Saturday, June 2, 2012

የአንዳንድ የጳጳሳቶቻችን ገበና ምን ይመስላል?

  ምንጭ፦ አባ ሰላማ ብሎግ
የአንዳንድ ጳጳሳቶቻችንን ገበናዎች ይፋ ስናደርግ ሀዘን ነው የሚሰማን። እንዲህ እያደረግን ያለነው ቤተክርስቲያኗ ምን አይነት ምግባረ ብልሹነት እየተስፋፋባት እንደሆነች ለማሳየት ነው እንጂ እነርሱን በግል ለማሳጣት አይደለም። ይህን መደበቅና ማለፍ ጉዳቱ ለቤተ ክርስቲያን እንደሆነ በግልጽ እየታየ ነው፤ ማኅበረ ቅዱሳን ገበናችሁን እሸፍንላችኋለሁ ማለቱ እርሱ የፈለገውን እንዲፈጽሙለትና «በእከክልኝ ልከክልህ» ቃል ኪዳን እንዲተሳሰሩና እንዳሻው እንዲጠቀምባቸው በማድረግ ቤተክርስቲያንን ከጥፋት ወደ ባሰ ጥፋት እየመራት ነው። እንደነዚህ ያሉትን አባቶች አሳፋሪ ታሪክ ማስፈራሪያ እያደረገ የሚሻውን እንዲፈጽሙለት እየተጠቀመበት ያለው ማኅበረ ቅዱሳንም ለጥቅሙ እንጂ ለቤተክርስቲያን እንዳልቆመ አስመስክሯል።
 እንደ እነዚህ ያሉትን «ብፁዓን» «ጻድቃን» «ቅዱሳን» ምንትስ እያለ መሸንገሉም በጥፋታቸው እንዲገፉ አድርጓቸዋል እንጂ በክፉ ሥራቸው እንዲጸጸቱና ንስሃ እንዲገቡ አልረዳቸውም። የራሳቸውን ጉድ ሌላውን አለሀጢአቱ በማውገዝ ለመሸፈን እያደረጉት ያለው ጥረትም ለማኅበረ ቅዱሳን በር እንዲከፈትለትና የሲኖዶሱ የበላይ አካል እንዲሆን ነው ያደረገው። ስለዚህ ገበናቸው እንዲህ ይፋ ቢሆን፣ ጉዳዩ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዘንድ ትኩረት አግኝቶ ለቤተክርስቲያኑ አንዳች መፍትሔ ያመጣ ይሆናል በሚል ሐሳብ ገበናቸውን መግለጽ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል። ምናልባት ልብ ገዝተው ንስሃ ይገቡ ይሆናል።

የአፋልጉኝ ማስተወቂያ
ይህ ልጅ አያሳዝንም? ……. አያሳሳም? …… እርሱ ጠፍቶ እንዳይመስለዎ። አባቱን ማግኘት ባይችልም አባቱን ይፈልጋል፤ እንደሌላው በህግ እንደተወለደ ልጅ ከእናቱ ጋር አባቱን ማግኘትና አብሮ ለመኖር አልታደለም። ያለው አማራጭ አባቴ ማነው? እያለ በመጠየቅ ማደግ ነው። ማን ያውቃል? የማንነት ጥያቄው አንድ ቀን ምላሽ ያገኝ ይሆናል።

Friday, June 1, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህም ነበር ! በቀሲስ መልአኩ


