Thursday, May 17, 2012

የቅዱስ ሲኖዶስ የስድስተኛ ቀን ውሎ



1ኛ የጴጥሮስ መልእክት5:8

"በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና" እንዳለው በመጠን አልኖርም ብሎ የታበየው ማቅ በትዕቢቱ ሊጠፋ ተቃርቧል።

                        To read in PDF Click here
                 የጽሁፍ ምንጭ፤ ዐውደምህረት ብሎግ
·        ማኅበረ ቅዱሳን የመፍረስ አደጋ ያሰጋዋል
·        ውግዘቱ ሥርአተ ቤተክርስቲያንን ያልተከተለ ነው፤ ይወገዛሉ የተባሉት ግለሰቦች ተጠርተው አልተጠየቁም
·        አባ ሠረቀብርሃንና / በጋሻው ስማቸው ይወገዙ ከተባሉት ውስጥ የለም
ቅዱስ ሲኖዶስ ትናንትና በነበረው የስድስተኛ ቀን ውሎው ሁለት ዋና ዋና ጉዳዮችን ያነሳ ሲሆን የጠዋቱ የማኅበራት ጉዳይ ነው። ከሰዓት በኋላ ደግሞ የተነሳው የሃይማኖት ህጸጽ አለባቸው ስለተባሉ ግለሰቦችና ማኅበራት ጉዳይ ነው።
በጠዋቱ ውሎ በማኅበራት ጉዳይ ላይ የተሰናዳው ጥልቅ ጥናት የቀረበ ሲሆን ጥናቱም በሃይማኖት ጸሎት ላይ ያለውንወነአምን በአሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሐዋርያትበሚለው መሰረት ጉባኤ የሚለው አንዲት ቤተክርስቲያንን ነውና ሌሎች ማኅበራት አያስፈልጉም። አንዲቷ ቤተክርስቲያን ራስዋ ማኅበር ናትና የሚል ጥቅል ይዘት ያለው ጥናት ቀርቦዋል። ጥናቱ ሁሉንም አባቶች ያስደሰተ ሲሆን፣ አንዳንድ አባቶች ከውሳኔ በፊት ጥናቱ ለሁላችንም ይሰጠንና እናንብበው ብለው ሲጠይቁ አቡነ ቄርሎስ ጥናቱ በጥሩ ሁኔታ ቀርቦአል። ትክክል የምንለውን ውሳኔ መወሰን ነው እንጂ ጽሁፉን እንደገና ወስደን የምናነበው ለምንድን ነው? ብለው በመጠየቃቸው ተባዝቶ ይሰጠን የሚለው ሀሳብ ቀርቶ በጉዳዩ ላይ ዛሬ ለመወሰን ቀጠሮ ተይዟል። ማኅበሯን ትልቅ ስጋት ውስጥ የከተታትም ይኸው ውሳኔ ነው ተብሏል።

«የማናውቃችሁ ሩቅ ምሥራቆች ያልላካችሁት ደብዳቤአችሁ ደርሶናል!»

በእውነቱ የት እንዳላችሁ፤ እነማን እንደሆናችሁ፤ ስንት እንደሆናችሁና ምን እንደምትፈልጉ ባናውቅም ያልጻፋችሁትና ያልደረሰን ደብዳቤአችሁ እንዲያው በደፈናው  ደርሶናል።
ካልታወቁና  በደፈናው ሩቅ ምሥራቆች ጽፈው የላኩት  ደብዳቤ ደርሶናል እንዴት ትላላችሁ? ብላችሁ ብትጠይቁን መልሳችን፤ በዘንድሮው ሲኖዶስ ያቀድነውና የጎነጎንነው ሁሉ ስላልተሳካ በዓለም የሚገኘው ምእመን ሁሉ በአዲስ አበባ «ታህሪር» አደባባይን እንዲፈጥር የሀገር ውስጡን ሕዝብ ሞራል ለመገንባት የምንጠቀምበት ስልት እንጂ በእርግጥ ከላይ የጠየቃችሁትን ዓይነት ግምት ስናስብ ከምዕራብም ይሁን ከምሥራቅ፤ ከደቡብ ይሁን ከሰሜን የተላከ ምንም ዓይነት የአድማ ደብዳቤ እስካሁን እጃችን አልገባም። ደብዳቤዎቹን እኛው በቢሮአችን እያረቀቅን፤ አቅጣጫ እያወጣንለት በግለሰብም ይሁን በጉባዔዎች ስም የምንጽፈው ራሳችን እንደሆንን እንድታውቁልን እንፈልጋለን።
  ከላይ የተጻፈውን ያልነው «ደጀ ሰላም» ብሎግ ከሩቅ ምሥራቅ መጣልኝ በማለት ያወጣውን ንባብ ካየነው በኋላ የገባበትን ጭንቀት በመጋራት የሩቅ ምስራቁን ደብዳቤ ግልጽ ለማድረግ ፈልገን እንጂ ለእኛ ብሎግ ከሩቅ ምሥራቅ የደረሰን የፈጠራ ደብዳቤ ኖሮ አይደለም።
«ደጀ ሰላም» ብሎግ ከጥላሁን ገሠሠ ዓለማዊ ዘፈን ጋር ወዳጅነት የያዘ መስሏል። ወደ ሩቅ ምሥራቅ ሄዶ «ጃፓኗን ወድጄ» እያለ ከሩቅ ምሥራቅ ተላከልኝ የሚለውን የፍቅር ደብዳቤ በገጹ ጽፎ አስነብቦናል። ሩቅ ምሥራቅ ማለት ጃፓንና አካባቢዋ ያሉ ሀገሮች ናቸው።
 የማቅ አፈቀላጤ «ደጀ ሰላም» ስንት ቆንጆዎችን ከወደ ሩቅ ምሥራቅ እንዳፈራ ለጊዜው ባናውቅም እሱ ግን የተላከለትን «ውዴ አንተ ነህ፤ ዶ/ር መስፍን ውዴ ነው፤እኔም የአንተ ውድ ነኝ» የሚል ደብዳቤ ደርሶኛል ሲል ያቀረበውን ደብዳቤ ተመልክተን በመግቢያችን ላይ  ያልተላከ ደብዳቤ ተላከ ለማለት ተገደድን።
«አዎ የማናውቃችሁ ሩቅ ምሥራቆች ያልተላከው ደብዳቤአችሁ ደርሶናል» በማለት!!
«ደጀ ሰላም» ብሎግ ከሌሎቹ የዓለም ማእዘን ተጻፈልን ሲል እንደቆየው ሁሉ አሁን ደግሞ ከቀረው  ሩቅ ምሥራቅ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እድሉን ለመጠቀም  ደብዳቤውን ራሱ ጽፎ ወይም በዶ/ር መስፍን አስጽፎ ሲያበቃ ከሩቅ ምሥራቅ የደረሰኝ ነው ሲል ብሎጉ ላይ በመለጠፍ ሰውን ሁሉ እንደጅል ሊያጃጅል ይሞክራል።

