Saturday, May 19, 2012

ማኅበረ ቅዱሳን የስኳር ልማቱን እንደሚቃወም ባደፈጠ ጥናቱ ውስጥ ገለጸ!


ስለዋልድባ ገዳም ጥናት አዘጋጅቻለሁ ካለ በኋላ አድፍጦ የቆየው ማቅ የመምህር ዕንቍ ባህርይ ደብዳቤ እንደደረሰው ጥናቱን ካዘገየበት ቆፍሮ በሽንፍን ካባ ለመግለጥ ተገዷል። ማቅ ከየትኛውም ወገን ገለልተኛ ሆኖ የደረሰበትን የጥናት ውጤት በኦፊሴል ማቅረብ ሲገባው  ጥናት ሳይሆን ወሬ ሰብስቦ ገዳማቱ እንደዚህ ይላሉ፣ መንግሥት ደግሞ እንደዚህ እየሰራ ነው በሚል ገደምዳሜ ጎዳና ለመሸወድ የሞከረ ዲስኩር ለማቅረብ ሞክሯል።
ገዳማቱ የሚያሰሙትን ጩኸት ማንም ሰምቶታል። መንግሥትም እየሰራ ስላለው ልማትም በግልጽ ተናግሯል። ማቅ ሁለቱን ሃሳቦች ለማስታረቅ የሄደ ሽማግሌ ይመስል ዙሪያ ጥምጥም በመሄድ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ሳይሆን እንደዚህ ተባለ፤ እንደዚያ ተደረገ የሚል ወሬ መለቃቀሙ ምናልባትም ያጠናውን ስውር ውጤት በይፋ ብገልጸው መምህር ዕንቍ ባህርይ በግልባጭ ባስታወቋቸው ብሄራዊ የመረጃና ደኅንነት፤ በፌዴራል ፖሊስ፤ በፌዴራል ጉዳዮች ወዘተ መስሪያ ቤቶች በተያዘብኝ የአሸባሪነት ጥቁር ስሜ  ወደ አደጋ ያደርሰኛል ብሎ በመስጋት በልቡ ያስቀመጣትን ሚጥሚጣ ጥናት እንደቀበረ እንገምታለን።
የመንግስትን የስኳር ልማት በግልጽ ብደግፍም ደግሞ በውጪ ሃገር ያሉ ደጋፊዎቼ ዓይንህን ላፈር ይሉኛል፤ መነኰሳቱም ለስንት ስንጠብቅህ፤ እንደዚህ ታዋርደናለህ? ይሉኛል ብሎ  እንዳደፈጠም የጫጫረው ወሬ በግልጽ ያሳብቅበታል።
አሁን ከማቅ መገለጽ ያለበት ኦፊሴላዊ መግለጫ መነኰሳቱ የሚናገሩትን ቃል መድገም  ሳይሆን ደረስኩበት ባለው ጥናት ላይ የስኳር ልማቱ የሚያደርሰው ጉዳት አለ ወይም የለም የሚል ቃል ብቻ እንጂ እንዲህ ተባለ፤ እንዲያ ተወራ የሚል ዲስኩር አይደለም።
ከዚያ ውጪ በሽብር ተግባር የተወጠረች ነፍሱን ለማቆየት ሸርተት፤ ሸርተት አያዋጣም።
 ይህንንም ያህል ለመጠንቀቅ ቢሞክርም ማቅ ባቀረበው የወሬ ዘገባ ላይ ቁና ቁና እየተነፈሰ አንዴ ስኳር ልማቱን እደግፋለሁ የሚልና በሌላ መልኩ ደግሞ ደጋፊዎቹ እንዳይቀየሙትም የስኳር ልማቱ አደገኛ ነው፤ እኔ የገባሁትን ውጥረት ተረዱልኝ የሚል ስሜት ያላቸውን የተቃውሞ ሃሳቡን አልፎ አልፎ ከዲስኩር ጽሁፎቹ መካከል ደንቅሮ ይታያል።

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ 10 ጳጳሳትን ይዘው ወደ አክሱም ሄዱ!

