ምንጭ፤ ዓውደ ምሕረት
በከላይነው ትዕዛዙ
ሰሞኑን
ጉባኤ አርድዕት የሚባል ማኅበር ተቋቋመ ከሚለው ዜና ከተሰማ ጀምሮ ማኅበሯ ከፍተኛ ስጋት ላይ ወድቃለች። ከዚህም የተነሳ ይህን ማኅበር አቋቁመዋል እና የማህበሩ ደጋፊ የመሆን ዕድል አላቸው የሚሉትን ሰው ሁሉ ከጠቅላይ ቤተክህነት የስልጣን መዋቅር ለማንሳት ቆርጠው ተነስዋል።
ለዚህም
የተከተሉት እስትራቴጂ ለማኅበሯ ድጋፍ የሚሰጡ የቤተክህነት ሰራተኞችን ተጠቅሞ ዝውውር ማድረግና ሊፈጠር ይችላል ብለው የሚጠረጥሩትን አንድነት ማላላት ነው። ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ የማኅበሩ ሰዎች በአሁኑ ሰዓት ብዙ ጊዜያቶችን የሚያጠፉት በእስክንድር ገብረክርስቶስና የጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ በሆነው በአቶ ተስፋዬ ውብሸት ቢሮ ውስጥ እንደሆነ የቤተክህነት ምንጮች ይገልጻሉ፡፡ ተስፋዬ ጠንቃቃና ከማኅበሩ ጋር ያለው ግንኙነት እንዲታወቅበት የማይፈልግ ሰው ሲሆን አስክንድር ግን ባለው ከፍተኛ የንዋይ ፍቅር ለማኅበሩ ያለ ይሉኝታ ሙሉ በሙሉ መገዛት የጀመረ ሰው ነው።
ማኅበሩ
ከመታው ድንጋጤ ለመረጋጋትና ከገባበትም ማጥ ለመውጣት የተለያዩ ሥልቶችን እያውጠነጠነ ቢሆንም
ብዙዎቹ ዘዴዎቹ ፈር ሊይዙለት አልቻለም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በጠቅላይ ቤተክህነት እየታየ ያለውን ነገር ስንመለከት ማኅበሯ ከከበባት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ነጻ ለመውጣት ካሳባቸው አማራጮች አንዱ መሆኑን እንረዳለን። ጤናማ አእምሮ ሊያስብ የሚገባውን ነገር ከማሰብ ይልቅ የተለያዩ ተንኮሎችንን የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን በሽብር ብሎጎቹ እየከፈተ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን ገና ለገና ጠንካራ ማኅበር ተቋቁሞ ቤተክርስቲያኒቱን ለብቻችን የማስተዳደር ፍላጎታችንን ይጋፋብናል። እየተቆጣጠርነው የመጣነውን የቤተክሀነቱን አስተዳደር ከቁጥትራችን ውጭ ያደርግብናል። በሚል ከወዲሁ በጉባኤ አርድዕትና በመስራች አባላቱ ላይ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፍቷል።
ከማኅበረ
ቅዱሳን ወጥተው ቤተክርስቲያን በሰጠቻቸው የስራ ኃላፊነት በቅንነት እያገለገሉ ያሉትን እነ ሊቀስዩማን ኃይለጊዮርጊስና መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤልን የመሳሰሉ የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች ቀድሞ መጮህ በሚል መርህ አንዲህ እና እንዲያ ናቸው በማለት ስማቸውን በማጥፋት ላይ ይገኛል። ቤተክርስቲያኒቱ ባሏት ሶስት መንፈሳዊ ኮሌጆች ትምህርቱን በብቃት ተከታትሎ የእውቀት ገንቦ መሆኑን በተግባር ያስመሰከረው መምህር አእመረንም በስጋ እውቀት ከነሱ እንደማያንስ በመንፈሳዊ እውቀት ደግሞ ከእግሩ ጣት ጋር እንኳ መድረስ እንደማይችሉ እየገባቸውም ቢሆን በተለመደው እኔን ያልተቀበለ ሁሉ መናፍቅ ነው በሚል አሸባሪ መንፈሳቸው ተመርተው ስሙን ማብጠልጠል ይዘዋል። ቅዱስነታቸው አቡነ ጳውሎስን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅመው ስማቸውን ማብጠልጠልን ሥራዬ ብለው የያዙት የማኅበረ ቅዱሳን የሽምቅ ውጊያ ብሎጎች ገና ለገና ጉባኤ አርድዕት እንዲቋቋም ፈቅደዋል በማለት ስማቸውን በክፉ በማንሳትና ተግባራቸውን በማኮሰስ የተቀናጀ ዘመቻ መክፈታቸውም አስገርሞዋል። እንዲያውም የጊዜው ማስፈራሪያ እርስዎን አንስተን አባ ህዝቅኤልን እንሾማለን የሚል ሆኗል።
እንደተለመደው
በኃይለ ጊዮርጊስ ዳኜ እና በአቶ ማንያዘዋል አበበ አማካኝነት የሚመራ የስለላ ሥራዎች በቤተክህነት ውስጥ እያካሄደ ያለው ማቅ በአሁኑ ሰዓት ደግሞ አቶ ሰሎሞን ቶልቻ በሚባል ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ለአቶ እስክንድር ገ/ክርስቶስ 30 ሺህ ብር በመክፈል በንቡረዕድ አባ ገብረማረያም ምትክ የገዳማት መምሪያ ኃላፊ ሆኖ በቤተክህነት የስልጣን ተዋረድ ላይ አለሁ ያለውን ግለሰብ እየተጠቀሙበት ይገኛል፡፡ እንደሚታወቀው የገዳማትን ጉዳይ መያዝ ያለበት በገዳም ኑሮ በሚያውቁ መነኮሳት ነው። በዚህም መሰረት በመነኩሴ ሲመራ የቆየውን መምሪያ በአሁኑ ሰዓት የአጥቢያ ቤተክርስቲያን ሰባኪ ለሆነ
ግለሰብ ያለምንም ውድድር መሰጠቱ ሁሉም የጠቅላይ ቤተክህነት ሠራተኞች ያዘኑበት ጉዳይ ሆኗል፡፡
ለአቶ
ሰሎሞን ቶልቻ እዚህ መድረስ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገለት ያለው ግለሰብ በጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ ውስጥ ጓድ መንግስቱ ኃይለማርያም በመባል የሚታወቀው አቶ እስክንድር ገብረክርስቶስ ነው፡፡ አቶ እስክንድር ከ12ኛ ክፍል በላይ ምንም ዓይነት የትምህርት ማስረጃ የሌለው፣ የቤተክህነት ትምህርትም ሆነ ክህነት የሌለው፣ አዲስ አበባ ተወልዶ አዲስ አበባ ያደገ በቤተክህነቱ ቋንቋ ጨዋ የሚባል ሰው ከመሆኑም በላይ ምንም ዓይነት ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር የሌለውና የአባቶችን ክብር እጠብቃለሁ በማለት ሥራውን በገንዘብ የሚለውጥ፣ እና በፓለቲካው አለምም
በትግል ህይወት የኖርሁ ታጋይና የኢህአዲግ መስራች ነኝ ለማለት የሚቃጣው ሰው ነው፡፡
ይህ ሰው ከቀበሌ ሊቀመንበርነት በግምገማ ተባሮ መውጣቱን (በሙስና ቅሌትና አቅም ማነስ) ምንጮችቻችን ሲገልጡ ወደ ቤተክህነት በመምጣት ባለቤቴ ማኅሌት የቴሌቪዥን ዜና አንባቢ ስለሆነች እኔም ከእርሷ የሪፖርተርነት ሙያ ሰልጥኛለሁ ብሎ ከባለቤቱ ማህሌት በተሰጠው ሰርተፍኬት የዜና ቤተክርስቲያን ሪፖርተር ሁኖ ተቀጠረ፡፡ ይህ ግለሰብ በዜና ቤተክርስቲያን የሚወጡ ጽሑፎችን ለመጻፍ የሚያስችል ዕውቀት እንደሌለው ከሊቃውንቱ በተደጋጋሚ ተገልጾለት “…በተቻለ መጠን የቤተክህነቱም ይሁን የዘመናዊ ትምህርት ስለሌለህ ወደ ቀበሌህ ብትመለስ ያለበለዚያም