Friday, June 15, 2012

የማህበረ ቅዱሳን ሦስቱ የሴል መሪዎች


             ምንጭ፤ዓውደ ምሕረት
ማኅበረ ቅዱሳን የሚባለው በሃይማኖት ስም የሚንቀሳቀሰው የፖለቲካ ድርጅት ዘርፈ ብዙ የአሰራር መንገዶች አሉት። አሰራሩ የማፊያነት ባሕርይ ስላለው የሚሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በተለያየ መንገድ እየከፋፈለ ያደርጋል። አላማውን የሚያስፈጽምበት እስከመሰለው ድረስ አዋጭ ብሎ የሚያምንበትን መንገድ ይጠቀማል። መንፈሳዊ ባሕርይ  ስለሌለው ልምድን ከመንፈስ ቅዱስ፤  በጸሎት ሳይሆን የፖለቲካ ድርጅቶችን አሠርር እየገመገመ ይጠቅመኛል የሚለውን መንገዶች ሁሉ ይጠቀማል።
ለዛሬ ስለሦስቱ ሴሎቹ እና ስለሴል መሪዎቹ እናቀርባለን።
አሉላ  ጥላሁን
            አሉላ ዋነኛ ስራው ግልጹንም ስውሩንም  ሚዲያ መቆጣጠርና መምራት ነው። ቱሪስት የነበረውን ቡድን ይመራል። ኤፍሬም እሸቴ የከፈታትን ደጀ ሰላምን ይመራል ይቆጣጠራል። ሪፖርተሮችዋን በደንብ ያንቀሳቅሳል። እነ ሱራፌልን፤ ጳውሎስ፤ መረዋን ሌሎችንም ይመራል። ለጥንቃቄ እንዲረዳ በእነርሱ ስር የሚንቀሳቀሱትን ሰዎች ደጀ ሰላም የማኅበረ ቅዱሳን አይደለችም ብለው እንዲያምኑ የሚያደርግ የተለያየ ዘዴዎችን ይፈጥራል። ያስጠናል። አንዳንዴም ማኅበረ ቅዱሳንን ሳይበዛ በልዝቡ ወረፍ ያደርጋል። ከዛም ዛሬስ እኛም አልቀረልንም ብለው እንዲያስወሩ ያደርጋል። በዚህም ተሳክቶለታል። አንዳንዶቹ ወሬ አቀባዮች ምለው ተገዝተው ደጀ ሰላም የማቅ አይደለም ብለው የሚያምኑ ናቸው። ሱራፌል ወደ አሜሪካ በሄደ ጊዜ እሱም ከማኅበሩ ዋና ጸሀፊ ከሙሉጌታ ጋር በመቃቃሩ ደጀ ሰላም ተቀዛቅዛ እንደነበር ይታወሳል።
        ከምርጫ 97 በኋላ ቅንጅት ለምን ተቀባይነት አገኘ ብላ ማኅበሯ ጥናት ስታደርግ ተቀባይነት ያገኘበት መንገድ ጠንካራ መሪዎች ስላሉት ወይም የተሻለ የፖለቲካ መስመር አሊያም ልብ የሚያደርስ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስላለው ሳይሆን ጋዜጦችን በሙሉ ደጋፊ አድርጎ ማቆም በመቻሉ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ በመደረሱ ማኅበሯም ሀሳብዋን ወደ ህዝቡ ለማድረስ የግል ሚዲያዎችን ከማቋቋም ጀምሮ አባላትዋን በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ዐምደኛ በማድረግ የምታደርገውን እንቅስቃሴ ይመራል፤ ይቆጣጠራል።
      አዲስ ነገር በማኅበሩ ፈንድ አድራጊነት በማኅበሩ ሰዎች በነመስፍንና ዓቢይ ሲቋቋም እሱ ኮፒ ኢዲተር ዳንኤል ክብረት አምደኛ፤ ኤፍሬም ሪፖርተር ሆነው በአብዛኛው የማኅበሩ አባላት የሚገኙበትና እንቅስቃሴውን በሙላት የሚቆጣጠሩበት ጋዜጣ እንደነበረች አይዘነጋም። ግን እነ መስፍን እንኳን የሆነ የተጠረጠረ ነገር ሁሉ የሚያስደነግጣቸውና እንደ ልጆች ኩኩሉ ጨዋታ ገና ቁጥር ሳይጀመር መደበቂያ የሚፈልጉ በመሆናቸው ጋዜጣዋ መክና ቀርታለች። አሉላ ከእነርሱ የተሻለ ሰብዕናም ድፍረትም ያለው በመሆኑ ሁሉ ሲፈረጥጡ እሱ ግን እዚሁ ቀርቷል።

Tuesday, June 12, 2012

የዲ/ን ብርሃኑ አድማስ መሠረታዊ ስህተቶች!

