Saturday, July 28, 2012

የሃይማኖታችን ሊቀ ካህናት


የጽሁፉ ባለቤት ገ/እግዚአብሔር ኪደ ይባላል። በአፍቃሬ ማኅበረ ቅዱሳን ብሎጎች ላይ ጽሁፉን በማቅረብ ይታወቃል። በፌስ ቡክ ገጹ ከሰጠን መረጃ ተነስተን ብሎጉ ላይ ካሰፈራቸው ጽሁፎች ውስጥ ይህንን ጽሁፉን መርጠነዋል። ጽሁፉ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ያለው፤ በቀደምት አበው አስተምህሮ ላይ የቆመ፤ በዘመናችን ውስጥ የሚታዩትን ብዙ የመዳኛ መንገዶች ውድቅ ያደረገ፤ የኢየሱስ ሊቀ ካህንነት በሌሎች ድካም በሚያሸንፋቸው ያልተተካ መሆኑን፤ ማዳኑ ፍጹምና ወደእሱ ለሚመጡት ሁሉ እስከ ዓለም ፍጻሜ እንደሚሰራ፤ በመሃላ የተሾመው ሊቀ ካህን «እኔ የበጎች በር (ደጅ) ነኝ» ይላልና ወደዚህ በር እንግባ እያለ ይነግረናል። ከዚህ እውነተኛው በር ውጪ ሌላ በር የለም።  ወደዚህ በር መሿለኪያ ወይም ውስጥ ለውስጥ መንገድ የለም። በመሃላ የተሾመ ሌላ ሊቀ ካህን የለም። «አንኳኩ ይከፈትላችኋል» ወዳለው የሕይወት ቃል እንድንቀርብ የሚናገረውን ይህንን ጽሁፍ መርጠነዋልና ካካፈለን ነገር እኛም አካፍለናችኋል።

    በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

 በክፍል ሁለት ትምህርታችን ሊቀ ካህናችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ እግዚአብሔር ሥርዓት ከሰዎች ተመርጠው ከሚሾሙት የብሉይ ኪዳን ሊቀ ካህናት ፍጹም የሚለይባቸውን ነጥቦች ማሳየት ጀምረን ነበር፡፡ የሚምር ነው፤ የታመነ ነው፤ በሰማያት ያለፈ ነው፤ በድካማችን የሚራራልን ነው ብለን አራት ነጥቦችን አይተናል፡፡ ለዛሬም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ካቆምንበት እንቀጥላለን፡፡ ቢችሉ አስቀድመው ይጸልዩ!

