ፊያሜታጋዜጣ
ልዩ ዕትም ነሐሴ 29 ቀን 1990
ከሲኖዶስ
ወደገዳም የተላኩ መምህራን በመቋሚያና በድንጋይ ተደበደቡ!
በሐምሌ
ወር 1990 በተደረገው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጠቅላላ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ሄደው የነሐሴን ወር እንዲያሳልፉ የተወሰነባቸው፣ ዲያቆን ግርማ በቀለ፣ የሰዋሰው ብርሃን ቅ/ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤት የሐዲስ ኪዳን መምህርና ዲያቆን ፅጌ ስጦታው የጐፋ ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ሰባኬ ወንጌል፣ በሄዱበት ገዳም የድንጋይ ናዳ እንደወረደባቸው ተገለፀ።
ድርጊቱ
ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታይ በሙሉ የሚያሳፍር፣ ለማመንም የሚያስቸግር ነው። ሆኖም የተፈፀመው አሳፋሪ ተግባር ግን እውነት ነው። ከቤተ ክህነቱ የደረሱን ተማኝ ምንጮች እንዳረጋገጡት፣ ቀደም ሲል ማህበረ ቅዱሳን በተባለው ክፍል በቀረበባቸው ሃይማኖታዊ ክስ መነሻነት ስለ ሁለቱ መምህራንና ተባባሪ የተባሉትን ተጨማሪ መምህራን አክሎ የቤተ ክህነቱ የሊቃውንት ጉባኤ የቀረበውን ክስ በማጣራት ጉዳዩን ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አቅርቦ ከታየ በኋላ ክሱን ፍሬ ቢስ በማድረግ ሁለቱ መምህራን በደብረ ሊባኖስ በሚገኙት የሐዲስ የትርጓሜ መምህር በመሄድ ለአንድ ወር እንዲቆዩ ቢወሰንም በሲኖዶሱ ትዕዛዝ ወደ ደብረ ሊባኖስ ያመሩትን መምህራን ቀድሞ የጠበቃቸው ነገር ቢኖር ግን የዱላ እና የድንጋይ መዓት መሆኑን እነዚህ ምንጮች ገልፀዋል።
በማህበረ
ቅዱሳን፣ መናፍቅና እምነትን የሚሸረሽሩ ከተባሉት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታዮች መካከል፣ ከዲያቆን ግርማ በቀለ እና ዲያቆን ፅጌ ስጦታ ሌላ አባ ገሪማ ተስፋዬ፣ አባ ቀፀላ፣ ዲያቆን ልዑለ ቃል እና ዲያቆን ኤልያስ የተባሉ የሚገኙበት ሲሆን፣ የሊቃውንት ጉባኤውም ሆነ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተከሳሾቹን በፍቅር ተቀብሎ፣ ጥቃቅን ነገሮች ቢኖሩ እንኳ በኃላፊነቱ መክሮና ዘክሮ ቤተ ክርስቲያናቸውን እንዲያገለግሉ መመሪያ ሰጥቶ ሲያሰናብት፣ በኃላፊነት ቁንጮ ከተቀመጠው ቅዱስ ሲኖዶስና የሊቃውንት ጉባኤ ይልቅ ለሃይማኖት ተቆርቋሪ በመምሰል እየተከታተሉ ጦርነት መክፈቱ ግን መሰረቱም በቀልና ጥላቻ እንጂ የሃይማኖት ቅንዓት አለመሆኑን ከድርጊታቸው ማወቅ ተችሏል ሲሉ ምንጮቹ ከሳሾቹን ይኰንኗቸዋል።