የማኅበረ ቅዱሳን ቀኝ እጅ  የሆነው / ብርሃኑ አድማስ በረጅም ስብከቱ «የተሐድሶዎች መሠረታዊ ስህተቶች» የሚል  ስብከት ለታዳሚዎቹ  ሲጠርቅ ተመልክተናል። በመሠረቱ «ተሐድሶ» የሚባል ተቋም የት እንዳለ የሚያውቀው ብርሃኑ ብቻ ሆኖ ስላነሳቸው ነጥቦች ግን ጥቂት ለማለት እንፈልጋለን።
ብርሃኑ በረጅሙ ስብከት ያነሳቸው ነጥቦች ሲጨመቁ ይህንን ይመስላሉ።
1/ሃይማኖትን መጠበቅ ግዴታ መሆኑን
2/ ሃይማኖት የማይታደስ መሆኑን
3/ ስለሃይማኖት የብርሃኑ አስተምህሮ ትክክል መሆኑን
4/ ስህተትን በማስተማር ማስተካከል የሚቻል መሆኑን
ያመላከተ ሆኖ ተገኝቷል። በነዚህ ነጥቦች ላይ ተንተርሰን የምናነሳቸው ነገሮች የሚከተለውን ይመስላሉ።

1/ሃይማኖትን የመጠበቅ ግዴታ፤
በኤፌሶን 44 ላይ አንዲት እምነት በማለት የተገለጸው የጥቅሱ ቃል  የትኛውን የእምነት ክፍል እንደሚወክል / ብርሃኑ አልተናገረም። ምክንያቱም ወንጌሉ «አንዲት እምነት» በማለት በጥቅል ያስቀምጣል እንጂ ይህችኛዋ ነች ብሎ በስም ለይቶ ባለማስቀመጡ / ብርሃኑ ሃይማኖትን ስለመጠበቅ ሲያስተምር «አንዲት እምነት» የሚለውን ቃል ተቀብለናል የሚሉ ሁሉ እኔ ነኝ ህጋዊው  የመጽሐፍ ቅዱስ ተጠሪ ማለታቸው ስለሚታወቅ ሁላችሁም የአንዲት እምነት ተቀባዮች ባላችሁበት ጸንታችሁ ኑሩ የሚል የወል ስብከትን የሚያስተላልፍ ድምጸት የነበረው ዲስኩር ሆኖ ተመዝግቧል።
ስለዚህ ስለ «ሃይማኖት መጠበቅ» እና የአንዲት እምነትን  አስተምህሮ ለማስረጽ  የተገባውን ሃይማኖት ክፍል ምን መምሰል እንዳለበት እንደመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ማብራራት የግድ ይሆንበት ነበር። ከዚያ ባሻገር ስለአንዲት እምነት ጠብቆ መቆየት በክርስትና ዙሪያ የተሰለፉት ሁሉ እኔ ነኝ ለዚያ የተገባሁት የማይል ስለሌለ የዲ/ ብርህኑ ስብከት ሚዛን የሚደፋ አይሆንም። 

ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ዘረኝነትን ለሚያራምዱ አባቶች ምሳሌ ናቸው

  ምንጭ፦ ዓውደ ምሕረት ብሎግ
ቀድሞ መልአከ አሚን አባ ዘካርያስ ይባሉ ነበር፡፡ በብፁዕ
 ወቅዱስ አቡነ ተ/ሃይማኖት አንብሮተ እድ ግንቦት 3ዐ ቀን 1979 ዓ.ም፣ እንደ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ታሪከ የቀሳፊውንና ተልእኮውን በሚገባ ባለመፈጸሙ መብረር የተሳነውን መልአክ ስም ወስደው «አቡነ ቀውስጦስ» ተብለው ተሾሙ፡፡ አባ ቀውስጦስ ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ የሚስማማቸው ሸዋ ነክ ነገር ብቻ ነው፡፡ ከቅዱሳን ሸዋ፣ ከቤተ ክርስቲያን አለቃ የሸዋ ተወላጅ፣ ዲያቆን ሲሾሙ የሸዋ ተወላጅ በአጭሩ ዘረኝነት የተጠናወታቸው ከጳጳስነት ይልቅ ያገር ሽማግሌነት የሚስማማቸው አባት ናቸው፡፡ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ያወዳጃቸውም በዋናነት ሸዋነት መሆኑን የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡
የአቡነ ቀውስጦስ ዘረኝነት ጐልቶ የታየው ለአቡነ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን ለማሳነጽ፣ ታቦት ለመቅረጽ፣ ገድል ለማጻፍ ባደረጉት ጥረት ነው፡፡ በጣልያን ወረራ በ1928 ዓ.ም የተገደሉት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስና የጐሬው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሚካኤል ለአንድ አይነት አላማ ሞተው ሳለ አቡነ ጴጥሮስ ብቻ እንዲታሰቡ መሯሯጣቸው ለምን ብሎ ለጠየቀ ሰው መልሱን በቀላሉ ማግኘት ይችላል፤ የአገር ልጅነት፡፡ አቡነ ሚካኤል ግን የሸዋ ተወላጅ ስላልሆኑ አስተዋሽ አጥተው የረባ መታሰቢያ ሳይኖራቸው እስካሁን አለ፡፡
የከፋ ዘረኝነት እና ፖለቲካ (በ1997 ዓ.ም ይግባኝ ለክርስቶስ ብለው ያሳተሙትን ይመለከቷል) የተጠናወታቸው አቡነ ቀውስጦስ ከግብር ልጆጃቸው የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጋር በመሆን የሸዋ ተወላጅ ለሆኑት ለአቡነ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ደፋ ቀና ብለው አሠርተው አስመርቀዋል፡፡ በዚህ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ እለት የወጣው “ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ” የተሠኘው መጽሔት ገፅ 53 ላይ ይህን የአቡነ ቀውስጦስን የዘረኝነት ሥራ የዜና ቤተክርስቲያን አዘጋጅ ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በቅኔው እንዲህ አጋልጦታል፡-