Tuesday, May 22, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን ከዳላስ ሚካኤል የዛሬ 2 ዓመት የቦጨቀው 120 ሺህ ዶላር የት ደረሰ?

ሰሚ ጆሮ ያለው ይስማ!!!!
የሚካኤልን ታቦት የከሰሱ ሰዎችን በማስቀደም ቤተክርስቲያኑን ለማፍረስ የሚታገሉት የወያኔ ተስፈኞች የጠሩት ስብሰባ መክሸፉን እንደሰማችሁ እናውቃለን። ህዝቡ እንደማይፈልጋቸው
፩ኛ፦ በምርጫ
፪ኛ፦ በጠሩት ስብሰባ ላይ ባለመገኘት እንደተፋቸው በድጋሚ አረጋግጦላቸዋል።

የሚካኤል ቤተክርስቲያን ከተቋቋመ ጀምሮ አንድ ጊዜ እንኳን በቦርድ አባልነት ተመርጠው  አገልግሎት ሰጥተው በማያውቁት በአቶ ጌታቸው ትርፌና ቤተክርስቲያኑ ከተመሰረተ ከቦርድ ወጥተው በማያውቁት በአቶ እዩኤል ነጋ አማካኝነት በቤተክርስቲያናችን ውስጥ የተሰገሰገውና የተሰባሰበው የፖለቲካ ድርጅት በቦርድ አባላት ምርጫ ላይ ተሳትፎ መሸነፉን ሁላችሁም የምታውቁት ነገር ነው።

ይህ ቡድን የሰላምና የአንድነት አስተባባሪ ኮሚቴ በመባል ይታወቃል። በውስጡም፦
፩ኛ፡- የሽማግሌዎች ኮሚቴ
፪ኛ፦ የአባላት ኮሚቴ እና
፫ኛ፦ የቀሳውስት ኮሚቴዎች አሉበት።
ለክፉ ቀን ያዋቀሩት ሽምቅ ድርጅት ነው። ይህ ሁሉ ደባ የሚፈጸመው ቤተክርስቲያናችንን ተገን በማድረግ ነው። ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ግለሰቦች ባለፈው ምርጫ ላይ ያቀረቧቸው ተወዳዳሪዎች ከዚህ ቡድን ድጋፍ በማግኘት ስልጣን ላይ አንዲቆዩና ደግመው እንዲመረጡ የተደረገው ሙከራ መክሸፉ ይታወሳል። በምርጫው ሲሸነፉ በመደናበር ሮጠው ከወያኔ እግር ስር ተደፉ። ወያኔም በገንዘብ ኃይል ድምጽ ገዝቶ ቢለግስም የምርጫዉን ዉጤት ግን መለወጥ አልቻለም።

የህዝብን ድምጽ አክብሮ መቀበል የተሳናቸው አቶ ጌታቸውና አቶ እዩኤልም ቀደም ሲል ምርጫውን እንዲያሸንፉ ሊረዳቸው ሞክሮ አቅም ወዳነሰው ቡድን ተመልሰው በውስጡ የተዋቀሩትን ኮሚቴዎች እንዲያንቀሳቅስ ትእዛዝ አስተላለፉ። ሁለቱ ግለሰቦች ደግሞ ቀደም ሲል ፕሮግራም በተያዘለት አመታዊ የምእመናን ስብሰባ ላይ ዶክተር ግርማንና አቶ አበራን ለማስወጣት የተንኮል ስራ ለመስራት ወስኑ። በምርጫ ያጡትን ወንበር ሁለቱን ተመራጮች በማባረር ዙረው ለመያዝ የተጠነሰሰ ሤራ ነበር። በዚህ መሰረት የወያኔ ተወካዮችም ከተቋቋመው ኮሚቴ ጋር ለመስራት ተስማሙ። በተደረሰው ስምምነት መሰረት ተስፈኛ ባለ ሃብቶች ሰብሰባውን እንዲጠሩ ተወሰነ። በጉባኤው ላይ የወያኔ ካህን መጋበዛቸው ይፋ ሲወጣ አቶ ጌታቸውና አቶ እዩኤል ከነተከታዮቻቸው ራሳቸውን ከስብሰባው አገለሉ። ወያኔወችም ብቻቸውን ቀሩ። ስብሰባውም ከሸፈ።

