የጽሁፉ ምንጭ፦ ዓውደ ምሕረት ብሎግ
To read in PDF ( Click Here )
አንዳንድ የዚህ ክፉ ነብሰ በላ የሆነ ድርጅት አመራሮችና አባለት “አባሠረቀንና አቡነ ጳውሎስን ብንገድል መንግስተ ሰማያት መግባታችን አይቀርም እንጸድቃለንም። በዚህ አንጠየቅም” እያሉ ሲያወሩ ስንሰማ ግራ እየገባን ይህ ከምን የመጣ አመለካከት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የማይደግፈውን አስተሳሰብ እንዲህ በድፍረት የሚናገሩት ለምንድን ነው እያልን ለአመታት የቆየን ቢሆንም በስተመጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ የሚሉት ለምን እንደሆነ በግልጽ ነግረውናል። እኛም ነገሩ ገብቶን ሰው በመግደል ገነት እንደሚወርሱ የሚያምኑ ሰለፊዎች መሆናቸውን አረጋግጠን ከየትኛው መጽሐፍ ይህን ትምህርት እንዳገኙት አውቀናል። ከማቅ ሰዎች ጋር በሀሳብና በአመለካከት ብቻ የተለያየን መሰሎን የነበረ ቢሆንም በምንመራበት መጽሐፍም ቢሆን ልዩነት እንዳለን አውቀናል።

ከዚህ እውነት በመነሳት “ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር” እንዲሉ በግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የታዩ ክስተቶችን የተመለከተ ትንታኔ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡
ከቅርብ
ጊዜ ወዲህ እራሱን በቅዱሳን ስም “ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል የሰየመው የፖለቲካ ድርጅት ለአለፉት ሁለት አሥርት
አመታት በቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ሆነ በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰው ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ ሁሉም
የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚያውቁት ሐቅ ነው፡፡
ከዚህ
በፊት በተደጋጋሚ እንዳስነበብናችሁ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የታቀፈውና በዲያቢሎስ መንፈስ የሚመራው ማቅን ለመሆኑ ማን
መሠረተው? እነማንስ ስም ሰጡት የሚለውን እውነታ ስንመለከት ‹‹ማቅ›› የተሀድሶ ኮሚቴ ይባሉ በነበሩ የደርግ
ደጋፊ አባላት የተመሠረተ ሲሆን ይኽ የጥፋት መልዕክተኛ ዘር ግንዱ እነኮሎኔል አጥናፉ አባተ ካቋቋሙት ”ጊዜያዊ
የተሐድሶ ጉባኤ” ይነሳል። ጊዜያዊ የተሐድሶ ጉባኤ የማኅበረ ቅዱሳን አባቱ መሆኑ ነው። ይኽ አባቱ የቤተ
ክርስቲያንን ሥርዓት ለማፍረስ እና በውስጥዋም ሥርዐት አልበኝነት በማንገስ ቤተ ክርስቲያን ደካማ እንድትሆን ለደርግ
ያገለገለ ነው። የእኛ ጊዜዋ ማቅ አገልግሎት ሁለት መልክ አለው - የሞተውን ሥርዐት ለመመለስ እና የየግል
ጥቅማቸውን ማሳደግ እንዲሁም በሃይማኖት ሽፋን ስውር አላማን ማስፈጸም ነው፡፡
”ከሞኝ
ደጅ ሞፈር ይቆረጣል” እንደሚባለው ይኽ ጊዜጣዊ የተሀድሶ ጉባኤ የመንደረተኝነቱን ቂም ለማርካት ሲል ብጹዕ ወቅዱስ
አቡነ ቴዎፍሎስን ፓትርያርክዋን በገመድ አሳንቆ ያስገደለ የሠይጣን መልእክተኛ ነው። እንኩዋን የቤተ ክርስቲያኒቱን
አደረጃጀት ሊያድስ ቀርቶ የዕሪያ መፈንጫ አድርጓት አረፈው። የያኔው የጊዜያዊ ተሀድሶ ጉባኤ አባላት ግማሹም
በሹመት ግማሹም በሞት ሲበታተኑ ያደረገው ቀለማቸውን ለውጠው ”ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል ሥያሜ የደርግ ወታደሮችን
ሰብስቦ(አዲሱ ማቅ የተመሰረተው በደርግ ወታደሮች አማካኝነት እንደሆነ ማኅበርዋ አትክድም)ወራሹን ማደራጀት ነበር።
ቤተ ክርስቲያኒቱን ተጠልሎ የወደቀ ሥርዐት ለማስመለስ ስለነበረ አባቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን ጉልላት እየናደ ሲደልቅ
ቆይቶ ልጁ ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ እንደሌሊት ሌባ መሠረትዋን እንዲሰረስር ክህነት ሰጥቶ ባረከና አደራጀው።