ምንጭ፤ዓውደ ምሕረት
ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው በሃይማኖት ስም የሚንቀሳቀሰው የፖለቲካ ድርጅት ዘርፈ ብዙ የአሰራር መንገዶች አሉት። አሰራሩ የማፊያነት ባሕርይ ስላለው የሚሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በተለያየ መንገድ እየከፋፈለ ያደርጋል። አላማውን የሚያስፈጽምበት እስከመሰለው ድረስ አዋጭ ብሎ የሚያምንበትን መንገድ ይጠቀማል። መንፈሳዊ ባሕርይ ስለሌለው ልምድን ከመንፈስ ቅዱስ፤ በጸሎት ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቶችን አሠርር እየገመገመ ይጠቅመኛል የሚለውን መንገዶች ሁሉ ይጠቀማል።
ለዛሬ ስለሦስቱ ሴሎቹ እና ስለሴል መሪዎቹ እናቀርባለን።
አሉላ ጥላሁን
አሉላ ዋነኛ ስራው ግልጹንም ስውሩንም ሚዲያ መቆጣጠርና መምራት ነው። ቱሪስት የነበረውን ቡድን ይመራል። ኤፍሬም እሸቴ የከፈታትን ደጀ ሰላምን ይመራል ይቆጣጠራል። ሪፖርተሮችዋን በደንብ ያንቀሳቅሳል። እነ ሱራፌልን፤ ጳውሎስ፤ መረዋን ሌሎችንም ይመራል። ለጥንቃቄ እንዲረዳ በእነርሱ ስር የሚንቀሳቀሱትን ሰዎች ደጀ ሰላም የማኅበረ ቅዱሳን አይደለችም ብለው እንዲያምኑ የሚያደርግ የተለያየ ዘዴዎችን ይፈጥራል። ያስጠናል። አንዳንዴም ማኅበረ ቅዱሳንን ሳይበዛ በልዝቡ ወረፍ ያደርጋል። ከዛም ዛሬስ እኛም አልቀረልንም ብለው እንዲያስወሩ ያደርጋል። በዚህም ተሳክቶለታል። አንዳንዶቹ ወሬ አቀባዮች ምለው ተገዝተው ደጀ ሰላም የማቅ አይደለም ብለው የሚያምኑ ናቸው። ሱራፌል ወደ አሜሪካ በሄደ ጊዜ እሱም ከማኅበሩ ዋና ጸሀፊ ከሙሉጌታ ጋር በመቃቃሩ ደጀ ሰላም ተቀዛቅዛ እንደነበር ይታወሳል።
ከምርጫ 97 በኋላ ቅንጅት ለምን ተቀባይነት አገኘ ብላ ማኅበሯ ጥናት ስታደርግ ተቀባይነት ያገኘበት መንገድ ጠንካራ መሪዎች ስላሉት ወይም የተሻለ የፖለቲካ መስመር አሊያም ልብ የሚያደርስ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስላለው ሳይሆን ጋዜጦችን በሙሉ ደጋፊ አድርጎ ማቆም በመቻሉ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመደረሱ ማኅበሯም ሀሳብዋን ወደ ህዝቡ ለማድረስ የግል ሚዲያዎችን ከማቋቋም ጀምሮ አባላትዋን በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ዐምደኛ በማድረግ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ይመራል፤ ይቆጣጠራል።
አዲስ ነገር በማኅበሩ ፈንድ አድራጊነት በማኅበሩ ሰዎች በነመስፍንና ዓቢይ ሲቋቋም እሱ ኮፒ ኢዲተር ዳንኤል ክብረት አምደኛ፤ ኤፍሬም ሪፖርተር ሆነው በአብዛኛው የማኅበሩ አባላት የሚገኙበትና እንቅስቃሴውን በሙላት የሚቆጣጠሩበት ጋዜጣ እንደነበረች አይዘነጋም። ግን እነ መስፍን እንኳን የሆነ የተጠረጠረ ነገር ሁሉ የሚያስደነግጣቸውና እንደ ልጆች ኩኩሉ ጨዋታ ገና ቁጥር ሳይጀመር መደበቂያ የሚፈልጉ በመሆናቸው ጋዜጣዋ መክና ቀርታለች። አሉላ ከእነርሱ የተሻለ ሰብዕናም ድፍረትም ያለው በመሆኑ ሁሉ ሲፈረጥጡ እሱ ግን እዚሁ ቀርቷል።