እንደአቅምህ በሆነ ሥራ ተቀጥረህ ቤተክህነት ብትሰራ ተብሎ ይመከራል፡፡…” እስክንድርም ወደ ፓትርያርኩ በአቡነ ፊሊጶስ አማካኝነት ከቀረበ በኋላ “…ከመንግስት ጋር ባለኝ ግንኙነት የዋልድባን ጉዳይ(ገጽታ) እኔ አስተካክለዋለሁ። ስለዚህ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለጊዜውም እንኳን ብሆን..” ብሎ በአማላጅ ያግባባል፡፡ ቅዱስ ፓትርያርኩም ይህ መምሪያ ሙያ ስለሚጠይቅ የመምሪያ ኃላፊው አቶ ስታሊን (በጋዜጠኝነት ሙያ የማስተርስ ዲግሪ ያላቸው) ክትትልና ቁጥጥር ሳይለየው ተጠሪነቱ ለአቶ ስታሊን ሁኖ ለጊዜው ይመደብ ብለው ሲስማሙ በብፅዕ አቡነ ፊሊጶስ ፊርማ ተመደበ፡፡
አቶ
እስክንድር በዋልድባ ጉዳይ እንኳን ለህዝቡ ትክክለኛ መረጃ ሊሰጥ ቀርቶ በዋልድባ ምክንያት በማኅበሩና በቤተክህነት መካከል ትልቅ መቃቃር የፈጠረ ሥራ ሠርቶ በመመለሱ ምክንያት ማኅበረ ቅዱሳን ‹‹ሙያ አልባ የቤተክርስቲያን ባለሥልጣኖች›› በማለት በነአቶ እስክንድር ላይ አስገራሚ ጽሁፍ አስነበበን፡፡
እንግዲህ
ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በጊዜያዊነት የተሰጠውን የመምሪያ ኃላፊነት እንዳይነጠቅ ከፍተኛ ሩጫ ማድረግ የጀመረው፡፡ ሩጫው አቅጣጫ አልባ ቢመስልም ተንኮል ግን አላጣውም። ስለዚህ በቀጥተኛ መንገድ በችሎታው ስራውን መቀጠል ካልቻለ በማኅበሩ በኩል ሆና ስልጣኑ ላይ ለመቆየት የግድ ከማኅበሩ ጋር ተግባብቶ ለማኅበሩ ታዞ በዚህም ከማኅበሩ የሚገኘውን ጥቅማ ትቅም ተቋድሶ መኖርን መረጠ። በዚህም ምክንያት የተለያየ እኩይ ተግባራትን ማድረግ ቀጠለበት፡፡ ለምሳሌ፡-
1ኛ.
በጠቅላይ ቤተክህነት የሚገኙ ሊቃውንትን የተለያየ ስም በመሥጠት በጡረታና በዝውውር እንዲዛወሩ አቡነ ፊሊጶስንና አቶ ተስፋዬን (ም/ሥራ አስኪያጅ) በማግባባት በርካታ ሰዎች ተዛዋውዋል ወይም ጡረታ ወጥተዋል፡፡
2ኛ
ወደ ፓትርያርኩ እና ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት በመቅረብ ከፊታቸው የውሸት ስልክ በመነጋገር አሁን የደወለልኝ አቶ አባይ ፀኃዬ ነው፣ አቶ መረሳ ነው፣ አለቃ ፀጋዬ ነው፣ ዶ/ር ሸፈራው ነው በማለት በአባቶች ዋነኛ ታጋይ መስሎ በመታየት ስለኢህአዲግ አቅጣጫ በውሸት ለማስረዳት ይሞክራል፡፡ (ይህ ሰው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከማኅበሩ ጋር በመሠረተው ግንኙነት አማካኝነት 250,000 ብር ተቀብሎአል፡፡ ለወደፊት ከመረጃ
ጋር ይቀርባል፡፡) ለማኅበረ ቅዱሳን አመራሮችም መንግስት ምንም አያደርጋችሁም፣ ስለናንተ በሚገባ አስረድተነዋል፤ በማለት ቢናገርም በአሁኑ ሰዓት የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አቶ እስክንድር የሚባል ሰው እንደማያውቁ፣ በመንግስት ስም መነገድ እንደማይችል እና ክትትል እየተደረገበት እንደሆነ ለፓትርያርኩና ለአራት ሊቃነ ጳጳሳት እንደተገለጸላቸውም ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡
3ኛ.