  • ·         መምህርን ዕንቍባሕርይ ከሰንበት ማደራጃ አይነሳም
  • ·         የሚወገዝ ሰውም የለም
  • ·         የዶ/ መስፍን ክህነት መሻር ይነሳልን ብለው ነበር አልተሳከላቸውም
  • ·         አባ አብርሃም የአሜሪካውን ሀገረ ስብከት /ቤት እንዲያስረክቡ ታዘዋል
  • ·         የማኅበረ ቅዱሳን ድረገጾች ውሸት እየፈበረኩ መዘገባቸውን ቀጥለዋልና የዘገቡትን ገልብጦ መረዳት ያስፈልጋል
                                   ምንጭ፦ዐውደ ምሕረት ብሎግ
ከሲኖዶስ ስብሰባ በስተጀርባ ሆኖ እንዳሻው ከሚጋልብባቸው ጳጳሳቱ ጋር የመከረውን ሁሉ ከስብሰባው መካሄድ ቀደም ብሎ የሲኖዶስ ውሳኔ አስመስሎ በማቅረብ ሕዝብን በተሳሳተ መረጃ ማደናገርና የተናገረው ሳይሆን ሲቀር ሊያፍር ሲገባው፣ ነገር ግን «ማፈር ደህና ሰንብት» ያለው ማኅበረ ቅዱሳን በድረገጾቹ ውሸት እየፈበረከና ምኞቱን የሲኖዶስ ውሳኔ አስመስሎ ማቅረቡን ቀጥሏል። ከሰሞኑ እንኳ እነእገሌ ዛሬ ይወገዛሉ አለ። ነገር ግን እንኳን ውግዘት እዚያ በሚያደርስ ሁኔታ የተደረገ ማጣራት አልተካሄደም። ማህበሩ በተሀድሶነት የከሰሳቸው ግለሰቦች ጉዳይ በተገቢው መንገድ ተጠንቶ ስላልቀረበና ግለሰቦቹም ተጠርተው ስላልተጠየቁና ምላሻቸው ስላልተሰማ፣ ጉዳዩ በዚህ የህግ አግባብ ተሰርቶ ወደፊት እንዲታይ የተባለውን፣ «ከዛሬ ጀምሮ በእያንዳንዱ የውሳኔ ሐሳብ ላይ በጥንቃቄ እየተወያየ እንደሚያጸድቀው ይጠበቃል።» ሲሉ የማቅ ድረገጾች እንደተለመደው የልባቸውን ተምኔት ጽፈዋል። ይህ እንደማይሆን፣ ቅዱስነታቸው 10 ጳጳሳትን ይዘው ለቅዱስ ያሬድ በዓል ወደአክሱም ተጉዘዋልና፣ ዛሬ፣ እንኳን ይህ ፈጽሞ ያልተጣራና በጥቅምቱ ሲኖዶስ ስብሰባ ላይ በተወሰነበት ደረጃ የሚገኘው ጉዳይ ውሳኔ ሊያገኝ ቀርቶ የሲኖዶስ ስብሰባም እንደሌለ ለማወቅ ተችሏል።
ሌላው የማኅበሩ ምኞትና የሲኖዶስ ውሳኔ ተደርጎ የተዘገበው መምህር ዕንቍባሕርይ ከማደራጃ መምሪያ ሀላፊነታቸው እንዲነሱ ተወሰነ፤ አባ ኅሩይም ወደሃላፊነታቸው እንዲመለሱ ሲኖዶሱ አዘዘ የሚለው ዘገባ ነው። ይህ ፈጽሞ ሊሆን የማይችል የማህበሪቱ ምኞት ነው።  

Friday, May 18, 2012

በማኅበረ ቅዱሳን ተጽዕኖ ህልውናውን የካደ ኮሌጅ

                                  የጽሁፉ ምንጭ፤ ዐውደ ምሕረት ብሎግ
                     To read in PDF ( Click Here )
 አንድ የቤተክርስቲያንን ልጅ ለማባረር ሲል እራሱን ሕጋዊ ሰውነት የሌለው አድርጎ የሚያሳይ የክስ ወረቀት ለሰበር ሰሚ ችሎት አቀረበ
    ኮሌጁበሰበር ሰሚ ችሎት ከረታ ለተማሪዎቹ ከፍተኛ አደጋ አለው
                                                             
