Wednesday, May 30, 2012

ማህበረ ቅዱሳን እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተሃድሶ ያስፈልጋታል የሚሉ ተሃድሶዎች!


ጽሁፍ በተስፋ አዲስ (ኢትዮ ሰን ድረ ገጽ በ 2003 ዓ/ም እንደተዘገበው)
ክፍል አንድ

ተሐድሶዎች እነማን ናቸው?

ብዙ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ስሄድ የስብከት ካሴት ሳዳምጥ፤ የተለያዩ ሥነ ጽሑፎችን ሳነብ ፡ተሃድሶዎች ተሐድሶዎች፡ የሚል ጩኸት እሰማለሁ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሥር የተቋቋመው ማህበረ ቅዱሳን የሚባለው ድርጅት አባላቱም ሆኑ አመራሮቹ ስለተሃድሶዎች በስብከታቸው እና በጽሑፋቸው ሁሉ በቀጥታም ሆነ በተዛዋዋሪ ሳያነሱ አያልፉም።

እኔም ተሐድሶዎችን ለማወቅ ብዙ ጥረት አድርጌአለሁ። ምን ዓይነት አቋም እንዳልቸውና የት እንደሚገኙ፤ አላማቸው ምን እንደሆነ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማሳወቅ ፈለግሁ። እነርሱ ግን ተሃድሶ የሚለውን  ስም አይቀበሉትም።  እኔ ተሃድሶዎች ስል አንባቢ በሚገባው ቋንቋ ለመጠቀም እንዳሰብሁ ይረዳልኝ። ማህበረ ቅዱሳን የሚባለው ማህበርም ከተሐድሶዎች ጋር ያለውን ቅራኔ ለማቅረብ እሞክራለሁ። አንባቢ የራሱን ተቃውሞም ሆነ ድጋፍ እንዲሠጥ አንዳችም ሳልቀንስ እና ሳልጨምር ትክክለኛውን መረጃ ለማቅረብ እሞክራለሁ። መነሻየ ግን ከማህበረ ቅዱሳን እና ከተሐድሶዎች ሥነ ጽሑፎች ነው። የሁለቱንም ቡድን እንቅሥቃሴ በተከታታይ አቀርባለሁ መልካም ንባብ።

ተሀድሶ ማለት ይላሉ ቤተ ክርስቲያን መታደስ አለባት የሚሉ ወገኖች ማደስ፣ መጠገን፣ ማጽዳት፣ ማለት ነው ይላሉ።ለምሳሌ ቤት ከተሠራ በኋላ ሳይታደስ ብዙ ከቆየ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ሊፈርስ ይችላል ስለዚህ ከመፍረሱ በፊት የሚደርግለት እንክብካቤ ቤቱን ያጸናዋል። እንደሸረሪት ድር፤ የጢስ ጠቀርሻ ያሉ ነገሮችም ከቤቱ ላይ ሊጠረጉ ይገባል። ማደስ ማለት ማፍረስ አይደለም በቤቱ ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፤ ማስወገድ እና በፈረሰው በኩል መጠገን ነው በሌላ አነጋገር መሠረቱን ሳይነኩ እና ሳያናውጡ ጥንታዊነቱን እንደያዘ ቤቱን ማሳመር ማለት ነው።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንም ብዙ ዘመን ከመኖሯ የተነሣ ብዙ ስሕተቶች ይገኙባታልና መጽዳት አላባት፤ ባህሉን ከሃይማኖቱ፤ ውሸቱን ከእውነቱ፤ ክፉውን ከደጉ መለየት አለባት የሚል ራእይ ያላቸውና ለዚህ ሌት ተቀን ያለ እረፍት የሚሠሩ ናቸው።