1. በመሐላ የተሾመ ሊቀ ካህናት ነው፡፡ 

 መሐላ የማይለወጥ ነገርን ያመለክታል፡፡ አንድ ሰው ይህን አላደርግም እንዲህም አላደርግም ብሎ ከማለ የነገሩን ሓቅነት ያመለክታል፡፡ሰዎች ከእነርሱ በሚበልጠው (ሎሌ በጌታው፣ ገረድ በእመቤቷ፣ ደቀ መዝሙር በመምህሩ፣ ልጅ በአባቱ) ይምላሉና ለማስረዳትም የሆነው መሓላ የሙግት (የክርክር የጸብ) ሁሉ ፍጻሜ ይሆናል፤ ስለዚህም እግዚአብሔር የተስፋውን ቃል ለሚወርሱ ፈቃዱ እንደማይለወጥ አብልጦ (አብዝቶ) ሊያሳያቸው ስለ ፈቀደ እግዚአብሔር ሊዋሽ (ሊፈርስ፣ ሊታበል) በማይቻል በሁለት  በማይለወጥ ነገር በፊታችን ያለውን ተስፋ ለመያዝ ለሸሸን ለእኛ ብርቱ መጽናናት ይሆንልን ዘንድ በመሐላ (በሥጋዌው) በመካከል ገባ፤ ይህም ተስፋ እንደ ነፍስ መልሕቅ አለን (ተስፋችንን አጽንተን ለያዝን ለእኛ ልቡናችን እንዳይነዋወጥ እንደ ወደብ የሚያጸናን ፍጹም ደስታ አለን) እርሱም እርግጥና ጽኑ የሆነ ወደ መጋረጃውም ውስጥ የገባ (እንደ መልከ ጼዴቅ ባለ ሹመት ተሹሞ ወደ ውሳጤ መንጦላዕት የገባ የዘላለም አስታራቅያችን ፊተውራርያችን ኢየሱስ ክርስቶስ) ነውእንዲል /ዕብ.616-19/፡፡ እንግዲያውስ ከሌዋውያን ክህነት በሚበልጥ ክህነት፣ እንደ መልከ ጼዴቅ ክህነት ዘላለማዊ በሆነ ክህነት የተሾመ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ የዘመነ ብሉይ ሊቃነ ካህናት ምንም እንኳን በእግዚአብሔር ጥሪ የተመረጡ ቢሆኑም አገልግሎታቸው ጊዜአዊ ስለ ነበረ ያለ መሓላ የተሾሙ ነበሩና፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከኦሪት ለምትበልጥ ለወንጌል መምህር ለመንግሥተ ሰማይም አስታራቂ ሆኖአልና በመሓላ የተሾመ ዘላለማዊ ሊቀ ካህናት ነው፡፡ ሐዋርያውም ስለዚሁ ሲናገር እንዲህ አለ፡- “እነርሱም ያለ መሓላ ካህናት ሆነዋልና፤ እርሱ ግን፡- ጌታ፡- አንተ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ ብሎ ማለ አይጸጸትም ብሎ በተናገረለት ከመሓላ ጋር ካህን ሆኖአልና ያለ መሓላ ካህን እንዳልሆነ መጠን እንዲሁ ኢየሱስ ለሚሻል ኪዳን ዋስ ሆኖአል” /ዕብ.720-22/፡፡ በዚህም ኦሪት ሥርየተ ኃጢአትን ማሰጠት ስላልቻለች እንደተሻረች ወንጌል ግን ማዳን ስለቻለች፣ ሥርየተ ኃጢአትን ማሰጠት ስለቻለች ሕልፈት ሽረት እንደሌለባት አወቅን፤ ተረዳን፡፡ ካህኑም አገልግሎቱም እንደዚሁ፡፡ ለምን ቢሉ ያለ መሓላ ከተሾሙት የብሉይ ኪዳን ሊቃነ ካህናት ይልቅ በመሓላ የተሾመ ሊቀ ካህናት ወልደ አብ ወልደ ማርያም ኢየሱስ ይበልጣልና፡፡  