ካለፈው የቀጠለ………………………………………
ሌላው በዘመናችን የተደረገ ነውበካምቦዲያ ውስጥ ኬሜን ሩዥ የተባለው ኮሚኒስታዊ ድርጅት ሥልጣኑን ይዞ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሆኑ የገዛ ወገኖቹን በገደለበት ወቅት ነውበዚያን ወቅት በሀገሪቱ  እየተፈለጉና  እየታደኑ ይገደሉ  የነበሩት አሉ የሚባሉት የሀገሪቱ ምሑራን ነበሩ በካምቦዲያ መማር ወንጀል ነበር ለመማር መጣጣር የሚያስቀጣ ነበር የነሞዛርትን ረቂቅ ሙዚቃ ያሰማምሩ የነበሩ እጆች የምዕራባውያንን  ባሕል ልታመጡ ነው ተብለው ተቆረጡት የታሪክ መዛግብትን የሚመረምሩ ዓይኖች በአብዮቱ ላይ ታሴራላችሁ ተብለው እንዲጠፉ ተደረጉ  ሊቃውንቱ በቁማቸው ተቀበሩ ገደል ተወረወሩ ማወቅ ወንጀል የሆነበት ወቅት ነበርና
ጊዜ ተመልሶ የመጣ የመሰለበት ወቅት አሁን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን አምጥቶልናል ሊቃውንቱን በመጀመሪያ የመናፍቅነት ጥላሸት ማስቀባት፤ ቢቻል የሆነ የሚከሰስበት ነገር መፈለግ ቤተክርስቲያን መናፍቅ ትበለውም፤ አትበለውም በእነርሱ ጥቁር መዝገብ መናፍቅ እንደሆነ ማወጅ ማሳደምና እንዲባረር ማድረግ ቀዳሚው ነገር ነው።  ከሳሽ ማኅበረ ቅዱሳን፤ ምስክር ማኅበረ ቅዱሳን፣ ፈራጅ ማኅበረ ቅዱሳን፤ ሕግ አስፈጻሚ ማኅበረ ቅዱሳን  በሆነበት ሁኔታ ጉዳይህ አሰቃቂ ፍጻሜ ያገኛል። ከእሱ ከተስማማህ ትድናለህ፤ ካልተስማማህ ትጠፋለህ።ለዚህ አስዛኝ ሁኔታ ምሳሌ ምሳሌ የሚሆነን በአንድ ወቅት ማኅበሩ በሚያወጣው ጋዜጣ ላይ የከፍተኛ የቴዎሎጂ ኮሌጅን፤ ከምክትል ዲኑ ጀምሮ የኮሌጁን ዋና ጸሐፊ፤ በኮሌጁ የአዲስ ኪዳንና የግዕዝ መምሕር፤ በኮሌጁ የአዲስ ኪዳንና የግእዝ መምህርበኮሌጁ የቤተክርስቲያን ታሪክ መምህር፤ የኮሌጁን ሥራ መሪና የእንግሊዝኛ መምህር ስድስት ተማሪዎችን  ጨምሮ ተሐድሶዎች ናቸው ብሎ አውጥቷል ይህም የኮሌጁን ሊቀ ጳጳስ ጨምሮ ወደ ቅድስት ሥላሴ የተዛወሩ ሦስት አስተማሪዎች ተሐድሶ ማለቱን ሳይጨምር ነውይህ ጸሐፊ እስከሚያታውሰው ኮሌጁ ያሉት አስተማሪዎች ከስምንት እስከ አሥር ቢሆኑ ነውስለሆነም በማኅበረ ቅዱሳን ሚዛን ኮሌጁ ካሉት አስተማሪዎች ዘጠና በመቶዎች መናፍቃን ነበሩ ማለት ነው
ይህን ታሪክ ስጽፍ በስሜታዊነት ቢሆን አትፈረዱብኝ ልቤ እየደማ ነውና የምጽፈው ወደማን አቤት ይባላል? ወደ ማንስ ይኬዳል ? እግዚአብሔር እንዲፈርድ ከመጥራት ሌላ ማን ይባላል ?
"ለመሆኑ የእነዚህ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ስም አደባባይ የወጣው ቤተ ክርስቲያን መክራበት ነው ? ለምናቸው አልቅሳላቸው እባካችሁ ልጆቼ ስህተት አግኜባችኋለሁና ተመለሱ ብላቸው ነው ?  በፍጹም ! ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት እንኳን የእነዚህን የቤተክርስቲያን ሊቃውንት የተከሰሱብትን ምክንያት አያውቁም ። ወንጀሉን የሚያነቡት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋዜጣ ላይ ነው። ከዚያም በየቤታቸው እነዚህን ካላባረራችሁልን የሚል ማስፈራራያ ይመጣላቸዋል።