የሚገኙት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነው ጳጳሳት፤ ቀሳውስት፤ ዲያቆናት፤ መምህራን፤ የድጓ፤ የቅኔ የቅዳሴ መምህራን የሰንበት ተማሪዎች፤ እንዲሁም ምእመናን ሁሉ ያሉበት የአስተሳሰብ ኃይል ነው። የታወቀ ማህበር ግን የላቸውም። አንዳንዶች ማህበር መሥርተዋል ። ኑራቸው እና ሥራቸው በዚያው በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ሲሆን በተለያየ ቦታ /ቤት እና በርካታ ማሰልጠኛዎች አሏቸው። በርካታ መነኮሳት እና ሰባኪዎች በነዚህ ቦታዎች ይሰለጥናሉ። ይህን ሁሉ እንቅሥቃሴ የሚያደርጉት ግን ቤተ ክህነቱ ሳይውቅ ነው። ቀሳውስቱ ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ በየቤተክርስቲያናቸው ሌሎች ቀሳውስት በመመልመል ያሰልጥናሉ። ከጳጳሳትም ውስጥ ለዚሁ ሥራ የሚውል በግላቸው ከፍተኛ እርዳታ ያደርጋሉ። ተሐድሶዎች ቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ ቁልፍ ቦታና ስልጣን አላቸው። በተለይ በአሁኑ ሰዓት በየአብያተ ክርስቲያናቱ  ሚሊዮኖች በብዛት ይገኛሉ። በገጠር አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት እና በገዳማት ሁሉ አሉ። ደሞዛቸውን የሚያገኙት ከዚያው ከቤተ ክርስቲያኒቱ ነው። ግን ከሌሎች የእምነት ድርጅቶችም እርዳታ ያገኛሉ ተብለው ይታማሉ። ተሐድሶዎች  እንደቀደምት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ አማኞች እንጂ እራሳቸውን ተሃድሶ ብለው አይጠሩም።  ስማቸው በሥራቸው ምክንያት ከሚጠሏቸው ወገኖች የተሰጣቸው ነው። በቤተ ክርስቲያን ባሕላዊ ትምህርት ጥልቅ የሆነ ዕውቀት ያላቸው ስለሆኑ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሁለንተና ደካማ ጎንም ሆነ ጠንካራ ጎን ለይተው የሚያውቁ ሊቃውንት ናቸው። የተሃድሶዎች እንቅሥቃሴ ከባድ እንቅሥቃሴ ነው ምክንያቱም እስከሞት ድረስ የቆረጡ ሲሆኑ ታላቅ ራዕይ ያላቸው ናቸው። በማኅበር መደራጀት ሳይሆን  በግል እያንዳንዱ አውቆ መስራት አለበት ስለሚሉ እዚህ ጋ ወይም እዚያ ጋር ናቸው ያሉት አይባልም። በአጭሩ የሌሉበት ቦታ የለም።
የማኅበረ ቅዱሳን ደጋፊ ነን የሚሉ ጳጳሳት ሳይቀሩ የዚህ ተሐድሶ የሚባለውን እንቅስቃሴ በስውር ይደግፋሉ። አሁን ባለው ሁኔታ ተሐድሶ የሚባሉት ክፍሎችን ከቤተክርስቲያኒቱ ማስወገድ በፍጹም አይቻልም። ከላይ እስከታች በተያያዘ ሰንሰለት የሚሰሩ ናቸው።

Monday, May 28, 2012

እውን “ማኅበረ ቅዱሳን” (ሰለፊያ) እየተዘጋ አይደለምን???