Thursday, July 26, 2012

የግንቦቱ ሲኖዶስ ካወገዛቸው ግለሰቦች መካከል ሦስቱ ውግዘቱን በመቃወም ጠቅላይ ቤተክህነቱን ይግባኝ ጠየቁ

ክፍል 2

የዲያቆን አግዛቸው ተፈራ አቤቱታ
ምንጭ፤ አባ ሰላማ ድረ ገጽ

ህልውናውንና የሚመራውን መንፈስ ቅዱስን ወደጎን ትቶ ለማኅበረ ቅዱሳን በማደር በህሊና፣ በታሪክና በእግዚአብሔር ፊት አሳፋሪ ስህተት የፈጸመው የግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ እፎይ ብዬ ተቀመጥኩ ለማለት ቢሞክርም፣ እፎይ የማያሰኙ አቤቱታዎች እየቀረቡበት መሆኑን ከዚህ ቀደም ገልጸናል፡፡ እስካሁን ድረስ ባለን መረጃ ዲያቆን አሸናፊ፣ ዲያቆን አግዛቸው እና መምህር ጽጌ አቤት ያሉ ሲሆን፣ አቤቱታቸውን ሰምቶ ችግራችሁ ምንድን ነው ብሎ ሊያነጋግራቸው የቻለ አካል ይኑር አይኑር እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ ባለፈው ጊዜ የዲ/ አሸናፊን አቤቱታ አቅርበንላችሁ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ የዲ/ አግዛቸውን አቤቱታ እናቀርባለን፡፡ ሙሉውን የዲያቆን አግዛቸውን ደብዳቤ ከዚህ ጽሑፍ በታች ያገኙታል . . .
/ አግዛቸው ተፈራ እስካሁን ድረስ 4 መጻህፍትን የጻፈ ሲሆን፣ እነርሱም፦ የተቀበረ መክሊት፣ ጥላና አካል፣ የለውጥ ያለህ!!! አልተሳሳትንምን? የተሰኙ ናቸው፡፡ የተቀበረ መክሊት የተሰኘው የመጀመሪያው መጽሐፍ ብዙዎችን ያነቃ ወደ እግዚአብሔር እውነት እንዲደርሱ የረዳ እና የተቀበረውን መክሊት ፍለጋ ተግተው እንዲቆፍሩ ያነሳሳ መጽሐፍ ነው፡፡ የተቀበረውን እውነት እውነቱን የሸፈነውን ሐሰትና ለስሕተት መግቢያ ከሆኑት በሮች ዋናውን የአተረጓጎም ችግር የሚያሳየው ይህ መጽሐፍ፣ አሁንም ድረስ በርካታ የአብነት ትምህርት መምህራንና ተማሪዎች፣ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችና ምዕመናን እንደ ጥሩ ምንጭ ኮለል ያለውን እውነት የሚቀዱበት መጽሐፍ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡
ጥላና አካል የተሰኘው ሁለተኛው መጽሐፍም ብሉይ ኪዳንንና ሐዲስ ኪዳንን በማነጻጸር በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እያታየ ያለውን ከፊል ኦሪታዊ ሥርአትን የሚገመግም፣ ብሉይ ኪዳን የአዲሱ ኪዳን ጥላና ምሳሌ እንደሆነና አማናዊውና አካሉ አዲስ ኪዳንም ለዚህ ዘመን ዋና ነገር መሆኑን የሚያብራራ መጽሐፍ ነው፡፡ ከብሉይ ኪዳን ዋና ዋና የሆኑ ነገሮችን ነቅሶ በማውጣት በሐዲስ ኪዳን ያላቸውን ትርጉም የሚያብራራ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሚታዩ አንዳንድ የብሉይ ኪዳንን ስም የያዙ ንዋያተ ቅድሳትና ልምምዶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆናቸውን ያሳያል፡፡ በአሁኑ ሰዓት መጽሐፉ በገበያ ላይ የሌለ ሲሆን ብዙዎች እየፈለጉት እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዲያቆኑ ከጻፋቸው መጻሕፍት ሁሉ በገጽ ብዛት ከፍተኛውን ደረጃ የያዘው የለውጥ ያለህ!!! የተባለው መጽሀፉ አሁንም በገበያ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ እንደእነዚህ ላሉት መጻሕፍት የማስታወቂያ ሰራተኛ ሆኖ እያገለገለ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን፣ ባለፈው አመት የግንዛቤ ማስጨበጫ በሚል በከፈተው ዘመቻ መጽሐፉን በቪዲዮ እያሳየ እንዳታነቡ የሚል መልዕክት ካስተላለፈ ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ እየተሸጠ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አያ ዘባርቄ ምሕረተ አብ እውነትን በማዛባት በታቦት ላይ «አልተሳሳትንም» በሚል ርእስ የሰጠው ትምህርት «አልተሳሳትንምንየሚል መጽሐፍን ወልዷል፡፡ መጽሐፉ / አግዛቸው ስለ ታቦት ምሕረተ አብ በደመ ነፍስ ለገበያ በሚስማማ መልኩ እንደቸረቸረው ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውንና በታሪክ የተመዘገበውን እውነት ያብራራበትና የምህረተ አብን ውትፍትፍስብከትምበድንቅ ብዕር የተቸበት መጽሐፍ ነው፡፡ በምሕረተ አብ ደንባራ በቅሎ ተጭነው ሲጓዙ የነበሩና የሌሎች ምዕመናንን ጥያቄ የመለሰ መጽሐፍ መሆኑን ያነበቡ ሁሉ የሚመሰክሩት እውነት ነው፡፡ ጥላና አካል እና አልተሳሳትንምን? የተሰኙት መጻሕፍት ከገበያ ፈጽሞ የጠፉ ሲሆን ፈላጊያቸው ብዙ ሰው ሆኖ ሳለ ደራሲው ለምን መልሶ እንደማያሳትማቸው ጥያቄ ሆኖብናልና በማሳተሙ ላይ ቢያስብብበት ጠቃሚ ነው እንላለን፡፡
እነዚህን መጻሕፍት የጻፈውና ተጠርቶ ሳይጠየቅ የተወገዘው / አግዛቸው የተላለፈበትን ውግዘት በመቃወም ለጠቅላይ ቤተ ክህነት አቤት ያለ ሲሆን፣ የጻፈው ደብዳቤ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ያለውን «ህጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” (ዮሐ. 751)» የሚለውን ጥቅስ በማስቀደም ይጀምራል፡፡ በመቀጠልም በቤተክርስቲያን ያሳለፈውን ጊዜ በአጭሩ ያስቀኛል፡፡ ይህም ማኅበረ ቅዱሳን እስካሁን ድረስ ስለእርሱ ጭሮ ጭሮ ሊያገኝ ያልቻለውንና እያዛባ ያቀረበውን አስተካክሎ ያቀረበ ነው፡፡