Thursday, May 31, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን እንዲህም ነበር! በቀሲስ መልአኩ

ቀሲስ መልአኩ ባወቀ  «ስውሩ አደጋ» ከሚለው መጽሐፍ  ስለ «ማኅበረ ቅዱሳን እና ሃይማኖተ አበው » ከጻፉት የተወሰደ።
 ተሐድሶ ምንድነው ?
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትን በሰፊው እያነጋገረ ያለው ነገር ቢኖር "ተሐድሶ " የሚለው ቃል ነው ቃሉ እንዲህ  እንደ አሁኑ ፕሮቴስታንታዊ ለሆነ አስተሳሰብ ከመዋሉና አከራካሪ ከመሆኑ በፊት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚጠቅሱት ታላላቅ የነገረ መለኮት ቃላት አንዱ ነውንስሐንና ውስጣዊ የሆነ የሕይወት ለውጥን፤ ወደ እግዚአብሔር መመለስን የሚያመለክት ነውበሌላ በኩል ደግሞ ሲኖዶሳዊ የሆነ ለውጥን (መሻሻልን ) ሊያመልክት ይችላል። ለምሳሌ በቅዱስ ፓትርያርኩና በብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ታስቦበትና ተመክሮበት ለቤተ ክርስቲያን ዕድገት ይረዳሉ የሚባሉ መሻሻሎችን፤ ለውጦችንና አዳዲስ ተቋሞችን ሁሉ ይመለከታል።  ከዚህም ታላቁና ቤተክርቲያንን በአስቸጋሪ መከራ ውስጥ መከታ ሆኖ እንድታልፍ ያደረጋት የሰበካ ጉባኤ መቋቋምና የቃለ ዓዋዲ ድንጋጌ ነው :: ይህ ድንጋጌ ብዙዎች እንደሚያስቡት የሰዎች የአስተሳሰብ ፈሊጥ ሳይሆን የሲኖዶስ ቀኖናዊ ውሳኔ ነው።  አሁን ግን "ተሐድሶ " የሚለውን ቃል ፕሮቴስታንቱ ዓለም ብቻ ሳይሆን የፖሊቲካው ዓለምም እየተጠቀመበት አስቸጋሪ ቃል ሆናል።
«ተሐድሶ በኦርቶዶክሱ ዓለም»
ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን እምነትን የምትጠብቅ እንጂ እምነትን በዘፈቀደ ወይም ባሰኛት መንገድ የምትቀያየር ስላይደለች ዛሬ ኣንዳንዶች ከዚህ ቤተክርስቲያን የወጡ ሰዎች እንደሚናገሩት «ተሐድሶ» የሚለውን ቃል እምነትን በተመለከተ አታውለውምሃይማኖት ምን ዓይነት መልክ እንዳላት ሐዋርያው ይሁዳ በመልእክቱ ጽፎልናል "አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለቅዱሳን የተሰጠች በማለት " ስለሆነም አትበረዝም፤ አትከለስም ወይም ብልየት እርጅና አያገኛትም። በሌላ በኩል ግን የክርስቲያን ሕይወት ዕለትለት ይታደሳልውስጣዊ የሆነውን የሕይወት ተሐድሶ የሚያገኘውን በንስሀ በጾም፤ በጸሎት ነው :: ይህን በተመለከተም በብዙ ቦታዎች ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራ።
በሌላ በኩል ደግሞ አስተዳደራዊ የአሠራር ለውጦችና አልፎ አልፎ ቀኖናዊ ለውጦች ይኖራሉ :: እነዚህም ቢሆኑ የሚከናወኑት በብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ስለሆነ ለውጡ ሲኖዶሳዊ ነው እንጂ የአመጽ ወይም የጥቂት ግለሰቦች አይደለም።
