ቀሲስ
መልአኩ ባወቀ «ስውሩ አደጋ» ከሚለው መጽሐፍ ስለ «ማኅበረ
ቅዱሳን እና ሃይማኖተ አበው » ከጻፉት የተወሰደ።
ተሐድሶ ምንድነው ?
በአሁኑ
ወቅት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናትን በሰፊው እያነጋገረ ያለው ነገር ቢኖር "ተሐድሶ " የሚለው ቃል ነው። ቃሉ እንዲህ
እንደ አሁኑ ፕሮቴስታንታዊ ለሆነ አስተሳሰብ ከመዋሉና አከራካሪ ከመሆኑ በፊት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚጠቅሱት ታላላቅ የነገረ መለኮት ቃላት አንዱ ነው። ንስሐንና ውስጣዊ የሆነ የሕይወት ለውጥን፤ ወደ እግዚአብሔር መመለስን የሚያመለክት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ሲኖዶሳዊ የሆነ ለውጥን (መሻሻልን ) ሊያመልክት ይችላል። ለምሳሌ በቅዱስ ፓትርያርኩና በብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ታስቦበትና ተመክሮበት ለቤተ ክርስቲያን ዕድገት ይረዳሉ የሚባሉ መሻሻሎችን፤ ለውጦችንና አዳዲስ ተቋሞችን ሁሉ ይመለከታል። ከዚህም ታላቁና ቤተክርቲያንን በአስቸጋሪ መከራ ውስጥ መከታ ሆኖ እንድታልፍ ያደረጋት የሰበካ ጉባኤ መቋቋምና የቃለ ዓዋዲ ድንጋጌ ነው :: ይህ ድንጋጌ ብዙዎች እንደሚያስቡት የሰዎች የአስተሳሰብ ፈሊጥ ሳይሆን የሲኖዶስ ቀኖናዊ ውሳኔ ነው። አሁን ግን "ተሐድሶ " የሚለውን ቃል ፕሮቴስታንቱ ዓለም ብቻ ሳይሆን የፖሊቲካው ዓለምም እየተጠቀመበት አስቸጋሪ ቃል ሆናል።
«ተሐድሶ
በኦርቶዶክሱ ዓለም»
ኦርቶዶክሳዊት
ቤተ ክርስቲያን እምነትን የምትጠብቅ እንጂ እምነትን በዘፈቀደ ወይም ባሰኛት መንገድ የምትቀያየር ስላይደለች ዛሬ ኣንዳንዶች ከዚህ ቤተክርስቲያን የወጡ ሰዎች እንደሚናገሩት «ተሐድሶ» የሚለውን ቃል እምነትን በተመለከተ አታውለውም። ሃይማኖት ምን ዓይነት መልክ እንዳላት ሐዋርያው ይሁዳ በመልእክቱ ጽፎልናል "አንድ ጊዜ ፈጽሞ ለቅዱሳን የተሰጠች በማለት "። ስለሆነም አትበረዝም፤
አትከለስም ወይም ብልየት እርጅና አያገኛትም። በሌላ በኩል ግን የክርስቲያን ሕይወት ዕለት ዕለት ይታደሳል። ውስጣዊ የሆነውን የሕይወት ተሐድሶ የሚያገኘውን በንስሀ ፤በጾም፤ በጸሎት
ነው :: ይህን በተመለከተም በብዙ ቦታዎች ቅዱሳት መጻሕፍት ይናገራ።
በሌላ
በኩል ደግሞ አስተዳደራዊ የአሠራር ለውጦችና አልፎ አልፎ ቀኖናዊ ለውጦች ይኖራሉ :: እነዚህም ቢሆኑ የሚከናወኑት በብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳት ስለሆነ ለውጡ ሲኖዶሳዊ ነው እንጂ የአመጽ ወይም የጥቂት ግለሰቦች አይደለም።
ይህም
በኦርቶዶክሱ ዓለም የተለመደ እንደሆነ በቤተ ክርስቲያንችን የከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤቶች ለብዙ ዓመታት በማስተማር ሥራ ላይ የተሰማሩትና አያሌ ደቀ መዛሙርትን ያፈሩት ሉሌ መላኩ "የቤተ ክድርስቲያን ታሪክ " በሚለው መጽሐፋቸው በግብጽ ቤተ ክርስቲያን የነበረውን ሲኖዶሳዊ ተሐድሶ ሲገልጡ ,,,«በኮፕቶች (በግብጾች ) ዘንድ የተሐድሶ አባት በመባል የሚታወቀው ቄርሎስ አራተኛ (1854-1861) የእስክንድርያ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ነው :: ዋነኛ ዓላማ አድርጎ የተነሣው ትምህርትን ማስፋፋት (የማሰራጨት ) ሰለነበር በግብጽ ካህናት ዘንድ ሰፍኖ የነበረውን የትምህርት ጉድለት፤ ዝቅተኛነትን ለማሻሻል ካህናት ተግተው እንዲማሩ አደረገ። ከፍተኛ መንፈሳዊ ትምህርት ቤትም ከፍቶ ዓለማዊና መንፈሳዊ ዕውቀት የነበራቸውን በማሰማራት መጻሕፍትን በገፍ በማቅረብ ካህናትና ምእምናን የቅብጥ (ኮፕት ) የዐረብኛ፤ የእንግሊዝኛ፤ የፈረንሳይኛ፤ የኢጣልያንኛ፤ የቱርክ .. ወዘተ ቋንቋዎችና የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶችን እንዲማሩ አደረገ »ይሉናል።
የገሞራው ጋዜጣ ጽሑፍ እና የሃይማኖተ አበው መዘጋት "
እንግዲህ
በዚህ ወቅት ነው ማን እንደጻፈው የማይታወቅ ጽሑፍ "ገሞራው " በሚባልና አሁን ከሕትመት ውጭ በሆነ የግል ጋዜጣ ላይ የወጣው። ጽሑፉ ሰፊ የሆነና የተሐድሶ ማኅበር እንዴት እንደሚንቀሳቀስና ዓላማውም ምን እንደሆነ የሚገልጥ ነበር። ከሁሉ የሚገርመው ግን ጽሑፉ ሰለተሐድሶ ሆኖ ሳለ ከጽሑፉ ጋር አብሮ የወጣው ግን በጎፋ ገብርኤል ለረጅም ጊዜ ያገለገሉና የኢትዮጵያዊው ስማእት የብጹእ
ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ልጅ የሆኑ መነኩሴና እርሳቸው የሚያስተምሩዋቸው የሃይማኖተ አበው ተማሪዎችን የያዘ ፎቶ ነበር ። እኚህ አባት
ጋዜጣው በወጣ ማግሥት ያለ ምንም ጥያቄ ከሚያገለግሉበት ደብር እንዲወገዱ ተደረገ። እምነት፤ ክህደታቸውን የጠየቀ፤ አጥፍተውም ከሆነ በንስሐ
እንዲመለሱ የመከረ ማንም አልነበረም። ማኅበረ ቅዱሳንም አባ እገሌ መናፍቅ ናቸው እያለ ይጽፍ ጀመረ። ይህ ሁኔታ ቢያሳዝናቸውና አቤት የሚሉበት
ቦታ ቢያጡ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስደው፤ ከብዙ እንግልት በኋላ ወደ ቤተክርስቲያናቸው እንዲመለሱ ተፈርዶላቸዋል። ዛሬ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ በታላቅ የሥልጣን ደረጃ ላይ ናቸው። የጋዜጣው ጽሑፍ መደምደሚያ ሃይማኖተ አበው የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበር የተሐድሶ ድርጅት አካል እንደሆነ የሚናገር ነበ።