ግንባር ቀደም የስብሰባው መሪዎች የነበሩትም ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፦
፩ኛ፦ አቶ ኃይሉ እጅጉ-

ቅዱስ ሲኖዶሱና ዘጠነኛ ቀኑ!


                                   ምንጭ፦ ዓውደ ምሕረት ብሎግ
  •  አባ አብርሃም የሀገረ ስብከቱን /ቤት ላለማስረከብ አስቂኝ መከራከሪያ አቀረቡ
  •     ማኅበሯ ሌላው መንገድ ሁሉ አላስኬድ ሲላት አይመጥንም በሚል የሰንበት ማደራጃ መምሪያ ኃላፊነትን ከመምህር እንቍባህርይ ላይ ለመንጠቅ የምታድረገው ሙከራ አልተሳካላትም።
  •     ማኅበረ ቅዱሳንን የመፍረስ ስጋትን ጥሎበት የነበረው የማኅበራት መተዳደሪያ ደንብ እንደገና ውድቅ እንዲሆን እንቅልፍ አጥቶበት የነበረ ሲሆን ድጋሚ እንዲጠና ታዟል።  

አባ አብርሃም ርስት ጉልቴ ነው ያሉትን የሀገረ ስብከቱን /ቤት እንዲያስረክቡ የታዘዙትን ትዕዛዝ ለመቃመም ከተነሳው ጥያቄ ጋር የማይሄድ እኔ ከእርስዎ እሻላለሁ የሚል መከራከሪያ አቀረቡ። እኔ ምን አለኝ እና ነው መልስ የምባለው? ሲሉ የነበሩት ሰው አሁን በራሴ ወጪ አጣሪ ተልኮ ከእኔ እና ከእርሰዎ ማን ጥሩ ስራ እንደሰራ ይጣራ? ሲሉ ጠይቀዋል። ይህም ጥያቄ አሜሪካ ለመመለስ ያላቸውን ከፍተኛ ጉጉት ያሳያል ተብሏል። ስውየውን የሚያስጨንቃቸው የቤተክርስቲያን ልጆች ባሉበት ቦታ ሁሉ ተገኝተው አባትነትን ማሳየት ሳይሆን ጥቅምና ምቾት ባለበት ቦታ ላይ መንቀባረር መሆኑንም አሜሪካ ለመመለስ ያላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ያሳያል።
አሁን በቅርቡ እንኳ ወደ ሐረር ሀገረ ስብከት እንደ ደረሱ ለኔ የተመደበችው መኪና የትኛዋ ነች? ብለው ሲጠይቁ ከእሳቸው በፊት ነበሩት አቡነ ዮሴፍ ይሄዱበት የነበረቸውን መኪና ሲያሳዩዋቸው ከት በለው ስቀው!  እኔ በዚህ መኪና ልሄድ? ብለው ጠይቀው ይህ መኪና ስለማይመጥነኝ በአስቸኳይ «ከሞኤንኮ» አዲስ መኪና ይገዛ ብለው አዲስ መኪና አስገዝተው በእስዋ መንፈላሰፍ ጀምረዋል። ድንቄም አባትነት።

Monday, May 21, 2012

የማቅ እጣ ፋንታ ምን ሊሆን!?


 ለደብዳቤ ቁጥር 1 እዚህ ይጫኑ
ለደብዳቤ ቁጥር 2 እዚህ ይጫኑ

-------------------------------------------
ከማደራጃ መምሪያው ድረ ገጽ የተገኘ