በማሳደድ፤በማሽሟጧጥ፤ በመደባደብ ብሎም
በመግደል ልዩ ለሆነ ሃሳብ ሁሉ ምላሽ ሲሰጥ ቆይቷል። አሁንም ይህ
አድራጎት አላቋረጠም። ከዚህ በታች ለሚቀርቡ አስረጂዎች ምላሽ መስጠት የሚችል አንድም ሰው እንደሌለ እርግጠኞች ስንሆን የሚሳደብ
ወይም የሚያንቋሽሽ ክርስቲያኖችን ግን በሺህዎች እንጠብቃለን።
- 1/ ስለታቦተ ጽዮን ትረካ፤
- 1,1 ስለታቦተ ጽዮን አመጣጥ ታሪክ የሚናገረውን «ክብረ ነገሥት» የተባለውን መጽሐፍ ማኅበረ ቅዱሳን ውሸታም ብሎታል።
ማኅበረ ቅዱሳን ትውፊትንና ባህልን፤ ልምድንና
አምልኰትን ለይቶ የማያውቅ የጅምላ እምነት አራማጅ መሆኑ ሲታወቅ፤ ራሱ እገዛበታለሁ የሚለውን ትውፊት ሲሽር እንጂ ሌሎች ሲሽሩ
ዓይኑ ደም የሚለብስ አስቸጋሪ ድርጅት ነው። እንደሚታወቀው ግራሃም ሐንኰክ የተባለ እንግሊዛዊ ምሁር /The sign of the
seal/ በሚል ርእስ እ/ኤ/አ በ1992 ዓ/ም ያሳተመውን መጽሐፍ ይህ የትውፊት ጠበቃ ነኝ የሚለው የጅምላ እምነት አራማጅ ማኅበር፤
/ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ/ በሚል ርእስ በጌታቸው ተስፋዬ አስተርጉሞ ያሳተመው መጽሐፍ እንደሚተርከው ታቦተ ጽዮን በንጉሥ ሰሎሞን ዘመን በልጁ ኢትዮጵያዊ ንጉሥ በቀዳማዊ
ምኒልክ እጅ ሳይሆን ወደኢትዮጵያ የመጣው በግብጽ ኤሌፋንታይን አቋርጦ ከዓመታት ቆይታ በኋላ የዓባይን ሸለቆ ተከትሎ ቀስ በቀስ
በጣና አድርጎ ነው የገባው በማለት ይናገራል። ስለዚህ «ክብረ ነገሥት» ስለታቦተ ጽዮን አመጣጥ የሚተርከው የእነ ቀዳማዊ ምኒልክ
ታሪክ በውሸታምነቱ ተመዝግቧል ማለት ነው። ማኅበረ ቅዱሳን የታቦተ ጽዮንን አመጣጥ በግራሃም ሃንኰክ አተራረክ መሰረት የሚያምን
ከሆነ ክብረ ነገሥትን ትረካ ዋጋ ቢስ ያደርገዋል። የሚገርመው አንድም የሊቃውንት ጉባዔ ይሁን የጳጳሳቱ ዓለም የክብረ ነገሥትን
ትረካ የሚቃወመውን የማኅበረ ቅዱሳን እትም መጽሐፍ ሲያወግዝ ወይም ታሪካችንን አፋልሷል ሲል አልተሰማም። ስለዚህ የክብረ ነገሥትን
ውሸታምነት አጽድቆታል ወይም የማኅበረ ቅዱሳንን የትርጉም አተራረክ ለመከላከል አቅም አጥቷል። ከዚህ አንጻር ስለታቦተ ጽዮን አመጣጥ
የሚናገር የተለያየ ሃሳብ በቤተክርስቲያኗ ውስጥ ስላለ እውነተኛው የትኛው እንደሆነ ለጊዜው አይታወቅም ማለት ነው።
- 1,2/ ታቦተ ጽዮን ወደኢትዮጵያ አልመጣችም በማለት መጽሐፈ እዝራ ካልዕ ይናገራል።
ከላይ እንዳስቀመጥነው ማኅበረ ቅዱሳን ክብረ ነገሥትን
ውሸታም በማለት በግብጽ በረሃ አድርጋ ነው ታቦተ ጽዮን የመጣችው የሚለውን የግራሃም ሃንኰክን መጽሐፍ ለተከታዮቹ ሲያከፋፍል የምንረዳው
ሁለት የተለያየ የአመጣጥ ትረካ መኖሩን ነበር። ይሁን እንጂ ሰማንያ አሀዱ በተባለው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በመጽሐፈ እዝራ ካልዕ
ምዕራፍ 1 ቁጥር 54 ላይ እንዲህ በማለት ከላይ የቀረቡትን ሃሳቦች ሁሉ ውድቅ በማድረግ ታቦተ ጽዮን ወደኢትዮጵያ እንደመጣች ሳይሆን
ወደባቢሎን መሄዷን በግልጽ ይናገራል።
«እግዚአብሔርን የሚያገለግሉበትን ንዋየ ቅድሳቱንና
ጥቃቅኑንና ታላላቁን ዕቃ ሁሉ የእግዚአብሔር ማደሪያ ታቦትንም፤ ከቤተመንግሥት ዕቃ ቤት ያለውን ሣጥኑንም ሁሉ ማርከው ወደ ባቢሎን
ወሰዱ» እዝራ ካልዕ 1፤54
ናቡከደነጾር ከ634-562 ዓ/ዓ የነበረ የባቢሎን
ንጉሥ ሲሆን እርስ በእርሳቸው ያልተስማሙት የክብረ ነገሥትና የታቦተ ጽዮንን ፍለጋ መጻሕፍት ትረካ ውድቅ በማድረግ ወደ ባቢሎን
ማርኰ ስለመውሰዱ ሰማንያ ወአሀዱ የተባለው መጽሐፍ ቅዱስ አፖክሪፋ መናገሩ ነገሩን ሁሉ መያዣ መጨበጪያ የሌለው አድርጎታል። አሁን
እንግዲህ ሊነሳ የተገባው ጥያቄ፤
- · ክብረ ነገሥት የተባለው መጽሐፍ ነው ትክክል?
- · ታቦተ ጽዮንን ፍለጋ የተባለው መጽሐፍ ትረካ ነው ትክክል? ወይስ
- · የለም! ሁለቱም የሚሉት ትክክል አይደለም፤ ታቦቱ ወደባቢሎን በምርኰ ተወስዷል የሚለው የመጽሐፈ እዝራ ካልዕ ቃል ነው ትክክል?