Wednesday, May 16, 2012

«በማቅ ላይ የተጻፉት ደብዳቤዎችና እና የገባበት ሽብር»

ማቅ ስንቱን ደብድቧል፤ አስደብድቧል፤ ከሀገር አስወጥቷል፤ የስንቱንስ ኃጢአት አዋጅ ነግሯል፤ አስነግሯል፤ በንግድ ጋዜጣው ላይ ሰዎች በሥጋ ድካም የሰሩትን አበሳ ስንት ገጽ ጽፏል?ብለን ብንጠይቅ  የሚችለውንና የሮጠውን ዘመን ሁሉ ሲያደርግ ቆይቷል።
እውነት ማቅ መልካም ስለሰራ ነው ወይ የተጠላው? ለቤተክርስቲያንስ ስለቆመ ነው? የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ሁሉ ዓይንህን ላፈር የሚሉት? እውነት መንግሥት ለሥልጣኑና ለአገዛዙ የማመቸው ማኅበር እንደሆነ አያውቅም?  ሲኖዶስ በእሱ እጅ እየታመሰ እንደቆየ እኛስ አንረዳም? በአሜሪካ ይሁን በአዲስ አበባ፣ በሰንበት ት/ቤቶች ጉባዔ ይሁን በሰንበቴው ማኅበር ማቅ እጁ የሌለበት ቦታ አለ?ብለን ብንጠይቅ እስከዛሬ ለዘራው ሁሉ ሰዓቱ ሲደርስ አሁን የቅጣት አዝመራውን እያፈሰ ነው እንላለን።
ከጥቂት አለቅላቂዎች በስተቀር ካህናቱ ሁሉ እንደጭራቅ የሚመለከቱት እንደሆነ ይታወቃል። መንግሥት አሸባሪ ነህ ብሎታል። በዘንድሮው ሲኖዶስ ተላላኪ አባላቱ እንኳን የዚህ ሽብር ቡድን ገመና መሸፈን አልቻሉም። እንኳን ያንን ያህል ተራምደው እንደድሮው ሊታደጉት ይቅርና የራሳቸውን የጥፋት ክንብንብ ባለበት ሸፍነው ማቆየት አልቻሉም። መ/ምስጢር ወ/ሩፋኤልና ካህሳይ ገ/እግዚአብሔር ሽፋናቸውን በፍትህ መንፈሳዊ ገጸ ንባብ እየገለጡ አደባባይ ላይ አሰጧቸው። በዜና ቤተክርስቲያን ገመና ገላጭነት ላይ 3 ቀናት ጉባዔ ተቀምጠው አንዴ ይቅረቡ፤ አንዴ ደግሞ ኰሚቴ ይቋቋም፤ ሌላ ጊዜ ደግሞ ይወገዙ፤ ሲጨንቃቸው ደግሞ ንብረት የለኝም ወዘተ የሚል ሰበብ በመፍጠር  «የባሰበት እመጫት» ያገባል እንዲሉ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ሲቆርጡና ሲቀጥሉ ሰንብተው ማቅን ከገባበት አጣብቂኝ ማውጣት አልቻሉም ብቻ ሳይሆን የራሳቸውም አጣብቂኝ አስጨንቋቸዋል።