የኢዮቤልዩ በዓሉን ለማክበር ጥቂት ዓመታት የቀሩትና ከተመሰረተ 69 ዓመት የሆነው የቅድስት ስላሴ ኮሌጅ ከመምህር አሰግድ ሣህሉ ጋር ባለው የሕግ ክርክር በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የገጠመውን ሽንፈት ሽሮ በድል እንድወጣ ያስችለኛል ያለውን የይግባኝ አቤቱታ ለሰበር ሰሚ ሲያቀርብ ሕጋዊ ሰውነት የሌለኝና ከአንድ ግለሰብ እንኳ ያነስኩ ነኝ ሲል ህልውናውን ካደ።
የኮሌጁ ጠበቃ እያለች የሕግ ክርክሩን በራሴ በኩል ልምራው የሚለው ማኅበረ ቅዱሳን አመራር በሆነው ደስታ በርሔ በተባለ ጠበቃ በኩል የሕግ ክርክሩን ቢቀጥልም በስር ፍርድ ቤት የገጠመውን ሽንፈት ይሽርልኛል ብሎ ላለፉት አምስት ወራት ሲያስብ ቆይቶ ባቀረበው አቤቱታ በተራ ቁጥር 2 ላይ ያለው የአቤቱታው ዝርዝር በሚለው አንቀጽ በግልጽ ህጋዊ ሰውነት የሌለው ኮሌጅ ነው ሲል የኮሌጁን ህልውና ክዷል።
እኔ ያልኩት ብቻ ትክክል ነው የጠላሁትም መናፍቅ ነው የሚል መመሪያ ያለው ማቅ ፍላጎቱ እንዲሳካ የማያደርገው ነገር እንደሌለው የሚያስረዳው አቤቱታ 69 አመቱን አንጋፋ ኮሌጅ እዚህ ግባ የሚባል ካሪኩለም የሌለው እናደረጃውም የትምህርት ሚኒስቴርን ተቀባይነት የማይመጥን በማለት የኮሌጁ ተማሪ የሆነው መምህር አሰግድ ይባረርልኝ የሚለው አቤቱታ ይህን ይመስላል።
የአቤቱታው ዝርዝር
በመሠረቱ አመልካች ኮሌጅ በራሱ ሕጋዊ ሰውነት የለውም፡፡ እንደ ሌሎች የትምህርት ተቋማት በትምህርት ሚኒስቴር ተመዝግቦና የንግድ ፈቃድ አውጥቶ የሚያስተምር ተቋም አይደለም፡፡ ቀደም ሲል በነበረው መንግስት ተዘግቶ ከቆየ በኋላ በቀጥታ በመንግስት ፈቃድ ቤተክርስቲያኗ ከፍታ የሐይማኖቷን ተከታዮች ለማነጽ መምህራንን የምታፈራበት ነው፡፡ የሚሰጠው የትምህርት ዓይነትም ሆነ ብዛት በትምህርት ሚኒስቴር ቁጥጥር የሚደረግበት አይደለም፡፡ በመሆኑም በስሙ ሊከሰሰም ሆነ ሊፈረድበት አይችልም፡፡ በሕግ ‹‹ሰው›› የሚለውን መስፈረትም አያሟላምና፡፡ ስለዚህ የስር /ቤቶች ጉዳዩን ተቀብለው ማስተናገድም ሆነ አስገዳጅ ውሳኔ መስጠታቸው መሠረታዊ የህግ ስህተት ነው፡፡
ይህ አቤቱታ ቀላል የማይባሉ ስህተቶች ያሉትና እራሱ ኮሌጁ ባለፉት አመታት ባስተማርኩዋቸው ተማሪዎቼ ደረስኩበት የሚለውን ስኬት የሚንድና ተማሪዎቹ ወደ ሌላ የትምህርት ተቋማት ሄደው ለመማር ያላቸውን ፍላጎት ከንቱ የሚያደርግ ነው። አንድ የቤተክርስቲያን ልጅን ካላባረርኩ በሚል ህልውና እስከመካድ ድረስ የደረሰ አቤቱታ ማቅረብ እጅግ በጣም አሳፋሪ የሆነ ተግባር ነው።