 የጽሁፉ ምንጭ፦ ዓውደ ምሕረት ብሎግ
To read in PDF ( Click Here )
አንዳንድ የዚህ ክፉ ነብሰ በላ የሆነ ድርጅት አመራሮችና አባለት “አባሠረቀንና አቡነ ጳውሎስን ብንገድል መንግስተ ሰማያት መግባታችን አይቀርም እንጸድቃለንም። በዚህ አንጠየቅም” እያሉ ሲያወሩ ስንሰማ ግራ እየገባን ይህ ከምን የመጣ አመለካከት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የማይደግፈውን አስተሳሰብ እንዲህ በድፍረት የሚናገሩት ለምንድን ነው እያልን ለአመታት የቆየን ቢሆንም በስተመጨረሻ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ የሚሉት ለምን እንደሆነ በግልጽ ነግረውናል። እኛም ነገሩ ገብቶን ሰው በመግደል ገነት እንደሚወርሱ የሚያምኑ ሰለፊዎች መሆናቸውን አረጋግጠን ከየትኛው መጽሐፍ ይህን ትምህርት እንዳገኙት አውቀናል። ከማቅ ሰዎች ጋር በሀሳብና በአመለካከት ብቻ የተለያየን መሰሎን የነበረ ቢሆንም በምንመራበት መጽሐፍም ቢሆን ልዩነት እንዳለን አውቀናል።
ከዚህ እውነት በመነሳት “ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር” እንዲሉ በግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ የታዩ ክስተቶችን የተመለከተ ትንታኔ መስጠት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቶአል፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እራሱን በቅዱሳን ስም “ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል የሰየመው የፖለቲካ ድርጅት ለአለፉት ሁለት አሥርት አመታት በቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ሆነ በሀገራችን ኢትዮጵያ ላይ እያደረሰው ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ ሁሉም የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችና ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የሚያውቁት ሐቅ ነው፡፡
ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ እንዳስነበብናችሁ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የታቀፈውና በዲያቢሎስ መንፈስ የሚመራው ማቅን ለመሆኑ ማን መሠረተው? እነማንስ ስም ሰጡት የሚለውን እውነታ ስንመለከት ‹‹ማቅ›› የተሀድሶ ኮሚቴ ይባሉ በነበሩ የደርግ ደጋፊ አባላት የተመሠረተ ሲሆን ይኽ የጥፋት መልዕክተኛ ዘር ግንዱ እነኮሎኔል አጥናፉ አባተ ካቋቋሙት ”ጊዜያዊ የተሐድሶ ጉባኤ” ይነሳል። ጊዜያዊ የተሐድሶ ጉባኤ የማኅበረ ቅዱሳን አባቱ መሆኑ ነው። ይኽ አባቱ የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት ለማፍረስ እና በውስጥዋም ሥርዐት አልበኝነት በማንገስ ቤተ ክርስቲያን ደካማ እንድትሆን ለደርግ ያገለገለ ነው። የእኛ ጊዜዋ ማቅ አገልግሎት ሁለት መልክ አለው - የሞተውን ሥርዐት ለመመለስ እና የየግል ጥቅማቸውን ማሳደግ እንዲሁም በሃይማኖት ሽፋን ስውር አላማን ማስፈጸም ነው፡፡

”ከሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል” እንደሚባለው ይኽ ጊዜጣዊ የተሀድሶ ጉባኤ የመንደረተኝነቱን ቂም ለማርካት ሲል ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ፓትርያርክዋን በገመድ አሳንቆ ያስገደለ የሠይጣን መልእክተኛ ነው። እንኩዋን የቤተ ክርስቲያኒቱን አደረጃጀት ሊያድስ ቀርቶ የዕሪያ መፈንጫ አድርጓት አረፈው። የያኔው የጊዜያዊ ተሀድሶ ጉባኤ አባላት ግማሹም በሹመት ግማሹም በሞት ሲበታተኑ ያደረገው ቀለማቸውን ለውጠው ”ማኅበረ ቅዱሳን” በሚል ሥያሜ የደርግ ወታደሮችን ሰብስቦ(አዲሱ ማቅ የተመሰረተው በደርግ ወታደሮች አማካኝነት እንደሆነ ማኅበርዋ አትክድም)ወራሹን ማደራጀት ነበር። ቤተ ክርስቲያኒቱን ተጠልሎ የወደቀ ሥርዐት ለማስመለስ ስለነበረ አባቱ የቤተ ክርስቲያኒቱን ጉልላት እየናደ ሲደልቅ ቆይቶ ልጁ ማኅበረ ቅዱሳን ደግሞ እንደሌሊት ሌባ መሠረትዋን እንዲሰረስር ክህነት ሰጥቶ ባረከና አደራጀው።

Sunday, May 27, 2012

ወርቁ እንዴት ደበሰ!(ሰቆ.ኤር. 4÷1)