ይህም በኦርቶዶክሱ ዓለም የተለመደ እንደሆነ በቤተ ክርስቲያንችን የከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ለብዙ ዓመታት በማስተማር ሥራ ላይ የተሰማሩትና አያሌ ደቀ መዛሙርትን ያፈሩት ሉሌ መላኩ "የቤተ ክድርስቲያን ታሪክ " በሚለው መጽሐፋቸው በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ሲኖዶሳዊ ተሐድሶ ሲገልጡ ,,,«በኮፕቶች (በግብጾች ) ዘንድ የተሐድሶ አባት በመባል የሚታወቀው ቄርሎስ አራተኛ (1854-1861) የእስክንድርያ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ነው :: ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የተነሣው ትምህርትን ማስፋፋት (የማሰራጨት ) ሰለነበር በግብጽ ካህናት ዘንድ ሰፍኖ የነበረውን የትምህርት ጉድለት፤ ዝቅተኛነትን ለማሻሻል ካህናት ተግተው እንዲማሩ አደረገከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤትም ከፍቶ ዓለማዊና መንፈሳዊ ዕውቀት የነበራቸውን በማሰማራት መጻሕፍትን በገፍ በማቅረብ ካህናትና ምእምናን የቅብጥ (ኮፕት ) የዐረብኛ፤ የእንግሊዝኛ፤ የፈረንሳይኛ፤ የኢጣልያንኛ፤ የቱርክ .. ወዘተ ቋንቋዎችና የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን እንዲማሩ አደረገ »ይሉናል።
የገሞራው ጋዜጣ ጽሑፍ እና የሃይማኖተ አበው መዘጋት "
እንግዲህ በዚህ ወቅት ነው ማን እንደጻፈው የማይታወቅ ጽሑፍ "ገሞራው " በሚባልና አሁን ከሕትመት ውጭ በሆነ የግል ጋዜጣ ላይ የወጣው።  ጽሑፉ ሰፊ የሆነና የተሐድሶ ማኅበር እንዴት እንደሚንቀሳቀስና ዓላማውም ምን እንደሆነ የሚገልጥ ነበር።  ከሁሉ የሚገርመው ግን ጽሑፉ ሰለተሐድሶ ሆኖ ሳለ ከጽሑፉ ጋር አብሮ የወጣው ግን በጎፋ ገብርኤል ለረጅም ጊዜ ያገለገሉና  የኢትዮጵያዊው ስማእት የብጹእ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ልጅ የሆኑ መነኩሴና እርሳቸው የሚያስተምሩዋቸው የሃይማኖተ አበው ተማሪዎችን የያዘ ፎቶ ነበር እኚህ አባት ጋዜጣው በወጣ ማግሥት ያለ ምንም ጥያቄ ከሚያገለግሉበት ደብር እንዲወገዱ ተደረገእምነት፤ ክህደታቸውን የጠየቀ፤ አጥፍተውም  ከሆነ በንስሐ እንዲመለሱ የመከረ ማንም አልነበረምማኅበረ ቅዱሳንም አባ እገሌ መናፍቅ ናቸው እያለ ይጽፍ ጀመረይህ ሁኔታ ቢያሳዝናቸውና  አቤት የሚሉበት ቦታ ቢያጡ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው፤ ከብዙ እንግልት በኋላ ወደ ቤተክርስቲያናቸው እንዲመለሱ ተፈርዶላቸዋልዛሬ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ በታላቅ የሥልጣን ደረጃ ላይ ናቸውየጋዜጣው ጽሑፍ መደምደሚያ ሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር የተሐድሶ ድርጅት አካል እንደሆነ የሚናገር ነበ።