ካለፈው የቀጠለ………………………………………
ሌላው
በዘመናችን የተደረገ ነው። በካምቦዲያ ውስጥ
ኬሜን ሩዥ የተባለው ኮሚኒስታዊ ድርጅት ሥልጣኑን ይዞ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሆኑ የገዛ ወገኖቹን በገደለበት ወቅት ነው። በዚያን ወቅት
በሀገሪቱ እየተፈለጉና እየታደኑ ይገደሉ የነበሩት አሉ
የሚባሉት የሀገሪቱ ምሑራን ነበሩ። በካምቦዲያ መማር ወንጀል ነበር። ለመማር መጣጣር የሚያስቀጣ ነበር። የነሞዛርትን ረቂቅ ሙዚቃ ያሰማምሩ የነበሩ እጆች የምዕራባውያንን ባሕል ልታመጡ
ነው ተብለው ተቆረጡት። የታሪክ መዛግብትን
የሚመረምሩ ዓይኖች በአብዮቱ ላይ ታሴራላችሁ ተብለው እንዲጠፉ ተደረጉ። ሊቃውንቱ በቁማቸው ተቀበሩ ገደል ተወረወሩ። ማወቅ ወንጀል የሆነበት ወቅት ነበርና።
ያ
ጊዜ ተመልሶ የመጣ የመሰለበት ወቅት አሁን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ማኅበረ ቅዱሳን አምጥቶልናል። ሊቃውንቱን በመጀመሪያ የመናፍቅነት ጥላሸት ማስቀባት፤ ቢቻል የሆነ የሚከሰስበት ነገር መፈለግ ቤተክርስቲያን መናፍቅ ትበለውም፤ አትበለውም በእነርሱ ጥቁር መዝገብ መናፍቅ እንደሆነ ማወጅ ማሳደምና እንዲባረር ማድረግ ቀዳሚው ነገር ነው። ከሳሽ ማኅበረ
ቅዱሳን፤ ምስክር ማኅበረ ቅዱሳን፣ ፈራጅ ማኅበረ ቅዱሳን፤ ሕግ አስፈጻሚ ማኅበረ ቅዱሳን በሆነበት ሁኔታ ጉዳይህ
አሰቃቂ ፍጻሜ ያገኛል። ከእሱ ከተስማማህ ትድናለህ፤ ካልተስማማህ
ትጠፋለህ።ለዚህ
አስዛኝ ሁኔታ ምሳሌ ምሳሌ የሚሆነን በአንድ ወቅት ማኅበሩ በሚያወጣው ጋዜጣ ላይ የከፍተኛ የቴዎሎጂ ኮሌጅን፤ ከምክትል ዲኑ ጀምሮ የኮሌጁን ዋና ጸሐፊ፤ በኮሌጁ የአዲስ ኪዳንና የግዕዝ መምሕር፤ በኮሌጁ የአዲስ ኪዳንና የግእዝ መምህር፤በኮሌጁ የቤተክርስቲያን
ታሪክ መምህር፤ የኮሌጁን ሥራ መሪና የእንግሊዝኛ መምህር ፤ ስድስት ተማሪዎችን ጨምሮ ተሐድሶዎች
ናቸው ብሎ አውጥቷል። ይህም የኮሌጁን
ሊቀ ጳጳስ ጨምሮ ወደ ቅድስት ሥላሴ የተዛወሩ ሦስት አስተማሪዎች ተሐድሶ ማለቱን ሳይጨምር ነው። ይህ ጸሐፊ
እስከሚያታውሰው ኮሌጁ ያሉት አስተማሪዎች ከስምንት እስከ አሥር ቢሆኑ ነው። ስለሆነም በማኅበረ
ቅዱሳን ሚዛን ኮሌጁ ካሉት አስተማሪዎች ዘጠና በመቶዎች መናፍቃን ነበሩ ማለት ነው።
ይህን
ታሪክ ስጽፍ በስሜታዊነት ቢሆን አትፈረዱብኝ ። ልቤ እየደማ
ነውና የምጽፈው። ወደማን አቤት ይባላል? ወደ ማንስ ይኬዳል ? እግዚአብሔር እንዲፈርድ ከመጥራት ሌላ ማን ይባላል ?
"ለመሆኑ የእነዚህ
ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ስም አደባባይ የወጣው ቤተ ክርስቲያን መክራበት ነው ? ለምናቸው አልቅሳላቸው እባካችሁ ልጆቼ ስህተት አግኜባችኋለሁና ተመለሱ ብላቸው ነው ? በፍጹም ! ብጹዓን
ሊቃነ ጳጳሳት እንኳን የእነዚህን የቤተክርስቲያን ሊቃውንት የተከሰሱብትን ምክንያት አያውቁም ። ወንጀሉን የሚያነቡት ከማኅበረ ቅዱሳን ጋዜጣ ላይ ነው። ከዚያም በየቤታቸው እነዚህን ካላባረራችሁልን የሚል ማስፈራራያ ይመጣላቸዋል።