Tuesday, June 12, 2012

የዲ/ን ብርሃኑ አድማስ መሠረታዊ ስህተቶች!

የማኅበረ ቅዱሳን ቀኝ እጅ  የሆነው / ብርሃኑ አድማስ በረጅም ስብከቱ «የተሐድሶዎች መሠረታዊ ስህተቶች» የሚል  ስብከት ለታዳሚዎቹ  ሲጠርቅ ተመልክተናል። በመሠረቱ «ተሐድሶ» የሚባል ተቋም የት እንዳለ የሚያውቀው ብርሃኑ ብቻ ሆኖ ስላነሳቸው ነጥቦች ግን ጥቂት ለማለት እንፈልጋለን።
ብርሃኑ በረጅሙ ስብከት ያነሳቸው ነጥቦች ሲጨመቁ ይህንን ይመስላሉ።
1/ሃይማኖትን መጠበቅ ግዴታ መሆኑን
2/ ሃይማኖት የማይታደስ መሆኑን
3/ ስለሃይማኖት የብርሃኑ አስተምህሮ ትክክል መሆኑን
4/ ስህተትን በማስተማር ማስተካከል የሚቻል መሆኑን
ያመላከተ ሆኖ ተገኝቷል። በነዚህ ነጥቦች ላይ ተንተርሰን የምናነሳቸው ነገሮች የሚከተለውን ይመስላሉ።

1/ሃይማኖትን የመጠበቅ ግዴታ፤
በኤፌሶን 44 ላይ አንዲት እምነት በማለት የተገለጸው የጥቅሱ ቃል  የትኛውን የእምነት ክፍል እንደሚወክል / ብርሃኑ አልተናገረም። ምክንያቱም ወንጌሉ «አንዲት እምነት» በማለት በጥቅል ያስቀምጣል እንጂ ይህችኛዋ ነች ብሎ በስም ለይቶ ባለማስቀመጡ / ብርሃኑ ሃይማኖትን ስለመጠበቅ ሲያስተምር «አንዲት እምነት» የሚለውን ቃል ተቀብለናል የሚሉ ሁሉ እኔ ነኝ ህጋዊው  የመጽሐፍ ቅዱስ ተጠሪ ማለታቸው ስለሚታወቅ ሁላችሁም የአንዲት እምነት ተቀባዮች ባላችሁበት ጸንታችሁ ኑሩ የሚል የወል ስብከትን የሚያስተላልፍ ድምጸት የነበረው ዲስኩር ሆኖ ተመዝግቧል።
ስለዚህ ስለ «ሃይማኖት መጠበቅ» እና የአንዲት እምነትን  አስተምህሮ ለማስረጽ  የተገባውን ሃይማኖት ክፍል ምን መምሰል እንዳለበት እንደመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ማብራራት የግድ ይሆንበት ነበር። ከዚያ ባሻገር ስለአንዲት እምነት ጠብቆ መቆየት በክርስትና ዙሪያ የተሰለፉት ሁሉ እኔ ነኝ ለዚያ የተገባሁት የማይል ስለሌለ የዲ/ ብርህኑ ስብከት ሚዛን የሚደፋ አይሆንም። 

ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ዘረኝነትን ለሚያራምዱ አባቶች ምሳሌ ናቸው

  ምንጭ፦ ዓውደ ምሕረት ብሎግ
ቀድሞ መልአከ አሚን አባ ዘካርያስ ይባሉ ነበር፡፡ በብፁዕ
 ወቅዱስ አቡነ ተ/ሃይማኖት አንብሮተ እድ ግንቦት 3ዐ ቀን 1979 ዓ.ም፣ እንደ ቅዳሴ ማርያም አንድምታ ታሪከ የቀሳፊውንና ተልእኮውን በሚገባ ባለመፈጸሙ መብረር የተሳነውን መልአክ ስም ወስደው «አቡነ ቀውስጦስ» ተብለው ተሾሙ፡፡ አባ ቀውስጦስ ከተሾሙበት ጊዜ አንስቶ የሚስማማቸው ሸዋ ነክ ነገር ብቻ ነው፡፡ ከቅዱሳን ሸዋ፣ ከቤተ ክርስቲያን አለቃ የሸዋ ተወላጅ፣ ዲያቆን ሲሾሙ የሸዋ ተወላጅ በአጭሩ ዘረኝነት የተጠናወታቸው ከጳጳስነት ይልቅ ያገር ሽማግሌነት የሚስማማቸው አባት ናቸው፡፡ ከማኅበረ ቅዱሳን ጋር ያወዳጃቸውም በዋናነት ሸዋነት መሆኑን የሚያውቅ ያውቀዋል፡፡
የአቡነ ቀውስጦስ ዘረኝነት ጐልቶ የታየው ለአቡነ ጴጥሮስ ቤተክርስቲያን ለማሳነጽ፣ ታቦት ለመቅረጽ፣ ገድል ለማጻፍ ባደረጉት ጥረት ነው፡፡ በጣልያን ወረራ በ1928 ዓ.ም የተገደሉት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስና የጐሬው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሚካኤል ለአንድ አይነት አላማ ሞተው ሳለ አቡነ ጴጥሮስ ብቻ እንዲታሰቡ መሯሯጣቸው ለምን ብሎ ለጠየቀ ሰው መልሱን በቀላሉ ማግኘት ይችላል፤ የአገር ልጅነት፡፡ አቡነ ሚካኤል ግን የሸዋ ተወላጅ ስላልሆኑ አስተዋሽ አጥተው የረባ መታሰቢያ ሳይኖራቸው እስካሁን አለ፡፡
የከፋ ዘረኝነት እና ፖለቲካ (በ1997 ዓ.ም ይግባኝ ለክርስቶስ ብለው ያሳተሙትን ይመለከቷል) የተጠናወታቸው አቡነ ቀውስጦስ ከግብር ልጆጃቸው የማኅበረ ቅዱሳን አመራሮች ጋር በመሆን የሸዋ ተወላጅ ለሆኑት ለአቡነ ጴጥሮስ ቤተ ክርስቲያን ደፋ ቀና ብለው አሠርተው አስመርቀዋል፡፡ በዚህ ቤተ ክርስቲያን ምረቃ እለት የወጣው “ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ” የተሠኘው መጽሔት ገፅ 53 ላይ ይህን የአቡነ ቀውስጦስን የዘረኝነት ሥራ የዜና ቤተክርስቲያን አዘጋጅ ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በቅኔው እንዲህ አጋልጦታል፡-

Sunday, June 10, 2012

ኢትዮጵያ ግብረሰዶምንና አራማጆቹ ምዕራባዊያንን አወገዘች !


‹‹ትልቁ ሀብታችን ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት ነው›› አቡነ ጳውሎስ

  ሪፖርተር ጋዜጣ፤ሰኔ 10/2012 -ትናንት በአዲሱ የአፍሪካ ኅብረት አዳራሽ በ‹‹ግብረሰዶምና ተያያዥ ማኅበራዊ ቀውሶች›› ላይ ለመነጋገር በተጠራው አገራዊ ኮንፈረንስ የተገኙት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች፣ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የፓርላማ አባላት፣ ወጣቶችና ሌሎች የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ‹‹ግብረሰዶምንና ግብረሰዶም የሚያስፋፉ ምዕራባዊያንን›› አወገዙ፡፡ በዚሁ ታሪካዊና አንገብጋቢ በተሰኘው አገራዊ ኮንፈረንስ ላይ ከ2,000 በላይ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ አምስቱ ዋና ዋና የሃይማኖት ተቋማት የኦርቶዶክት ተዋህዶ፣ የእስልምና፣ የካቶሊክ፣ የወንጌላዊት መካነ ኢየሱስና የወንጌላዊያን አብያተ ክርስቲያናት ያወጡትን የግብረሰዶማዊነት የተቃውሞ መግለጫ በአንድ ድምፅ እንደግፋለን ብለዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነትን ካልተቀበላችሁ በማለት የሰብዓዊ መብት ጥያቄ የሚያነሱና ዕርዳታ እንከለክላለን ለሚሉ የምዕራብ አገሮችም ‹‹ዕርዳታቸው በአፍንጫችን ይውጣ›› የሚል ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡

በስብሰባው ላይ የተገኙት የሃይማኖት ተቋማትን በሙሉ ወክለው ጉባዔውን በፀሎት የከፈቱት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት ሕግ ሳይጻፍ ጊዜ ጀምሮ ከእግዚአብሔር ጋር ትውውቅ ነበራቸው፤ የዛሬ ሳይንቲስቶችም ኢትዮጵያ የሰው ልጅ መገኛ መሆንዋን ይናገራሉ፤›› በማለት በዓለም ላይ ያሉ ሕዝቦች በሙሉ እርስ በርስ ተረጋግጠዋል፤ ብቸኛ ነፃ አገር ኢትዮጵያ ነች ብለዋል፡፡ ‹‹አሁንም የተረገጡትና የማንነት ቀውስ ያለባቸው ወገኖች ተናገሩ ብላ የምትሰማ አይደለችም፡፡ ባህላችን አልተለወጠም፣ ታሪካችን አልተቀነሰም፣ ማንነታችን አልተበረዘም፤ እንዲሁ ዝም ብለን የምንለወጥ አይደለንም፤›› ሲሉ አስታውቀዋል፡፡