ክፍል
2
የዲያቆን
አግዛቸው ተፈራ አቤቱታ
ምንጭ፤ አባ ሰላማ ድረ ገጽ
ምንጭ፤ አባ ሰላማ ድረ ገጽ
ህልውናውንና
የሚመራውን መንፈስ ቅዱስን ወደጎን ትቶ ለማኅበረ ቅዱሳን በማደር በህሊና፣ በታሪክና በእግዚአብሔር ፊት አሳፋሪ ስህተት የፈጸመው የግንቦቱ ሲኖዶስ ስብሰባ እፎይ ብዬ ተቀመጥኩ ለማለት ቢሞክርም፣ እፎይ የማያሰኙ አቤቱታዎች እየቀረቡበት መሆኑን ከዚህ ቀደም ገልጸናል፡፡ እስካሁን ድረስ ባለን መረጃ ዲያቆን አሸናፊ፣ ዲያቆን አግዛቸው እና መምህር ጽጌ አቤት ያሉ ሲሆን፣ አቤቱታቸውን ሰምቶ ችግራችሁ ምንድን ነው ብሎ ሊያነጋግራቸው የቻለ አካል ይኑር አይኑር እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡ ባለፈው ጊዜ የዲ/ን አሸናፊን አቤቱታ አቅርበንላችሁ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ የዲ/ን አግዛቸውን አቤቱታ እናቀርባለን፡፡ ሙሉውን የዲያቆን አግዛቸውን ደብዳቤ ከዚህ ጽሑፍ በታች ያገኙታል . . .
ዲ/ን አግዛቸው ተፈራ እስካሁን ድረስ 4 መጻህፍትን የጻፈ ሲሆን፣ እነርሱም፦ የተቀበረ መክሊት፣ ጥላና አካል፣ የለውጥ ያለህ!!! አልተሳሳትንምን? የተሰኙ ናቸው፡፡ የተቀበረ መክሊት የተሰኘው የመጀመሪያው መጽሐፍ ብዙዎችን ያነቃ ወደ እግዚአብሔር እውነት እንዲደርሱ የረዳ እና የተቀበረውን መክሊት ፍለጋ ተግተው እንዲቆፍሩ ያነሳሳ መጽሐፍ ነው፡፡ የተቀበረውን እውነት እውነቱን የሸፈነውን ሐሰትና ለስሕተት መግቢያ ከሆኑት በሮች ዋናውን የአተረጓጎም ችግር የሚያሳየው ይህ መጽሐፍ፣ አሁንም ድረስ በርካታ የአብነት ትምህርት መምህራንና ተማሪዎች፣ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችና ምዕመናን እንደ ጥሩ ምንጭ ኮለል ያለውን እውነት የሚቀዱበት መጽሐፍ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል፡፡
ጥላና
አካል የተሰኘው ሁለተኛው መጽሐፍም ብሉይ ኪዳንንና ሐዲስ ኪዳንን በማነጻጸር በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እያታየ ያለውን ከፊል ኦሪታዊ ሥርአትን የሚገመግም፣ ብሉይ ኪዳን የአዲሱ ኪዳን ጥላና ምሳሌ እንደሆነና አማናዊውና አካሉ አዲስ ኪዳንም ለዚህ ዘመን ዋና ነገር መሆኑን የሚያብራራ መጽሐፍ ነው፡፡ ከብሉይ ኪዳን ዋና ዋና የሆኑ ነገሮችን ነቅሶ በማውጣት በሐዲስ ኪዳን ያላቸውን ትርጉም የሚያብራራ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሚታዩ አንዳንድ የብሉይ ኪዳንን ስም የያዙ ንዋያተ ቅድሳትና ልምምዶች መጽሐፍ ቅዱሳዊ አለመሆናቸውን ያሳያል፡፡ በአሁኑ ሰዓት መጽሐፉ በገበያ ላይ የሌለ ሲሆን ብዙዎች እየፈለጉት እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዲያቆኑ
ከጻፋቸው መጻሕፍት ሁሉ በገጽ ብዛት ከፍተኛውን ደረጃ የያዘው የለውጥ ያለህ!!! የተባለው መጽሀፉ አሁንም በገበያ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ እንደእነዚህ ላሉት መጻሕፍት የማስታወቂያ ሰራተኛ ሆኖ እያገለገለ ያለው ማኅበረ ቅዱሳን፣ ባለፈው አመት የግንዛቤ ማስጨበጫ በሚል በከፈተው ዘመቻ መጽሐፉን በቪዲዮ እያሳየ እንዳታነቡ የሚል መልዕክት ካስተላለፈ ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ እየተሸጠ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡
አያ
ዘባርቄ ምሕረተ አብ እውነትን በማዛባት በታቦት ላይ «አልተሳሳትንም» በሚል ርእስ የሰጠው ትምህርት «አልተሳሳትንምን?» የሚል መጽሐፍን ወልዷል፡፡ መጽሐፉ ዲ/ን አግዛቸው ስለ ታቦት ምሕረተ አብ በደመ ነፍስ ለገበያ በሚስማማ መልኩ እንደቸረቸረው ሳይሆን መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውንና በታሪክ የተመዘገበውን እውነት ያብራራበትና የምህረተ አብን ውትፍትፍ “ስብከትም” በድንቅ ብዕር የተቸበት መጽሐፍ ነው፡፡ በምሕረተ አብ ደንባራ በቅሎ ተጭነው ሲጓዙ የነበሩና የሌሎች ምዕመናንን ጥያቄ የመለሰ መጽሐፍ መሆኑን ያነበቡ ሁሉ የሚመሰክሩት እውነት ነው፡፡ ጥላና አካል እና አልተሳሳትንምን? የተሰኙት መጻሕፍት ከገበያ ፈጽሞ የጠፉ ሲሆን ፈላጊያቸው ብዙ ሰው ሆኖ ሳለ ደራሲው ለምን መልሶ እንደማያሳትማቸው ጥያቄ ሆኖብናልና በማሳተሙ ላይ ቢያስብብበት ጠቃሚ ነው እንላለን፡፡
እነዚህን
መጻሕፍት የጻፈውና ተጠርቶ ሳይጠየቅ የተወገዘው ዲ/ን አግዛቸው የተላለፈበትን ውግዘት በመቃወም ለጠቅላይ ቤተ ክህነት አቤት ያለ ሲሆን፣ የጻፈው ደብዳቤ በዮሐንስ ወንጌል ላይ ያለውን «ህጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” (ዮሐ. 7፡51)» የሚለውን ጥቅስ በማስቀደም ይጀምራል፡፡ በመቀጠልም በቤተክርስቲያን ያሳለፈውን ጊዜ በአጭሩ ያስቀኛል፡፡ ይህም ማኅበረ ቅዱሳን እስካሁን ድረስ ስለእርሱ ጭሮ ጭሮ ሊያገኝ ያልቻለውንና እያዛባ ያቀረበውን አስተካክሎ ያቀረበ ነው፡፡