የዜና ቤተክርስቲያን መምሪያ ኃላፊ እኔ ነኝ፣ አቡነ ጳውሎስ መጋቢ ሚስጢር ወልደሩፋኤልንና መ/ር ካህሳይ (የዜና ቤተክርስቲያን አዘጋጆች) ተቆጣጠር ብለውኛል፡፡ ከዚህ በኋላ ይህንን እድል በመጠቀም የማኅበሩን ገጽታ በዜና ቤተክርስቲን እናስተካክለዋለን እያለ ለማኅበሩ ሥራ አመራር ገልጿል፡፡ ከዚህም አልፎ እምቢ ቢል ግን ወልደሩፋኤልን እናባርረዋለን በማለት ከማኅበሩ ጋር እንደሚዶልት መረጃ ተገኝቷል፡፡ ይህንን በተመለከተም ስለአፈጻጸሙ ከሰሎሞን ቶልቻ ጋር ተነጋገሩበት እንዳላቸው ታውቋል፡፡
4ኛ. እንዲሁም በዋነኛነት
በአሁኑ ሰዓት ለማኅበሩ ህልውና አደጋ በመሆን ላይ ባለው በሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ አማካኝነት እየተሰሩ ባሉ ሥራዎች ማለትም ‹‹በሊቃውንቱ መካከል አንድነትን መፍጠር እንዲሁም በጳጳሳት መካከል ስለማኅበሩ በቂ ግንዛቤ እንዲኖር ማድረግ ›› የሚሉ ሥራዎች እንዳሉ የሚያውቀው የማኅበሯ አመራር የሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ አካሄድ የፈጠረበትን ሥጋት ለአቶ እስክንድር ያዋያል፡፡ አቶ እስክንድርም “…የኃይለጊዮርጊስንና የሊቃውንቱን እቅዶች አፈራርሳለሁ፡፡ እሱንም ከአባቶች ጋር እና ከሊቃውንቱ እንለያይዋለን ይህንን ደግሞ ከአቶ ተስፋዬ ውብሸት ጋር ተነጋግረናል…” በማለት ለማኅበሯ አመራሮች የማጽናኛ ቃል ከተናገረ በኋላ በማግስቱም፤
- ለፓትርያርኩና
ለተለያዩ ጳጳሳት እየዞረ “…ሊቀ ስዩማን ኃይለጊዮርጊስ ከመንግስት ጋር
ስር የሰደደ ግጭት ውስጥ ነው፣ መንግስት ይፈልገዋል፣ በዘረኝነት ከነአቡነ አብርሃም ጋር ይገናኛል፣ የማኅበሩ አመራርም ጓደኞቹ ናቸው በማለት ያሥወራል፡፡ አባቶችም አይ እስክንድር ይህ እኮ ‹‹የህዝብ ግንኙነት ሥራ ሳይሆን ህዝብ ማደናገር›› ነው በማለት ከመለሱለት በኋላ “…ሊቀሥዩማን በኛ በኩል ከ15 ዓመታት በላይ በተለያዩ ኃላፊነት አይተነዋል፣ ለኃይለጊዮርጊስ እንደ ሐዋርያት ዘር የለውም፣ ከማኅበሩ ጋርም ቢሆን ለ15 ዓመታት እንደታገለ ማኅበሩም በደጀሰላም ድህረ-ገጽ ገልጾታል፡፡