           የጽሁፉ ምንጭ፤ቤተ ጳውሎስ/.www.betepawlos.com/
  /  ከደጀ ብርሃን፦ ቅዱሱን መጽሐፍ መሠረት አድርጎ ከወዲያም ይሁን ከወዲህ ያሉትንና ራሳቸውን የጽድቅ ሰራተኞች አድርገው የሚቆጥሩ ነገር ግን በዚያ ሥፍራ ተቀምጠው ያልተገኙትን ሁሉ የተመለከተበትን ይህንን ድንቅ ጽሑፍ እንድታነቡት አቅርበናል። /                  
ገና ሻዩን አዝዤ ወደ አፌ ላስጠጋው ስል ከወዲያ ማዶ ለመቆም የምትጣጣረውን መኪና እያየሁ ዓይኔ ተተክሎ ቀረ፡፡ መኪናዋን አላወቅኋትም፡፡ ዓይኔ ግን በእርሷ ላይ ቀረ፡፡ የሾፌሩ በር ተከፍቶ የወጣው ሰው ግን የማውቀው ወንድም ነበረ፡፡ ወዲያው ግን ማወቄ ወደ አለማወቅ ተለወጠ፡፡ እንኳን የእርሱን ህልውና የራሴን ህልውና ያጣሁት መሰለኝ፡፡ እውኑ ሕልም መሰለኝ፡፡ የጨበጥኩት የጉም ስፍር ሆነብኝ፡፡ ሻዩን ሳልቀምሰው አፌ እሬት ሆነብኝ፡፡ አጠገቤ ያሉትን ሰዎች ሁሉ ሕልውናቸውን መቀበል ከበደኝ፡፡ ዓለም ለቅጽበት ውሸት፣ የአሳብ ቤት ሆነችብኝ፡፡ ዓይኔ እዚያች መኪና ላይ የተተከለው የቀጠርኩት ሰው መጣ ብሎ አይደለም፡፡ ራሴን ቀጥሬ ራሴን እየጋበዝኩ ነበር፡፡ ያም ሰው እንደሚያገኘኝ ፍጹም አላሰበም፤ ነገር ግን ቀጠሮው ሞላ፡፡ እንደዚህ ባንገናኝ እመርጥ ነበር፡፡ በዓለም ግን የሆነው እንጂ የመረጡት አይታይም፡፡ ወዳጅ የሆነ ሰው ሊያየውም ላያየውም የሚገባ ሁኔታ ነበር፡፡ ማየቱ ለማጽናናት፣ አለማየቱ ላለመሰበር ነው። የመጣው ትንሽ ኬክ ቢጤ ገዝቶ ሊበላ ነው፡፡
ወደ እኔ መጓዝ ጀመረ፣ ይበልጥ ልቤ ፈራ፡፡ ያላየኝን ሰው ቀድሜ ዓይቼ የአሳብ ፍልሚያ ውስጥ ገባሁ፡፡ ያየ ታጋይ ነው፣ ያላየ ምን አለበት! ይህ ወንድሜ ቁመናው ያማረ፣ አንገቱ የንጉሥ ሕለተ ወርቅ የመሰለ፣ መልኩ የብር እንኮይ፣ አለባበሱ የጥቅምት አበባ፣ ቆፍጣናነቱ የድሮ ወታደር፣ አነጋገሩ በሥልጣን የተሞላ፣ ለሚረግጠው የሚጠነቀቅ፣ ለሚለብሰው የሚጨነቅ፣ በአጠገብ ሲያፍ ሽቶው የሚያውድ ነበር፡፡ መኪናውን የያዘ እንደሆነ እንደ መኪና ሳይሆን ያለ አቅሟ እንደ ጀት ሁኚ እያለ ያስጨንቃታል። እንደ ንጉሥ ሞተረኛ ለራሱ ድምጽ እያሰማ በመኪናው ጥሩምባ አድባሩን እያወከ ይነጉዳል። ብዙም አልናገረውም ነበር፡፡ ምክንያቱም ወደ መሬት ገና አልወረደም ነበርና ስለማንደማመጥ ነው፡፡ ከመፈለጉ የተነሣ ኩሩ፣ ከመወደዱ የተነሣ ውድ ነበር፡፡ ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርብ ብዙ ዘመን ነገርኩት፡፡ እኔን ላለማስቀየም ብቻ በትዕግሥት ይሰማኛል፡፡ ነገር ግን እሺታው የውሃ ሽታ ሆኖ ይቀራል፡፡ የአሁኗ ዓለም እንደ እርሱ ያታላለችው ሰው አልነበረም፡፡ እኔም ሰው ነኝና ደክሞኝ ተውኩት። ዛሬ ያየሁት ከብዙ ወራቶች በኋላ ነው፡፡ ያቺ የቡልጋ አልቃሽ ያለችው በጆሮዬ አቃጨለ፡-
      ‹‹ምን ቆንጆ ቢሆኑ ቢረዝሙ እንዳክርማ
               መጠቅለል አይቀርም በነጠላ ሸማ››