ማህበረ ቅዱሳን እና የወደፊት እቅዱ!

ሐምሌ 19 2004 .. ዐውደ ምሕረት/www.awdemihret.blogspot.com) (ይህን ጽሁፍ ያገኘነው ፌስቡክ ላይ ነው። ጸሀፊው ራሱንማህበሩ ውስጥ ሆነን የማህበሩን አደጋ ገልጠን የጠቆምን የቁርጥ ቀን የቤተክርስቲያን ልጆችሲል ይገልጻል። ጸሃፊው አለኝ በሚላቸው መረጃዎች መሰረት ጽሁፉን አዘጋጅቷል። የማኅበሩን የኑፋቄ ትምህርት ጨምሮ ጊዜ የምጠብቅላቸው ሌሎች መረጃዎች አሉኝ የሚለው ጸሐፊ እንደ ውስጥ አዋቂ የማኅበሩ እቅዶች እነዚህ ናቸው ሲል ይነግረናል። እንደ ጸሐፊው እምነት ማኅበሩ ከቤተክርስቲያን ተገንጥሎ እስከ መውጣት የጨከነራዕይያለው ነው። ለዚህም የሚረዳውን ጥናት የጨረሰ ሲሆን ተጨማሪ ጥናቶችን ለማድረግ ግብጽ ድረስ ሰው ልኳል ይለናል። በብሎጋችን እንዲወጡላችሁ የምትፈልጉዋቸው ጽሁፎች ካሉዋችሁ awdemihret@live.com ብላችሁ ብትልኩልን ይደርሰናል።  መልካም ንባብ)

ማህበረ ቅዱሳን ሁለት አይነት እቅድ አለው። አንደኛው ቤተክርስቲያኒቱን መቆጣጠር ሲሆን አሱ ካልተሳካ ደግሞ ሁለተኛውን ማለትም ሂደቶችን አይቶ በቂ የሚለውን አቅም ከገነባ በኃላ ወደፊት ተገንጥሎ የመውጣት ድብቅ ራዕይ አለው፡፡ ሁለተኛው አላማውም በቤተክርስቲያን ላይ አደጋ ለመፍጠርና አባላቱን ይዞ የራሱን ቤተ እምነት መመስረት ሲሆን ጉዞውን 40 በመቶ አድርሷል፡፡ ይህን እቅዱን ለማሳካት የተጠና እስትራቴጂ አዘጋጅቶ ተግባር ላይ አውሏል፡፡