አቤቱታው ኮሌጁ በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ    “…/ቤቱ ወደ ኮሌጅ ደረጃ ከፍ እንዲል የታቀደበት ዋናው ዓላማ የቤተክርስቲያኒቱን ከፍተኛ ትምህርት የተማሩ ሊቃውንት ዘመናዊውንም ትምህርት በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀስሙ የማድረጉን ጥረት ሊሟሉ የሚችሉ የሃይማኖትና የግብረ ገብነት መምህራንና የወንጌል ልዑካንን መልሰው እንዲያፈሩ፣ ለማድረግ ከኮሌጁ በዘመናዊውና በጥንታዊው ትምህርት በከፍተና ደረጃ ሰልጥነው የሚወጡት መምህራንም ለተከታዩ ትውልድ የኢትዮጵን መንፈሳዊ ቅርስ ለማስተላለፍ እንዲችሉ ታቅዶ ነበር፡፡…”የሚለውን የኮሌጁን ራዕይና እንዲሁም ይህ ኮሌጅ በመከፈቱ ደረስኩበት የሚለውን ስኬት ማለትም“…ተቋሙ 48 ዓመታት ዕድሜው በርካታ ኢትዮጵያውያንን በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በዲፕሎማ እና በሰርቲፊኬት ያስመረቀ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በመንፈሳዊ አገልግሎት እስከ ፓትርያርክነት፣ በዩኒቨርስቲ መምህርነት እስከ ፕሮፌሰርነት፣ በመንግሥት መሥሪያ ቤት አገልግሎት እስከ ሚኒስትርነት፣ ደረጃ የደረሱ ይገኙበታል፡፡የሚለውን ዋጋ የሚያሳጣ ነው።
የክስ ሂደቱ ዝርዝር ምንድን ነው?
ኮሌጁ የቀድሞ የዲፕሎማ ተማሪዎቹ የዲግሪ ፕሮግራም ለመቀጠል እንደሚችሉ በፈቀደው መሰረት መምህር አሰግድ ሣህሉ ከዚህ ቀደም የኮሌጁ ዲፕሎማ ያለው በመሆኑ እድሉን ለመጠቀም ለመማር ይመዘገባል። ወዲያውኑ ያለበቂ ምክንያት የእግዚአብሔርን ሀሳብ ለምን ታገለግላለህ? በማለት በማኅበረ ቅዱሳን አድሮ ገና በልጅነቱ ሲዋጋው የነበረው ሰይጣን መንፈሱ ታወከበትና መምህሩን ከትምህርት ከበታው ለማባረር ግድግዳ መቧጠጥ ጀመረ።
መጀመሪያ የተጠቀመው ሁሌም የሚያደርገውን የፕሮፓጋንዳ ጦርነት አስቀድሞ ማወጅ ነበረ። ለዚህም ማቅ በሚያስተዳድረውና በፈረንጆቹ 2009 `Owned by mahebere kiduasan` የሚል ቃልን ለጥቂት ቀናት ከለጠፈበት በኃላ ያወረደው ደጀ ሰለም የተባለው የመአት፣ የክስ እና የነቀፋ ብሎጉ  ላይ ኮሌጁ የትምህርትህን አቁም ጥያቄ ከማቅረቡ ከወር በፊት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪውን አባረረ በማለት መምህሩ ጨርሶ የማያውቃቸውን የፈጠራ ታሪኮች በመደርደርሰፊ ሪፖርታዥ ሰራ። በዚህ ጊዜ መምህሩ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ አድሮ ማኅበሩን እንቅልፍ አሳጥጦ እያንቀሳቀሰ ያለው የክስና የአሳዳጅነት መንፈስ አሁንም እንደተከተለው አወቀና የሚገለጥበትን ጊዜ በጸሎት መጠበቅ ጀመረ።
ማኅበረ ቅዱሳን ደጀ ሰላም ላይ ተባረረ በማለት ካስነገረ ከአንድ ወር በኃላም ይኼን ለማስፈጸም ወደ ኮሌጁ ሄዱ በሰራው ሴራ መምህር አሰግድ ወደ ኮሌጁ ቅጥር ጊቢ እንዳይገባ የሚል ትዕዛዝ በኮሌጁ ዲን በኩል ለጥበቃዎች ተላለፈ። መምህሩም በሕጋዊ መስመር የገባሁ ተማሪ ስለሆንኩ በሕጋዊ መንገድ ካልሆነ በቀር እንዳትገባ በሚል የቃል ትዕዛዝ ትምህርቴን አላቆምም በማለቱ ከአንድ ሣምንት በኃላ በወረቀት ታግደሃል ተባለ። እሱም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲመለከተው የሕግ ክፍተት እንዳለበት ስለተረዳ ኮሌጁን ከሰሰ። የክስ ወረቀት ለኮሌጁ እንደደረሰ ያወቀው ማኅበረ ቅዱሳን አላማዬ ግብ ሳይመታ ሊቀር ነው በማለት የኮሌጁን ዲን ጉዳዩን ለኔ ጣሉት ብሎ ደስታ በርሔ የተባለ የአመራር አባሉን የኮሌጁ ጠበቃ አድርጎ በማቆም ከዚህ በፊት በፈጠራ ወሬ እንዲታገድ ያደረገው ተማሪ ትምህርቱን እንዳይቀጥል ለማድረግ የሀሰት ማስረጃዎችን በማደራጀት መከራከር ጀመረ። ፍርድ ቤቱ ክሱ እንዲንቀሳቀስ ሲያዝ ወዲያውኑም መምህር አሰግድ ሣህሉ ወደ ትምህርት ገበታው እንዲመለስ በማዘዙ መሞህሩ ትምህርቱን ቀጥሎ እንዲከራከር ተደረገ። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ተመልክቶ በሐምሌ 7 ቀን 2003 .. ለመምህር አሰግድ በመፍረድ የሚከተለውን ውሳኔ አስተላለፈ።