 ከእቅዶቹ ዋና ዋናዎቹ እንደሚከተሉት ይቀርባሉ
1- ወደፊት ማህበሩ ቤተክርሰቲያኒቱን ከተቆጣጣረ ወይም ደግሞ ከተገነጠለ የራሱ አገልጋዮችን ብቻ መጠቀም ስለሚፈልግ ለሚገነጥለው ቤተ እምነት አገልጋይ እንዲሆኑ ካህናትንና መነኮሳትን በገዳማትና በአብነት /ቤቶች በጥንቃቄ ማሰልጠን እንዲቻል ከፍተኛ በጀት መድቧል፡፡ ይህን ስውር ተልእኮ ሊቃነ ጳጳሳቱ ነቅተው እንዳያስቆሙት በዘዴና በጥንቃቄ መያዝ
2- ጵጵስና ለቀሳውስት እንዲሰጥ በቅ/ሲኖዶስ ግፊት እንዲያደርጉ የማህበሩ አባላት የሆኑ ጥቂት ጳጳሳትን ማሳመን በዚህ ጉዳይ ጥናት እንዲሰሩ ስንታየሁ የተባሉ አንድ ቄስ ግብጽ ሃገር ተልከዋል፡፡
3- በቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ የማህበሩን አላማ በስውር የሚያስፈጽሙ ጳጳሳት እንዲሾሙ ማህበሩ መነኮሳትን መልምሎ በምርጫው ግዜ አባቶች ድምጽ እንዲሰጣቸው በየቤታቸው እየዞሩ የማግባባት ስራ መስራት፡፡ ማግባባቱ ለሃገረስብከታቸው እስከ ሁለት መቶ ብር በጀት ድጎማ ማድረግን፣ በግል እጅ መንሻ ማዘጋጀትን በአንዳንድ በልማት እቅዶቻቸው ውስጥ የማማከር ድጋፍ ማድረግን ይጨምራል፡፡ ለቤተክርስቲያን ቢጠቅሙም ለማህበሩ አካሄድ ግን አደገኛ ናቸው ያሏቸው አባቶች እንዳይሾሙ አባላት በሆኑ ጥቂት አባቶች በኩል መታገልና በቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ወቅት በእያንዳንዱ ሊቃነ ጳጳሳት ማረፊያ ተሰሚ የሆኑ አባላትንና አንዳንድ ባለጸጎችን በመላክ የማሳመን ስራን መስራት፡፡ እንቢ ያሉትን ማስፈራራት
4- የማህበሩን አካሄድ ትክክል አይደለም መታየት አለበት የሚሉ ጳጳሳትን ሰባኪያንን የአስተዳደር ሰዎችንና የመንግስት አካላትን ህዝቡ እንዲጠላቸው መናፍቃን ሆነዋል ተወግዘዋል ሌላ ተልእኮ አላቸው ወዘተ የመሳሰሉትን ቀለሞች በመቀባት ሃይላቸውን ለማድክም መሞከር፡፡ ይህን በአሜሪካና በአውሮጳ በገንዘብ የሚደግፍ ኮሚቴ በነያሬድ /መድህን በነዳንኤል ክብረት በነህብረት የሺጥላ በነፋንቱ ወልዴ በነዶ/ መስፍን የተቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው የማህሩን የጥፋት አላማ የሚያደናቅፉትን ሁሉ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድባቸው በፋይናንስ መደጎም ሲሆን በስውር ሲዲ እያዘጋጁ መበተን፣ ስብሰባ እያዘጋጁ ባለጠጎችን ቤተክርስቲያን ልትፈርስ ስለሆነ እንድረስላት ገንዘባችሁን ስጡን በማለት የማህበሩን አቅም ማደራጀት፣
5- ለጥምቀት ምንጣፍ የሚያነጥፉ የዋህ ወጣቶችን ቀስ ብሎ ወደ ማህበሩ በማስገባት ቤተክርስቲያን አደጋ ላይ ነች ድረሱላት በማለት የአመጽ ትምህርታቸውን አስተምሮ ወደ ነውጥ እንቅስቃሴ እንዲገቡ በማድረግ ተጨማሪ ሃይል እንዲሆኑ ማሰልጠን፣
6- በአዲስ አበባ እና በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ የሰንበት /ቤቶች ሰርጎ መግባትና የማህበሩን መሰረት ማስፋት ካልተቻለ በየአጥቢአው ቢሮ በመክፈት ሰንበት ትምህርት ቤቶችን መበጥበጥ እና ማፈራረስ
7- በመንግስት ፖለቲካ ውስጥ የሚደረገውን ጣልቃ ገብነት በተጠና ሁኔታ ማጠናከር ይህም በሃገር ውስጥ ያሉ አባላት መንግስት እንዳይመታቸው የቤተክርስቲያኑን ጉዳይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ በውጭ ያሉት ግን የተለያዩ ሚዲያዎችን እየተጠቀሙ መንግስትን እንዲቃወሙ ተደርጎ እስትራቴጂው ተቀርጿል፡፡ ደጀ ሰላም፣ አንድ አድርገን፣ደቂቀ ናቡቴ፣ savewaldeba, ecadforum … የተባሉትን ድረ ገጾች በመጠቀም ጸረ ሰላም ቅስቀሳዎችን ማጠናከር ፡፡
8- ማህበረ ቅዱሳንን ራሱን ችሎ እንዲወጣ የገንዘብ አቅሙን ቋሚ በሆነ ሁኔታ ማጠናከር ይህም የማህበሩን ህንጻ መገንባት፣የቤተክርስቲያን ልጆች በተለይ መንግስት ሰራተኞች ለቤተክርስቲያናቸው ሳይሆን ለማህበሩ አስራት አንዲከፍሉ ማድረግ፣ በተለያዩ ቦታዎች የንግድ ተቋማትን መመስረት፣ አንድ ባንክ በአባላቱ አክስዮን (እንቅስቃሴው ተጀምሯል።) መክፈት ወዘተ
9- በቤተክርስቲያን መድረኮችና በግል ሚዲያዎች ላይ የህዝብን ሰላም የሚያውክ የጽንፈኝነት ቅስቀሳ ማጠናከር፡፡ ይህን እንዲመሩ የተወሰኑ መምህራንን መድቦ ጽንፈኝነትን በሃይማኖት ቤተሰቦች ላይ ሽብርን እና ቅራኔን በሃማኖቶች መካከል የማስፋት ስራን አጠናክሮ መቀጠል፣ እንዲሁም በአንዳንድ የአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ፣ ባህር ዳር፣ መቀሌ፣ ጎንደር፣ አርባ ምንጭ፣ደሴ፣ በአውሮፓ አሜሪካ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ባሉ ትላልቅ አብያተክርስቲያናት ያሉ መምህራንን በጥቅም በመደለል በቤተክርስቲያን መድረክ ማህበሩን ማስተዋወቅ ችግር ተፈጥሯል፣ ቤተክርስቲያን መሪ የላትም ሲኖዶሱ የሞተ ነው መንግስት ቤተክርስቲያንን እየገደለ ነው እያሉ ሁከት በመፍጠር ህዝቡ እንዲታወክ ቤተክቲያንን እንዲሰለችና እረኞቹን ከበጎቹ ነጥለው ወደ አዲሱ ቤተእምነታቸው እንዲቀላቀሉ መሳብ

10- ቤተክርስቲያን በራሷ እንዳትተማመን በስነ ልቦና ጦርነት ማሽመድመድ ይህም ጠንከረው የሚሰሩ ሰባኪዎቿንና ሰራተኞቿን በሃይማኖት ስም ከስሶ በማዳከም ፈሪ እንድትሆን ማድረግ ዝም ማሰኘት፡፡ ልጆቿን በየአሉበት ፈልጋ እንዳታስተምር ባገኘችው አጋጣሚ ሁሉ ሰብካ ወደ በረቷ መስብሰብ እንዳትችልማከላከል የንስሃ አባቶች እንኳ ልጆቻቸውን በየቤታው ሄደው እንዳያስተምሩ፣ በቤተክርስቲያን ግቢ የሚደረጉ ጉባኤዎችን የመናፍቃን እጅ አሉባቸውና ምእመናን እንዳይሄዱ ቅስቀሳ ማድረግ፣ማህበረ ቅዱሳን ከጠራው ጉባኤ ውጭ ሌሎቹ የተሳሳቱ አድርጎ ማቅረብ፣ መዝሙር እንዳይዘመር፣ ሰባኪዎችን ሁሉ ሰው እንዲፈራቸው፣ ከፍተኛ ቅስቀሳ በማድረግ ቤተክርስቲያን ዝም እንድትል እና ሌሎች እንዲቀድሟት ለማድረግ አባቶችንም ስርአት ተጣሰ ህግ ፈረሰ ብለው በማደናገር ለክፉ ተልኮአቸው ተባባሪ እንዲሆኑ ማድረግ።